Surah አል በለድ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል በለድ - Aya count 20
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
لَا أُقْسِمُ بِهَٰذَا الْبَلَدِ ( 1 ) አል በለድ - Aya 1
በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡ አል በለድ - Aya 1
وَأَنتَ حِلٌّ بِهَٰذَا الْبَلَدِ ( 2 ) አል በለድ - Aya 2
አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡ አል በለድ - Aya 2
وَوَالِدٍ وَمَا وَلَدَ ( 3 ) አል በለድ - Aya 3
በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡ አል በለድ - Aya 3
لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ فِي كَبَدٍ ( 4 ) አል በለድ - Aya 4
ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡ አል በለድ - Aya 4
أَيَحْسَبُ أَن لَّن يَقْدِرَ عَلَيْهِ أَحَدٌ ( 5 ) አል በለድ - Aya 5
በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን? አል በለድ - Aya 5
يَقُولُ أَهْلَكْتُ مَالًا لُّبَدًا ( 6 ) አል በለድ - Aya 6
«ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡ አል በለድ - Aya 6
أَيَحْسَبُ أَن لَّمْ يَرَهُ أَحَدٌ ( 7 ) አል በለድ - Aya 7
አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን? አል በለድ - Aya 7
أَلَمْ نَجْعَل لَّهُ عَيْنَيْنِ ( 8 ) አል በለድ - Aya 8
ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን? አል በለድ - Aya 8
وَلِسَانًا وَشَفَتَيْنِ ( 9 ) አል በለድ - Aya 9
ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡ አል በለድ - Aya 9
وَهَدَيْنَاهُ النَّجْدَيْنِ ( 10 ) አል በለድ - Aya 10
ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን? አል በለድ - Aya 10
فَلَا اقْتَحَمَ الْعَقَبَةَ ( 11 ) አል በለድ - Aya 11
ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡ አል በለድ - Aya 11
وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْعَقَبَةُ ( 12 ) አል በለድ - Aya 12
ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? አል በለድ - Aya 12
فَكُّ رَقَبَةٍ ( 13 ) አል በለድ - Aya 13
(እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡ አል በለድ - Aya 13
أَوْ إِطْعَامٌ فِي يَوْمٍ ذِي مَسْغَبَةٍ ( 14 ) አል በለድ - Aya 14
ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡ አል በለድ - Aya 14
يَتِيمًا ذَا مَقْرَبَةٍ ( 15 ) አል በለድ - Aya 15
የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤ አል በለድ - Aya 15
أَوْ مِسْكِينًا ذَا مَتْرَبَةٍ ( 16 ) አል በለድ - Aya 16
ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡ አል በለድ - Aya 16
ثُمَّ كَانَ مِنَ الَّذِينَ آمَنُوا وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ وَتَوَاصَوْا بِالْمَرْحَمَةِ ( 17 ) አል በለድ - Aya 17
(ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡ አል በለድ - Aya 17
أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ ( 18 ) አል በለድ - Aya 18
እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡ አል በለድ - Aya 18
وَالَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِنَا هُمْ أَصْحَابُ الْمَشْأَمَةِ ( 19 ) አል በለድ - Aya 19
እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡ አል በለድ - Aya 19
عَلَيْهِمْ نَارٌ مُّؤْصَدَةٌ ( 20 ) አል በለድ - Aya 20
በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡ አል በለድ - Aya 20
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah