Surah አል-አዕራፍ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል-አዕራፍ - Aya count 206
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
المص ( 1 ) አል-አዕራፍ - Aya 1
አ.ለ.መ.ሰ (አሊፍ፤ ላም ፤ሚም፤ ሷድ)፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 1
كِتَابٌ أُنزِلَ إِلَيْكَ فَلَا يَكُن فِي صَدْرِكَ حَرَجٌ مِّنْهُ لِتُنذِرَ بِهِ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ ( 2 ) አል-አዕራፍ - Aya 2
(ይህ) ወደ አንተ የተወረደ መጽሐፍ ነው፡፡ በደረትህም ውስጥ ከእርሱ ጭንቀት አይኑር፡፡ (የተወረደውም) በእርሱ ልታስፈራራበትና ለምእምናን መገሠጫ እንዲኾን ነው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 2
اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ وَلَا تَتَّبِعُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ ۗ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ ( 3 ) አል-አዕራፍ - Aya 3
ከጌታችሁ ወደእናንተ የተወረደውን ተከተሉ፡፡ ከአላህም ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ፡፡ ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 3
وَكَم مِّن قَرْيَةٍ أَهْلَكْنَاهَا فَجَاءَهَا بَأْسُنَا بَيَاتًا أَوْ هُمْ قَائِلُونَ ( 4 ) አል-አዕራፍ - Aya 4
ከከተማም ልናጠፋት የሻነው ወዲያውም ብርቱ ቅጣታችን ሌሊት ወይም ቀን እነርሱ በቀትር አርፈው ሳሉ የመጣባቸው ብዙ ናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 4
فَمَا كَانَ دَعْوَاهُمْ إِذْ جَاءَهُم بَأْسُنَا إِلَّا أَن قَالُوا إِنَّا كُنَّا ظَالِمِينَ ( 5 ) አል-አዕራፍ - Aya 5
ቅጣታችንም በመጣባቸው ጊዜ «ጸሎታቸው እኛ በደለኞች ነበርን» ከማለት በቀር ሌላ አልነበረም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 5
فَلَنَسْأَلَنَّ الَّذِينَ أُرْسِلَ إِلَيْهِمْ وَلَنَسْأَلَنَّ الْمُرْسَلِينَ ( 6 ) አል-አዕራፍ - Aya 6
እነዚያንም ወደነሱ የተላከባቸውን (ሕዝቦች) በእርግጥ መልክተኞቹንም እንጠይቃለን፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 6
فَلَنَقُصَّنَّ عَلَيْهِم بِعِلْمٍ ۖ وَمَا كُنَّا غَائِبِينَ ( 7 ) አል-አዕራፍ - Aya 7
በእነርሱም ላይ (የነበሩበትን ሁሉ) ከዕውቀት ጋር በእርግጥ እንተርክላቸዋለን፡፡ የራቅንም አልነበርንም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 7
وَالْوَزْنُ يَوْمَئِذٍ الْحَقُّ ۚ فَمَن ثَقُلَتْ مَوَازِينُهُ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ ( 8 ) አል-አዕራፍ - Aya 8
ትክክለኛውም ሚዛን የዚያን ቀን ነው፡፡ ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸው ሰዎችም እነዚያ እነርሱ የፈለጉትን ያገኙ ናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 8
وَمَنْ خَفَّتْ مَوَازِينُهُ فَأُولَٰئِكَ الَّذِينَ خَسِرُوا أَنفُسَهُم بِمَا كَانُوا بِآيَاتِنَا يَظْلِمُونَ ( 9 ) አል-አዕራፍ - Aya 9
ሚዛኖቻቸው የቀለሉባቸው ሰዎችም እነዚያ እነርሱ ተአምራቶቻችንን ይክዱ በነበሩት ምክንያት ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 9
وَلَقَدْ مَكَّنَّاكُمْ فِي الْأَرْضِ وَجَعَلْنَا لَكُمْ فِيهَا مَعَايِشَ ۗ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُونَ ( 10 ) አል-አዕራፍ - Aya 10
በምድርም ላይ በእርግጥ አስመቸናችሁ፡፡ በእርሷም ላይ ለናንተ መኖሪያዎችን አደረግንላችሁ፤ ምስጋናችሁ በጣም ጥቂት ነው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 10
وَلَقَدْ خَلَقْنَاكُمْ ثُمَّ صَوَّرْنَاكُمْ ثُمَّ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ لَمْ يَكُن مِّنَ السَّاجِدِينَ ( 11 ) አል-አዕራፍ - Aya 11
በእርግጥም ፈጠርናችሁ፡፡ ከዚያም ቀረጽናችሁ፡፡ ከዚያም ለመላእክቶች «ለአዳም ስገዱ» አልን፡፡ ወዲያውም ሰገዱ፡፡ ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ሲቀር ከሰጋጆቹ አልኾነም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 11
قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسْجُدَ إِذْ أَمَرْتُكَ ۖ قَالَ أَنَا خَيْرٌ مِّنْهُ خَلَقْتَنِي مِن نَّارٍ وَخَلَقْتَهُ مِن طِينٍ ( 12 ) አል-አዕራፍ - Aya 12
(አላህ) «ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ» አለው፡፡ «እኔ ከርሱ የበለጥኩ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፡፡ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው» አለ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 12
قَالَ فَاهْبِطْ مِنْهَا فَمَا يَكُونُ لَكَ أَن تَتَكَبَّرَ فِيهَا فَاخْرُجْ إِنَّكَ مِنَ الصَّاغِرِينَ ( 13 ) አል-አዕራፍ - Aya 13
ከእርሷ ውረድ፤ በእርሷ ውስጥ ልትኮራ አይገባህምና፡፡ ውጣም አንተ ከወራዶቹ ነህና አለው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 13
قَالَ أَنظِرْنِي إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ ( 14 ) አል-አዕራፍ - Aya 14
«እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ» አለ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 14
قَالَ إِنَّكَ مِنَ الْمُنظَرِينَ ( 15 ) አል-አዕራፍ - Aya 15
፡-አንተ ከሚቆዩት ነህ አለው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 15
قَالَ فَبِمَا أَغْوَيْتَنِي لَأَقْعُدَنَّ لَهُمْ صِرَاطَكَ الْمُسْتَقِيمَ ( 16 ) አል-አዕራፍ - Aya 16
«ስለአጠመምከኝም ለእነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ» አለ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 16
ثُمَّ لَآتِيَنَّهُم مِّن بَيْنِ أَيْدِيهِمْ وَمِنْ خَلْفِهِمْ وَعَنْ أَيْمَانِهِمْ وَعَن شَمَائِلِهِمْ ۖ وَلَا تَجِدُ أَكْثَرَهُمْ شَاكِرِينَ ( 17 ) አል-አዕራፍ - Aya 17
«ከዚያም ከስተፊቶቻቸው ከኋላቸውም ከቀኞቻቸውም ከግራዎቻቸውም በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ፡፡ አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ኾነው አታገኛቸውም» (አለ)፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 17
قَالَ اخْرُجْ مِنْهَا مَذْءُومًا مَّدْحُورًا ۖ لَّمَن تَبِعَكَ مِنْهُمْ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكُمْ أَجْمَعِينَ ( 18 ) አል-አዕራፍ - Aya 18
«የተጠላህ ብራሪ ስትኾን ከእርሷ ውጣ፡፡ ከእነርሱ የተከተለህ ከእናንተ ከመላችሁም ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ» አለው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 18
وَيَا آدَمُ اسْكُنْ أَنتَ وَزَوْجُكَ الْجَنَّةَ فَكُلَا مِنْ حَيْثُ شِئْتُمَا وَلَا تَقْرَبَا هَٰذِهِ الشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ الظَّالِمِينَ ( 19 ) አል-አዕራፍ - Aya 19
«አዳም ሆይ! አንተም ሚስትህም በገነት ተቀመጡ፡፡ ከሻችሁትም ስፍራ ብሉ፡፡ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፡፡ (ራሳቸውን) ከሚበድሉት ትኾናላችሁና» (አላቸው)፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 19
فَوَسْوَسَ لَهُمَا الشَّيْطَانُ لِيُبْدِيَ لَهُمَا مَا وُورِيَ عَنْهُمَا مِن سَوْآتِهِمَا وَقَالَ مَا نَهَاكُمَا رَبُّكُمَا عَنْ هَٰذِهِ الشَّجَرَةِ إِلَّا أَن تَكُونَا مَلَكَيْنِ أَوْ تَكُونَا مِنَ الْخَالِدِينَ ( 20 ) አል-አዕራፍ - Aya 20
ሰይጣንም ከሐፍረተ ገላቸው የተሸሸገውን ለእነርሱ ሊገልጽባቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው፡፡ «ጌታችሁም መልኣኮች እንዳትኾኑ ወይም ከዘላለም ነዋሪዎች እንዳትኾኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ አልከለከላችሁም» አላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 20
وَقَاسَمَهُمَا إِنِّي لَكُمَا لَمِنَ النَّاصِحِينَ ( 21 ) አል-አዕራፍ - Aya 21
«እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሩዋችሁ ነኝ» ሲልም አማለላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 21
فَدَلَّاهُمَا بِغُرُورٍ ۚ فَلَمَّا ذَاقَا الشَّجَرَةَ بَدَتْ لَهُمَا سَوْآتُهُمَا وَطَفِقَا يَخْصِفَانِ عَلَيْهِمَا مِن وَرَقِ الْجَنَّةِ ۖ وَنَادَاهُمَا رَبُّهُمَا أَلَمْ أَنْهَكُمَا عَن تِلْكُمَا الشَّجَرَةِ وَأَقُل لَّكُمَا إِنَّ الشَّيْطَانَ لَكُمَا عَدُوٌّ مُّبِينٌ ( 22 ) አል-አዕራፍ - Aya 22
በማታለልም አዋረዳቸው፡፡ ከዛፊቱም በቀመሱ ጊዜ ኀፍረተ ገላቸው ለሁለቱም ተገለጠችላቸው፡፡ ከገነት ቅጠልም በላያቸው ላይ ይደርቱ ጀመር፡፡ ጌታቸውም «ከዚህ ዛፍ አልከለከልኋችሁምን ሰይጣንም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነው አላልኳችሁምን» ሲል ጠራቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 22
قَالَا رَبَّنَا ظَلَمْنَا أَنفُسَنَا وَإِن لَّمْ تَغْفِرْ لَنَا وَتَرْحَمْنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ ( 23 ) አል-አዕራፍ - Aya 23
«ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን፡፡ ለእኛ ባትምር ባታዝንልንም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 23
قَالَ اهْبِطُوا بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ ۖ وَلَكُمْ فِي الْأَرْضِ مُسْتَقَرٌّ وَمَتَاعٌ إِلَىٰ حِينٍ ( 24 ) አል-አዕራፍ - Aya 24
(አላህ) « ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ውረዱ፡፡ ለእናንተም በምድር ላይ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ» አላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 24
قَالَ فِيهَا تَحْيَوْنَ وَفِيهَا تَمُوتُونَ وَمِنْهَا تُخْرَجُونَ ( 25 ) አል-አዕራፍ - Aya 25
«በእርሷ ላይ ትኖራላችሁ፡፡ በእርሷም ላይ ትሞታላችሁ፡፡ ከእርሷም ውስጥ ትወጣላችሁ» አላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 25
يَا بَنِي آدَمَ قَدْ أَنزَلْنَا عَلَيْكُمْ لِبَاسًا يُوَارِي سَوْآتِكُمْ وَرِيشًا ۖ وَلِبَاسُ التَّقْوَىٰ ذَٰلِكَ خَيْرٌ ۚ ذَٰلِكَ مِنْ آيَاتِ اللَّهِ لَعَلَّهُمْ يَذَّكَّرُونَ ( 26 ) አል-አዕራፍ - Aya 26
የአዳም ልጆች ሆይ! ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም በእርግጥ በናንተ ላይ አወረድን፡፡ አላህን የመፍራትም ልብስ ይህ የተሻለ ነው፡፡ ይህ ከአላህ ታምራቶች ነው፡፡ ይገሠጹ ዘንድ (አወረደላቸው)፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 26
يَا بَنِي آدَمَ لَا يَفْتِنَنَّكُمُ الشَّيْطَانُ كَمَا أَخْرَجَ أَبَوَيْكُم مِّنَ الْجَنَّةِ يَنزِعُ عَنْهُمَا لِبَاسَهُمَا لِيُرِيَهُمَا سَوْآتِهِمَا ۗ إِنَّهُ يَرَاكُمْ هُوَ وَقَبِيلُهُ مِنْ حَيْثُ لَا تَرَوْنَهُمْ ۗ إِنَّا جَعَلْنَا الشَّيَاطِينَ أَوْلِيَاءَ لِلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ ( 27 ) አል-አዕራፍ - Aya 27
የአዳም ልጆች ሆይ! ሰይጣን አባትና እናታችሁን ኀፍረተ ገላቸውን ሊያሳያቸው ልብሶቻቸውን ከነሱ የገፈፋቸው ሲኾን ከገነት እንዳወጣቸው ሁሉ እናንተን አይሞክራችሁ፡፡ እነሆ እርሱ ከነሰራዊቱ ከማታዩዋቸው ስፍራ ያዩዋችኋልና፡፡ እኛ ሰይጣናትን ለእነዚያ ለማያምኑት ወዳጆች አድርገናል፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 27
وَإِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً قَالُوا وَجَدْنَا عَلَيْهَا آبَاءَنَا وَاللَّهُ أَمَرَنَا بِهَا ۗ قُلْ إِنَّ اللَّهَ لَا يَأْمُرُ بِالْفَحْشَاءِ ۖ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ ( 28 ) አል-አዕራፍ - Aya 28
መጥፎንም ሥራ በሠሩ ጊዜ በእርሷ ላይ አባቶቻችንን አገኘን አላህም በእርሷ አዞናል ይላሉ፡፡ «አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም፡፡ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን» በላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 28
قُلْ أَمَرَ رَبِّي بِالْقِسْطِ ۖ وَأَقِيمُوا وُجُوهَكُمْ عِندَ كُلِّ مَسْجِدٍ وَادْعُوهُ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ ۚ كَمَا بَدَأَكُمْ تَعُودُونَ ( 29 ) አል-አዕራፍ - Aya 29
ጌታዬ በማስተካከል አዘዘ፡፡ በየመስጊዱም ዘንድ ፊቶቻችሁን (እርሱን ለመገዛት) አስተካክሉ፡፡ ሃይማኖትንም ለእርሱ ፍጹም አድርጋችሁ ተገዙት፡፡ እንደጀመራችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 29
فَرِيقًا هَدَىٰ وَفَرِيقًا حَقَّ عَلَيْهِمُ الضَّلَالَةُ ۗ إِنَّهُمُ اتَّخَذُوا الشَّيَاطِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ اللَّهِ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُم مُّهْتَدُونَ ( 30 ) አል-አዕራፍ - Aya 30
ከፊሉን ወደ ቅን መንገድ መራ፡፡ ከፊሎቹም በእነሱ ላይ ጥመት ተረጋግጦባቸዋል፡፡ እነርሱ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋልና፡፡ እነርሱም (ቅኑን መንገድ) የተመራን ነን ብለው ያስባሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 30
يَا بَنِي آدَمَ خُذُوا زِينَتَكُمْ عِندَ كُلِّ مَسْجِدٍ وَكُلُوا وَاشْرَبُوا وَلَا تُسْرِفُوا ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُسْرِفِينَ ( 31 ) አል-አዕራፍ - Aya 31
የአዳም ልጆች ሆይ! (ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን) ጌጦቻችሁን በመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ፡፡ ብሉም፤ ጠጡም፤ አታባክኑም፡፡ እርሱ አባካኞችን አይወድምና፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 31
قُلْ مَنْ حَرَّمَ زِينَةَ اللَّهِ الَّتِي أَخْرَجَ لِعِبَادِهِ وَالطَّيِّبَاتِ مِنَ الرِّزْقِ ۚ قُلْ هِيَ لِلَّذِينَ آمَنُوا فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا خَالِصَةً يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ ( 32 ) አል-አዕራፍ - Aya 32
«የአላህን ጌጥ ያችን ለባሮቹ የፈጠራትን ከሲሳይም ጥሩዎቹን እርም ያደረገ ማን ነው» በላቸው፡፡ «እርሷ በትንሣኤ ቀን ለእነዚያ ላመኑት ብቻ ስትኾን በቅርቢቱ ሕይወት ተገቢያቸው ናት» በላቸው፡፡ እንደዚሁ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 32
قُلْ إِنَّمَا حَرَّمَ رَبِّيَ الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ وَالْإِثْمَ وَالْبَغْيَ بِغَيْرِ الْحَقِّ وَأَن تُشْرِكُوا بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا وَأَن تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ ( 33 ) አል-አዕራፍ - Aya 33
«ጌታዬ እርም ያደረገው መጥፎ ሥራዎችን፣ ከርሷ የተገለጸውንና የተደበቀውን ኃጢኣትንም፣ ያላግባብ መበደልንም፣ በርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን (ጣዖት) በአላህ ማጋራታችሁን፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው» በላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 33
وَلِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌ ۖ فَإِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ لَا يَسْتَأْخِرُونَ سَاعَةً ۖ وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ ( 34 ) አል-አዕራፍ - Aya 34
ለሕዝብም ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው፡፡ ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፡፡ (ከጊዜያቱ) አይቀደሙምም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 34
يَا بَنِي آدَمَ إِمَّا يَأْتِيَنَّكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَقُصُّونَ عَلَيْكُمْ آيَاتِي ۙ فَمَنِ اتَّقَىٰ وَأَصْلَحَ فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ ( 35 ) አል-አዕራፍ - Aya 35
የአዳም ልጆች ሆይ! ከእናንተ ውስጥ በናንተ ላይ አንቀጾቼን የሚያነቡ መልከተኞች ቢመጧችሁ ከእናንተ ክሕደትን የተጠነቀቁና መልካምንም የሠሩ በነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፡፡ እነሱም አያዝኑም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 35
وَالَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَاسْتَكْبَرُوا عَنْهَا أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ ( 36 ) አል-አዕራፍ - Aya 36
እነዚያም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 36
فَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِآيَاتِهِ ۚ أُولَٰئِكَ يَنَالُهُمْ نَصِيبُهُم مِّنَ الْكِتَابِ ۖ حَتَّىٰ إِذَا جَاءَتْهُمْ رُسُلُنَا يَتَوَفَّوْنَهُمْ قَالُوا أَيْنَ مَا كُنتُمْ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ ۖ قَالُوا ضَلُّوا عَنَّا وَشَهِدُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا كَافِرِينَ ( 37 ) አል-አዕራፍ - Aya 37
በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ከአስዋሸ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው እነዚያ (ከተጻፈላቸው) ከመጽሐፉ ውስጥ ሲኾን ዕድላቸው ያገኛቸዋል፡፡ (የሞት) መልክተኞቻችንም የሚገድሏቸው ኾነው በመጡባቸው ጊዜ «ከአላህ ሌላ ትገዟቸው የነበራችሁት የት አሉ» ይሏቸዋል፡፡ «ከእኛ ተሰወሩን» ይላሉ፡፡ እነርሱም ከሃዲያን እንደነበሩ በነፍሶቻቸው ላይ ይመሰክራሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 37
قَالَ ادْخُلُوا فِي أُمَمٍ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِكُم مِّنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ فِي النَّارِ ۖ كُلَّمَا دَخَلَتْ أُمَّةٌ لَّعَنَتْ أُخْتَهَا ۖ حَتَّىٰ إِذَا ادَّارَكُوا فِيهَا جَمِيعًا قَالَتْ أُخْرَاهُمْ لِأُولَاهُمْ رَبَّنَا هَٰؤُلَاءِ أَضَلُّونَا فَآتِهِمْ عَذَابًا ضِعْفًا مِّنَ النَّارِ ۖ قَالَ لِكُلٍّ ضِعْفٌ وَلَٰكِن لَّا تَعْلَمُونَ ( 38 ) አል-አዕራፍ - Aya 38
«ከጋኔንም ከሰውም ከእናንተ በፊት በእርግጥ ካለፉት ሕዝቦች ጋር ኾናችሁ እሳት ውስጥ ግቡ» ይላቸዋል፡፡ አንዲቱ ሕዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር (ያሳሳተቻትን) ብጤዋን ትረግማለች፡፡ መላውም በውስጧ ተሰብስበው በተገናኙም ጊዜ የኋለኛይቱ ለመጀመሪያይቱ (ተከታዮች ለአስከታዮች) «ጌታችን ሆይ! እነዚህ አሳሳቱን፡፡ ከእሳትም ስቃይ እጥፍን ስጣቸው» ትላለች፡፡ (አላህም)፡- ለሁሉም እጥፍ አለው ግን አታውቁም ይላቸዋል፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 38
وَقَالَتْ أُولَاهُمْ لِأُخْرَاهُمْ فَمَا كَانَ لَكُمْ عَلَيْنَا مِن فَضْلٍ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْسِبُونَ ( 39 ) አል-አዕራፍ - Aya 39
«መጀመሪያይቱም ለኋለኛይቱ ለእናንተ በእኛ ላይ ምንም ብልጫ አልነበራችሁም» ትላለች፡፡ «ትሠሩትም በነበራችሁት ቅጣቱን ቅመሱ» (ይላቸዋል)፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 39
إِنَّ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَاسْتَكْبَرُوا عَنْهَا لَا تُفَتَّحُ لَهُمْ أَبْوَابُ السَّمَاءِ وَلَا يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ حَتَّىٰ يَلِجَ الْجَمَلُ فِي سَمِّ الْخِيَاطِ ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُجْرِمِينَ ( 40 ) አል-አዕራፍ - Aya 40
እነዚያ አንቀጾቻችንን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ ለእነርሱ የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸውም፡፡ ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባም ድረስ ገነትን አይገቡም፡፡ እንደዚሁም አጋሪዎችን እንቀጣለን፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 40
لَهُم مِّن جَهَنَّمَ مِهَادٌ وَمِن فَوْقِهِمْ غَوَاشٍ ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الظَّالِمِينَ ( 41 ) አል-አዕራፍ - Aya 41
ለእነርሱ ከገሀነም እሳት (በሥራቸው) ምንጣፍ ከበላያቸውም (የእሳት) መሸፈኛዎች አሏቸው፡፡ እንደዚሁም በደለኞችን እንቀጣለን፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 41
وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ ( 42 ) አል-አዕራፍ - Aya 42
እነዚያም ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ነፍስን ችሎታዋን እንጂ አናስገድድምና፤ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 42
وَنَزَعْنَا مَا فِي صُدُورِهِم مِّنْ غِلٍّ تَجْرِي مِن تَحْتِهِمُ الْأَنْهَارُ ۖ وَقَالُوا الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي هَدَانَا لِهَٰذَا وَمَا كُنَّا لِنَهْتَدِيَ لَوْلَا أَنْ هَدَانَا اللَّهُ ۖ لَقَدْ جَاءَتْ رُسُلُ رَبِّنَا بِالْحَقِّ ۖ وَنُودُوا أَن تِلْكُمُ الْجَنَّةُ أُورِثْتُمُوهَا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ ( 43 ) አል-አዕራፍ - Aya 43
በደረቶቻቸው ውስጥ ያለውንም ጥላቻ እናስወግዳለን፡፡ ወንዞች በሥሮቻቸው ይፈሳሉ፡፡ «ለዚያም ወደዚህ (ላደረሰን ሥራ) ለመራን አላህ ምስጋና ይገባው፡፡ አላህ ባልመራንም ኖሮ አንመራም ነበር፡፡ የጌታችን መልክተኞች በእውነት ላይ ሲኾኑ በእርግጥ መጥተውልናል» ይላሉ፡፡ ይህች ገነት ትሠሩት በነበራችሁት ተሰጣችኋት በማለት ይጠራሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 43
وَنَادَىٰ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ أَصْحَابَ النَّارِ أَن قَدْ وَجَدْنَا مَا وَعَدَنَا رَبُّنَا حَقًّا فَهَلْ وَجَدتُّم مَّا وَعَدَ رَبُّكُمْ حَقًّا ۖ قَالُوا نَعَمْ ۚ فَأَذَّنَ مُؤَذِّنٌ بَيْنَهُمْ أَن لَّعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ ( 44 ) አል-አዕራፍ - Aya 44
የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎች «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን፡፡ ጌታችሁ የዛተባችሁንስ እውነት ኾኖ አገኛችሁትን» ሲሉ ይጣራሉ፡፡ «አዎን አገኘን» ይላሉ፡፡ በመካከላቸውም «የአላህ ርግማን በበደለኞች ላይ ይኹን» ሲል ለፋፊ ይለፍፋል፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 44
الَّذِينَ يَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ وَيَبْغُونَهَا عِوَجًا وَهُم بِالْآخِرَةِ كَافِرُونَ ( 45 ) አል-አዕራፍ - Aya 45
(በደለኞች) እነዚያ ከአላህ መንገድ የሚከለክሉ፣ (የአላህም መንገድ) እንድትጣመምም የሚፈልጉዋት፣ እነርሱም በመጨረሻዋ ዓለም ከሓዲዎች የኾኑ ናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 45
وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ ۚ وَعَلَى الْأَعْرَافِ رِجَالٌ يَعْرِفُونَ كُلًّا بِسِيمَاهُمْ ۚ وَنَادَوْا أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَن سَلَامٌ عَلَيْكُمْ ۚ لَمْ يَدْخُلُوهَا وَهُمْ يَطْمَعُونَ ( 46 ) አል-አዕራፍ - Aya 46
በመካከላቸውም ግርዶሽ አልለ፡፡ በአዕራፍም ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቁ ሰዎች አልሉ፡፡ የገነትንም ሰዎች ሰላም ለናንተ ይኹን በማለት ይጣራሉ፡፡ እነርሱም (የአዕራፍ ሰዎች) የሚከጅሉ ሲኾኑ ገና አልገቧትም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 46
وَإِذَا صُرِفَتْ أَبْصَارُهُمْ تِلْقَاءَ أَصْحَابِ النَّارِ قَالُوا رَبَّنَا لَا تَجْعَلْنَا مَعَ الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ ( 47 ) አል-አዕራፍ - Aya 47
ዓይኖቻቸውም ወደ እሳት ሰዎች አቅጣጫ በተዞሩ ጊዜ፡- «ጌታችን ሆይ! ከበደለኞች ጋር አታድርገን» ይላሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 47
وَنَادَىٰ أَصْحَابُ الْأَعْرَافِ رِجَالًا يَعْرِفُونَهُم بِسِيمَاهُمْ قَالُوا مَا أَغْنَىٰ عَنكُمْ جَمْعُكُمْ وَمَا كُنتُمْ تَسْتَكْبِرُونَ ( 48 ) አል-አዕራፍ - Aya 48
የአዕራፍም ሰዎች በምልክታቸው የሚያውቁዋቸውን (ታላላቅ) ሰዎች ይጣራሉ፡፡ «ስብስባችሁና በብዛታችሁ የምትኮሩ መኾናችሁም ከእናንተ ምንም አልጠቀማችሁ» ይሏቸዋል፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 48
أَهَٰؤُلَاءِ الَّذِينَ أَقْسَمْتُمْ لَا يَنَالُهُمُ اللَّهُ بِرَحْمَةٍ ۚ ادْخُلُوا الْجَنَّةَ لَا خَوْفٌ عَلَيْكُمْ وَلَا أَنتُمْ تَحْزَنُونَ ( 49 ) አል-አዕራፍ - Aya 49
እነዚያ አላህ በችሮታው አያገኛቸውም ብላችሁ የማላችሁት (ደካሞች) እነዚህ ናቸውን «ገነትን ግቡ ፍርሃት የለባችሁም እናንተም አታዝኑም» (ተባሉ ይሏቸዋል)፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 49
وَنَادَىٰ أَصْحَابُ النَّارِ أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَنْ أَفِيضُوا عَلَيْنَا مِنَ الْمَاءِ أَوْ مِمَّا رَزَقَكُمُ اللَّهُ ۚ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ حَرَّمَهُمَا عَلَى الْكَافِرِينَ ( 50 ) አል-አዕራፍ - Aya 50
የእሳትም ሰዎች የገነትን ሰዎች «በእኛ ላይ ከውሃ አፍስሱብን ወይም አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ (ጣሉልን)» ብለው ጠሩዋቸዋል፡፡ እነርሱም «አላህ በከሓዲዎች ላይ እርም አድርጓቸዋል» ይሏቸዋል፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 50
الَّذِينَ اتَّخَذُوا دِينَهُمْ لَهْوًا وَلَعِبًا وَغَرَّتْهُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا ۚ فَالْيَوْمَ نَنسَاهُمْ كَمَا نَسُوا لِقَاءَ يَوْمِهِمْ هَٰذَا وَمَا كَانُوا بِآيَاتِنَا يَجْحَدُونَ ( 51 ) አል-አዕራፍ - Aya 51
እነዚያ ሃይማኖታቸውን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው የያዙ የቅርቢቱም ሕይወት ያታለለቻቸው ይህንን ቀናቸውን መገናኘትን እንደረሱ በተአምራታችንም ይክዱ እንደነበሩ ዛሬ እንረሳቸዋልን፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 51
وَلَقَدْ جِئْنَاهُم بِكِتَابٍ فَصَّلْنَاهُ عَلَىٰ عِلْمٍ هُدًى وَرَحْمَةً لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ ( 52 ) አል-አዕራፍ - Aya 52
ከዕውቀት ጋርም የዘረዘርነው የኾነን መጽሐፍ ለሚያምኑ ሕዝቦች መምሪያና እዝነት ሲኾን በእርግጥ አመጣንላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 52
هَلْ يَنظُرُونَ إِلَّا تَأْوِيلَهُ ۚ يَوْمَ يَأْتِي تَأْوِيلُهُ يَقُولُ الَّذِينَ نَسُوهُ مِن قَبْلُ قَدْ جَاءَتْ رُسُلُ رَبِّنَا بِالْحَقِّ فَهَل لَّنَا مِن شُفَعَاءَ فَيَشْفَعُوا لَنَا أَوْ نُرَدُّ فَنَعْمَلَ غَيْرَ الَّذِي كُنَّا نَعْمَلُ ۚ قَدْ خَسِرُوا أَنفُسَهُمْ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا يَفْتَرُونَ ( 53 ) አል-አዕራፍ - Aya 53
(የዛቻውን) ፍጻሜውን እንጂ ሌላ አይጠባበቁም፡፡ ፍጻሜው በሚመጣበት ቀን እነዚያ ከመምጣቱ በፊት የረሱት ሰዎች «የጌታችን መልክተኞች በእርግጥ በውነት መጥተዋል፡፡ ለእኛ ያማልዱም ዘንድ አማላጆች አልሉን ወይስ ከዚያ እንሠራው ከነበርነው ሌላን ሥራ እንሠራ ዘንድ (ወደ ምድረ ዓለም) እንመለሳለን» ይላሉ፡፡ ነፍሶቻቸውን በእርግጥ አከሰሩ፡፡ ይቀጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ጠፋቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 53
إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ يَطْلُبُهُ حَثِيثًا وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ وَالنُّجُومَ مُسَخَّرَاتٍ بِأَمْرِهِ ۗ أَلَا لَهُ الْخَلْقُ وَالْأَمْرُ ۗ تَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ ( 54 ) አል-አዕራፍ - Aya 54
ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም (ስልጣኑ) በዐርሹ ላይ ተደላደለ፡፡ (አላህ) ሌሊትን በቀን ፈጥኖ የሚፈልገው ሲኾን ይሸፍናል፡፡ ፀሐይንና ጨረቃንም ከዋክብትንም በትእዛዙ የተገሩ ሲኾኑ (ፈጠራቸው)፡፡ ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ) ላቀ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 54
ادْعُوا رَبَّكُمْ تَضَرُّعًا وَخُفْيَةً ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ ( 55 ) አል-አዕራፍ - Aya 55
ጌታችሁን ተዋርዳችሁ በድብቅም ለምኑት፡፡ እርሱ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 55
وَلَا تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ بَعْدَ إِصْلَاحِهَا وَادْعُوهُ خَوْفًا وَطَمَعًا ۚ إِنَّ رَحْمَتَ اللَّهِ قَرِيبٌ مِّنَ الْمُحْسِنِينَ ( 56 ) አል-አዕራፍ - Aya 56
በምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ፡፡ ፈርታችሁና ከጅላችሁም ተገዙት፡፡ የአላህ ችሮታ ከበጎ አድራጊዎች ቅርብ ነውና፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 56
وَهُوَ الَّذِي يُرْسِلُ الرِّيَاحَ بُشْرًا بَيْنَ يَدَيْ رَحْمَتِهِ ۖ حَتَّىٰ إِذَا أَقَلَّتْ سَحَابًا ثِقَالًا سُقْنَاهُ لِبَلَدٍ مَّيِّتٍ فَأَنزَلْنَا بِهِ الْمَاءَ فَأَخْرَجْنَا بِهِ مِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ ۚ كَذَٰلِكَ نُخْرِجُ الْمَوْتَىٰ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ ( 57 ) አል-አዕራፍ - Aya 57
እርሱም ያ ነፋሶችን ከችሮታው (ከዝናም) በፊት አብሳሪዎች አድርጎ የሚልክ ነው፡፡ ከባዳዎችንም ደመናዎች በተሸከሙ ጊዜ ሙት ወደ ኾነ አገር እንነዳዋለን፡፡ በእርሱም ውሃን እናወርዳለን፡፡ ከፍሬዎችም ሁሉ በእርሱ እናወጣለን፡፡ እንደዚሁ ትገነዘቡ ዘንድ ሙታንን (ከመቃብር) እናወጣለን፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 57
وَالْبَلَدُ الطَّيِّبُ يَخْرُجُ نَبَاتُهُ بِإِذْنِ رَبِّهِ ۖ وَالَّذِي خَبُثَ لَا يَخْرُجُ إِلَّا نَكِدًا ۚ كَذَٰلِكَ نُصَرِّفُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَشْكُرُونَ ( 58 ) አል-አዕራፍ - Aya 58
መልካሙም አገር በጌታው ፈቃድ በቃዩ (ያማረ ኾኖ) ይወጣል፡፡ ያም መጥፎ የኾነው (በቃዩ) ደካማ ኾኖ እንጂ አይወጣም፡፡ እንደዚሁ ለሚያመሰግኑ ሕዝቦች ታምራትን እናብራራለን፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 58
لَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَقَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ ( 59 ) አል-አዕራፍ - Aya 59
ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ አላቸውም፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ለእናንተ ከርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 59
قَالَ الْمَلَأُ مِن قَوْمِهِ إِنَّا لَنَرَاكَ فِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ ( 60 ) አል-አዕራፍ - Aya 60
ከሕዝቦቹ (የካዱት) መሪዎቹ፡- «እኛ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ኾነህ በእርግጥ እናይሃለን» አሉት፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 60
قَالَ يَا قَوْمِ لَيْسَ بِي ضَلَالَةٌ وَلَٰكِنِّي رَسُولٌ مِّن رَّبِّ الْعَالَمِينَ ( 61 ) አል-አዕራፍ - Aya 61
አላቸው «ወገኖቼ ሆይ! ምንም መሳሳት የለብኝም፡፡ ግን እኔ ከዓለማት ጌታ መልእክተኛ ነኝ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 61
أُبَلِّغُكُمْ رِسَالَاتِ رَبِّي وَأَنصَحُ لَكُمْ وَأَعْلَمُ مِنَ اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ ( 62 ) አል-አዕራፍ - Aya 62
«የጌታዬን መልክቶች አደርስላችኋለሁ፡፡ ለእናንተም እመክራችኋለሁ፡፡ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ዐውቃለሁ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 62
أَوَعَجِبْتُمْ أَن جَاءَكُمْ ذِكْرٌ مِّن رَّبِّكُمْ عَلَىٰ رَجُلٍ مِّنكُمْ لِيُنذِرَكُمْ وَلِتَتَّقُوا وَلَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ ( 63 ) አል-አዕራፍ - Aya 63
«አላህን ልትፈሩና ይታዘንላችሁም ዘንድ ከእናንተው (ጎሳ) በኾነ ሰው ላይ እንዲያስጠነቅቃችሁ ከጌታችሁ ግሳጼ ቢመጣላችሁ ትደነቃላችሁን» (አላቸው)፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 63
فَكَذَّبُوهُ فَأَنجَيْنَاهُ وَالَّذِينَ مَعَهُ فِي الْفُلْكِ وَأَغْرَقْنَا الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا ۚ إِنَّهُمْ كَانُوا قَوْمًا عَمِينَ ( 64 ) አል-አዕራፍ - Aya 64
ወዲያውም አስተባበሉት፡፡ እርሱንና እነዚያንም ከእርሱ ጋር ያሉትን (አማኞች) በታንኳዋ ውስጥ አዳንናቸው፡፡ እነዚያንም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትን አሰጠምን፡፡ እነርሱ (ልበ) ዕውራን ሕዝቦች ነበሩና፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 64
وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمْ هُودًا ۗ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ ( 65 ) አል-አዕራፍ - Aya 65
ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን፡፡ «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ (የአላህን ቅጣት) አትፈሩምን» አላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 65
قَالَ الْمَلَأُ الَّذِينَ كَفَرُوا مِن قَوْمِهِ إِنَّا لَنَرَاكَ فِي سَفَاهَةٍ وَإِنَّا لَنَظُنُّكَ مِنَ الْكَاذِبِينَ ( 66 ) አል-አዕራፍ - Aya 66
ከሕዝቦቹ እነዚያ የካዱት መሪዎች «እኛ በሞኝነት ላይ ኾነህ በእርግጥ እናይሃለን፡፡ እኛም ከውሸተኞቹ ነህ ብለን እንጠረጥርሃለን» አሉት፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 66
قَالَ يَا قَوْمِ لَيْسَ بِي سَفَاهَةٌ وَلَٰكِنِّي رَسُولٌ مِّن رَّبِّ الْعَالَمِينَ ( 67 ) አል-አዕራፍ - Aya 67
(እርሱም) አላቸው «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ሞኝነት የለብኝም፡፡ ግን እኔ ከዓለማት ጌታ የተላክሁ ነኝ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 67
أُبَلِّغُكُمْ رِسَالَاتِ رَبِّي وَأَنَا لَكُمْ نَاصِحٌ أَمِينٌ ( 68 ) አል-አዕራፍ - Aya 68
«የጌታዬን መልክቶች አደርስላችኋለሁ፡፡ እኔም ለእናንተ ታማኝ መካሪ ነኝ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 68
أَوَعَجِبْتُمْ أَن جَاءَكُمْ ذِكْرٌ مِّن رَّبِّكُمْ عَلَىٰ رَجُلٍ مِّنكُمْ لِيُنذِرَكُمْ ۚ وَاذْكُرُوا إِذْ جَعَلَكُمْ خُلَفَاءَ مِن بَعْدِ قَوْمِ نُوحٍ وَزَادَكُمْ فِي الْخَلْقِ بَسْطَةً ۖ فَاذْكُرُوا آلَاءَ اللَّهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ( 69 ) አል-አዕራፍ - Aya 69
«ከጌታችሁ የኾነ ግሣጼ ከእናንተው ውስጥ ባንድ ሰው ላይ ያስጠነቀቃችሁ ዘንድ ቢመጣባችሁ ትደነቃላችሁን ከኑሕም ሕዝቦች በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በፍጠረትም ግዙፍነትን በጨመረላችሁ ጊዜ አስታውሱ፡፡ የሻችሁትንም ታገኙ ዘንድ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 69
قَالُوا أَجِئْتَنَا لِنَعْبُدَ اللَّهَ وَحْدَهُ وَنَذَرَ مَا كَانَ يَعْبُدُ آبَاؤُنَا ۖ فَأْتِنَا بِمَا تَعِدُنَا إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِينَ ( 70 ) አል-አዕራፍ - Aya 70
«አላህን ብቻውን እንድንገዛ አባቶቻችንም ይገዙት የነበረውን (አማልክት) እንድንተው መጣህብን ከውነተኞች ከኾንክ የምታስፈራብንን (ቅጣት) አምጣብን» አሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 70
قَالَ قَدْ وَقَعَ عَلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ رِجْسٌ وَغَضَبٌ ۖ أَتُجَادِلُونَنِي فِي أَسْمَاءٍ سَمَّيْتُمُوهَا أَنتُمْ وَآبَاؤُكُم مَّا نَزَّلَ اللَّهُ بِهَا مِن سُلْطَانٍ ۚ فَانتَظِرُوا إِنِّي مَعَكُم مِّنَ الْمُنتَظِرِينَ ( 71 ) አል-አዕራፍ - Aya 71
«ከጌታችሁ የኾነ ቅጣትና ቁጣ በእናንተ ላይ በእውነት ተረጋገጠ፡፡ እናንተና አባቶቻችሁም (አማልክት ብላችሁ) በጠራችኋቸው ስሞች አላህ በእርሷ ምንም ማስረጃ ያላወረደባት ስትኾን ትከራከሩኛላችሁን ተጠባባቁም እኔ ከእናንተ ጋር ከተጠባባቂዎቹ ነኝና» አለ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 71
فَأَنجَيْنَاهُ وَالَّذِينَ مَعَهُ بِرَحْمَةٍ مِّنَّا وَقَطَعْنَا دَابِرَ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا ۖ وَمَا كَانُوا مُؤْمِنِينَ ( 72 ) አል-አዕራፍ - Aya 72
እርሱንና እነዚያንም አብረውት የነበሩትን ከእኛ በኾነው ችሮታ (ከቅጣት) አዳንናቸው፡፡ የእነዚያንም በተአምራታችን ያስተባበሉትንና አማኞች ያልነበሩትን መሠረት ቆረጥን፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 72
وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۗ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ قَدْ جَاءَتْكُم بَيِّنَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ هَٰذِهِ نَاقَةُ اللَّهِ لَكُمْ آيَةً ۖ فَذَرُوهَا تَأْكُلْ فِي أَرْضِ اللَّهِ ۖ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوءٍ فَيَأْخُذَكُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ ( 73 ) አል-አዕራፍ - Aya 73
ወደ ሰሙድም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፡፡ አላቸው «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ (እውነተኛ ለመኾኔ) ከጌታችሁ የኾነች ምልክት በእርግጥ መጥታላችኋለች፡፡ ይህች ለእናንተ ተዓምር ስትኾን የአላህ ግመል ናትና ተዋት፡፡ በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ፤ (ትጠጣም)፡፡ በክፉ አትንኳትም፡፡ አሳማሚ ቅጣት ይይዛችኋልና፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 73
وَاذْكُرُوا إِذْ جَعَلَكُمْ خُلَفَاءَ مِن بَعْدِ عَادٍ وَبَوَّأَكُمْ فِي الْأَرْضِ تَتَّخِذُونَ مِن سُهُولِهَا قُصُورًا وَتَنْحِتُونَ الْجِبَالَ بُيُوتًا ۖ فَاذْكُرُوا آلَاءَ اللَّهِ وَلَا تَعْثَوْا فِي الْأَرْضِ مُفْسِدِينَ ( 74 ) አል-አዕራፍ - Aya 74
«ከዓድም በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በምድሪቱም ላይ ባስቀመጣችሁ ጊዜ አስታውሱ፡፡ ከሜዳዎቿ (ሸክላ) ሕንጻዎችን ትገነባላችሁ፡፡ ከተራራዎችም ቤቶችን ትጠርባላችሁ፡፡ ስለዚህ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ፡፡ በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ኾናችሁ አታበላሹ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 74
قَالَ الْمَلَأُ الَّذِينَ اسْتَكْبَرُوا مِن قَوْمِهِ لِلَّذِينَ اسْتُضْعِفُوا لِمَنْ آمَنَ مِنْهُمْ أَتَعْلَمُونَ أَنَّ صَالِحًا مُّرْسَلٌ مِّن رَّبِّهِ ۚ قَالُوا إِنَّا بِمَا أُرْسِلَ بِهِ مُؤْمِنُونَ ( 75 ) አል-አዕራፍ - Aya 75
ከወገኖቹ እነዚያ የኮሩት መሪዎች ለእነዚያ ለተሸነፉት ከነሱ ላመኑት፡- «ሷሊህ ከጌታው መላኩን ታውቃላችሁን» አሏቸው፡፡ « (አዎን)፡- እኛ እርሱ በተላከበት ነገር አማኞች ነን» አሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 75
قَالَ الَّذِينَ اسْتَكْبَرُوا إِنَّا بِالَّذِي آمَنتُم بِهِ كَافِرُونَ ( 76 ) አል-አዕራፍ - Aya 76
እነዚያ የኮሩት፡- «እኛ በዚያ እናንተ በርሱ ባመናችሁበት ከሓዲዎች ነን» አሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 76
فَعَقَرُوا النَّاقَةَ وَعَتَوْا عَنْ أَمْرِ رَبِّهِمْ وَقَالُوا يَا صَالِحُ ائْتِنَا بِمَا تَعِدُنَا إِن كُنتَ مِنَ الْمُرْسَلِينَ ( 77 ) አል-አዕራፍ - Aya 77
ወዲያውም ግመሊቱን ወጓት፡፡ ከጌታቸውም ትዕዛዝ ወጡ፡፡ አሉም፡- «ሷሊህ ሆይ! ከመልክተኞቹ እንደኾንክ የምታስፈራራብንን (ቅጣት) አምጣብን፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 77
فَأَخَذَتْهُمُ الرَّجْفَةُ فَأَصْبَحُوا فِي دَارِهِمْ جَاثِمِينَ ( 78 ) አል-አዕራፍ - Aya 78
ወዲያውም የምድር መንቀጥቀጥ (ጩኸትም) ያዘቻቸው፡፡ በቤቶቻቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አነጉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 78
فَتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَا قَوْمِ لَقَدْ أَبْلَغْتُكُمْ رِسَالَةَ رَبِّي وَنَصَحْتُ لَكُمْ وَلَٰكِن لَّا تُحِبُّونَ النَّاصِحِينَ ( 79 ) አል-አዕራፍ - Aya 79
(ሷሊህ) ከእነርሱም ዞረ፡፡ (እንዲህም) አለ «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልክት በእርግጥ አደረስኩላችሁ፡፡ ለእናንተም መከርኳችሁ፡፡ ግን መካሪዎችን አትወዱም፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 79
وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنْ أَحَدٍ مِّنَ الْعَالَمِينَ ( 80 ) አል-አዕራፍ - Aya 80
ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «አስቀያሚን ሥራ ትሠራላችሁን በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 80
إِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الرِّجَالَ شَهْوَةً مِّن دُونِ النِّسَاءِ ۚ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ مُّسْرِفُونَ ( 81 ) አል-አዕራፍ - Aya 81
«እናንተ ከሴቶች ሌላ ወንዶችን በመከጀል በእርግጥ ትመጡባቸዋላችሁ፡፡ በእውነቱ እናንተ ወሰንን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 81
وَمَا كَانَ جَوَابَ قَوْمِهِ إِلَّا أَن قَالُوا أَخْرِجُوهُم مِّن قَرْيَتِكُمْ ۖ إِنَّهُمْ أُنَاسٌ يَتَطَهَّرُونَ ( 82 ) አል-አዕራፍ - Aya 82
የሕዝቦቹም መልስ « (ሎጥንና ተከታዮቹን) ከከተማችሁ አውጧቸው፡፡ እነሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 82
فَأَنجَيْنَاهُ وَأَهْلَهُ إِلَّا امْرَأَتَهُ كَانَتْ مِنَ الْغَابِرِينَ ( 83 ) አል-አዕራፍ - Aya 83
እርሱንና ቤተሰቦቹንም አዳንናቸው ሚስቱ ብቻ ስትቀር፡፡ እርሷ (ለጥፋት) ከቀሩት ኾነች፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 83
وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا ۖ فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُجْرِمِينَ ( 84 ) አል-አዕራፍ - Aya 84
በእነሱም ላይ (የእሳት) ዝናብን አዘነብንባቸው፡፡ የኃጢአተኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 84
وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا ۗ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ قَدْ جَاءَتْكُم بَيِّنَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ فَأَوْفُوا الْكَيْلَ وَالْمِيزَانَ وَلَا تَبْخَسُوا النَّاسَ أَشْيَاءَهُمْ وَلَا تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ بَعْدَ إِصْلَاحِهَا ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ ( 85 ) አል-አዕራፍ - Aya 85
ወደ መድየንም (ምድያን) ወንድማቸውን ሹዓይብን (ላክን)፤ አላቸው፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ ከጌታችሁ ዘንድ ግልጽ ማስረጃ በእርግጥ መጥታላችኋለች፡፡ ስፍርንና ሚዛንን ሙሉ፡፡ ሰዎችንም አንዳቾቻቸውን (ገንዘቦቻቸውን) አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ፡፡ ይህ ምእምናን እንደኾናችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 85
وَلَا تَقْعُدُوا بِكُلِّ صِرَاطٍ تُوعِدُونَ وَتَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ مَنْ آمَنَ بِهِ وَتَبْغُونَهَا عِوَجًا ۚ وَاذْكُرُوا إِذْ كُنتُمْ قَلِيلًا فَكَثَّرَكُمْ ۖ وَانظُرُوا كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُفْسِدِينَ ( 86 ) አል-አዕራፍ - Aya 86
« (ሰዎችን) የምታስፈራሩና ከአላህም መንገድ በእርሱ ያመኑትን የምታግዱ መጥመሟንም የምትፈልጉዋት ኾናችሁ በየመንገዱ አትቀመጡ፡፡ ጥቂቶችም በነበራችሁና ባበዛችሁ ጊዜ አስታውሱ፡፡ የአጥፊዎችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 86
وَإِن كَانَ طَائِفَةٌ مِّنكُمْ آمَنُوا بِالَّذِي أُرْسِلْتُ بِهِ وَطَائِفَةٌ لَّمْ يُؤْمِنُوا فَاصْبِرُوا حَتَّىٰ يَحْكُمَ اللَّهُ بَيْنَنَا ۚ وَهُوَ خَيْرُ الْحَاكِمِينَ ( 87 ) አል-አዕራፍ - Aya 87
«ከእናንተም በዚያ እኔ በእርሱ በተላክሁበት ያመኑ ጭፍሮችና ያላመኑ ጭፍሮችም ቢኖሩ በመካከላችን አላህ እስከሚፈርድ ታገሱ፡፡ እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 87
قَالَ الْمَلَأُ الَّذِينَ اسْتَكْبَرُوا مِن قَوْمِهِ لَنُخْرِجَنَّكَ يَا شُعَيْبُ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَكَ مِن قَرْيَتِنَا أَوْ لَتَعُودُنَّ فِي مِلَّتِنَا ۚ قَالَ أَوَلَوْ كُنَّا كَارِهِينَ ( 88 ) አል-አዕራፍ - Aya 88
ከሕዝቦቹ እነዚያ የኮሩት መሪዎች፡- «ሹዓይብ ሆይ! አንተንና እነዚያን ከአንተጋር ያመኑትን ከከተማችን በእርግጥ እናስወጣችኋለን፡፡ ወይም ወደ ሃይማኖታችን መመለስ አለባችሁ አሉ፡፡ የጠላንም ብንኾን» አላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 88
قَدِ افْتَرَيْنَا عَلَى اللَّهِ كَذِبًا إِنْ عُدْنَا فِي مِلَّتِكُم بَعْدَ إِذْ نَجَّانَا اللَّهُ مِنْهَا ۚ وَمَا يَكُونُ لَنَا أَن نَّعُودَ فِيهَا إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّنَا ۚ وَسِعَ رَبُّنَا كُلَّ شَيْءٍ عِلْمًا ۚ عَلَى اللَّهِ تَوَكَّلْنَا ۚ رَبَّنَا افْتَحْ بَيْنَنَا وَبَيْنَ قَوْمِنَا بِالْحَقِّ وَأَنتَ خَيْرُ الْفَاتِحِينَ ( 89 ) አል-አዕራፍ - Aya 89
«አላህ ከእርሷ ከአዳነን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ በእርግጥ ውሸትን ቀጠፍን፡፡ አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ለእኛ ወደእርሷ ልንመለስ አይገባንም፡፡ ጌታችን ዕውቀቱ ሁሉን ነገር ሰፋ፡፡ በአላህ ላይ ተጠጋን፡፡ ጌታችን ሆይ! በኛና በወገኖቻችን መካከል በውነት ፍረድ፡፡ አንተም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህ» (አለ) አል-አዕራፍ - Aya 89
وَقَالَ الْمَلَأُ الَّذِينَ كَفَرُوا مِن قَوْمِهِ لَئِنِ اتَّبَعْتُمْ شُعَيْبًا إِنَّكُمْ إِذًا لَّخَاسِرُونَ ( 90 ) አል-አዕራፍ - Aya 90
ከወገኖቹም እነዚያ የካዱት መሪዎች «ሹዓይብን ብትከተሉ እናንተ ያን ጊዜ ከሳሪዎች ናችሁ» አሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 90
فَأَخَذَتْهُمُ الرَّجْفَةُ فَأَصْبَحُوا فِي دَارِهِمْ جَاثِمِينَ ( 91 ) አል-አዕራፍ - Aya 91
ወዲያውም የምድር መንቀጥቀጥ (ጩኸትም) ያዘቻቸው፡፡ በከተማቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አነጉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 91
الَّذِينَ كَذَّبُوا شُعَيْبًا كَأَن لَّمْ يَغْنَوْا فِيهَا ۚ الَّذِينَ كَذَّبُوا شُعَيْبًا كَانُوا هُمُ الْخَاسِرِينَ ( 92 ) አል-አዕራፍ - Aya 92
እነዚያ ሹዓይብን ያሰተባበሉት በእርሷ እንዳልነበሩባት ኾኑ፡፡ እነዚ ሹዓይብን ያስተባበሉት እነርሱ ከሳሪዎች ኾኑ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 92
فَتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَا قَوْمِ لَقَدْ أَبْلَغْتُكُمْ رِسَالَاتِ رَبِّي وَنَصَحْتُ لَكُمْ ۖ فَكَيْفَ آسَىٰ عَلَىٰ قَوْمٍ كَافِرِينَ ( 93 ) አል-አዕራፍ - Aya 93
ከእነርሱም (ትቷቸው) ዞረ፡- «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልክቶች በእርግጥ አደረስኩላችሁ፡፡ ለእናንተም መከርኩ፡፡ ታዲያ በከሓዲዎች ሰዎች ላይ እንዴት አዝናለሁ» አለም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 93
وَمَا أَرْسَلْنَا فِي قَرْيَةٍ مِّن نَّبِيٍّ إِلَّا أَخَذْنَا أَهْلَهَا بِالْبَأْسَاءِ وَالضَّرَّاءِ لَعَلَّهُمْ يَضَّرَّعُونَ ( 94 ) አል-አዕራፍ - Aya 94
በከተማ አንድንም ነቢይ አልላክንም ሰዎችዋን ይዋደቁ ዘንድ በድህነትና በጉዳት የያዝናቸው ብንኾን እንጂ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 94
ثُمَّ بَدَّلْنَا مَكَانَ السَّيِّئَةِ الْحَسَنَةَ حَتَّىٰ عَفَوا وَّقَالُوا قَدْ مَسَّ آبَاءَنَا الضَّرَّاءُ وَالسَّرَّاءُ فَأَخَذْنَاهُم بَغْتَةً وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ ( 95 ) አል-አዕራፍ - Aya 95
ከዚያም እስከበዙና «አባቶቻችንን ድህነትና በሺታ በእርግጥ ነክቷቸዋል፡፡ (ይኽም የጊዜ ልማድ ነው)» እስካሉ ድረስ በመጥፎው ስፍራ በጎውን ለወጥን፡፡ ወዲያውም እነርሱ የማያውቁ ኾነው በድንገት ያዝናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 95
وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ الْقُرَىٰ آمَنُوا وَاتَّقَوْا لَفَتَحْنَا عَلَيْهِم بَرَكَاتٍ مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ وَلَٰكِن كَذَّبُوا فَأَخَذْنَاهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ ( 96 ) አል-አዕራፍ - Aya 96
የከተማዋም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር፡፡ ግን አስተባበሉ፡፡ ይሠሩት በነበሩትም ኃጢኣት ያዝናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 96
أَفَأَمِنَ أَهْلُ الْقُرَىٰ أَن يَأْتِيَهُم بَأْسُنَا بَيَاتًا وَهُمْ نَائِمُونَ ( 97 ) አል-አዕራፍ - Aya 97
የከተማዋ ሰዎችም እነሱ የተኙ ኾነው ቅጣታችን ሌሊት ሊመጣባቸው አይፈሩምን አል-አዕራፍ - Aya 97
أَوَأَمِنَ أَهْلُ الْقُرَىٰ أَن يَأْتِيَهُم بَأْسُنَا ضُحًى وَهُمْ يَلْعَبُونَ ( 98 ) አል-አዕራፍ - Aya 98
የከተማዋ ሰዎችም እነሱ የሚጫወቱ ኾነው ሳሉ ቅጣታችን ቀን በረፋድ ሊመጣባቸው አይፈሩምን አል-አዕራፍ - Aya 98
أَفَأَمِنُوا مَكْرَ اللَّهِ ۚ فَلَا يَأْمَنُ مَكْرَ اللَّهِ إِلَّا الْقَوْمُ الْخَاسِرُونَ ( 99 ) አል-አዕራፍ - Aya 99
የአላህንም ማዘናጋት አይፈሩምን የአላህንም ማዘናጋት ከከሳሪዎች ሕዝቦች በስተቀር የሚተማመን የለም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 99
أَوَلَمْ يَهْدِ لِلَّذِينَ يَرِثُونَ الْأَرْضَ مِن بَعْدِ أَهْلِهَا أَن لَّوْ نَشَاءُ أَصَبْنَاهُم بِذُنُوبِهِمْ ۚ وَنَطْبَعُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَهُمْ لَا يَسْمَعُونَ ( 100 ) አል-አዕራፍ - Aya 100
ለእነዚያ ምድርን ከባለቤቶችዋ (ጥፋት) በኋላ ለሚወርሱት ብንሻ ኖሮ በኃጢኣቶቻቸው የምንቀጣቸው መኾናችን አልተገለጸላቸውምን በልቦቻቸውም ላይ እናትማለን፡፡ ስለዚህ እነርሱ አይሰሙም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 100
تِلْكَ الْقُرَىٰ نَقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنبَائِهَا ۚ وَلَقَدْ جَاءَتْهُمْ رُسُلُهُم بِالْبَيِّنَاتِ فَمَا كَانُوا لِيُؤْمِنُوا بِمَا كَذَّبُوا مِن قَبْلُ ۚ كَذَٰلِكَ يَطْبَعُ اللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِ الْكَافِرِينَ ( 101 ) አል-አዕራፍ - Aya 101
እነዚህ ከተሞች (ከኑሕ እስከ ሹዓይብ ሰዎች የተነገሩት) ከወሬዎቻቸው ባንተ ላይ እንተርካለን፡፡ መልክተኞቻቸውም በግልጽ ተዓምራት በእርግጥ መጥተዋቸዋል፡፡ ከመምጣታቸው በፊት ባስተባበሉትም ነገር የሚያምኑ አልኾኑም፡፡ እንደዚሁ አላህ በከሓዲያን ልቦች ላይ ያትማል፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 101
وَمَا وَجَدْنَا لِأَكْثَرِهِم مِّنْ عَهْدٍ ۖ وَإِن وَجَدْنَا أَكْثَرَهُمْ لَفَاسِقِينَ ( 102 ) አል-አዕራፍ - Aya 102
ለብዙዎቻቸውም በቃል ኪዳናቸው መሙላትን አላገኘንም፡፡ አብዛኞቻቸውንም በእርግጥ አመጸኞች ኾነው አገኘናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 102
ثُمَّ بَعَثْنَا مِن بَعْدِهِم مُّوسَىٰ بِآيَاتِنَا إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَئِهِ فَظَلَمُوا بِهَا ۖ فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُفْسِدِينَ ( 103 ) አል-አዕራፍ - Aya 103
ከዚያም ከበኋላቸው ሙሳን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቶቹ በተዓምራታችን ላክነው፡፡ በእርሷም ካዱ፡፡ ያጥፊዎችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 103
وَقَالَ مُوسَىٰ يَا فِرْعَوْنُ إِنِّي رَسُولٌ مِّن رَّبِّ الْعَالَمِينَ ( 104 ) አል-አዕራፍ - Aya 104
ሙሳም አለ፡- «ፈርዖን ሆይ! እኔ ከዓለማት ጌታ የተላክሁ መልክተኛ ነኝ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 104
حَقِيقٌ عَلَىٰ أَن لَّا أَقُولَ عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ ۚ قَدْ جِئْتُكُم بِبَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ فَأَرْسِلْ مَعِيَ بَنِي إِسْرَائِيلَ ( 105 ) አል-አዕራፍ - Aya 105
«»በአላህ ላይ ከእውነት በቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው፡፡ ከጌታችሁ በተዓምር በእርግጥ መጣኋችሁ፡፡ የእስራኤልንም ልጆች ከእኔ ጋር ልቀቅ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 105
قَالَ إِن كُنتَ جِئْتَ بِآيَةٍ فَأْتِ بِهَا إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِينَ ( 106 ) አል-አዕራፍ - Aya 106
(ፈርዖንም «በተዓምር የመጣህ እንደኾንክ ከውነተኞቹ ከኾንክ እርሷን አምጣት» አለው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 106
فَأَلْقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ ثُعْبَانٌ مُّبِينٌ ( 107 ) አል-አዕራፍ - Aya 107
በትሩንም ጣለ፡፡ እርስዋም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ኾነች፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 107
وَنَزَعَ يَدَهُ فَإِذَا هِيَ بَيْضَاءُ لِلنَّاظِرِينَ ( 108 ) አል-አዕራፍ - Aya 108
እጁንም አወጣ፡፡ እርሷም ወዲያውኑ ለተመልካቾች ነጭ ኾነች፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 108
قَالَ الْمَلَأُ مِن قَوْمِ فِرْعَوْنَ إِنَّ هَٰذَا لَسَاحِرٌ عَلِيمٌ ( 109 ) አል-አዕራፍ - Aya 109
ከፈርዖን ሰዎች መማክርቶቹ፡- «ይህ በእርግጥ ዐዋቂ ድግምተኛ ነው» አሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 109
يُرِيدُ أَن يُخْرِجَكُم مِّنْ أَرْضِكُمْ ۖ فَمَاذَا تَأْمُرُونَ ( 110 ) አል-አዕራፍ - Aya 110
«ከምድራችሁ ሊያወጣችሁ ይሻል» (አሉ)፡፡ «ታዲያ ምን ታዛላችሁ» (አለ) አል-አዕራፍ - Aya 110
قَالُوا أَرْجِهْ وَأَخَاهُ وَأَرْسِلْ فِي الْمَدَائِنِ حَاشِرِينَ ( 111 ) አል-አዕራፍ - Aya 111
(እነርሱም) አሉ «እርሱንና ወንድሙን አቆይ፡፡ ወደ ከተሞቹም ሁሉ ሰብሳቢዎችን (ዘበኞች) ላክ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 111
يَأْتُوكَ بِكُلِّ سَاحِرٍ عَلِيمٍ ( 112 ) አል-አዕራፍ - Aya 112
«ዐዋቂ ድግምተኛ የኾነን ሁሉ ያመጡልሃልና፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 112
وَجَاءَ السَّحَرَةُ فِرْعَوْنَ قَالُوا إِنَّ لَنَا لَأَجْرًا إِن كُنَّا نَحْنُ الْغَالِبِينَ ( 113 ) አል-አዕራፍ - Aya 113
ድግምተኞቹም ወደ ፈርዖን መጡ፡፡ «እኛ አሸናፊዎች ብንኾን ለእኛ በእርግጥ ዋጋ አለን» አሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 113
قَالَ نَعَمْ وَإِنَّكُمْ لَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ ( 114 ) አል-አዕራፍ - Aya 114
«አዎን እናንተም በእርግጥ ከባለሟሎቹ ትኾናላችሁ» አላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 114
قَالُوا يَا مُوسَىٰ إِمَّا أَن تُلْقِيَ وَإِمَّا أَن نَّكُونَ نَحْنُ الْمُلْقِينَ ( 115 ) አል-አዕራፍ - Aya 115
«ሙሳ ሆይ (በትርህን) ወይም (በፊት) ትጥላለህ ወይም እኛ ጣዮች እንኾናለን» አሉት፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 115
قَالَ أَلْقُوا ۖ فَلَمَّا أَلْقَوْا سَحَرُوا أَعْيُنَ النَّاسِ وَاسْتَرْهَبُوهُمْ وَجَاءُوا بِسِحْرٍ عَظِيمٍ ( 116 ) አል-አዕራፍ - Aya 116
«ጣሉ» አላቸው፡፡ (ገመዶቻቸውን) በጣሉም ጊዜ የሰዎቹን ዓይኖች ደገሙባቸው፡፡ አስፈራሩዋቸውም፡፡ ትልቅ ድግምትንም አመጡ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 116
وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ أَنْ أَلْقِ عَصَاكَ ۖ فَإِذَا هِيَ تَلْقَفُ مَا يَأْفِكُونَ ( 117 ) አል-አዕራፍ - Aya 117
ወደ ሙሳም፡- «በትርህን ጣል» ስንል ላክን፡፡ (ጣላትም) ወዲያውኑም የሚቀጣጥፉትን (ማታለያ) ትውጣለች፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 117
فَوَقَعَ الْحَقُّ وَبَطَلَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ ( 118 ) አል-አዕራፍ - Aya 118
እውነቱም ተገለጸ፡፡ ይሠሩት የነበሩትም (ድግምት) ተበላሸ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 118
فَغُلِبُوا هُنَالِكَ وَانقَلَبُوا صَاغِرِينَ ( 119 ) አል-አዕራፍ - Aya 119
እዚያ ዘንድ ተሸነፉም፡፡ ወራዶችም ኾነው ተመለሱ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 119
وَأُلْقِيَ السَّحَرَةُ سَاجِدِينَ ( 120 ) አል-አዕራፍ - Aya 120
ድግምተኞቹም ሰጋጆች ኾነው ወደቁ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 120
قَالُوا آمَنَّا بِرَبِّ الْعَالَمِينَ ( 121 ) አል-አዕራፍ - Aya 121
አሉ፡- «በዓለማት ጌታ አመንን፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 121
رَبِّ مُوسَىٰ وَهَارُونَ ( 122 ) አል-አዕራፍ - Aya 122
«በሙሳና በሃሩን ጌታ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 122
قَالَ فِرْعَوْنُ آمَنتُم بِهِ قَبْلَ أَنْ آذَنَ لَكُمْ ۖ إِنَّ هَٰذَا لَمَكْرٌ مَّكَرْتُمُوهُ فِي الْمَدِينَةِ لِتُخْرِجُوا مِنْهَا أَهْلَهَا ۖ فَسَوْفَ تَعْلَمُونَ ( 123 ) አል-አዕራፍ - Aya 123
ፈርዖን አለ፡- «እኔ ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት በእርሱ አመናችሁን ይህ በከተማይቱ ውስጥ ሰዎቿን ከእርሷ ለማውጣት በእርግጥ የተስማማችሁበት ተንኮል ነው፡፡ ወደፊትም (የሚደርስባችሁን) ታውቃላችሁ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 123
لَأُقَطِّعَنَّ أَيْدِيَكُمْ وَأَرْجُلَكُم مِّنْ خِلَافٍ ثُمَّ لَأُصَلِّبَنَّكُمْ أَجْمَعِينَ ( 124 ) አል-አዕራፍ - Aya 124
«እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማፈራረቅ በእርግጥ እቆራርጣለሁ፡፡ ከዚያም ሁላችሁንም በእርግጥ እሰቅላችኋለሁ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 124
قَالُوا إِنَّا إِلَىٰ رَبِّنَا مُنقَلِبُونَ ( 125 ) አል-አዕራፍ - Aya 125
አሉ፡- «እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 125
وَمَا تَنقِمُ مِنَّا إِلَّا أَنْ آمَنَّا بِآيَاتِ رَبِّنَا لَمَّا جَاءَتْنَا ۚ رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَتَوَفَّنَا مُسْلِمِينَ ( 126 ) አል-አዕራፍ - Aya 126
«የጌታችንም ተዓምራቶች በመጡልን ጊዜ ከማመናችን በቀር ከእኛ አትጠላም፡፡ ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ፡፡ ሙስሊሞች ኾነን ግደለን፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 126
وَقَالَ الْمَلَأُ مِن قَوْمِ فِرْعَوْنَ أَتَذَرُ مُوسَىٰ وَقَوْمَهُ لِيُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ وَيَذَرَكَ وَآلِهَتَكَ ۚ قَالَ سَنُقَتِّلُ أَبْنَاءَهُمْ وَنَسْتَحْيِي نِسَاءَهُمْ وَإِنَّا فَوْقَهُمْ قَاهِرُونَ ( 127 ) አል-አዕራፍ - Aya 127
ከፈርዖንም ሰዎች ታላላቆቹ (ለፈርዖን) «ሙሳንና ሰዎቹን በምድር ላይ እንዲያበላሹና (ሙሳም) አንተንና አማልክቶችህን እንዲተው ትተዋቸዋለህን» አሉ፡፡ «ወንዶች ልጆቻቸውን እንገድላለን፡፡ ሴቶቻቸውንም እናስቀራለን፡፡ እኛም ከበላያቸው ነን፡፡ አሸናፊዎች (ነን)» አለ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 127
قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ اسْتَعِينُوا بِاللَّهِ وَاصْبِرُوا ۖ إِنَّ الْأَرْضَ لِلَّهِ يُورِثُهَا مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ ۖ وَالْعَاقِبَةُ لِلْمُتَّقِينَ ( 128 ) አል-አዕራፍ - Aya 128
ሙሳ ለሰዎቹ፡- «ለአላህ ተገዙ ታገሱም፡፡ ምድር ለአላህ ናትና፡፡ ከባሮቹ ለሚሻው ያወርሳታል፡፡ ምሰጉንዋም ፍጻሜ ለጥንቁቆቹ ናት» አላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 128
قَالُوا أُوذِينَا مِن قَبْلِ أَن تَأْتِيَنَا وَمِن بَعْدِ مَا جِئْتَنَا ۚ قَالَ عَسَىٰ رَبُّكُمْ أَن يُهْلِكَ عَدُوَّكُمْ وَيَسْتَخْلِفَكُمْ فِي الْأَرْضِ فَيَنظُرَ كَيْفَ تَعْمَلُونَ ( 129 ) አል-አዕራፍ - Aya 129
«ከመምጣትህም በፊት ከመጣኽልንም በኋላ ተሰቃየን» አሉት፡፡ «ጌታችሁ ጠላቶቻችሁን ሊያጠፋ እንዴት እንደምትሠሩም ይመለከት ዘንድ በምድር ላይ ሊተካችሁ ይሻል» አላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 129
وَلَقَدْ أَخَذْنَا آلَ فِرْعَوْنَ بِالسِّنِينَ وَنَقْصٍ مِّنَ الثَّمَرَاتِ لَعَلَّهُمْ يَذَّكَّرُونَ ( 130 ) አል-አዕራፍ - Aya 130
የፈርዖንንም ቤተሰቦች እንዲገሰጹ በድርቅ ዓመታትና ከፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ ያዝናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 130
فَإِذَا جَاءَتْهُمُ الْحَسَنَةُ قَالُوا لَنَا هَٰذِهِ ۖ وَإِن تُصِبْهُمْ سَيِّئَةٌ يَطَّيَّرُوا بِمُوسَىٰ وَمَن مَّعَهُ ۗ أَلَا إِنَّمَا طَائِرُهُمْ عِندَ اللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ ( 131 ) አል-አዕራፍ - Aya 131
ደጊቱም ነገር (ምቾት) በመጣችላቸው ጊዜ «ይህች ለእኛ (ተገቢ) ናት» ይላሉ፡፡ ክፉትም ብታገኛቸው በሙሳና አብረውት ባሉት ገደቢስነት ያመካኛሉ፡፡ ንቁ! ገደቢስነታቸው አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 131
وَقَالُوا مَهْمَا تَأْتِنَا بِهِ مِنْ آيَةٍ لِّتَسْحَرَنَا بِهَا فَمَا نَحْنُ لَكَ بِمُؤْمِنِينَ ( 132 ) አል-አዕራፍ - Aya 132
(ለሙሳም) «በማንኛይቱም ተዓምር በእርሷ ልትደግምብን ብትመጣብን እኛ ለአንተ የምናምንልህ አይደለንም» አሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 132
فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ الطُّوفَانَ وَالْجَرَادَ وَالْقُمَّلَ وَالضَّفَادِعَ وَالدَّمَ آيَاتٍ مُّفَصَّلَاتٍ فَاسْتَكْبَرُوا وَكَانُوا قَوْمًا مُّجْرِمِينَ ( 133 ) አል-አዕራፍ - Aya 133
ወዲያም የወሃን ማጥለቅለቅ አንበጣንም ነቀዝንም እንቁራሪቶችንም ደምንም የተለያዩ ተዓምራት ሲኾኑ በነሱ ላይ ላክን ኮሩም ተንኮለኞችም ሕዝቦች ነበሩ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 133
وَلَمَّا وَقَعَ عَلَيْهِمُ الرِّجْزُ قَالُوا يَا مُوسَى ادْعُ لَنَا رَبَّكَ بِمَا عَهِدَ عِندَكَ ۖ لَئِن كَشَفْتَ عَنَّا الرِّجْزَ لَنُؤْمِنَنَّ لَكَ وَلَنُرْسِلَنَّ مَعَكَ بَنِي إِسْرَائِيلَ ( 134 ) አል-አዕራፍ - Aya 134
በእነርሱም ላይ ቅጣቱ በወደቀባቸው ጊዜ «ሙሳ ሆይ! ጌታህን ላንተ ቃል ኪዳን በገባልህ ነገር ለእኛ ለምንልን፡፡ ከእኛ ቅጣቱን ብታነሳልን ለአንተ በእርግጥ እናምንልሃለን፡፡ የእስራኤልንም ልጆች ከአንተ ጋር በእርግጥ እንለቃለን፤» አሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 134
فَلَمَّا كَشَفْنَا عَنْهُمُ الرِّجْزَ إِلَىٰ أَجَلٍ هُم بَالِغُوهُ إِذَا هُمْ يَنكُثُونَ ( 135 ) አል-አዕራፍ - Aya 135
እነርሱም ደራሾቹ እኾኑበት ጊዜ ድረስ ቅጣትን ከእነሱ ላይ ባነሳን ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ቃላቸውን ያፈርሳሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 135
فَانتَقَمْنَا مِنْهُمْ فَأَغْرَقْنَاهُمْ فِي الْيَمِّ بِأَنَّهُمْ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَكَانُوا عَنْهَا غَافِلِينَ ( 136 ) አል-አዕራፍ - Aya 136
እነርሱ በተዓምራታችን ስለአስተባበሉም ከእርሷ ዘንጊዎች ስለኾኑም፤ ከእነሱ ተበቀልን፡፡ በባሕርም ውስጥ አሰጠምናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 136
وَأَوْرَثْنَا الْقَوْمَ الَّذِينَ كَانُوا يُسْتَضْعَفُونَ مَشَارِقَ الْأَرْضِ وَمَغَارِبَهَا الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا ۖ وَتَمَّتْ كَلِمَتُ رَبِّكَ الْحُسْنَىٰ عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ بِمَا صَبَرُوا ۖ وَدَمَّرْنَا مَا كَانَ يَصْنَعُ فِرْعَوْنُ وَقَوْمُهُ وَمَا كَانُوا يَعْرِشُونَ ( 137 ) አል-አዕራፍ - Aya 137
እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ሕዝቦች ያችን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምሥራቆችዋንም ምዕራቦቿንም አወረስናቸው፡፡ የጌታህም መልካሚቱ ቃል በእስራኤል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች፡፡ ፈርዖንና ሰዎቹም ይሠሩት የነበረውን (ሕንጻ) ዳስ ያደርጉትም የነበረውን አፈረስን፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 137
وَجَاوَزْنَا بِبَنِي إِسْرَائِيلَ الْبَحْرَ فَأَتَوْا عَلَىٰ قَوْمٍ يَعْكُفُونَ عَلَىٰ أَصْنَامٍ لَّهُمْ ۚ قَالُوا يَا مُوسَى اجْعَل لَّنَا إِلَٰهًا كَمَا لَهُمْ آلِهَةٌ ۚ قَالَ إِنَّكُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ ( 138 ) አል-አዕራፍ - Aya 138
የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሻገርናቸው፡፡ ለእነርሱ በኾኑ ጣዖታት (መገዛት) ላይ በሚዘወትሩ ሕዝቦች ላይ አለፉም፡፡ «ሙሳ ሆይ፡- ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን» አሉት፡፡ «እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናችሁ፤» አላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 138
إِنَّ هَٰؤُلَاءِ مُتَبَّرٌ مَّا هُمْ فِيهِ وَبَاطِلٌ مَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ ( 139 ) አል-አዕራፍ - Aya 139
«እነዚህ እነርሱ በውስጡ ያሉበት ነገር ጠፊ ነው፡፡ ይሰሩት የነበሩትም ብልሹ ነው» (አላቸው)፤ አል-አዕራፍ - Aya 139
قَالَ أَغَيْرَ اللَّهِ أَبْغِيكُمْ إِلَٰهًا وَهُوَ فَضَّلَكُمْ عَلَى الْعَالَمِينَ ( 140 ) አል-አዕራፍ - Aya 140
«ከአላህ ሌላ እርሱ ከዓለማት ያበለጣችሁ ሲኾን (የምትገዙት) አምላክን እፈልግላችኋለሁን» አለ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 140
وَإِذْ أَنجَيْنَاكُم مِّنْ آلِ فِرْعَوْنَ يَسُومُونَكُمْ سُوءَ الْعَذَابِ ۖ يُقَتِّلُونَ أَبْنَاءَكُمْ وَيَسْتَحْيُونَ نِسَاءَكُمْ ۚ وَفِي ذَٰلِكُم بَلَاءٌ مِّن رَّبِّكُمْ عَظِيمٌ ( 141 ) አል-አዕራፍ - Aya 141
ከፈርዖንም ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሱዋችሁ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚገድሉ ሴቶቻችሁንም የሚተዉ ሲኾኑ ባዳናችሁ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ በዚህም ውስጥ ከጌታችሁ ዘንድ የኾነ ከባድ ፈተና አለበት፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 141
وَوَاعَدْنَا مُوسَىٰ ثَلَاثِينَ لَيْلَةً وَأَتْمَمْنَاهَا بِعَشْرٍ فَتَمَّ مِيقَاتُ رَبِّهِ أَرْبَعِينَ لَيْلَةً ۚ وَقَالَ مُوسَىٰ لِأَخِيهِ هَارُونَ اخْلُفْنِي فِي قَوْمِي وَأَصْلِحْ وَلَا تَتَّبِعْ سَبِيلَ الْمُفْسِدِينَ ( 142 ) አል-አዕራፍ - Aya 142
ሙሳንም ሰላሳን ሌሊት (ሊጾምና ልናነጋግረው) ቀጠርነው፡፡ በዐስርም (ሌሊት) ሞላናት፡፡ የጌታውም ቀጠሮ አርባ ሌሊት ሲኾን ተፈጸመ፡፡ ሙሳም ለወንድሙ ሃሩን «በሕዝቦቼ ላይ ተተካኝ፡፡ አሳምርም የአጥፊዎችንም መንገድ አትከተል» አለው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 142
وَلَمَّا جَاءَ مُوسَىٰ لِمِيقَاتِنَا وَكَلَّمَهُ رَبُّهُ قَالَ رَبِّ أَرِنِي أَنظُرْ إِلَيْكَ ۚ قَالَ لَن تَرَانِي وَلَٰكِنِ انظُرْ إِلَى الْجَبَلِ فَإِنِ اسْتَقَرَّ مَكَانَهُ فَسَوْفَ تَرَانِي ۚ فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُ لِلْجَبَلِ جَعَلَهُ دَكًّا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقًا ۚ فَلَمَّا أَفَاقَ قَالَ سُبْحَانَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُؤْمِنِينَ ( 143 ) አል-አዕራፍ - Aya 143
ሙሳም ለቀጠሯችን በመጣና ጌታውም ባነጋገረው ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! (ነፍስህን) አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና» አለ፡፡ (አላህም)፡- «በፍጹም አታየኝም ግን ወደ ተራራው ተመልከት፡፡ በስፍራውም ቢረጋ በእርግጥ ታየኛለህ» አለው፡፡ ጌታው ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው፡፡ ሙሳም ጮሆ ወደቀ፡፡ በአንሰራራም ጊዜ «ጥራት ይገባህ፡፡ ወዳንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም (በወቅቱ) የምእምናን መጀመሪያ ነኝ» አለ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 143
قَالَ يَا مُوسَىٰ إِنِّي اصْطَفَيْتُكَ عَلَى النَّاسِ بِرِسَالَاتِي وَبِكَلَامِي فَخُذْ مَا آتَيْتُكَ وَكُن مِّنَ الشَّاكِرِينَ ( 144 ) አል-አዕራፍ - Aya 144
(አላህም) አለው፡- «ሙሳ ሆይ! እኔ በመልክቶቼና በማናገሬ በሰዎች ላይ መረጥኩህ፡፡ የሰጡህንም ያዝ፡፡ ከአመስጋኞቹም ኹን፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 144
وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَيْءٍ مَّوْعِظَةً وَتَفْصِيلًا لِّكُلِّ شَيْءٍ فَخُذْهَا بِقُوَّةٍ وَأْمُرْ قَوْمَكَ يَأْخُذُوا بِأَحْسَنِهَا ۚ سَأُرِيكُمْ دَارَ الْفَاسِقِينَ ( 145 ) አል-አዕራፍ - Aya 145
ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼንና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት፡፡ (አልንም) በብርታትም ያዛት፡፡ ሕዝቦችህንም በመልካሟ እንዲይዙ እዘዛቸው፡፡ የአመጸኞቹን አገር በእርግጥ አሳያችኋለሁ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 145
سَأَصْرِفُ عَنْ آيَاتِيَ الَّذِينَ يَتَكَبَّرُونَ فِي الْأَرْضِ بِغَيْرِ الْحَقِّ وَإِن يَرَوْا كُلَّ آيَةٍ لَّا يُؤْمِنُوا بِهَا وَإِن يَرَوْا سَبِيلَ الرُّشْدِ لَا يَتَّخِذُوهُ سَبِيلًا وَإِن يَرَوْا سَبِيلَ الْغَيِّ يَتَّخِذُوهُ سَبِيلًا ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَكَانُوا عَنْهَا غَافِلِينَ ( 146 ) አል-አዕራፍ - Aya 146
እነዚያን ያለአግባብ በምድር ላይ የሚኮሩትን ከአንቀጾቼ በእርግጥ አዞራቸዋለሁ፡፡ ተዓምርንም ሁሉ ቢያዩ በርሷ አያምኑም፡፡ ቅንንም መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው አይዙትም፡፡ ግን የጥመትን መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው ይይዙታል፡፡ ይህ እነርሱ በአንቀጾቻችን ስለአስተባበሉና ከእርሷም ዘንጊዎች ስለኾኑ ነው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 146
وَالَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَلِقَاءِ الْآخِرَةِ حَبِطَتْ أَعْمَالُهُمْ ۚ هَلْ يُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ ( 147 ) አል-አዕራፍ - Aya 147
እነዚያም በአንቀጾቻችንና መጨረሻይቱን ዓለም በመገናኘት ያስተባበሉት ሥራዎቻቸው ተበላሹ፡፡ ይሠሩት የነበረውን እንጂ ይመነዳሉን አል-አዕራፍ - Aya 147
وَاتَّخَذَ قَوْمُ مُوسَىٰ مِن بَعْدِهِ مِنْ حُلِيِّهِمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ ۚ أَلَمْ يَرَوْا أَنَّهُ لَا يُكَلِّمُهُمْ وَلَا يَهْدِيهِمْ سَبِيلًا ۘ اتَّخَذُوهُ وَكَانُوا ظَالِمِينَ ( 148 ) አል-አዕራፍ - Aya 148
የሙሳም ሕዝቦች ከእርሱ (መኼድ) በኋላ ከጌጦቻቸው ወይፈንን አካልን ለርሱ ማግሳት ያለውን (አምላክ አድርገው) ያዙ፡፡ እርሱ የማያናግራቸው መንገድንም የማይመራቸው መኾኑን አይመለከቱምን (አምላክ አድርገው) ያዙት፡፡ በዳዮችም ኾኑ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 148
وَلَمَّا سُقِطَ فِي أَيْدِيهِمْ وَرَأَوْا أَنَّهُمْ قَدْ ضَلُّوا قَالُوا لَئِن لَّمْ يَرْحَمْنَا رَبُّنَا وَيَغْفِرْ لَنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ ( 149 ) አል-አዕራፍ - Aya 149
በተጸጸቱና እነሱም በእርግጥ የተሳሳቱ መኾናቸውን ባዩ ጊዜ፡- «ጌታችን ባያዝንልንና ባይምረን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 149
وَلَمَّا رَجَعَ مُوسَىٰ إِلَىٰ قَوْمِهِ غَضْبَانَ أَسِفًا قَالَ بِئْسَمَا خَلَفْتُمُونِي مِن بَعْدِي ۖ أَعَجِلْتُمْ أَمْرَ رَبِّكُمْ ۖ وَأَلْقَى الْأَلْوَاحَ وَأَخَذَ بِرَأْسِ أَخِيهِ يَجُرُّهُ إِلَيْهِ ۚ قَالَ ابْنَ أُمَّ إِنَّ الْقَوْمَ اسْتَضْعَفُونِي وَكَادُوا يَقْتُلُونَنِي فَلَا تُشْمِتْ بِيَ الْأَعْدَاءَ وَلَا تَجْعَلْنِي مَعَ الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ ( 150 ) አል-አዕራፍ - Aya 150
ሙሳም እየተቆጣና እያዘነ ወደ ሕዝቦቹ በተመለሰ ጊዜ «ከእኔ በኋላ በእኔ ላይ የተካችሁት ነገር ከፋ! የጌታችሁን ትእዛዝ ተቻኮላችሁን» አላቸው፡፡ ሰሌዳዎቹንም ጣላቸው፡፡ የወንድሙንም ራስ (ጸጉር) ወደርሱ የሚጎትተው ሲኾን ያዘ፡፡ (ወንድሙም)፡- «የናቴ ልጅ ሆይ! ሕዝቦቹ ናቁኝ፡፡ ሊገድሉኝም ተቃራቡ፡፡ ስለዚህ በእኔ ጠላቶችን አታስደስትብኝ፡፡ ከአመጸኞች ሕዝቦችም ጋር አታድርገኝ» አለው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 150
قَالَ رَبِّ اغْفِرْ لِي وَلِأَخِي وَأَدْخِلْنَا فِي رَحْمَتِكَ ۖ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ ( 151 ) አል-አዕራፍ - Aya 151
(ሙሳም)፡- «ጌታዬ ሆይ! ለእኔም ለወንድሜም ማር፡፡ በእዝነትህም ውስጥ አግባን፡፡ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» አለ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 151
إِنَّ الَّذِينَ اتَّخَذُوا الْعِجْلَ سَيَنَالُهُمْ غَضَبٌ مِّن رَّبِّهِمْ وَذِلَّةٌ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُفْتَرِينَ ( 152 ) አል-አዕራፍ - Aya 152
እነዚያ ወይፈኑን (አምላክ አድርገው) የያዙ ከጌታቸው ዘንድ ቁጣ፤ በቅርቢቱም ሕይወት ውርደት በእርግጥ ያገኛቸዋል፡፡ እንዲሁም ቀጣፊዎችን እንቀጣለን፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 152
وَالَّذِينَ عَمِلُوا السَّيِّئَاتِ ثُمَّ تَابُوا مِن بَعْدِهَا وَآمَنُوا إِنَّ رَبَّكَ مِن بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ ( 153 ) አል-አዕራፍ - Aya 153
እነዚያም ኃጢአቶችን የሠሩ ከዚያም ከእርሷ በኋላ የተጸጸቱ ያመኑም ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 153
وَلَمَّا سَكَتَ عَن مُّوسَى الْغَضَبُ أَخَذَ الْأَلْوَاحَ ۖ وَفِي نُسْخَتِهَا هُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلَّذِينَ هُمْ لِرَبِّهِمْ يَرْهَبُونَ ( 154 ) አል-አዕራፍ - Aya 154
ከሙሳም ቁጣው በበረደ ጊዜ ሰሌዳዎቹን በግልባጫቸው ውስጥ ለእነዚያ እነርሱ ጌታቸውን የሚፈሩ ለኾኑት መምሪያና እዝነት ያለባቸው ሲኾኑ ያዘ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 154
وَاخْتَارَ مُوسَىٰ قَوْمَهُ سَبْعِينَ رَجُلًا لِّمِيقَاتِنَا ۖ فَلَمَّا أَخَذَتْهُمُ الرَّجْفَةُ قَالَ رَبِّ لَوْ شِئْتَ أَهْلَكْتَهُم مِّن قَبْلُ وَإِيَّايَ ۖ أَتُهْلِكُنَا بِمَا فَعَلَ السُّفَهَاءُ مِنَّا ۖ إِنْ هِيَ إِلَّا فِتْنَتُكَ تُضِلُّ بِهَا مَن تَشَاءُ وَتَهْدِي مَن تَشَاءُ ۖ أَنتَ وَلِيُّنَا فَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا ۖ وَأَنتَ خَيْرُ الْغَافِرِينَ ( 155 ) አል-አዕራፍ - Aya 155
ሙሳም ከሕዝቦቹ ውስጥ ለቀጠሮዋችን ሰባን ሰዎች መረጠ፡፡ ብርቱ የምድር እንቅጥቃጤ በያዘቻቸውም ጊዜ ሙሳ አለ «ጌታዬ ሆይ! በሻህ ኖሮ ከአሁን በፊት በአጠፋሃቸው ነበር፡፡ እኔንም (ባጠፋኸኝ ነበር)፡፡ ከእኛ ቂሎቹ በሠሩት ነገር ታጠፋናለህን እርሷ (ፈተናይቱ) ያንተ ፈተና እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡ በእርሷ የምትሻውን ታሳስታለህ፡፡ የምትሻውንም ታቀናለህ፡፡ አንተ ረዳታችን ነህና ለእኛ ምሕረት አድርግልን፡፡ እዘንልንም፡፡ አንተም ከመሓሪዎች ሁሉ በላጭ ነህ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 155
وَاكْتُبْ لَنَا فِي هَٰذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْآخِرَةِ إِنَّا هُدْنَا إِلَيْكَ ۚ قَالَ عَذَابِي أُصِيبُ بِهِ مَنْ أَشَاءُ ۖ وَرَحْمَتِي وَسِعَتْ كُلَّ شَيْءٍ ۚ فَسَأَكْتُبُهَا لِلَّذِينَ يَتَّقُونَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَالَّذِينَ هُم بِآيَاتِنَا يُؤْمِنُونَ ( 156 ) አል-አዕራፍ - Aya 156
«ለእኛም በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካሟን በመጨረሻይቱም (መልካሟን) ጻፍልን፡፡ እኛ ወደ አንተ ተመለስን፡፡» (ሲል ሙሳ ጸለየ፤ አላህም) አለ፡- «ቅጣቴ በእርሱ የምሻውን ሰው እቀጣበታለሁ፡፡ ችሮታየም ነገሩን ሁሉ ሰፋች፡፡ ለእነዚያም ለሚጠነቀቁ፣ ዘካንም ለሚሰጡ፣ ለእነዚያም እነሱ በአንቀጾቻችን ለሚያምኑ በእርግጥ» እጽፋታለሁ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 156
الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الرَّسُولَ النَّبِيَّ الْأُمِّيَّ الَّذِي يَجِدُونَهُ مَكْتُوبًا عِندَهُمْ فِي التَّوْرَاةِ وَالْإِنجِيلِ يَأْمُرُهُم بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَاهُمْ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ وَيَضَعُ عَنْهُمْ إِصْرَهُمْ وَالْأَغْلَالَ الَّتِي كَانَتْ عَلَيْهِمْ ۚ فَالَّذِينَ آمَنُوا بِهِ وَعَزَّرُوهُ وَنَصَرُوهُ وَاتَّبَعُوا النُّورَ الَّذِي أُنزِلَ مَعَهُ ۙ أُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ ( 157 ) አል-አዕራፍ - Aya 157
ለእነዚያ ያንን እነሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ የኾነውን መልክተኛ የሚከተሉ ለኾኑት (በእርግጥ እጽፍለታለሁ)፡፡ በበጎ ሥራ ያዛቸዋል፡፡ ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል፡፡ መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፡፡ መጥፎ ነገሮችንም በእነርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል፡፡ ከእነሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያንም በእነርሱ ላይ የነበሩትን እንዛዝላዎች (ከባድ ሕግጋቶች) ያነሳላቸዋል፡፡ እነዚያም በእርሱ ያመኑ ያከበሩትም የረዱትም ያንንም ከእርሱ ጋር የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ እነዚያ እነሱ የሚያድኑ ናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 157
قُلْ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُمْ جَمِيعًا الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ يُحْيِي وَيُمِيتُ ۖ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ النَّبِيِّ الْأُمِّيِّ الَّذِي يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَكَلِمَاتِهِ وَاتَّبِعُوهُ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ ( 158 ) አል-አዕራፍ - Aya 158
(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው፡- «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደናንተ ወደሁላችሁም የአላህ መልክተኛ ነኝ፡፡ (እርሱም) ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ የኾነ ነው፡፡ እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ በአላህ በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ ነቢይ በኾነው መልክተኛው እመኑ፡፡ ቅንንም መንገድ ትመሩ ዘንድ ተከተሉት፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 158
وَمِن قَوْمِ مُوسَىٰ أُمَّةٌ يَهْدُونَ بِالْحَقِّ وَبِهِ يَعْدِلُونَ ( 159 ) አል-አዕራፍ - Aya 159
ከሙሳም ሕዝቦች በእውነት የሚመሩት በእርሱም (ፍርድን) የሚያስተካክሉ ጭፍሮች አሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 159
وَقَطَّعْنَاهُمُ اثْنَتَيْ عَشْرَةَ أَسْبَاطًا أُمَمًا ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ إِذِ اسْتَسْقَاهُ قَوْمُهُ أَنِ اضْرِب بِّعَصَاكَ الْحَجَرَ ۖ فَانبَجَسَتْ مِنْهُ اثْنَتَا عَشْرَةَ عَيْنًا ۖ قَدْ عَلِمَ كُلُّ أُنَاسٍ مَّشْرَبَهُمْ ۚ وَظَلَّلْنَا عَلَيْهِمُ الْغَمَامَ وَأَنزَلْنَا عَلَيْهِمُ الْمَنَّ وَالسَّلْوَىٰ ۖ كُلُوا مِن طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ ۚ وَمَا ظَلَمُونَا وَلَٰكِن كَانُوا أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ ( 160 ) አል-አዕራፍ - Aya 160
ዐሥራ ሁለት ነገዶች ሕዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው፡፡ ወደ ሙሳም ወገኖቹ መጠጣትን በፈለጉበት ጊዜ «ድንጋዩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክን፡፡ (መታውም) ከእርሱ ዐሥራ ሁለት ምንጮችም ፈለቁ፡፡ ሰዎቹ ሁሉ መጠጫቸውን በእርግጥ ዐወቁ፡፡ በእነሱም ላይ ደመናን አጠለልን፡፡ በእነሱም ላይ መናንና ድርጭትን አወረድን፡፡ «ከሰጠናችሁም መልካም ሲሳይ ብሉ» (አልን፤ ጸጋችንን በመካዳቸው) አልበደሉንምም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 160
وَإِذْ قِيلَ لَهُمُ اسْكُنُوا هَٰذِهِ الْقَرْيَةَ وَكُلُوا مِنْهَا حَيْثُ شِئْتُمْ وَقُولُوا حِطَّةٌ وَادْخُلُوا الْبَابَ سُجَّدًا نَّغْفِرْ لَكُمْ خَطِيئَاتِكُمْ ۚ سَنَزِيدُ الْمُحْسِنِينَ ( 161 ) አል-አዕራፍ - Aya 161
ለእነርሱም በተባሉ ጊዜ (አስታውስ) «በዚህች ከተማ ተቀመጡ፡፡ ከእርሷም በሻችሁት ስፍራ ብሉ፡፡ (የምንፈልገው) የኃጢኣታችንን መርገፍ ነው በሉም፡፡ የከተማይቱንም በር አጎንብሳችሁ ግቡ፡፡ ኃጢኣቶቻችሁን ለእናንተ እንምራለንና፡፡ በጎ ለሠሩት በእርግጥ እንጨምራለን፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 161
فَبَدَّلَ الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنْهُمْ قَوْلًا غَيْرَ الَّذِي قِيلَ لَهُمْ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ رِجْزًا مِّنَ السَّمَاءِ بِمَا كَانُوا يَظْلِمُونَ ( 162 ) አል-አዕራፍ - Aya 162
ከእነሱም ውስጥ እነዚያ (ራሳቸውን) የበደሉት ሰዎች ከዚያ ለእነርሱ ከተባለው ሌላ የኾነን ቃል ለወጡ፡፡ በእነርሱም ላይ ይበድሉ በነበሩት በደል መዐትን ከሰማይ ላክንባቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 162
وَاسْأَلْهُمْ عَنِ الْقَرْيَةِ الَّتِي كَانَتْ حَاضِرَةَ الْبَحْرِ إِذْ يَعْدُونَ فِي السَّبْتِ إِذْ تَأْتِيهِمْ حِيتَانُهُمْ يَوْمَ سَبْتِهِمْ شُرَّعًا وَيَوْمَ لَا يَسْبِتُونَ ۙ لَا تَأْتِيهِمْ ۚ كَذَٰلِكَ نَبْلُوهُم بِمَا كَانُوا يَفْسُقُونَ ( 163 ) አል-አዕራፍ - Aya 163
ከዚያችም በባህሩ ዳርቻ ከነበረችው ከተማ በቅዳሜ (ቀን) ወሰን ባለፉ ጊዜ በሰንበታቸው ቀን ዐሳዎቻቸው የተከማቹ ኾነው በሚመጡላቸው ጊዜ (የኾነውን) ጠይቃቸው፡፡ ሰንበትንም በማያከብሩበት (በሌላው) ቀን አይመጡላቸውም፡፡ እንደዚሁ ያምጹበት በነበሩት ምክንያት እንሞክራቸዋለን፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 163
وَإِذْ قَالَتْ أُمَّةٌ مِّنْهُمْ لِمَ تَعِظُونَ قَوْمًا ۙ اللَّهُ مُهْلِكُهُمْ أَوْ مُعَذِّبُهُمْ عَذَابًا شَدِيدًا ۖ قَالُوا مَعْذِرَةً إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ ( 164 ) አል-አዕራፍ - Aya 164
ከእነሱም (ከፊሎቹ) ሕዝቦች «አላህ አጥፊያቸው ወይም በብርቱ ቅጣት ቀጪአቸው የኾኑትን ሕዝቦች ለምን ትገስፃጻላችሁ» ባሉ ጊዜ (ገሳጮቹ) «ወደ ጌታችሁ በቂ ምክንያት እንዲኾንና እነርሱም ቢከለከሉ ብለን ነው» አሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 164
فَلَمَّا نَسُوا مَا ذُكِّرُوا بِهِ أَنجَيْنَا الَّذِينَ يَنْهَوْنَ عَنِ السُّوءِ وَأَخَذْنَا الَّذِينَ ظَلَمُوا بِعَذَابٍ بَئِيسٍ بِمَا كَانُوا يَفْسُقُونَ ( 165 ) አል-አዕራፍ - Aya 165
በእርሱም የተገሰጹበትን ነገር በተዉ ጊዜ እነዚያን ከክፉ የሚከለከሉትን አዳንን፤ እነዚያንም የበደሉትን ያምጹ በነበሩት ምክንያት በብርቱ ቅጣት ያዝናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 165
فَلَمَّا عَتَوْا عَن مَّا نُهُوا عَنْهُ قُلْنَا لَهُمْ كُونُوا قِرَدَةً خَاسِئِينَ ( 166 ) አል-አዕራፍ - Aya 166
ከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነሱ «ወረዶች ዝንጀሮች ኹኑ አልን፤» (ኾኑም)፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 166
وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكَ لَيَبْعَثَنَّ عَلَيْهِمْ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ مَن يَسُومُهُمْ سُوءَ الْعَذَابِ ۗ إِنَّ رَبَّكَ لَسَرِيعُ الْعِقَابِ ۖ وَإِنَّهُ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ ( 167 ) አል-አዕራፍ - Aya 167
ጌታህም እስከ ትንሣኤ ቀን ክፉ ቅጣትን የሚያቀምሳቸውን ሰው በነሱ ላይ በእርግጥ የሚልክ መኾኑን ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሳቸው)፡፡ ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ፈጣን ነው፡፡ እርሱም በእርግጥ እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 167
وَقَطَّعْنَاهُمْ فِي الْأَرْضِ أُمَمًا ۖ مِّنْهُمُ الصَّالِحُونَ وَمِنْهُمْ دُونَ ذَٰلِكَ ۖ وَبَلَوْنَاهُم بِالْحَسَنَاتِ وَالسَّيِّئَاتِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ ( 168 ) አል-አዕራፍ - Aya 168
(የእስራኤልን ልጆች) በምድር ላይ የተለያዩ ሕዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው፡፡ ከእነሱ መልካሞች አሉ፡፡ ከእነሱም ከዚያ ሌላ አልሉ፡፡ ይመለሱ ዘንድም በተድላዎችም በመከራዎችም ሞከርናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 168
فَخَلَفَ مِن بَعْدِهِمْ خَلْفٌ وَرِثُوا الْكِتَابَ يَأْخُذُونَ عَرَضَ هَٰذَا الْأَدْنَىٰ وَيَقُولُونَ سَيُغْفَرُ لَنَا وَإِن يَأْتِهِمْ عَرَضٌ مِّثْلُهُ يَأْخُذُوهُ ۚ أَلَمْ يُؤْخَذْ عَلَيْهِم مِّيثَاقُ الْكِتَابِ أَن لَّا يَقُولُوا عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ وَدَرَسُوا مَا فِيهِ ۗ وَالدَّارُ الْآخِرَةُ خَيْرٌ لِّلَّذِينَ يَتَّقُونَ ۗ أَفَلَا تَعْقِلُونَ ( 169 ) አል-አዕራፍ - Aya 169
ከኋላቸውም፡- መጽሐፉን የወረሱ መጥፎ ምትኮች ተተኩ፡፡ የዚህን የቅርቡን ጠፊ ጥቅም ይይዛሉ፡፡ ብጤውም ጥቅም ቢመጣላቸው የሚይዙት ሲኾኑ « (በሠራነው)፡- ለኛ ምሕረት ይደረግልናል» ይላሉ፡፡ በአላህ ላይ ከእውነት በቀር እንዳይናገሩ በእነርሱ ላይ የመጽሐፉ ቃል ኪዳን አልተያዘባቸውምን በእርሱ ውስጥ ያለውንም አላነበቡምን የመጨረሻይቱም አገር ለእነዚያ ጌታቸውን ለሚፈሩት በላጭ ናት፡፡ አታውቁምን አል-አዕራፍ - Aya 169
وَالَّذِينَ يُمَسِّكُونَ بِالْكِتَابِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ إِنَّا لَا نُضِيعُ أَجْرَ الْمُصْلِحِينَ ( 170 ) አል-አዕራፍ - Aya 170
እነዚያም መጽሐፉን ጠብቀው የሚይዙ ሶላትንም በደንቡ የሰገዱ እኛ የመልካም ሠሪዎችን ዋጋ አናጠፋም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 170
وَإِذْ نَتَقْنَا الْجَبَلَ فَوْقَهُمْ كَأَنَّهُ ظُلَّةٌ وَظَنُّوا أَنَّهُ وَاقِعٌ بِهِمْ خُذُوا مَا آتَيْنَاكُم بِقُوَّةٍ وَاذْكُرُوا مَا فِيهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ ( 171 ) አል-አዕራፍ - Aya 171
የጡርን ተራራ ነቅለን ከበላያቸው እንደ ጥላ ኾኖ በአነሳነውና እርሱም በነሱ ላይ ወዳቂ መኾኑን ባረጋገጡ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «የሰጠናችሁን በብርታት ያዙ፡፡ ትጠነቀቁም ዘንድ በውስጡ ያለውን ተገንዘቡ» (አልን)፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 171
وَإِذْ أَخَذَ رَبُّكَ مِن بَنِي آدَمَ مِن ظُهُورِهِمْ ذُرِّيَّتَهُمْ وَأَشْهَدَهُمْ عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَلَسْتُ بِرَبِّكُمْ ۖ قَالُوا بَلَىٰ ۛ شَهِدْنَا ۛ أَن تَقُولُوا يَوْمَ الْقِيَامَةِ إِنَّا كُنَّا عَنْ هَٰذَا غَافِلِينَ ( 172 ) አል-አዕራፍ - Aya 172
ጌታህም ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን ባወጣና «ጌታችሁ አይደለሁምን» ሲል በነፍሶቻቸው ላይ ባስመሰከራቸው ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡ «ጌታችን ነህ መሰከርን» አሉ፡፡ «በትንሣኤ ቀን ከዚህ (ኪዳን) ዘንጊዎች ነበርን እንዳትሉ፡፡» አል-አዕራፍ - Aya 172
أَوْ تَقُولُوا إِنَّمَا أَشْرَكَ آبَاؤُنَا مِن قَبْلُ وَكُنَّا ذُرِّيَّةً مِّن بَعْدِهِمْ ۖ أَفَتُهْلِكُنَا بِمَا فَعَلَ الْمُبْطِلُونَ ( 173 ) አል-አዕራፍ - Aya 173
ወይም «(ጣዖታትን) ያጋሩት ከእኛ በፊት የነበሩት አባቶቻችን ብቻ ናቸው፡፡ እኛም ከእነሱ በኋላ የኾን ዘሮች ነበርን፡፡ አጥፊዎቹ በሠሩት ታጠፋናለህን» እንዳትሉ (አስመሰከርናችሁ)፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 173
وَكَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ الْآيَاتِ وَلَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ ( 174 ) አል-አዕራፍ - Aya 174
እንደዚሁም (እንዲያስቡ) እንዲመለሱም አንቀጾችን እናብራራለን፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 174
وَاتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ الَّذِي آتَيْنَاهُ آيَاتِنَا فَانسَلَخَ مِنْهَا فَأَتْبَعَهُ الشَّيْطَانُ فَكَانَ مِنَ الْغَاوِينَ ( 175 ) አል-አዕራፍ - Aya 175
የዚያንም ተዓምራታችንን የሰጠነውንና ከእርሷ የወጣውን ሰይጣንም ያስከተለውን ከጠማሞቹም የኾነውን ሰው ወሬ በእነርሱ ላይ አንብብላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 175
وَلَوْ شِئْنَا لَرَفَعْنَاهُ بِهَا وَلَٰكِنَّهُ أَخْلَدَ إِلَى الْأَرْضِ وَاتَّبَعَ هَوَاهُ ۚ فَمَثَلُهُ كَمَثَلِ الْكَلْبِ إِن تَحْمِلْ عَلَيْهِ يَلْهَثْ أَوْ تَتْرُكْهُ يَلْهَث ۚ ذَّٰلِكَ مَثَلُ الْقَوْمِ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا ۚ فَاقْصُصِ الْقَصَصَ لَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ ( 176 ) አል-አዕራፍ - Aya 176
በሻንም ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር፡፡ እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ፡፡ ፍላጎቱንም ተከተለ፡፡ ብጤውም ብታባርረው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ ወይም ብትተወው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ እንደ ኾነ ውሻ ነው፡፡ ይህ የእነዚያ በአንቀጾቻችን ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ነው፡፡ ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 176
سَاءَ مَثَلًا الْقَوْمُ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَأَنفُسَهُمْ كَانُوا يَظْلِمُونَ ( 177 ) አል-አዕራፍ - Aya 177
የእነዚያ በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትና ነፍሶቻቸውን ይበድሉ የነበሩት ሰዎች ምሳሌ ከፋ! አል-አዕራፍ - Aya 177
مَن يَهْدِ اللَّهُ فَهُوَ الْمُهْتَدِي ۖ وَمَن يُضْلِلْ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ ( 178 ) አል-አዕራፍ - Aya 178
አላህ የሚያቀናው ሰው ቅን እርሱ ነው፡፡ የሚያጠመውም ሰው እነዚያ ከሳሪዎቹ እነሱ ናቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 178
وَلَقَدْ ذَرَأْنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرًا مِّنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ ۖ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا ۚ أُولَٰئِكَ كَالْأَنْعَامِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ ۚ أُولَٰئِكَ هُمُ الْغَافِلُونَ ( 179 ) አል-አዕራፍ - Aya 179
ከጋኔንም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ለእነርሱ በርሳቸው የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው፡፡ ለእነሱም በሳቸው የማያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸው፡፡ ለእነሱም በሳቸው የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸው፡፡ እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው፡፡ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው፤ አል-አዕራፍ - Aya 179
وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ فَادْعُوهُ بِهَا ۖ وَذَرُوا الَّذِينَ يُلْحِدُونَ فِي أَسْمَائِهِ ۚ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ ( 180 ) አል-አዕራፍ - Aya 180
ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፡፡ (ስትጸልዩ) በእርሷም ጥሩት፡፡ እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው፡፡ ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይምመነዳሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 180
وَمِمَّنْ خَلَقْنَا أُمَّةٌ يَهْدُونَ بِالْحَقِّ وَبِهِ يَعْدِلُونَ ( 181 ) አል-አዕራፍ - Aya 181
ከፈጠርናቸውም ሰዎች በእውነት የሚመሩ በእርሱም (ፍርድን) የሚያስተካክሉ ሕዝቦች አልሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 181
وَالَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا سَنَسْتَدْرِجُهُم مِّنْ حَيْثُ لَا يَعْلَمُونَ ( 182 ) አል-አዕራፍ - Aya 182
እነዚያንም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትን ከማያውቁት ስፍራ ቀስ በቀስ (ምቾትን በመጨመር) እናዘነጋቸዋለን፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 182
وَأُمْلِي لَهُمْ ۚ إِنَّ كَيْدِي مَتِينٌ ( 183 ) አል-አዕራፍ - Aya 183
ለእነርሱም ጊዜ እሰጣቸዋለሁ ጥበቤ ብርቱ ነውና፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 183
أَوَلَمْ يَتَفَكَّرُوا ۗ مَا بِصَاحِبِهِم مِّن جِنَّةٍ ۚ إِنْ هُوَ إِلَّا نَذِيرٌ مُّبِينٌ ( 184 ) አል-አዕራፍ - Aya 184
በነቢያቸው (በሙሐመድ) ምንም ዕብደት የሌለበት መኾኑን አያስተውሉምን እርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 184
أَوَلَمْ يَنظُرُوا فِي مَلَكُوتِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا خَلَقَ اللَّهُ مِن شَيْءٍ وَأَنْ عَسَىٰ أَن يَكُونَ قَدِ اقْتَرَبَ أَجَلُهُمْ ۖ فَبِأَيِّ حَدِيثٍ بَعْدَهُ يُؤْمِنُونَ ( 185 ) አል-አዕራፍ - Aya 185
በሰማያትና በምድር ግዛት ውስጥ ከማንኛው ነገር አላህ በፈጠረውም ሁሉ የሞት ጊዜያቸውም በእርግጥ መቅረቡ የሚፈራ መኾኑን አያስተውሉምን ከእርሱም (ከቁርኣን) ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 185
مَن يُضْلِلِ اللَّهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ ۚ وَيَذَرُهُمْ فِي طُغْيَانِهِمْ يَعْمَهُونَ ( 186 ) አል-አዕራፍ - Aya 186
አላህ የሚያጠመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኝ የለውም፡፡ በጥምመታቸውም ውስጥ እየዋለሉ ይተዋቸዋል፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 186
يَسْأَلُونَكَ عَنِ السَّاعَةِ أَيَّانَ مُرْسَاهَا ۖ قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِندَ رَبِّي ۖ لَا يُجَلِّيهَا لِوَقْتِهَا إِلَّا هُوَ ۚ ثَقُلَتْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ لَا تَأْتِيكُمْ إِلَّا بَغْتَةً ۗ يَسْأَلُونَكَ كَأَنَّكَ حَفِيٌّ عَنْهَا ۖ قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِندَ اللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ ( 187 ) አል-አዕራፍ - Aya 187
ከሰዓቲቱ መቼ እንደምትረጋ (እንደምትመጣ) ይጠይቁሃል፡፡ «ዕውቀቷ በጌታዬ ዘንድ ነው፡፡ በጊዜዋ እርሱ እንጂ ሌላ አይገልጣትም፡፡ በሰማያትና በምድርም ከበደች፡፡ በድንገት ቢኾን እንጂ አትመጣችሁም» በላቸው፡፡ ከእርሷ አጥብቀህ እንደ ተረዳህ አድርገው ይጠይቁሃል፡፡ «ዕውቀቷ አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም» በላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 187
قُل لَّا أَمْلِكُ لِنَفْسِي نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ الْغَيْبَ لَاسْتَكْثَرْتُ مِنَ الْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِيَ السُّوءُ ۚ إِنْ أَنَا إِلَّا نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ ( 188 ) አል-አዕራፍ - Aya 188
«አላህ የሻውን በስተቀር ለእራሴ ጥቅምንም ጉዳትንም ማምጣት አልችልም፡፡ ሩቅንም (ምስጢር) የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር፡፡ እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 188
هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَجَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا لِيَسْكُنَ إِلَيْهَا ۖ فَلَمَّا تَغَشَّاهَا حَمَلَتْ حَمْلًا خَفِيفًا فَمَرَّتْ بِهِ ۖ فَلَمَّا أَثْقَلَت دَّعَوَا اللَّهَ رَبَّهُمَا لَئِنْ آتَيْتَنَا صَالِحًا لَّنَكُونَنَّ مِنَ الشَّاكِرِينَ ( 189 ) አል-አዕራፍ - Aya 189
እርሱ ያ ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁ ከእርሷም መቀናጆዋን ወደርሷ ይረካ ዘንድ ያደረገ ነው፡፡ በተገናኛትም ጊዜ ቀላልን እርግዝና አረገዘች፡፡ እርሱንም (ፅንሱን) ይዛው ኼደች፡፡ በከበደችም ጊዜ «ደግን ልጅ ብትሰጠን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንኾናለን፤» ሲሉ ጌታቸውን አላህን ለመኑ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 189
فَلَمَّا آتَاهُمَا صَالِحًا جَعَلَا لَهُ شُرَكَاءَ فِيمَا آتَاهُمَا ۚ فَتَعَالَى اللَّهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ ( 190 ) አል-አዕራፍ - Aya 190
መልካም ልጅ በሰጣቸውም ጊዜ በሰጣቸው ልጅ (ስም) ለእርሱ ተጋሪዎችን አደረጉለት፡፡ አላህም ከሚያጋሩት ሁሉ ላቀ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 190
أَيُشْرِكُونَ مَا لَا يَخْلُقُ شَيْئًا وَهُمْ يُخْلَقُونَ ( 191 ) አል-አዕራፍ - Aya 191
ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን (በአላህ) ያጋራሉን አል-አዕራፍ - Aya 191
وَلَا يَسْتَطِيعُونَ لَهُمْ نَصْرًا وَلَا أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ ( 192 ) አል-አዕራፍ - Aya 192
ለእነርሱም መርዳትን የማይችሉትን ነፍሶቻቸውንም የማይረዱትን (ያጋራሉን) አል-አዕራፍ - Aya 192
وَإِن تَدْعُوهُمْ إِلَى الْهُدَىٰ لَا يَتَّبِعُوكُمْ ۚ سَوَاءٌ عَلَيْكُمْ أَدَعَوْتُمُوهُمْ أَمْ أَنتُمْ صَامِتُونَ ( 193 ) አል-አዕራፍ - Aya 193
(ጣዖቶቹን) ወደ ቅን መንገድ ብትጠሩዋቸውም አይከተሉዋችሁም፡፡ ብትጠሩዋቸው ወይም እናንተ ዝምተኞችም ብትኾኑ በእናንተ ላይ እኩል ነው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 193
إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ ( 194 ) አል-አዕራፍ - Aya 194
እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገ³ቸው ብጤዎቻችሁ ተገዢዎች ናቸው፡፡ እውነተኞችም እንደኾናችሁ ጥሩዋቸውና ለእናንተ ይመልሱላችሁ፤ (መመለስ ግን አይችሉም)፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 194
أَلَهُمْ أَرْجُلٌ يَمْشُونَ بِهَا ۖ أَمْ لَهُمْ أَيْدٍ يَبْطِشُونَ بِهَا ۖ أَمْ لَهُمْ أَعْيُنٌ يُبْصِرُونَ بِهَا ۖ أَمْ لَهُمْ آذَانٌ يَسْمَعُونَ بِهَا ۗ قُلِ ادْعُوا شُرَكَاءَكُمْ ثُمَّ كِيدُونِ فَلَا تُنظِرُونِ ( 195 ) አል-አዕራፍ - Aya 195
ለእነርሱ በእርሳቸው የሚኼዱባቸው እግሮች አሉዋቸውን ወይስ ለእነሱ በርሳቸው የሚጨብጡባቸው እጆች አሉዋቸውን ወይስ ለእነሱ በእርሳቸው የሚያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸውን ወይስ ለእነሱ በእርሳቸው የሚሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸውን «ያጋራችኋቸውን ጥሩ ከዚያም ተተናኮሉኝ፡፡ ጊዜም አትስጡኝ፤ (አልፈራችሁም)» በላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 195
إِنَّ وَلِيِّيَ اللَّهُ الَّذِي نَزَّلَ الْكِتَابَ ۖ وَهُوَ يَتَوَلَّى الصَّالِحِينَ ( 196 ) አል-አዕራፍ - Aya 196
«የእኔ ረዳቴ ያ መጽሐፉን (ቁርኣንን) ያወረደልኝ አላህ ነውና፤ እርሱም መልካም ሠሪዎችን ይረዳል» (በላቸው)፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 196
وَالَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَا أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ ( 197 ) አል-አዕራፍ - Aya 197
እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትገ³ቸው ሊረÇችሁ አይችሉም፡፡ ነፍሶቻቸውንም አይረዱም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 197
وَإِن تَدْعُوهُمْ إِلَى الْهُدَىٰ لَا يَسْمَعُوا ۖ وَتَرَاهُمْ يَنظُرُونَ إِلَيْكَ وَهُمْ لَا يُبْصِرُونَ ( 198 ) አል-አዕራፍ - Aya 198
«ወደ ቅንም መንገድ (እንዲመሩዋችሁ) ብትጠሩዋቸው አይሰሙም፤» (በላቸው)፡፡ እነርሱንም የማያዩ ሲኾኑ ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 198
خُذِ الْعَفْوَ وَأْمُرْ بِالْعُرْفِ وَأَعْرِضْ عَنِ الْجَاهِلِينَ ( 199 ) አል-አዕራፍ - Aya 199
ገርን ጠባይ ያዝ፡፡ በመልካምም እዘዝ፡፡ ባለጌዎቹንም ተዋቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 199
وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ ( 200 ) አል-አዕራፍ - Aya 200
ከሰይጣንም (በኩል) ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 200
إِنَّ الَّذِينَ اتَّقَوْا إِذَا مَسَّهُمْ طَائِفٌ مِّنَ الشَّيْطَانِ تَذَكَّرُوا فَإِذَا هُم مُّبْصِرُونَ ( 201 ) አል-አዕራፍ - Aya 201
እነዚያ የተጠነቀቁት ከሰይጣን የኾነ ዘዋሪ በነካቸው ጊዜ (ጌታቸውን) ይገነዘባሉ፡፡ ወዲያውም እነሱ ተመልካቾች ይኾናሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 201
وَإِخْوَانُهُمْ يَمُدُّونَهُمْ فِي الْغَيِّ ثُمَّ لَا يُقْصِرُونَ ( 202 ) አል-አዕራፍ - Aya 202
ወንድሞቻቸውም ጥመትን ይጨምሩላቸዋል፤ ከዚያም (እነርሱ) አይገቱም፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 202
وَإِذَا لَمْ تَأْتِهِم بِآيَةٍ قَالُوا لَوْلَا اجْتَبَيْتَهَا ۚ قُلْ إِنَّمَا أَتَّبِعُ مَا يُوحَىٰ إِلَيَّ مِن رَّبِّي ۚ هَٰذَا بَصَائِرُ مِن رَّبِّكُمْ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ ( 203 ) አል-አዕራፍ - Aya 203
በተዓምርም ባልመጣሃቸው ጊዜ (በራስህ) «ለምን አትፈጥራትም» ይላሉ፡፡ ከጌታዬ ወደኔ የተወረደውን ብቻ እከተላለሁ፡፡ ይህ (ቁርኣን) ከጌታችሁ ሲኾን ለሚያምኑ ሕዝቦች መረጃዎችና መምሪያ እዝነትም ነው በላቸው፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 203
وَإِذَا قُرِئَ الْقُرْآنُ فَاسْتَمِعُوا لَهُ وَأَنصِتُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ ( 204 ) አል-አዕራፍ - Aya 204
ቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፡፡ ጸጥም በሉ፡፡ ይታዘንላችኋልና፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 204
وَاذْكُر رَّبَّكَ فِي نَفْسِكَ تَضَرُّعًا وَخِيفَةً وَدُونَ الْجَهْرِ مِنَ الْقَوْلِ بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ الْغَافِلِينَ ( 205 ) አል-አዕራፍ - Aya 205
ጌታህንም በምስጢር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በኾነ ቃል በጧትም በማታም አውሳው፡፡ ከዘንጊዎቹም አትኹን፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 205
إِنَّ الَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيُسَبِّحُونَهُ وَلَهُ يَسْجُدُونَ ۩ ( 206 ) አል-አዕራፍ - Aya 206
እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት (መላእክት) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፡፡ ያወድሱታልም፡፡ ለእርሱም ብቻ ይሰግዳሉ፡፡ አል-አዕራፍ - Aya 206
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah