Surah አል ሓቃህ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ሓቃህ - Aya count 52
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
الْحَاقَّةُ ( 1 ) አል ሓቃህ - Aya 1
እውነትን አረጋጋጪቱ (ትንሣኤ)፡፡ አል ሓቃህ - Aya 1
مَا الْحَاقَّةُ ( 2 ) አል ሓቃህ - Aya 2
አረጋጋጪቱም (እርሷ) ምንድን ናት! አል ሓቃህ - Aya 2
وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْحَاقَّةُ ( 3 ) አል ሓቃህ - Aya 3
አረጋጋጪቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? አል ሓቃህ - Aya 3
كَذَّبَتْ ثَمُودُ وَعَادٌ بِالْقَارِعَةِ ( 4 ) አል ሓቃህ - Aya 4
ሰሙድና ዓድ በቆርቋሪይቱ (ትንሣኤ) አስተባበሉ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 4
فَأَمَّا ثَمُودُ فَأُهْلِكُوا بِالطَّاغِيَةِ ( 5 ) አል ሓቃህ - Aya 5
ሠሙድማ ወሰን በሌላት ጩኸት ተጠፋ፤ (ተወደሙ)፡፡ አል ሓቃህ - Aya 5
وَأَمَّا عَادٌ فَأُهْلِكُوا بِرِيحٍ صَرْصَرٍ عَاتِيَةٍ ( 6 ) አል ሓቃህ - Aya 6
ዓድማ በኀይል በምትንሻሻ ብርቱ ነፋስ ተጠፉ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 6
سَخَّرَهَا عَلَيْهِمْ سَبْعَ لَيَالٍ وَثَمَانِيَةَ أَيَّامٍ حُسُومًا فَتَرَى الْقَوْمَ فِيهَا صَرْعَىٰ كَأَنَّهُمْ أَعْجَازُ نَخْلٍ خَاوِيَةٍ ( 7 ) አል ሓቃህ - Aya 7
ተከታታይ በኾኑ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት መዓልቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት፡፡ ሕዝቦቹንም፤ በውስጧ የተጣሉ ኾነው ልክ ክፍት የኾኑ የዘንባባ ግንዶች መስለው ታያቸዋለህ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 7
فَهَلْ تَرَىٰ لَهُم مِّن بَاقِيَةٍ ( 8 ) አል ሓቃህ - Aya 8
ለእነርሱም ቀሪን ታያለህን? አል ሓቃህ - Aya 8
وَجَاءَ فِرْعَوْنُ وَمَن قَبْلَهُ وَالْمُؤْتَفِكَاتُ بِالْخَاطِئَةِ ( 9 ) አል ሓቃህ - Aya 9
ፈርዖን ከበፊቱ የነበሩትም ሰዎች ተገልባጮቹም (ከተሞች) በኀጢአት (ሥራዎች) መጡ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 9
فَعَصَوْا رَسُولَ رَبِّهِمْ فَأَخَذَهُمْ أَخْذَةً رَّابِيَةً ( 10 ) አል ሓቃህ - Aya 10
የጌታቸውንም መልእክተኛ ትዕዛዝ ጣሱ፡፡ የበረታችንም አያያዝ ያዛቸው፡፡ አል ሓቃህ - Aya 10
إِنَّا لَمَّا طَغَى الْمَاءُ حَمَلْنَاكُمْ فِي الْجَارِيَةِ ( 11 ) አል ሓቃህ - Aya 11
እኛ ውሃው ባየለ ጊዜ በተንሻላይቱ ታንኳ ውስጥ ጫንናችሁ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 11
لِنَجْعَلَهَا لَكُمْ تَذْكِرَةً وَتَعِيَهَا أُذُنٌ وَاعِيَةٌ ( 12 ) አል ሓቃህ - Aya 12
ለእናንተ መገሰጫ ልናደርጋት አጥኒ የኾነችም ጆሮ ታጠናት ዘንድ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 12
فَإِذَا نُفِخَ فِي الصُّورِ نَفْخَةٌ وَاحِدَةٌ ( 13 ) አል ሓቃህ - Aya 13
በቀንዱም አንዲት መንነፋት በተነፋች ጊዜ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 13
وَحُمِلَتِ الْأَرْضُ وَالْجِبَالُ فَدُكَّتَا دَكَّةً وَاحِدَةً ( 14 ) አል ሓቃህ - Aya 14
ምድርና ጋራዎችም (ከስፍራቸው) በተነሱና አንዲትን መሰባበር በተሰባበሩ ጊዜ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 14
فَيَوْمَئِذٍ وَقَعَتِ الْوَاقِعَةُ ( 15 ) አል ሓቃህ - Aya 15
በዚያ ቀን ኋኝቱ (ትንሣኤ) ትኾናለች፡፡ አል ሓቃህ - Aya 15
وَانشَقَّتِ السَّمَاءُ فَهِيَ يَوْمَئِذٍ وَاهِيَةٌ ( 16 ) አል ሓቃህ - Aya 16
ሰማይም ትቀደዳለች፡፡ ስለዚህ እርሷ በዚያ ቀን ደካማ ናት፡፡ አል ሓቃህ - Aya 16
وَالْمَلَكُ عَلَىٰ أَرْجَائِهَا ۚ وَيَحْمِلُ عَرْشَ رَبِّكَ فَوْقَهُمْ يَوْمَئِذٍ ثَمَانِيَةٌ ( 17 ) አል ሓቃህ - Aya 17
መላእክትም በየጫፎችዋ ላይ ይኾናሉ፡፡ የጌታህንም ዐርሽ በዚያ ቀን ስምንት መላእክት ከበላያቸው ይሸከማሉ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 17
يَوْمَئِذٍ تُعْرَضُونَ لَا تَخْفَىٰ مِنكُمْ خَافِيَةٌ ( 18 ) አል ሓቃህ - Aya 18
በዚያ ቀን ከእናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲኾኑ ትቅቀረባላችሁ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 18
فَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِيَمِينِهِ فَيَقُولُ هَاؤُمُ اقْرَءُوا كِتَابِيَهْ ( 19 ) አል ሓቃህ - Aya 19
መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ) «እንኩ፤ መጽሐፌን አንብቡ» ይላል፡፡ አል ሓቃህ - Aya 19
إِنِّي ظَنَنتُ أَنِّي مُلَاقٍ حِسَابِيَهْ ( 20 ) አል ሓቃህ - Aya 20
«እኔ ምርመራየን የምገናኝ መኾኔን አረጋገጥኩ፤» (ተዘጋጀሁም ይላል)፡፡ አል ሓቃህ - Aya 20
فَهُوَ فِي عِيشَةٍ رَّاضِيَةٍ ( 21 ) አል ሓቃህ - Aya 21
እርሱም በተወደደች ኑሮ ውሰጥ ይኾናል፡፡ አል ሓቃህ - Aya 21
فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ ( 22 ) አል ሓቃህ - Aya 22
በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 22
قُطُوفُهَا دَانِيَةٌ ( 23 ) አል ሓቃህ - Aya 23
ፍሬዎችዋ ቅርቦች የኾኑ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 23
كُلُوا وَاشْرَبُوا هَنِيئًا بِمَا أَسْلَفْتُمْ فِي الْأَيَّامِ الْخَالِيَةِ ( 24 ) አል ሓቃህ - Aya 24
በአለፉት ቀናት ውስጥ (በምድረ ዓለም) ባስቀደማችሁት ምክንያት ብሉ፤ ጠጡም፤ (ይባላሉ)፡፡ አል ሓቃህ - Aya 24
وَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِشِمَالِهِ فَيَقُولُ يَا لَيْتَنِي لَمْ أُوتَ كِتَابِيَهْ ( 25 ) አል ሓቃህ - Aya 25
መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ» ይላል፡፡ አል ሓቃህ - Aya 25
وَلَمْ أَدْرِ مَا حِسَابِيَهْ ( 26 ) አል ሓቃህ - Aya 26
«ምርመራየንም ምን እንደኾነ ባላወቅኩ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 26
يَا لَيْتَهَا كَانَتِ الْقَاضِيَةَ ( 27 ) አል ሓቃህ - Aya 27
«እርሷ (ሞት ሕይወቴን) ምነው ፈጻሚ በኾነች፡፡ አል ሓቃህ - Aya 27
مَا أَغْنَىٰ عَنِّي مَالِيَهْ ۜ ( 28 ) አል ሓቃህ - Aya 28
«ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አላብቃቃኝ፤ (አልጠቀመኝም)፡፡ አል ሓቃህ - Aya 28
هَلَكَ عَنِّي سُلْطَانِيَهْ ( 29 ) አል ሓቃህ - Aya 29
«ኀይሌ ከእኔ ላይ ጠፋ» (ይላል)፡፡ አል ሓቃህ - Aya 29
خُذُوهُ فَغُلُّوهُ ( 30 ) አል ሓቃህ - Aya 30
«ያዙት፤ እሰሩትም፡፡ አል ሓቃህ - Aya 30
ثُمَّ الْجَحِيمَ صَلُّوهُ ( 31 ) አል ሓቃህ - Aya 31
«ከዚያም በእሳት ውሰጥ አግቡት፡፡ አል ሓቃህ - Aya 31
ثُمَّ فِي سِلْسِلَةٍ ذَرْعُهَا سَبْعُونَ ذِرَاعًا فَاسْلُكُوهُ ( 32 ) አል ሓቃህ - Aya 32
«ከዚያም ርዝመቷ ሰባ ክንድ በኾነች ሰንሰለት ውስጥ አግቡት፡፡» አል ሓቃህ - Aya 32
إِنَّهُ كَانَ لَا يُؤْمِنُ بِاللَّهِ الْعَظِيمِ ( 33 ) አል ሓቃህ - Aya 33
እርሱ ታላቅ በኾነው አላህ አያምንም ነበርና፡፡ አል ሓቃህ - Aya 33
وَلَا يَحُضُّ عَلَىٰ طَعَامِ الْمِسْكِينِ ( 34 ) አል ሓቃህ - Aya 34
ድኾችንም በማብላት ላይ አያግባባም ነበርና፡፡ አል ሓቃህ - Aya 34
فَلَيْسَ لَهُ الْيَوْمَ هَاهُنَا حَمِيمٌ ( 35 ) አል ሓቃህ - Aya 35
ለእርሱም ዛሬ እዚህ ዘመድ የለውም፡፡ አል ሓቃህ - Aya 35
وَلَا طَعَامٌ إِلَّا مِنْ غِسْلِينٍ ( 36 ) አል ሓቃህ - Aya 36
ምግብም ከእሳት ሰዎች ቁስል እጣቢ (እዥ) በስተቀር የለውም፡፡ አል ሓቃህ - Aya 36
لَّا يَأْكُلُهُ إِلَّا الْخَاطِئُونَ ( 37 ) አል ሓቃህ - Aya 37
ኀጢኣተኞች እንጅ ሌላ አይበላውም፤ (ይባላል)፡፡ አል ሓቃህ - Aya 37
فَلَا أُقْسِمُ بِمَا تُبْصِرُونَ ( 38 ) አል ሓቃህ - Aya 38
በምታዩትም ነገር እምላለሁ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 38
وَمَا لَا تُبْصِرُونَ ( 39 ) አል ሓቃህ - Aya 39
በማታዩትም ነገር፡፡ አል ሓቃህ - Aya 39
إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ ( 40 ) አል ሓቃህ - Aya 40
እርሱ (ቁርኣን) የተከበረ መልክተኛ ቃል ነው፡፡ አል ሓቃህ - Aya 40
وَمَا هُوَ بِقَوْلِ شَاعِرٍ ۚ قَلِيلًا مَّا تُؤْمِنُونَ ( 41 ) አል ሓቃህ - Aya 41
እርሱም የባለቅኔ ቃል (ግጥም) አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 41
وَلَا بِقَوْلِ كَاهِنٍ ۚ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ ( 42 ) አል ሓቃህ - Aya 42
የጠንቋይም ቃል አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታስታውሳላችሁ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 42
تَنزِيلٌ مِّن رَّبِّ الْعَالَمِينَ ( 43 ) አል ሓቃህ - Aya 43
ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ አል ሓቃህ - Aya 43
وَلَوْ تَقَوَّلَ عَلَيْنَا بَعْضَ الْأَقَاوِيلِ ( 44 ) አል ሓቃህ - Aya 44
በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት (ያላልነውን) በቀጠፈ ኖሮ፤ አል ሓቃህ - Aya 44
لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِالْيَمِينِ ( 45 ) አል ሓቃህ - Aya 45
በኀይል በያዝነው ነበር፡፡ አል ሓቃህ - Aya 45
ثُمَّ لَقَطَعْنَا مِنْهُ الْوَتِينَ ( 46 ) አል ሓቃህ - Aya 46
ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር (የተንጠለጠለበትን ጅማት) በቆረጥን ነበር፡፡ አል ሓቃህ - Aya 46
فَمَا مِنكُم مِّنْ أَحَدٍ عَنْهُ حَاجِزِينَ ( 47 ) አል ሓቃህ - Aya 47
ከእናንተም ውስጥ ከእርሱ ላይ ከልካዮች ምንም አይኖሩም፡፡ አል ሓቃህ - Aya 47
وَإِنَّهُ لَتَذْكِرَةٌ لِّلْمُتَّقِينَ ( 48 ) አል ሓቃህ - Aya 48
እርሱም (ቁርኣን) ለጥንቁቆቹ መገሠጫ ነው፡፡ አል ሓቃህ - Aya 48
وَإِنَّا لَنَعْلَمُ أَنَّ مِنكُم مُّكَذِّبِينَ ( 49 ) አል ሓቃህ - Aya 49
እኛም ከእናንተ ውስጥ አስተባባዮች መኖራቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ አል ሓቃህ - Aya 49
وَإِنَّهُ لَحَسْرَةٌ عَلَى الْكَافِرِينَ ( 50 ) አል ሓቃህ - Aya 50
እርሱም (ቁርኣን) በከሓዲዎቹ ላይ ጸጸት ነው፡፡ አል ሓቃህ - Aya 50
وَإِنَّهُ لَحَقُّ الْيَقِينِ ( 51 ) አል ሓቃህ - Aya 51
እርሱም የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡ አል ሓቃህ - Aya 51
فَسَبِّحْ بِاسْمِ رَبِّكَ الْعَظِيمِ ( 52 ) አል ሓቃህ - Aya 52
የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡ አል ሓቃህ - Aya 52
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah