Surah አል-ረዕድ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል-ረዕድ - Aya count 43
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
المر ۚ تِلْكَ آيَاتُ الْكِتَابِ ۗ وَالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ الْحَقُّ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ ( 1 ) አል-ረዕድ - Aya 1
አ.ለ.መ.ረ (አሊፍ ላም ሚም ራ) ይህች (አናቅጽ) ከመጽሐፉ አንቀጾች ናት፡፡ ያም ከጌታህ ወዳንተ የተወረደው እውነት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያምኑም፡፡ አል-ረዕድ - Aya 1
اللَّهُ الَّذِي رَفَعَ السَّمَاوَاتِ بِغَيْرِ عَمَدٍ تَرَوْنَهَا ۖ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ ۖ وَسَخَّرَ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ ۖ كُلٌّ يَجْرِي لِأَجَلٍ مُّسَمًّى ۚ يُدَبِّرُ الْأَمْرَ يُفَصِّلُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُم بِلِقَاءِ رَبِّكُمْ تُوقِنُونَ ( 2 ) አል-ረዕድ - Aya 2
አላህ ያ ሰማያትን የምታዩዋት አዕማድ ሳትኖር ያነሳት ከዚያም በዐርሹ (ዙፋኑ) ላይ (ስልጣኑ) የተደላደለ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ነው፡፡ ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ፡፡ ነገሩን ሁሉ ያስተናብራል፡፡ በጌታችሁ መገናኘት ታረጋግጡ ዘንድ ተዓምራቶችን ይዘረዝራል፡፡ አል-ረዕድ - Aya 2
وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ ۖ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ ( 3 ) አል-ረዕድ - Aya 3
እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በሷም ተራራዎችንና ወንዞችን ያደረገ በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ዓይነቶችን ያደረገ ነው፡፡ ሌሊትን በቀን ይሸፍናል፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ምልክቶች አሉ፡፡ አል-ረዕድ - Aya 3
وَفِي الْأَرْضِ قِطَعٌ مُّتَجَاوِرَاتٌ وَجَنَّاتٌ مِّنْ أَعْنَابٍ وَزَرْعٌ وَنَخِيلٌ صِنْوَانٌ وَغَيْرُ صِنْوَانٍ يُسْقَىٰ بِمَاءٍ وَاحِدٍ وَنُفَضِّلُ بَعْضَهَا عَلَىٰ بَعْضٍ فِي الْأُكُلِ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ ( 4 ) አል-ረዕድ - Aya 4
በምድርም የተጎራበቱ ቁርጥራጮች አልሉ፡፡ ከወይኖችም አትክልቶች አዝርዕቶችም መንታዎችና መንታዎች ያልኾኑ ዘንባባዎችም አልሉ፡፡ በአንድ ውሃ ይጠጣሉ፤ (በጣዕምም ይለያያሉ)፡፡ ከፊሉዋንም በከፊሉ ላይ በሚበላው ሰብል እናበልጣለን፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች ተዓምራት አለበት፡፡ አል-ረዕድ - Aya 4
وَإِن تَعْجَبْ فَعَجَبٌ قَوْلُهُمْ أَإِذَا كُنَّا تُرَابًا أَإِنَّا لَفِي خَلْقٍ جَدِيدٍ ۗ أُولَٰئِكَ الَّذِينَ كَفَرُوا بِرَبِّهِمْ ۖ وَأُولَٰئِكَ الْأَغْلَالُ فِي أَعْنَاقِهِمْ ۖ وَأُولَٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ ( 5 ) አል-ረዕድ - Aya 5
ብትደነቅም ዐፈር በኾንን ጊዜ እና አዲስ ፍጥረት እንኾናለን ማለታቸው (ታላቅ) ድንቅ ነው፡፡ እነዚህ እነዚያ በጌታቸው የካዱት ናቸው፡፡ እነዚህም እንዛዝላዎች በአንገቶቻቸው ላይ ያሉባቸው ናቸው፡፡ እነዚሀም የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 5
وَيَسْتَعْجِلُونَكَ بِالسَّيِّئَةِ قَبْلَ الْحَسَنَةِ وَقَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِمُ الْمَثُلَاتُ ۗ وَإِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغْفِرَةٍ لِّلنَّاسِ عَلَىٰ ظُلْمِهِمْ ۖ وَإِنَّ رَبَّكَ لَشَدِيدُ الْعِقَابِ ( 6 ) አል-ረዕድ - Aya 6
ከእነሱ በፊት የመሰሎቻቸው ቅጣቶች በእርግጥ ያለፉ ሲኾኑ ከመልካሙ በፊት በመጥፎው ያስቸኩሉሃል፡፡ ጌታህም ለሰዎች ከመበደላቸው ጋር በእርግጥ የምህረት ባለቤት ነው፡፡ ጌታህም በእርግጥ ቅጣተ ብርቱ ነው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 6
وَيَقُولُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْلَا أُنزِلَ عَلَيْهِ آيَةٌ مِّن رَّبِّهِ ۗ إِنَّمَا أَنتَ مُنذِرٌ ۖ وَلِكُلِّ قَوْمٍ هَادٍ ( 7 ) አል-ረዕድ - Aya 7
እነዚያም የካዱት በእርሱ ላይ ከጌታው ተዓምር ለምን አልተወረደለትም ይላሉ፡፡ አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ፡፡ ለሕዝብም ሁሉ መሪ አላቸው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 7
اللَّهُ يَعْلَمُ مَا تَحْمِلُ كُلُّ أُنثَىٰ وَمَا تَغِيضُ الْأَرْحَامُ وَمَا تَزْدَادُ ۖ وَكُلُّ شَيْءٍ عِندَهُ بِمِقْدَارٍ ( 8 ) አል-ረዕድ - Aya 8
አላህ ሴት ሁሉ የምታረግዘውን ያውቃል፡፡ ማሕጸኖችም የሚያጎድሉትን የሚጨምሩትንም (ያውቃል)፡፡ ነገሩም ሁሉ እርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነው፡፤ አል-ረዕድ - Aya 8
عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ الْكَبِيرُ الْمُتَعَالِ ( 9 ) አል-ረዕድ - Aya 9
ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ታላቅ የላቀ ነው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 9
سَوَاءٌ مِّنكُم مَّنْ أَسَرَّ الْقَوْلَ وَمَن جَهَرَ بِهِ وَمَنْ هُوَ مُسْتَخْفٍ بِاللَّيْلِ وَسَارِبٌ بِالنَّهَارِ ( 10 ) አል-ረዕድ - Aya 10
ከእናንተ ውስጥ ቃሉን ዝቅ ያደረገ ሰው በእርሱ የጮኸም ሰው እርሱ በሌሊት ተደባቂም በቀን (ተገልጾ) ኺያጅም የኾነ ሰው (እርሱ ዘንድ) እኩል ነው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 10
لَهُ مُعَقِّبَاتٌ مِّن بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ يَحْفَظُونَهُ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا مَا بِأَنفُسِهِمْ ۗ وَإِذَا أَرَادَ اللَّهُ بِقَوْمٍ سُوءًا فَلَا مَرَدَّ لَهُ ۚ وَمَا لَهُم مِّن دُونِهِ مِن وَالٍ ( 11 ) አል-ረዕድ - Aya 11
ለእርሱ (ለሰው) ከስተፊቱም ከኋላውም በአላህ ትዕዛዝ (ከክፉ) የሚጠብቁት ተተካኪዎች (መላእክት) አሉት፡፡ አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን (ኹኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም፡፡ አላህም በሰዎች ላይ ክፉን በሻ ጊዜ ለእርሱ መመለስ የለውም፡፡ ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም ተከላካይ የላቸውም፡፡ አል-ረዕድ - Aya 11
هُوَ الَّذِي يُرِيكُمُ الْبَرْقَ خَوْفًا وَطَمَعًا وَيُنشِئُ السَّحَابَ الثِّقَالَ ( 12 ) አል-ረዕድ - Aya 12
እርሱ ያ የምትፈሩና የምትከጅሉም ስትሆኑ ብልጭታን የሚያሳያችሁ ከባዶች ደመናዎችንም የሚያስገኝ ነው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 12
وَيُسَبِّحُ الرَّعْدُ بِحَمْدِهِ وَالْمَلَائِكَةُ مِنْ خِيفَتِهِ وَيُرْسِلُ الصَّوَاعِقَ فَيُصِيبُ بِهَا مَن يَشَاءُ وَهُمْ يُجَادِلُونَ فِي اللَّهِ وَهُوَ شَدِيدُ الْمِحَالِ ( 13 ) አል-ረዕድ - Aya 13
ነጎድጓድም አላህን በማመስገን ያጠራል፡፡ መላእክትም እርሱን ለመፍራት (ያጠሩታል)፡፡ መብረቆችንም ይልካል፡፡ እነርሱም (ከሓዲዎች) በአላህ የሚከራከሩ ሲሆኑ በእርሷ የሚሻውን ሰው ይመታል፡፡ እርሱም ኀይለ ብርቱ ነው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 13
لَهُ دَعْوَةُ الْحَقِّ ۖ وَالَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِهِ لَا يَسْتَجِيبُونَ لَهُم بِشَيْءٍ إِلَّا كَبَاسِطِ كَفَّيْهِ إِلَى الْمَاءِ لِيَبْلُغَ فَاهُ وَمَا هُوَ بِبَالِغِهِ ۚ وَمَا دُعَاءُ الْكَافِرِينَ إِلَّا فِي ضَلَالٍ ( 14 ) አል-ረዕድ - Aya 14
ለእርሱ (ለአላህ) የእውነት መጥሪያ አለው፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የሚገዙዋቸው (ጣዖታት) ወደ አፉ ይደርስ ዘንድ ወደ ውሃ መዳፎቹን (በሩቅ ሆኖ) እንደሚዘረጋ (ሰው መልስ) እንጂ ለነርሱ በምንም አይመልሱላቸውም፡፡ እርሱም ወደ አፉ ደራሽ አይደለም፡፡ የከሓዲዎችም ጥሪ በከንቱ እንጂ አይደለም፡፡ አል-ረዕድ - Aya 14
وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَظِلَالُهُم بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ ۩ ( 15 ) አል-ረዕድ - Aya 15
በሰማያትና በምድርም ያሉት ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ፡ ጥላዎቻቸውም በጧቶችና በሠርኮች ይሰግዳሉ፡፡ አል-ረዕድ - Aya 15
قُلْ مَن رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ قُلِ اللَّهُ ۚ قُلْ أَفَاتَّخَذْتُم مِّن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ لَا يَمْلِكُونَ لِأَنفُسِهِمْ نَفْعًا وَلَا ضَرًّا ۚ قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الْأَعْمَىٰ وَالْبَصِيرُ أَمْ هَلْ تَسْتَوِي الظُّلُمَاتُ وَالنُّورُ ۗ أَمْ جَعَلُوا لِلَّهِ شُرَكَاءَ خَلَقُوا كَخَلْقِهِ فَتَشَابَهَ الْخَلْقُ عَلَيْهِمْ ۚ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ ( 16 ) አል-ረዕድ - Aya 16
«የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው» በላቸው፡፡ «አላህ ነው» በል፡፡ «ለነፍሶቻቸው ጥቅምንም ጉዳትንም የማይችሉን ረዳቶች ከርሱ ሌላ ያዛችሁን» በላቸው፡፡ «ዕውርና የሚያይ ይስተካከላሉን ወይስ ጨለማዎችና ብርሃን ይስተካከላሉን ወይስ ለአላህ እንደርሱ አፈጣጠር የፈጠሩን ተጋሪዎች አደረጉለትና ፍጥረቱ በእነሱ ላይ ተመሳሰለባቸውን» በል፤ «አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው» በል፡፡ አል-ረዕድ - Aya 16
أَنزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَسَالَتْ أَوْدِيَةٌ بِقَدَرِهَا فَاحْتَمَلَ السَّيْلُ زَبَدًا رَّابِيًا ۚ وَمِمَّا يُوقِدُونَ عَلَيْهِ فِي النَّارِ ابْتِغَاءَ حِلْيَةٍ أَوْ مَتَاعٍ زَبَدٌ مِّثْلُهُ ۚ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الْحَقَّ وَالْبَاطِلَ ۚ فَأَمَّا الزَّبَدُ فَيَذْهَبُ جُفَاءً ۖ وَأَمَّا مَا يَنفَعُ النَّاسَ فَيَمْكُثُ فِي الْأَرْضِ ۚ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الْأَمْثَالَ ( 17 ) አል-ረዕድ - Aya 17
ከሰማይ ውሃን አወረደ፡፡ ሸለቆዎቹም በመጠናቸው ፈሰሱ፡፡ ጎርፉም አሰፋፊውን ኮረፋት ተሸከመ፡፡ ለጌጥ ወይም ለዕቃ ፍላጎት በእርሱ ላይ እሳት የሚያነዱበትም (ማዕድን) ብጤው የኾነ ኮረፋት አልለው፡፡ እንደዚሁ አላህ ለእውነትና ለውሸት ምሳሌን ያደርጋል፡፡ ኮረፋቱማ ግብስብስ ኾኖ ይጠፋል፡፡ ለሰዎች የሚጠቅመውማ በምድር ላይ ይቆያል፡፡ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ይገልፃል፡፡ አል-ረዕድ - Aya 17
لِلَّذِينَ اسْتَجَابُوا لِرَبِّهِمُ الْحُسْنَىٰ ۚ وَالَّذِينَ لَمْ يَسْتَجِيبُوا لَهُ لَوْ أَنَّ لَهُم مَّا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا وَمِثْلَهُ مَعَهُ لَافْتَدَوْا بِهِ ۚ أُولَٰئِكَ لَهُمْ سُوءُ الْحِسَابِ وَمَأْوَاهُمْ جَهَنَّمُ ۖ وَبِئْسَ الْمِهَادُ ( 18 ) አል-ረዕድ - Aya 18
ለእነዚያ ለጌታቸው ለታዘዙት መልካም ነገር (ገነት) አልላቸው፡፡ እነዚያም ለእርሱ ያልታዘዙት ለእነሱ በምድር ያለው ሁሉ ከእርሱም ጋር ብጤው ቢኖራቸው ኖሮ በእርሱ በተበዡበት ነበር፡፡ እነዚያ ለእነሱ ክፉ ምርመራ አለባቸው፡፡ መኖሪያቸውም ገሀነም ናት፡፡ ፍራሻቸውም ከፋች! አል-ረዕድ - Aya 18
أَفَمَن يَعْلَمُ أَنَّمَا أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ الْحَقُّ كَمَنْ هُوَ أَعْمَىٰ ۚ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُولُو الْأَلْبَابِ ( 19 ) አል-ረዕድ - Aya 19
ከጌታህ ወዳንተ የተወረደው እውነት መኾኑን የሚያውቅ ሰው እንደዚያ እርሱ ዕውር እንደኾነው ሰው ነውን የሚገሠጹት የአእምሮ ባለቤቶች ብቻ ናቸው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 19
الَّذِينَ يُوفُونَ بِعَهْدِ اللَّهِ وَلَا يَنقُضُونَ الْمِيثَاقَ ( 20 ) አል-ረዕድ - Aya 20
እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳን የሚሞሉ የጠበቀውንም ኪዳን የማያፈርሱ ናቸው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 20
وَالَّذِينَ يَصِلُونَ مَا أَمَرَ اللَّهُ بِهِ أَن يُوصَلَ وَيَخْشَوْنَ رَبَّهُمْ وَيَخَافُونَ سُوءَ الْحِسَابِ ( 21 ) አል-ረዕድ - Aya 21
እነዚያም አላህ እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቀጥሉ ጌታቸውንም የሚያከብሩ መጥፎንም ቁጥጥር የሚፈሩ ናቸው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 21
وَالَّذِينَ صَبَرُوا ابْتِغَاءَ وَجْهِ رَبِّهِمْ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَنفَقُوا مِمَّا رَزَقْنَاهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً وَيَدْرَءُونَ بِالْحَسَنَةِ السَّيِّئَةَ أُولَٰئِكَ لَهُمْ عُقْبَى الدَّارِ ( 22 ) አል-ረዕድ - Aya 22
እነዚያም የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ የታገሱ፣ ሶላትንም አዘውትረው የሰገዱ፣ እኛ ከሰጠናቸው ሲሳይም በምስጢርም ኾነ በግልጽ የመጸወቱ፣ ክፉውንም ነገር በበጎ የሚገፈትሩ ናቸው፡፡ እነዚያ ለእነሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለቻቸው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 22
جَنَّاتُ عَدْنٍ يَدْخُلُونَهَا وَمَن صَلَحَ مِنْ آبَائِهِمْ وَأَزْوَاجِهِمْ وَذُرِّيَّاتِهِمْ ۖ وَالْمَلَائِكَةُ يَدْخُلُونَ عَلَيْهِم مِّن كُلِّ بَابٍ ( 23 ) አል-ረዕድ - Aya 23
(እርሷም) የመኖሪያ ገነቶች ናት፡፡ ይገቡባታል፡፡ ከአባቶቻቸውም፣ ከሚስቶቻቸውም፣ ከዝርያቸውም መልካም የሠራ ሰው (ይገባታል)፡፡ መላእክትም በእነርሱ ላይ ከየደጃፉ ሁሉ ይገባሉ፡፡ አል-ረዕድ - Aya 23
سَلَامٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى الدَّارِ ( 24 ) አል-ረዕድ - Aya 24
«ሰላም ለእናንተ ይኹን፡፡ (ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር!» (ይሏቸዋል)፡፡ አል-ረዕድ - Aya 24
وَالَّذِينَ يَنقُضُونَ عَهْدَ اللَّهِ مِن بَعْدِ مِيثَاقِهِ وَيَقْطَعُونَ مَا أَمَرَ اللَّهُ بِهِ أَن يُوصَلَ وَيُفْسِدُونَ فِي الْأَرْضِ ۙ أُولَٰئِكَ لَهُمُ اللَّعْنَةُ وَلَهُمْ سُوءُ الدَّارِ ( 25 ) አል-ረዕድ - Aya 25
እነዚያም የአላህን ቃል ኪዳን ከጠበቀ በኋላ የሚያፈርሱ አላህም እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ በምድርም ላይ የሚያበላሹ እነዚያ ለነሱ እርግማን አለባቸው፡፡ ለእነሱም መጥፎ አገር (ገሀነም) አላቸው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 25
اللَّهُ يَبْسُطُ الرِّزْقَ لِمَن يَشَاءُ وَيَقْدِرُ ۚ وَفَرِحُوا بِالْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا فِي الْآخِرَةِ إِلَّا مَتَاعٌ ( 26 ) አል-ረዕድ - Aya 26
አላህ ለሚሻው ሰው ሲሳይን ያሰፋል፤ ያጠባልም፡፡ (ከሓዲዎች) በቅርቢቱም ሕይወት ተደሰቱ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱ አንጻር (ትንሽ) መጠቀሚያ እንጂ ምንም አይደለችም፡፡ አል-ረዕድ - Aya 26
وَيَقُولُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْلَا أُنزِلَ عَلَيْهِ آيَةٌ مِّن رَّبِّهِ ۗ قُلْ إِنَّ اللَّهَ يُضِلُّ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَنْ أَنَابَ ( 27 ) አል-ረዕድ - Aya 27
እነዚያም የካዱት «በእርሱ ላይ ከጌታው ተዓምር ለምን አልተወረደም» ይላሉ፡፡ «አላህ የሚሻውን ያጠምማል፡፡ የተመለሰውንም ሰው ወደርሱ ይመራል» በላቸው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 27
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ ( 28 ) አል-ረዕድ - Aya 28
(እነሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡ አል-ረዕድ - Aya 28
الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ طُوبَىٰ لَهُمْ وَحُسْنُ مَآبٍ ( 29 ) አል-ረዕድ - Aya 29
እነዚያ ያመኑትና መልካም ሥራዎችን የሠሩት ለእነሱ ደግ ኑሮ መልካም መመለሻም አላቸው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 29
كَذَٰلِكَ أَرْسَلْنَاكَ فِي أُمَّةٍ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهَا أُمَمٌ لِّتَتْلُوَ عَلَيْهِمُ الَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَهُمْ يَكْفُرُونَ بِالرَّحْمَٰنِ ۚ قُلْ هُوَ رَبِّي لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ مَتَابِ ( 30 ) አል-ረዕድ - Aya 30
እንደዚሁ ከበፊትዋ ብዙ ሕዝቦች በእርግጥ ያለፉ ወደኾነችው ሕዝብ እነርሱ በአልረሕማን የሚክዱ ሲኾኑ ያንን ወደ አንተ ያወረድነውን ቁርኣን በእነርሱ ላይ ታነብላቸው ዘንድ ላክንህ፡፡ «እርሱ (አልረሕማን) ጌታዬ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ በርሱ ላይ ተጠጋሁ፡፡ መመለሻየም ወደርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 30
وَلَوْ أَنَّ قُرْآنًا سُيِّرَتْ بِهِ الْجِبَالُ أَوْ قُطِّعَتْ بِهِ الْأَرْضُ أَوْ كُلِّمَ بِهِ الْمَوْتَىٰ ۗ بَل لِّلَّهِ الْأَمْرُ جَمِيعًا ۗ أَفَلَمْ يَيْأَسِ الَّذِينَ آمَنُوا أَن لَّوْ يَشَاءُ اللَّهُ لَهَدَى النَّاسَ جَمِيعًا ۗ وَلَا يَزَالُ الَّذِينَ كَفَرُوا تُصِيبُهُم بِمَا صَنَعُوا قَارِعَةٌ أَوْ تَحُلُّ قَرِيبًا مِّن دَارِهِمْ حَتَّىٰ يَأْتِيَ وَعْدُ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُخْلِفُ الْمِيعَادَ ( 31 ) አል-ረዕድ - Aya 31
ቁርኣንም በእርሱ ተራራዎች በተነዱበት ወይም በእርሱ ምድር በተቆራረጠችበት ወይም በእርሱ ሙታን እንዲናገሩ በተደረጉበት ኖሮ (የመካ ከሓዲዎች ባላመኑ ነበር)፡፡ በእውነቱ ነገሩ ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያ ያመኑት ሰዎች እነሆ አላህ በሻ ኖሮ ሰዎችን በመላ በእርግጥ ይመራቸው እንደነበረ አያውቁምን እነዚያም የካዱት በሥራቸው ምክንያት (አጥፊ) ዐደጋ የምታገኛቸው ከመኾን ወይም የአላህ ቀጠሮ እስኪመጣ በአገራቸው አቅራቢያ (አንተ) የምትሰፍርባቸው ከመኾን አይወገዱም፡፡ አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና፡፡ አል-ረዕድ - Aya 31
وَلَقَدِ اسْتُهْزِئَ بِرُسُلٍ مِّن قَبْلِكَ فَأَمْلَيْتُ لِلَّذِينَ كَفَرُوا ثُمَّ أَخَذْتُهُمْ ۖ فَكَيْفَ كَانَ عِقَابِ ( 32 ) አል-ረዕድ - Aya 32
ከአንተ በፊት በነበሩትም መልክተኞች በእርግጥ ተላግጦባቸዋል፡፡ ለእነዚያም ለካዱት ጊዜን ሰጠኋቸው፡፡ ከዚያም (በቅጣት) ያዝኩዋቸው፡፡ ቅጣቴም እንዴት ነበር! አል-ረዕድ - Aya 32
أَفَمَنْ هُوَ قَائِمٌ عَلَىٰ كُلِّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ ۗ وَجَعَلُوا لِلَّهِ شُرَكَاءَ قُلْ سَمُّوهُمْ ۚ أَمْ تُنَبِّئُونَهُ بِمَا لَا يَعْلَمُ فِي الْأَرْضِ أَم بِظَاهِرٍ مِّنَ الْقَوْلِ ۗ بَلْ زُيِّنَ لِلَّذِينَ كَفَرُوا مَكْرُهُمْ وَصُدُّوا عَنِ السَّبِيلِ ۗ وَمَن يُضْلِلِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِنْ هَادٍ ( 33 ) አል-ረዕድ - Aya 33
እርሱ በነፍስ ሁሉ ላይ በሠራቸው ሥራ ተጠባባቂ የኾነው (አላህ እንደዚህ እንዳልኾነው ጣዖት ብጤ ነውን) ለአላህም ተጋሪዎችን አደረጉ፡፡ ጥሯቸው «አላህን በምድር ውስጥ የማያውቀው ኖሮ ትነግሩታላችሁን ወይስ ከቃል በግልጽ (ፍቺ በሌለው ከንቱ ቃል ተጋሪዎች በማለት ትጠሩዋቸዋላችሁን)» በላቸው፡፡ በእውነቱ ለእነዚያ ለካዱት ተንኮላቸው ተሸለመላቸው፡፡ ከእውነቱ መንገድም ታገዱ፡፡ አላህም ያጠመመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡ አል-ረዕድ - Aya 33
لَّهُمْ عَذَابٌ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۖ وَلَعَذَابُ الْآخِرَةِ أَشَقُّ ۖ وَمَا لَهُم مِّنَ اللَّهِ مِن وَاقٍ ( 34 ) አል-ረዕድ - Aya 34
ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወት ቅጣት አላቸው፡፡ የመጨረሻይቱም (ዓለም) ቅጣት በጣም የበረታ ነው፡፡ ለእነሱም ከአላህ (ቅጣት) ምንም ጠባቂ የላቸውም፡፡ አል-ረዕድ - Aya 34
مَّثَلُ الْجَنَّةِ الَّتِي وُعِدَ الْمُتَّقُونَ ۖ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ۖ أُكُلُهَا دَائِمٌ وَظِلُّهَا ۚ تِلْكَ عُقْبَى الَّذِينَ اتَّقَوا ۖ وَّعُقْبَى الْكَافِرِينَ النَّارُ ( 35 ) አል-ረዕድ - Aya 35
ያች ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት ገነት ምጣኔዋ (እንደሚነገራችሁ ነው)፡፡ ከሥርዋ ወንዞች ይፈስሳሉ፡፡ ምግቧ (ሁልጊዜ) የማይቋረጥ፤ ነው፡፡ ጥላዋም (እንደዚሁ)፡፡ ይህች የእነዚያ የተጠነቀቁት መጨረሻ ናት፡፡ የከሃዲዎችም መጨረሻ እሳት ናት፡፡ አል-ረዕድ - Aya 35
وَالَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ يَفْرَحُونَ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْكَ ۖ وَمِنَ الْأَحْزَابِ مَن يُنكِرُ بَعْضَهُ ۚ قُلْ إِنَّمَا أُمِرْتُ أَنْ أَعْبُدَ اللَّهَ وَلَا أُشْرِكَ بِهِ ۚ إِلَيْهِ أَدْعُو وَإِلَيْهِ مَآبِ ( 36 ) አል-ረዕድ - Aya 36
እነዚያም መጽሐፉን የሰጠናቸው ወዳንተ በተወረደው ይደሰታሉ፡፡ ከአሕዛብም ከፊሉን የሚክዱ ሰዎች አልሉ፡፡ «እኔ የታዘዝኩት አላህን ብቻ እንድገዛ በእርሱም እንደዳላጋራ ነው፡፡ ወደእርሱ እጠራለሁ፤ መመለሻዬም ወደእርሱ ነው» በላቸው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 36
وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَاهُ حُكْمًا عَرَبِيًّا ۚ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَمَا جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا وَاقٍ ( 37 ) አል-ረዕድ - Aya 37
እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ሲኾን አወረድነው፡፡ ዕውቀቱ ከመጣልህም በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን ብትከተል ከአላህ ቅጣት ምንም ረዳትም ጠባቂም የለህም፡፡ አል-ረዕድ - Aya 37
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ وَجَعَلْنَا لَهُمْ أَزْوَاجًا وَذُرِّيَّةً ۚ وَمَا كَانَ لِرَسُولٍ أَن يَأْتِيَ بِآيَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ لِكُلِّ أَجَلٍ كِتَابٌ ( 38 ) አል-ረዕድ - Aya 38
ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ለእነርሱም ሚስቶችንና ልጆችን አድርገናል፡፡ ለማንኛውም መልክተኛ በአላህ ፈቃድ እንጂ ተዓምር ሊያመጣ አይገባውም፡፡ ለጊዜው ሁሉ ጽሑፍ አለው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 38
يَمْحُو اللَّهُ مَا يَشَاءُ وَيُثْبِتُ ۖ وَعِندَهُ أُمُّ الْكِتَابِ ( 39 ) አል-ረዕድ - Aya 39
አላህ የሚሻውን ያብሳል፤ ያጸድቃልም፡፡ የመጽሐፉ መሠረትም እርሱ ዘንድ ነው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 39
وَإِن مَّا نُرِيَنَّكَ بَعْضَ الَّذِي نَعِدُهُمْ أَوْ نَتَوَفَّيَنَّكَ فَإِنَّمَا عَلَيْكَ الْبَلَاغُ وَعَلَيْنَا الْحِسَابُ ( 40 ) አል-ረዕድ - Aya 40
የዚያንም ያስፈራራናቸውን ከፊሉን ብናሳይህ (መልካም ነው)፡፡ ወይም ብንገድልህ (ወቀሳ የለብህም)፡፡ በአንተ ላይ ያለብህ ማድረስ ብቻ ነው፡፡ ምርመራውም በኛ ላይ ነው፡፤ አል-ረዕድ - Aya 40
أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّا نَأْتِي الْأَرْضَ نَنقُصُهَا مِنْ أَطْرَافِهَا ۚ وَاللَّهُ يَحْكُمُ لَا مُعَقِّبَ لِحُكْمِهِ ۚ وَهُوَ سَرِيعُ الْحِسَابِ ( 41 ) አል-ረዕድ - Aya 41
እኛ ምድርን ከጫፎችዋ የምናጎድላት ኾነን የምንመጣባት መኾናችንን አላዩምን አላህም ይፈርዳል፡፡ ለፍርዱም ገልባጭ የለውም፡፡ እርሱም ምርመራው ፈጣን ነው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 41
وَقَدْ مَكَرَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ فَلِلَّهِ الْمَكْرُ جَمِيعًا ۖ يَعْلَمُ مَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ ۗ وَسَيَعْلَمُ الْكُفَّارُ لِمَنْ عُقْبَى الدَّارِ ( 42 ) አል-ረዕድ - Aya 42
እነዚያም ከእነሱ በፊት የነበሩት በእርግጥ መከሩ፡፡ አዘንግቶም የመያዙ ዘዴ በሙሉ የአላህ ነው፡፡ ነፍስ ሁሉ የምትሠራውን ያውቃል፡፡ ከሓዲዎችም የመጨረሻይቱ አገር ለማን እንደምትኾን ወደፊት ያውቃሉ፡፡ አል-ረዕድ - Aya 42
وَيَقُولُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَسْتَ مُرْسَلًا ۚ قُلْ كَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا بَيْنِي وَبَيْنَكُمْ وَمَنْ عِندَهُ عِلْمُ الْكِتَابِ ( 43 ) አል-ረዕድ - Aya 43
እነዚያም የካዱት ሰዎች «መልክተኛ አይደለህም» ይላሉ፡፡ «በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህና እርሱ ዘንድ የመጽሐፉ ዕውቀት ባለው ሰው በቃ» በላቸው፡፡ አል-ረዕድ - Aya 43
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah