Surah ሁድ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah ሁድ - Aya count 123
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
الر ۚ كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ ( 1 ) ሁድ - Aya 1
አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርኣን) አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ (የተወረደ) ነው፡፡ ሁድ - Aya 1
أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ ( 2 ) ሁድ - Aya 2
(እንዲህ በላቸው)፡- «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ ለእናንተ ከርሱ (የተላክሁ) አስፈራሪና አብሳሪ ነኝ፡፡» ሁድ - Aya 2
وَأَنِ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ يُمَتِّعْكُم مَّتَاعًا حَسَنًا إِلَىٰ أَجَلٍ مُّسَمًّى وَيُؤْتِ كُلَّ ذِي فَضْلٍ فَضْلَهُ ۖ وَإِن تَوَلَّوْا فَإِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ كَبِيرٍ ( 3 ) ሁድ - Aya 3
ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት፡፡ ከዚያም ወደእርሱ ተመለሱ፡፡ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ መልካምን መጥቀም ይጠቅማችኋልና፡፡ የትሩፋትንም ባለቤት ሁሉ ችሮታውን (ምንዳውን) ይሰጠዋል፡፡ ብትሸሹም እኔ በእናንተ ላይ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ፡፡ ሁድ - Aya 3
إِلَى اللَّهِ مَرْجِعُكُمْ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ( 4 ) ሁድ - Aya 4
መመለሻችሁ ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ ሁድ - Aya 4
أَلَا إِنَّهُمْ يَثْنُونَ صُدُورَهُمْ لِيَسْتَخْفُوا مِنْهُ ۚ أَلَا حِينَ يَسْتَغْشُونَ ثِيَابَهُمْ يَعْلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعْلِنُونَ ۚ إِنَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ ( 5 ) ሁድ - Aya 5
ንቁ! እነሱ ከእርሱ (ከአላህ) ይደበቁ ዘንድ ደረቶቻቸውን ያጥፋሉ፡፡ ንቁ! ልብሶቻቸውን በሚከናነቡ ጊዜ የሚደብቁትን የሚገልጹትንም ሁሉ ያውቃል፡፡ እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡ ሁድ - Aya 5
وَمَا مِن دَابَّةٍ فِي الْأَرْضِ إِلَّا عَلَى اللَّهِ رِزْقُهَا وَيَعْلَمُ مُسْتَقَرَّهَا وَمُسْتَوْدَعَهَا ۚ كُلٌّ فِي كِتَابٍ مُّبِينٍ ( 6 ) ሁድ - Aya 6
በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለ ቢኾን እንጂ፡፡ ማረፊያዋንም መርጊያዋንም ያውቃል፡፡ ሁሉም ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡ ሁድ - Aya 6
وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَكَانَ عَرْشُهُ عَلَى الْمَاءِ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا ۗ وَلَئِن قُلْتَ إِنَّكُم مَّبْعُوثُونَ مِن بَعْدِ الْمَوْتِ لَيَقُولَنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا إِنْ هَٰذَا إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ ( 7 ) ሁድ - Aya 7
እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ ነው፡፡ ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር፡፡ የትኛችሁ ሥራው ያማረ መሆኑን ይፈትናችሁ ዘንድ (ፈጠራቸው)፡፡ «እናንተ ከሞት በኋላ በእርግጥ ተቀስቃሾች ናችሁ» ብትልም እነዚያ የካዱት ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም ይላሉ፡፡ ሁድ - Aya 7
وَلَئِنْ أَخَّرْنَا عَنْهُمُ الْعَذَابَ إِلَىٰ أُمَّةٍ مَّعْدُودَةٍ لَّيَقُولُنَّ مَا يَحْبِسُهُ ۗ أَلَا يَوْمَ يَأْتِيهِمْ لَيْسَ مَصْرُوفًا عَنْهُمْ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا بِهِ يَسْتَهْزِئُونَ ( 8 ) ሁድ - Aya 8
ቅጣቱንም ወደ ተቆጠሩ (ጥቂት) ጊዜያቶች ከእነርሱ ብናቆይላቸው «(ከመውረድ) የሚከለክለው ምንድን ነው» ይላሉ፡፡ ንቁ! በሚመጣባቸው ቀን ከእነሱ ላይ ተመላሽ አይደለም፡፡ በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩትም (ቅጣት) በእነርሱ ላይ ይወርድባቸዋል፡፡ ሁድ - Aya 8
وَلَئِنْ أَذَقْنَا الْإِنسَانَ مِنَّا رَحْمَةً ثُمَّ نَزَعْنَاهَا مِنْهُ إِنَّهُ لَيَئُوسٌ كَفُورٌ ( 9 ) ሁድ - Aya 9
ሰውንም ከእኛ ችሮታን ብናቀምሰው ከዚያም ከርሱ ብንወስዳት እርሱ በእርግጥ ተስፋ ቆራጭ ክህደተ ብርቱ ነው፡፡ ሁድ - Aya 9
وَلَئِنْ أَذَقْنَاهُ نَعْمَاءَ بَعْدَ ضَرَّاءَ مَسَّتْهُ لَيَقُولَنَّ ذَهَبَ السَّيِّئَاتُ عَنِّي ۚ إِنَّهُ لَفَرِحٌ فَخُورٌ ( 10 ) ሁድ - Aya 10
ካገኘችውም ችግር በኋላ ጸጋዎችን ብናቀምሰው «ችግሮች ከኔ ላይ በእርግጥ ተወገዱ» ይላል (አያመሰግንም)፡፡ እርሱ ተደሳች ጉረኛ ነውና፡፡ ሁድ - Aya 10
إِلَّا الَّذِينَ صَبَرُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أُولَٰئِكَ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ كَبِيرٌ ( 11 ) ሁድ - Aya 11
ግን እነዚያ የታገሱ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ እነዚያ ለእነሱ ምሕረትና ታላቅ ምንዳ አልላቸው፡፡ ሁድ - Aya 11
فَلَعَلَّكَ تَارِكٌ بَعْضَ مَا يُوحَىٰ إِلَيْكَ وَضَائِقٌ بِهِ صَدْرُكَ أَن يَقُولُوا لَوْلَا أُنزِلَ عَلَيْهِ كَنزٌ أَوْ جَاءَ مَعَهُ مَلَكٌ ۚ إِنَّمَا أَنتَ نَذِيرٌ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ ( 12 ) ሁድ - Aya 12
በእርሱ ላይ የገንዘብ ድልብ ለምን አልተወረደም ወይም ከርሱ ጋር መልአክ ለምን አልመጣም ማለታቸውንም በመፍራት ወደ አንተ ከሚወርደው ከፊሉን ልትተው በእርሱም ልብህ ጠባብ ሊኾን ይፈራልሃል፡፡ አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ተጠባባቂ ነው፡፡ ሁድ - Aya 12
أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَاهُ ۖ قُلْ فَأْتُوا بِعَشْرِ سُوَرٍ مِّثْلِهِ مُفْتَرَيَاتٍ وَادْعُوا مَنِ اسْتَطَعْتُم مِّن دُونِ اللَّهِ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ ( 13 ) ሁድ - Aya 13
ይልቁንም «(ቁርኣንን) ቀጣጠፈው» ይላሉን፡- «እውነተኞች እንደሆናችሁ ብጤው የሆኑን ዐስር የተቀጣጠፉ ሱራዎች አምጡ፡፡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን (ረዳት) ጥሩ» በላቸው፡፡ ሁድ - Aya 13
فَإِلَّمْ يَسْتَجِيبُوا لَكُمْ فَاعْلَمُوا أَنَّمَا أُنزِلَ بِعِلْمِ اللَّهِ وَأَن لَّا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ ( 14 ) ሁድ - Aya 14
ለእናንተም (ጥሪውን) ባይቀበሏችሁ የተወረደው በአላህ እውቀት ብቻ መሆኑንና ከእርሱ ሌላ አምላክ አለመኖሩን ዕወቁ፡፡ ታዲያ እናንተ የምትሰልሙ ናችሁን (ስለሙ በላቸው)፡፡ ሁድ - Aya 14
مَن كَانَ يُرِيدُ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا وَزِينَتَهَا نُوَفِّ إِلَيْهِمْ أَعْمَالَهُمْ فِيهَا وَهُمْ فِيهَا لَا يُبْخَسُونَ ( 15 ) ሁድ - Aya 15
ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) በእርሷ ውስጥ ወደነሱ እንሞላላቸዋለን፡፡ እነሱም በርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸውም፤ ሁድ - Aya 15
أُولَٰئِكَ الَّذِينَ لَيْسَ لَهُمْ فِي الْآخِرَةِ إِلَّا النَّارُ ۖ وَحَبِطَ مَا صَنَعُوا فِيهَا وَبَاطِلٌ مَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ ( 16 ) ሁድ - Aya 16
እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ ከእሳት በቀር የሌላቸው ናቸው፡፡ የሠሩትም ሥራ በርሷ ውስጥ ተበላሸ፡፡ (በቅርቢቱ ዓለም) ይሠሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው፡፡ ሁድ - Aya 16
أَفَمَن كَانَ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّهِ وَيَتْلُوهُ شَاهِدٌ مِّنْهُ وَمِن قَبْلِهِ كِتَابُ مُوسَىٰ إِمَامًا وَرَحْمَةً ۚ أُولَٰئِكَ يُؤْمِنُونَ بِهِ ۚ وَمَن يَكْفُرْ بِهِ مِنَ الْأَحْزَابِ فَالنَّارُ مَوْعِدُهُ ۚ فَلَا تَكُ فِي مِرْيَةٍ مِّنْهُ ۚ إِنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّكَ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ ( 17 ) ሁድ - Aya 17
ከጌታው ከአስረጅ ጋር የኾነ ሰው፤ ከእርሱም (ከአላህ) የኾነ መስካሪ የሚከተለው፣ ከእርሱ በፊትም የሙሳ መጽሐፍ መሪና እዝነት ሲኾን (የመሰከረለት) የቅርቢቱን ሕይወት እንደሚሻው ሰው ነውን እነዚያ በእርሱ (በቁርኣን) ያምናሉ፡፡ ከአሕዛቦቹም በእርሱ የሚክድ ሰው እሳት መመለሻው ናት፡፡ ከእርሱም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን፡፡ እርሱ ከጌታህ የሆነ እውነት ነው፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም፡፡ ሁድ - Aya 17
وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا ۚ أُولَٰئِكَ يُعْرَضُونَ عَلَىٰ رَبِّهِمْ وَيَقُولُ الْأَشْهَادُ هَٰؤُلَاءِ الَّذِينَ كَذَبُوا عَلَىٰ رَبِّهِمْ ۚ أَلَا لَعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ ( 18 ) ሁድ - Aya 18
በአላህ ላይ እብለትን ከሚቀጣጥፍም ይበልጥ በዳይ ማነው እነዚያ በጌታቸው ላይ ይቀርባሉ፡፡ መስካሪዎቹም «እነዚህ በጌታቸው ላይ የዋሹት ናቸው» ይላሉ፡፡ ንቁ! የአላህ ርግማን በበዳዮች ላይ ይሁን፡፡ ሁድ - Aya 18
الَّذِينَ يَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ وَيَبْغُونَهَا عِوَجًا وَهُم بِالْآخِرَةِ هُمْ كَافِرُونَ ( 19 ) ሁድ - Aya 19
(እነሱም) እነዚያ ከአላህ መንገድ የሚከለክሉ መጥመሟንም የሚፈልጓት ናቸው፡፡ እነሱም መጨረሻይቱን ዓለም እነሱ ከሓዲዎች ናቸው፡፤ ሁድ - Aya 19
أُولَٰئِكَ لَمْ يَكُونُوا مُعْجِزِينَ فِي الْأَرْضِ وَمَا كَانَ لَهُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِنْ أَوْلِيَاءَ ۘ يُضَاعَفُ لَهُمُ الْعَذَابُ ۚ مَا كَانُوا يَسْتَطِيعُونَ السَّمْعَ وَمَا كَانُوا يُبْصِرُونَ ( 20 ) ሁድ - Aya 20
እነዚያ በምድር ውስጥ (ከአላህ) የሚያመልጡ አልነበሩም፡፡ ከአላህም ሌላ ለእነርሱ ረዳቶች አልነበሯቸውም፡፡ ለእነሱ ቅጣቱ ይደራረብላቸዋል፡፡ (እውነትን) መስማትን የሚችሉ አልነበሩም የሚያዩም አልነበሩም፡፡ ሁድ - Aya 20
أُولَٰئِكَ الَّذِينَ خَسِرُوا أَنفُسَهُمْ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا يَفْتَرُونَ ( 21 ) ሁድ - Aya 21
እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ከእነሱም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር የጠፋቸው ናቸው፡፡ ሁድ - Aya 21
لَا جَرَمَ أَنَّهُمْ فِي الْآخِرَةِ هُمُ الْأَخْسَرُونَ ( 22 ) ሁድ - Aya 22
እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም በጣም ከሳሪዎቹ እነሱ መሆናቸው ጥርጥር የለውም፡፡ ሁድ - Aya 22
إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَأَخْبَتُوا إِلَىٰ رَبِّهِمْ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ ( 23 ) ሁድ - Aya 23
እነዚያ ያመኑትና በጎ ሥራዎችን የሠሩት ወደ ጌታቸውም የተዋረዱት እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ ሁድ - Aya 23
مَثَلُ الْفَرِيقَيْنِ كَالْأَعْمَىٰ وَالْأَصَمِّ وَالْبَصِيرِ وَالسَّمِيعِ ۚ هَلْ يَسْتَوِيَانِ مَثَلًا ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ ( 24 ) ሁድ - Aya 24
የሁለቱ ክፍሎች ምሳሌ እንደ ዕውርና እንደ ደንቆሮ እንደሚያይና እንደሚሰማም ብጤ ነው፡፡ በምሳሌ ይተካከላሉን አትገሰጹምን ሁድ - Aya 24
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ إِنِّي لَكُمْ نَذِيرٌ مُّبِينٌ ( 25 ) ሁድ - Aya 25
ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክን፡፡ (አላቸውም)፡- «እኔ ለእናንተ ግልጽ አስፈራሪ (አስጠንቃቂ) ነኝ፡፡» ሁድ - Aya 25
أَن لَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۖ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ أَلِيمٍ ( 26 ) ሁድ - Aya 26
«አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ በእናንተ ላይ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁና፡፡» ሁድ - Aya 26
فَقَالَ الْمَلَأُ الَّذِينَ كَفَرُوا مِن قَوْمِهِ مَا نَرَاكَ إِلَّا بَشَرًا مِّثْلَنَا وَمَا نَرَاكَ اتَّبَعَكَ إِلَّا الَّذِينَ هُمْ أَرَاذِلُنَا بَادِيَ الرَّأْيِ وَمَا نَرَىٰ لَكُمْ عَلَيْنَا مِن فَضْلٍ بَلْ نَظُنُّكُمْ كَاذِبِينَ ( 27 ) ሁድ - Aya 27
ከሕዝቦቹም እነዚያ የካዱት መሪዎቹ ብጤያችን ሰው ሆነህ እንጂ አናይህም፡፡ እነዚያም እነሱ ሐሳበ ጥሬዎች የሆኑት ወራዶቻችን እንጂ ሌላ ተከትሎህ አናይህም፡፡ ለእናንተም በእኛ ላይ ምንም ብልጫን አናይም፡፡ ከቶውንም ውሸታሞች መሆናችሁን እንጠረጥራችኋለን አሉ፡፡ ሁድ - Aya 27
قَالَ يَا قَوْمِ أَرَأَيْتُمْ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّي وَآتَانِي رَحْمَةً مِّنْ عِندِهِ فَعُمِّيَتْ عَلَيْكُمْ أَنُلْزِمُكُمُوهَا وَأَنتُمْ لَهَا كَارِهُونَ ( 28 ) ሁድ - Aya 28
«ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ ከጌታዬ በግልጽ ማስረጃ ላይ ብሆን ከእርሱም ዘንድ የሆነን ችሮታ (ነብይነት) ቢሰጠኝና በእናንተ ላይ ብትደበቅባችሁ እናንተ ለርቯ ጠይዎች ስትሆኑ እርቯን (በመቀበል) እናስገድዳችኋለን» አላቸው፡፡ ሁድ - Aya 28
وَيَا قَوْمِ لَا أَسْأَلُكُمْ عَلَيْهِ مَالًا ۖ إِنْ أَجْرِيَ إِلَّا عَلَى اللَّهِ ۚ وَمَا أَنَا بِطَارِدِ الَّذِينَ آمَنُوا ۚ إِنَّهُم مُّلَاقُو رَبِّهِمْ وَلَٰكِنِّي أَرَاكُمْ قَوْمًا تَجْهَلُونَ ( 29 ) ሁድ - Aya 29
«ሕዝቦቼም ሆይ! በርሱ (በተላክሁበት ማድረስ) ላይ ገንዘብን አልጠይቃችሁም፡፡ ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ እኔም እነዚያን ያመኑትን አባራሪ አይደለሁም፡፡ እነርሱ ጌታቸውን የሚገናኙ ናቸውና፡፡ ግን እኔም የምትሳሳቱ ሕዝቦች ሆናችሁ አያችኋለሁ፡፡» ሁድ - Aya 29
وَيَا قَوْمِ مَن يَنصُرُنِي مِنَ اللَّهِ إِن طَرَدتُّهُمْ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ ( 30 ) ሁድ - Aya 30
«ሕዝቦቼም ሆይ ባባርራቸው ከአላህ (ቅጣት) የሚያድነኝ ማን ነው አትገሰጹምን» ሁድ - Aya 30
وَلَا أَقُولُ لَكُمْ عِندِي خَزَائِنُ اللَّهِ وَلَا أَعْلَمُ الْغَيْبَ وَلَا أَقُولُ إِنِّي مَلَكٌ وَلَا أَقُولُ لِلَّذِينَ تَزْدَرِي أَعْيُنُكُمْ لَن يُؤْتِيَهُمُ اللَّهُ خَيْرًا ۖ اللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا فِي أَنفُسِهِمْ ۖ إِنِّي إِذًا لَّمِنَ الظَّالِمِينَ ( 31 ) ሁድ - Aya 31
«ለእናንተም እኔ ዘንድ የአላህ ግምጃ ቤቶች አልሉ ሩቅንም ዐውቃለሁ አልላችሁም፡፡ እኔም መልአክ ነኝ አልላችሁም፡፡ ለእነዚያም ዓይኖቻችሁ ለሚያዋርዷቸው አላህ ደግ ነገርን (እምነትን) አይሰጣቸውም አልልም፡፡ አላህ በነፍሶቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር አዋቂ ነው፡፡ እኔ ያን ጊዜ ከበደለኞች እሆናለሁና» (አላቸው)፡፡ ሁድ - Aya 31
قَالُوا يَا نُوحُ قَدْ جَادَلْتَنَا فَأَكْثَرْتَ جِدَالَنَا فَأْتِنَا بِمَا تَعِدُنَا إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِينَ ( 32 ) ሁድ - Aya 32
«ኑህ ሆይ! በእርግጥ ተከራከርከን፡፡ እኛን መከራከርህንም አበዛኸው፡፡ ከእውነተኞቹም እንደሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት አምጣው» አሉ፡ ሁድ - Aya 32
قَالَ إِنَّمَا يَأْتِيكُم بِهِ اللَّهُ إِن شَاءَ وَمَا أَنتُم بِمُعْجِزِينَ ( 33 ) ሁድ - Aya 33
«እርሱን የሚያመጣባችሁ የሻ እንደ ሆነ አላህ ብቻ ነው፡፡ እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም» አላቸው፡፡ ሁድ - Aya 33
وَلَا يَنفَعُكُمْ نُصْحِي إِنْ أَرَدتُّ أَنْ أَنصَحَ لَكُمْ إِن كَانَ اللَّهُ يُرِيدُ أَن يُغْوِيَكُمْ ۚ هُوَ رَبُّكُمْ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ ( 34 ) ሁድ - Aya 34
«ለእናንተም ልመክራችሁ ብሻ አላህ ሊያጠማችሁ ሽቶ እንደ ኾነ ምክሬ አይጠቅማችሁም፡፡ እርሱ ጌታችሁ ነው፡፡ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ» (አላቸው)፡፡ ሁድ - Aya 34
أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَاهُ ۖ قُلْ إِنِ افْتَرَيْتُهُ فَعَلَيَّ إِجْرَامِي وَأَنَا بَرِيءٌ مِّمَّا تُجْرِمُونَ ( 35 ) ሁድ - Aya 35
«ይልቁንም ቀጠፈው ይላሉን ብቀጥፈው ኃጢኣቴ (ቅጣቱ) በኔ ላይ ነው፡፡ እኔም ከምታጠፉት (ጥፋት) ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡ ሁድ - Aya 35
وَأُوحِيَ إِلَىٰ نُوحٍ أَنَّهُ لَن يُؤْمِنَ مِن قَوْمِكَ إِلَّا مَن قَدْ آمَنَ فَلَا تَبْتَئِسْ بِمَا كَانُوا يَفْعَلُونَ ( 36 ) ሁድ - Aya 36
ወደ ኑሕም እነሆ «ከሕዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር (ወደፊት) አያምኑም፡፡ ይሠሩትም በነበሩት (ክህደት) አትዘን ማለት ተወረደ፡፡» ሁድ - Aya 36
وَاصْنَعِ الْفُلْكَ بِأَعْيُنِنَا وَوَحْيِنَا وَلَا تُخَاطِبْنِي فِي الَّذِينَ ظَلَمُوا ۚ إِنَّهُم مُّغْرَقُونَ ( 37 ) ሁድ - Aya 37
(አላህም) «በጥበቃችንና በትእዛዛችንም ሆነህ መርከቢቱን ሥራ፡፡ በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታናግረኝ እነሱ በእርግጥ ሰማጮች ናቸውና» (አለው)፡፡ ሁድ - Aya 37
وَيَصْنَعُ الْفُلْكَ وَكُلَّمَا مَرَّ عَلَيْهِ مَلَأٌ مِّن قَوْمِهِ سَخِرُوا مِنْهُ ۚ قَالَ إِن تَسْخَرُوا مِنَّا فَإِنَّا نَسْخَرُ مِنكُمْ كَمَا تَسْخَرُونَ ( 38 ) ሁድ - Aya 38
ከወገኖቹም መሪዎቹ በእርሱ አጠገብ ባለፉ ቁጥር ከእርሱ እየተሳለቁ መርከቢቱን ይሠራል፡፡ «ከእኛ ብትሳለቁ እኛም እንደተሳለቃችሁብን ከናንተ እንሳለቅባችኋለን» አላቸው፡፡ ሁድ - Aya 38
فَسَوْفَ تَعْلَمُونَ مَن يَأْتِيهِ عَذَابٌ يُخْزِيهِ وَيَحِلُّ عَلَيْهِ عَذَابٌ مُّقِيمٌ ( 39 ) ሁድ - Aya 39
«የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትን በእርሱም ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበት ሰው (ማን እንደ ሆነ) ወደፊት ታውቃላችሁ» (አላቸው)፡፡ ሁድ - Aya 39
حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَمْرُنَا وَفَارَ التَّنُّورُ قُلْنَا احْمِلْ فِيهَا مِن كُلٍّ زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ وَأَهْلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيْهِ الْقَوْلُ وَمَنْ آمَنَ ۚ وَمَا آمَنَ مَعَهُ إِلَّا قَلِيلٌ ( 40 ) ሁድ - Aya 40
ትእዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ «በእርሷ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት (ወንድና ሴት) ፤ ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን» አልነው፡፡ ከእርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም፡፡ ሁድ - Aya 40
وَقَالَ ارْكَبُوا فِيهَا بِسْمِ اللَّهِ مَجْرَاهَا وَمُرْسَاهَا ۚ إِنَّ رَبِّي لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ ( 41 ) ሁድ - Aya 41
«መሄዷም መቆሟም በአላህ ስም ነው እያላችሁም በውስጧ ተሳፈሩ፡፡ ጌታ መሓሪ አዛኝ ነውና» አላቸው፡፡ ሁድ - Aya 41
وَهِيَ تَجْرِي بِهِمْ فِي مَوْجٍ كَالْجِبَالِ وَنَادَىٰ نُوحٌ ابْنَهُ وَكَانَ فِي مَعْزِلٍ يَا بُنَيَّ ارْكَب مَّعَنَا وَلَا تَكُن مَّعَ الْكَافِرِينَ ( 42 ) ሁድ - Aya 42
እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ በእነርሱ (ይዛቸው) የምትንሻለል ስትሆን (በአላህ ስም ተቀመጡባት)፡፡ ኑሕም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ «ልጄ ሆይ! ከኛ ጋር ተሳፈር ከከሓዲዎቹም አትሁን» ሲል ጠራው፡፡ ሁድ - Aya 42
قَالَ سَآوِي إِلَىٰ جَبَلٍ يَعْصِمُنِي مِنَ الْمَاءِ ۚ قَالَ لَا عَاصِمَ الْيَوْمَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ إِلَّا مَن رَّحِمَ ۚ وَحَالَ بَيْنَهُمَا الْمَوْجُ فَكَانَ مِنَ الْمُغْرَقِينَ ( 43 ) ሁድ - Aya 43
(ልጁም) «ከውሃው ወደሚጠብቀኝ ተራራ እጠጋለሁ» አለ፡፡ (አባቱም)፡- «ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም (እርሱ) ያዘነለት ካልሆነ በቀር» አለው፡፡ ማዕበሉም በመካከላቸው ጋረደ፡፡ ከሰጣሚዎቹም ሆነ፡፡ ሁድ - Aya 43
وَقِيلَ يَا أَرْضُ ابْلَعِي مَاءَكِ وَيَا سَمَاءُ أَقْلِعِي وَغِيضَ الْمَاءُ وَقُضِيَ الْأَمْرُ وَاسْتَوَتْ عَلَى الْجُودِيِّ ۖ وَقِيلَ بُعْدًا لِّلْقَوْمِ الظَّالِمِينَ ( 44 ) ሁድ - Aya 44
ተባለም፡- «ምድር ሆይ! ውሃሽን ዋጪ፡፡ ሰማይም ሆይ (ዝናብሽን) ያዢ፡፡ ውሃውም ሰረገ፡፡ ቅጣቱም ተፈጸም፡፡ ጁዲይ በሚባልም ተራራ ላይ (መርከቢቱ) ተደላደለች፡፡ ለከሓዲዎችም ሰዎች ጥፋት ተገባቸው (ጠፉ)» ተባለ፡፡ ሁድ - Aya 44
وَنَادَىٰ نُوحٌ رَّبَّهُ فَقَالَ رَبِّ إِنَّ ابْنِي مِنْ أَهْلِي وَإِنَّ وَعْدَكَ الْحَقُّ وَأَنتَ أَحْكَمُ الْحَاكِمِينَ ( 45 ) ሁድ - Aya 45
ኑሕም ጌታውን ጠራ፡፡ አለም «ጌታዬ ሆይ! ልጄ ከቤተሰቤ ነው፡፡ ኪዳንህም እውነት ነው፡፡ አንተም ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ዐዋቂ ነህ፡፡» ሁድ - Aya 45
قَالَ يَا نُوحُ إِنَّهُ لَيْسَ مِنْ أَهْلِكَ ۖ إِنَّهُ عَمَلٌ غَيْرُ صَالِحٍ ۖ فَلَا تَسْأَلْنِ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۖ إِنِّي أَعِظُكَ أَن تَكُونَ مِنَ الْجَاهِلِينَ ( 46 ) ሁድ - Aya 46
(አላህም) «ኑሕ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም፤ እርሱ መልካም ያልሆነ ሥራ ነው፤ በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ፤ እኔ ከሚሳሳቱት ሰዎች እንዳትሆን እገስጽሀለሁ» አለ፡፡ ሁድ - Aya 46
قَالَ رَبِّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ أَنْ أَسْأَلَكَ مَا لَيْسَ لِي بِهِ عِلْمٌ ۖ وَإِلَّا تَغْفِرْ لِي وَتَرْحَمْنِي أَكُن مِّنَ الْخَاسِرِينَ ( 47 ) ሁድ - Aya 47
«ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ለእኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን እኔ ባንተ እጠበቃለሁ፡፡ ለእኔም ባትምረኝና ባታዝንልኝ ከከሳሪዎቹ እሆናለሁ» አለ፡፡ ሁድ - Aya 47
قِيلَ يَا نُوحُ اهْبِطْ بِسَلَامٍ مِّنَّا وَبَرَكَاتٍ عَلَيْكَ وَعَلَىٰ أُمَمٍ مِّمَّن مَّعَكَ ۚ وَأُمَمٌ سَنُمَتِّعُهُمْ ثُمَّ يَمَسُّهُم مِّنَّا عَذَابٌ أَلِيمٌ ( 48 ) ሁድ - Aya 48
«ኑሕ ሆይ! ከእኛ በሆነ ሰላም ባንተ ላይና አንተም ጋር ባሉት ሕዝቦች (ትውልድ) ላይ በሆኑ በረከቶችም የተጎናጸፍክ ሆነህ ውረድ፡፡ (ከእነሱው ዘሮች የሆኑ) ሕዝቦችም በቅርቢቱ ዓለም በእርግጥ እናስመቻቸዋለን፡፡ ከዚያም ከኛ የሆነ አሳማሚ ቅጣት ይነካቸዋል» ተባለ፡፡ ሁድ - Aya 48
تِلْكَ مِنْ أَنبَاءِ الْغَيْبِ نُوحِيهَا إِلَيْكَ ۖ مَا كُنتَ تَعْلَمُهَا أَنتَ وَلَا قَوْمُكَ مِن قَبْلِ هَٰذَا ۖ فَاصْبِرْ ۖ إِنَّ الْعَاقِبَةَ لِلْمُتَّقِينَ ( 49 ) ሁድ - Aya 49
ይህቺ ከሩቁ ወሬዎች ናት፡፡ ወደ አንተ እናወርዳታለን፡፡ አንተም ሕዝቦችህም ከዚህ በፊት የምታውቋት አልነበራችሁም፡፡ ታገስም፤ ምስጉን የሆነችው ፍጻሜ ለሚጠነቀቁት ናትና፡፡ ሁድ - Aya 49
وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمْ هُودًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ إِنْ أَنتُمْ إِلَّا مُفْتَرُونَ ( 50 ) ሁድ - Aya 50
ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን (ላክን)፡፡ አላቸው፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ እናንተም ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም፡፡ ሁድ - Aya 50
يَا قَوْمِ لَا أَسْأَلُكُمْ عَلَيْهِ أَجْرًا ۖ إِنْ أَجْرِيَ إِلَّا عَلَى الَّذِي فَطَرَنِي ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ ( 51 ) ሁድ - Aya 51
«ሕዝቦቼ ሆይ! በእርሱ (በማድረሴ) ላይ ምንዳን አልጠይቃችሁም፡፡ ምንዳዬ በዚህ በፈጠረኝ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ አታውቁምን ሁድ - Aya 51
وَيَا قَوْمِ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ يُرْسِلِ السَّمَاءَ عَلَيْكُم مِّدْرَارًا وَيَزِدْكُمْ قُوَّةً إِلَىٰ قُوَّتِكُمْ وَلَا تَتَوَلَّوْا مُجْرِمِينَ ( 52 ) ሁድ - Aya 52
«ሕዝቦቼም ሆይ! ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ ከዚያም ወደርሱ ተጸጸቱ፡፡ ዝናብን በእናንተ ላይ ተከታታይ አድርጎ ይልክላችኋልና፡፡ ወደ ኃይላችሁም ኃይልን ይጨምርላችኋል፡፡ አመጸኞችም ሆናችሁ አትሽሹ፡፡» ሁድ - Aya 52
قَالُوا يَا هُودُ مَا جِئْتَنَا بِبَيِّنَةٍ وَمَا نَحْنُ بِتَارِكِي آلِهَتِنَا عَن قَوْلِكَ وَمَا نَحْنُ لَكَ بِمُؤْمِنِينَ ( 53 ) ሁድ - Aya 53
አሉ፡- «ሁድ ሆይ! በአስረጅ አልመጣህልንም፡፡ እኛም ላንተ ንግግር ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው አይደለንም፡፡ እኛም ለአንተ አማኞች አይደለንም፡፡ ሁድ - Aya 53
إِن نَّقُولُ إِلَّا اعْتَرَاكَ بَعْضُ آلِهَتِنَا بِسُوءٍ ۗ قَالَ إِنِّي أُشْهِدُ اللَّهَ وَاشْهَدُوا أَنِّي بَرِيءٌ مِّمَّا تُشْرِكُونَ ( 54 ) ሁድ - Aya 54
«ከፊሎቹ አማልክቶቻችን በክፉ ነገር (በዕብደት) ለክፈውሃል እንጂ ሌላን አንልም» (አሉ)፡፡ «እኔ አላህን አስመሰክራለሁ፡፡ ከምታጋሩትም እኔ ንጹሕ መሆኔን መስክሩ» አላቸው፡፡ ሁድ - Aya 54
مِن دُونِهِ ۖ فَكِيدُونِي جَمِيعًا ثُمَّ لَا تُنظِرُونِ ( 55 ) ሁድ - Aya 55
ከእርሱ ሌላ (አማልክትን ከምታጋሩት ንጹህ ነኝ)፡፡ ሁላችሁም ሆናችሁ ተንኮልን ሥሩብኝ፤ ከዚያም አታቆዩኝ፡፡ ሁድ - Aya 55
إِنِّي تَوَكَّلْتُ عَلَى اللَّهِ رَبِّي وَرَبِّكُم ۚ مَّا مِن دَابَّةٍ إِلَّا هُوَ آخِذٌ بِنَاصِيَتِهَا ۚ إِنَّ رَبِّي عَلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ ( 56 ) ሁድ - Aya 56
«እኔ በጌታዬና በጌታችሁ በአላህ ላይ ተጠጋሁ፡፡ በምድር ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም እርሱ አናትዋን የያዛት ብትሆን እንጂ፡፡ ጌታዬ (ቃሉም ሥራውም) በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነው» (አላቸው)፡፡ ሁድ - Aya 56
فَإِن تَوَلَّوْا فَقَدْ أَبْلَغْتُكُم مَّا أُرْسِلْتُ بِهِ إِلَيْكُمْ ۚ وَيَسْتَخْلِفُ رَبِّي قَوْمًا غَيْرَكُمْ وَلَا تَضُرُّونَهُ شَيْئًا ۚ إِنَّ رَبِّي عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ حَفِيظٌ ( 57 ) ሁድ - Aya 57
«ብትዞሩም በእርሱ ወደእናንተ የተላክሁበትን ነገር በእርግጥ አድርሼላችኋለሁ፡፡ ጌታዬ ከእናንተ ሌላ ሕዝብም ይተካል ምንም አትጎዱትምም፡፡ ጌታዬ በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነውና» (አላቸው)፡፡ ሁድ - Aya 57
وَلَمَّا جَاءَ أَمْرُنَا نَجَّيْنَا هُودًا وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ بِرَحْمَةٍ مِّنَّا وَنَجَّيْنَاهُم مِّنْ عَذَابٍ غَلِيظٍ ( 58 ) ሁድ - Aya 58
ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሁድንና እነዚያን ከእሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን፡፡ ከብርቱ ቅጣትም አዳናቸው፡፡ ሁድ - Aya 58
وَتِلْكَ عَادٌ ۖ جَحَدُوا بِآيَاتِ رَبِّهِمْ وَعَصَوْا رُسُلَهُ وَاتَّبَعُوا أَمْرَ كُلِّ جَبَّارٍ عَنِيدٍ ( 59 ) ሁድ - Aya 59
ይህች (ነገድ) ዓድ ናት፡፡ በጌታቸው ታምራት ካዱ፡፡ መልክተኞቹንም አመጹ፤ የኃያል ሞገደኛን ሁሉ ትዕዛዝም ተከተሉ፡፡ ሁድ - Aya 59
وَأُتْبِعُوا فِي هَٰذِهِ الدُّنْيَا لَعْنَةً وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ أَلَا إِنَّ عَادًا كَفَرُوا رَبَّهُمْ ۗ أَلَا بُعْدًا لِّعَادٍ قَوْمِ هُودٍ ( 60 ) ሁድ - Aya 60
በዚህች በቅርቢቱ ዓለምም እርግማን እንዲከተላቸው ተደረጉ፡፡ በትንሣኤም ቀን (እንደዚሁ)፡፡ ንቁ! ዓዶች ጌታቸውን ካዱ፡፡ ንቁ! የሁድ ሕዝቦች ለሆኑት ዓዶች (ከእዝነት) መራቅ ይገባቸው፡፡ ሁድ - Aya 60
وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَاسْتَعْمَرَكُمْ فِيهَا فَاسْتَغْفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي قَرِيبٌ مُّجِيبٌ ( 61 ) ሁድ - Aya 61
ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን (ላክን)፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ እርሱ ከምድር ፈጠራችሁ፡፡ በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ፡፡ ምሕረቱንም ለምኑት፡፡ ከዚህም ወደእርሱ ተመለሱ፡፡ ጌታዬ ቅርብ (ለለመነው) ተቀባይ ነውና» አላቸው፡፡ ሁድ - Aya 61
قَالُوا يَا صَالِحُ قَدْ كُنتَ فِينَا مَرْجُوًّا قَبْلَ هَٰذَا ۖ أَتَنْهَانَا أَن نَّعْبُدَ مَا يَعْبُدُ آبَاؤُنَا وَإِنَّنَا لَفِي شَكٍّ مِّمَّا تَدْعُونَا إِلَيْهِ مُرِيبٍ ( 62 ) ሁድ - Aya 62
«ሷሊህ ሆይ! ከዚህ በፊት በእኛ ውስጥ (መሪ ልትሆን) በእርግጥ የምትከጅል ነበርክ፡፡ አባቶቻችን የሚገዙትን ከመገዛት ትከለክለናለህን እኛም ወደርሱ ከምትጠራን ነገር በእርግጥ አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ነን» አሉ፡፡ ሁድ - Aya 62
قَالَ يَا قَوْمِ أَرَأَيْتُمْ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّي وَآتَانِي مِنْهُ رَحْمَةً فَمَن يَنصُرُنِي مِنَ اللَّهِ إِنْ عَصَيْتُهُ ۖ فَمَا تَزِيدُونَنِي غَيْرَ تَخْسِيرٍ ( 63 ) ሁድ - Aya 63
«ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ ከጌታዬ በሆነ ማስረጃ ላይ ብሆን ከእርሱም የሆነን ችሮታ (ነቢይነት) ቢሰጠኝና ባልታዘዘው ከአላህ (ቅጣት) የሚያድነኝ ማነው ከማሳሳትም በስተቀር ምንም አትጨምሩልኝም» አላቸው፡፡ ሁድ - Aya 63
وَيَا قَوْمِ هَٰذِهِ نَاقَةُ اللَّهِ لَكُمْ آيَةً فَذَرُوهَا تَأْكُلْ فِي أَرْضِ اللَّهِ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوءٍ فَيَأْخُذَكُمْ عَذَابٌ قَرِيبٌ ( 64 ) ሁድ - Aya 64
ሕዝቦቼም ሆይ! ይህቺ ለእናንተ ተዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናት፡፡ ተውዋትም፡፡ በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ፡፡ በክፉም አትንኳት፡፡ ቅርብ የሆነ ቅጣት ይይዛችኋልና» (አላቸው)፡፡ ሁድ - Aya 64
فَعَقَرُوهَا فَقَالَ تَمَتَّعُوا فِي دَارِكُمْ ثَلَاثَةَ أَيَّامٍ ۖ ذَٰلِكَ وَعْدٌ غَيْرُ مَكْذُوبٍ ( 65 ) ሁድ - Aya 65
ወግተው ገደሏትም፡፡ (ሷሊህ) «በአገራችሁም ሶስትን ቀናት (ብቻ) ተጠቀሙ፡፡ ይህ የማይዋሽ ቀጠሮ ነው» አላቸው፡፡ ሁድ - Aya 65
فَلَمَّا جَاءَ أَمْرُنَا نَجَّيْنَا صَالِحًا وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ بِرَحْمَةٍ مِّنَّا وَمِنْ خِزْيِ يَوْمِئِذٍ ۗ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ الْقَوِيُّ الْعَزِيزُ ( 66 ) ሁድ - Aya 66
ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሷሊህንና እነዚያን ከሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው እዝነት አዳን፡፡ ከዚያም ቀን ውርደት (አዳንናቸው)፡፡ ጌታህ እርሱ ብርቱው አሸናፊው ነውና፡፡ ሁድ - Aya 66
وَأَخَذَ الَّذِينَ ظَلَمُوا الصَّيْحَةُ فَأَصْبَحُوا فِي دِيَارِهِمْ جَاثِمِينَ ( 67 ) ሁድ - Aya 67
እነዚያንም የበደሉትን ጩኸት ያዛቸው፡፡ በቤቶቻቸውም ውስጥ የተንበረከኩ ሆነው ሞተው አነጉ፡፡ ሁድ - Aya 67
كَأَن لَّمْ يَغْنَوْا فِيهَا ۗ أَلَا إِنَّ ثَمُودَ كَفَرُوا رَبَّهُمْ ۗ أَلَا بُعْدًا لِّثَمُودَ ( 68 ) ሁድ - Aya 68
በእሷ ውስጥ እንዳልኖሩባት ሆኑ፡፡ ንቁ! ሰሙዶች ጌታቸውን በእርግጥ ካዱ፡፡ ንቁ! ለሰሙዶች (ከአላህ እዝነት) መራቅ ተገባቸው፡፡ ሁድ - Aya 68
وَلَقَدْ جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ ۖ فَمَا لَبِثَ أَن جَاءَ بِعِجْلٍ حَنِيذٍ ( 69 ) ሁድ - Aya 69
መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በ(ልጅ) ብስራት በእርግጥ መጡት፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ፡፡ ሁድ - Aya 69
فَلَمَّا رَأَىٰ أَيْدِيَهُمْ لَا تَصِلُ إِلَيْهِ نَكِرَهُمْ وَأَوْجَسَ مِنْهُمْ خِيفَةً ۚ قَالُوا لَا تَخَفْ إِنَّا أُرْسِلْنَا إِلَىٰ قَوْمِ لُوطٍ ( 70 ) ሁድ - Aya 70
እጆቻቸውም ወደ እርሱ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፡፡ ከነሱም ፍርሃት ተሰማው፡፡ «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና» አሉት፡፡ ሁድ - Aya 70
وَامْرَأَتُهُ قَائِمَةٌ فَضَحِكَتْ فَبَشَّرْنَاهَا بِإِسْحَاقَ وَمِن وَرَاءِ إِسْحَاقَ يَعْقُوبَ ( 71 ) ሁድ - Aya 71
ሚስቱም የቆመች ስትኾን (አትፍራ አሉት) ሳቀችም፡፡ በኢስሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ (በልጁ) በያዕቁብ (አበሰርናት)፡፡ ሁድ - Aya 71
قَالَتْ يَا وَيْلَتَىٰ أَأَلِدُ وَأَنَا عَجُوزٌ وَهَٰذَا بَعْلِي شَيْخًا ۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيْءٌ عَجِيبٌ ( 72 ) ሁድ - Aya 72
(እርሷም) ዋልኝ! እኔ አሮጊት ይህም ባሌ ሽማግሌ ሆኖ ሳለ እወልዳለሁን ይህ በእርግጥ አስደናቂ ነገር ነው አለች፡፡ ሁድ - Aya 72
قَالُوا أَتَعْجَبِينَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۖ رَحْمَتُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الْبَيْتِ ۚ إِنَّهُ حَمِيدٌ مَّجِيدٌ ( 73 ) ሁድ - Aya 73
«ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ችሮታና በረከቶቹ በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን እርሱ ምስጉን ለጋስ ነውና» አሉ፡፡ ሁድ - Aya 73
فَلَمَّا ذَهَبَ عَنْ إِبْرَاهِيمَ الرَّوْعُ وَجَاءَتْهُ الْبُشْرَىٰ يُجَادِلُنَا فِي قَوْمِ لُوطٍ ( 74 ) ሁድ - Aya 74
ከኢብራሂም ፍራቻው በሌደለትና ብስራት በመጣችለትም ጊዜ በሉጥ ሕዝቦች (ነገር) ይከራከረን ጀመር፡፡ ሁድ - Aya 74
إِنَّ إِبْرَاهِيمَ لَحَلِيمٌ أَوَّاهٌ مُّنِيبٌ ( 75 ) ሁድ - Aya 75
ኢብራሂም በእርግጥ ታጋሽ አልቃሻ መላሳ ነውና፡፡ ሁድ - Aya 75
يَا إِبْرَاهِيمُ أَعْرِضْ عَنْ هَٰذَا ۖ إِنَّهُ قَدْ جَاءَ أَمْرُ رَبِّكَ ۖ وَإِنَّهُمْ آتِيهِمْ عَذَابٌ غَيْرُ مَرْدُودٍ ( 76 ) ሁድ - Aya 76
«ኢብራሂም ሆይ! ከዚህ (ክርክር) ተው፡፡ እነሆ የጌታህ ትዕዛዝ በእርግጥ መጥቷል፡፡ እነሱም የማይመለስ ቅጣት የሚመጣባቸው ናቸው» (አሉት)፡፡ ሁድ - Aya 76
وَلَمَّا جَاءَتْ رُسُلُنَا لُوطًا سِيءَ بِهِمْ وَضَاقَ بِهِمْ ذَرْعًا وَقَالَ هَٰذَا يَوْمٌ عَصِيبٌ ( 77 ) ሁድ - Aya 77
መልክተኞቻችንም ሉጥን በመጡት ጊዜ በነሱ (ምክንያት) አዘነ፡፡ ልቡም በነሱ ተጨነቀ፡፡ «ይህ ብርቱ ቀን ነውም» አለ፡፡ ሁድ - Aya 77
وَجَاءَهُ قَوْمُهُ يُهْرَعُونَ إِلَيْهِ وَمِن قَبْلُ كَانُوا يَعْمَلُونَ السَّيِّئَاتِ ۚ قَالَ يَا قَوْمِ هَٰؤُلَاءِ بَنَاتِي هُنَّ أَطْهَرُ لَكُمْ ۖ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَلَا تُخْزُونِ فِي ضَيْفِي ۖ أَلَيْسَ مِنكُمْ رَجُلٌ رَّشِيدٌ ( 78 ) ሁድ - Aya 78
ሕዝቦቹም ወደርሱ እየተጣደፉ መጡት፡፡ ከዚህም በፊት መጥፎ ሥራዎችን ይሠሩ ነበር፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! እኝህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው፡፡ እነሱ ለእናንተ ይልቅ በጣም የጸዱ ናቸው፤ (አግቧቸው)፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ በእንግዶቼም አታሳፍሩኝ፡፡ ከእናንተ ውስጥ ቅን ሰው የለምን» አላቸው፡፡ ሁድ - Aya 78
قَالُوا لَقَدْ عَلِمْتَ مَا لَنَا فِي بَنَاتِكَ مِنْ حَقٍّ وَإِنَّكَ لَتَعْلَمُ مَا نُرِيدُ ( 79 ) ሁድ - Aya 79
«ከሴቶች ልጆችህ ለእኛ ምንም ጉዳይ የለንም፡፡ አንተም የምንሻውን በእርግጥ ታውቃለህ» አሉት፡፡ ሁድ - Aya 79
قَالَ لَوْ أَنَّ لِي بِكُمْ قُوَّةً أَوْ آوِي إِلَىٰ رُكْنٍ شَدِيدٍ ( 80 ) ሁድ - Aya 80
«በእናንተ ላይ ለኔ ኀይል በኖረኝ ወይም ወደ ብርቱ ወገን ብጠጋ ኖሮ (የምሠራውን በሠራሁ ነበር)» አላቸው፡፡ ሁድ - Aya 80
قَالُوا يَا لُوطُ إِنَّا رُسُلُ رَبِّكَ لَن يَصِلُوا إِلَيْكَ ۖ فَأَسْرِ بِأَهْلِكَ بِقِطْعٍ مِّنَ اللَّيْلِ وَلَا يَلْتَفِتْ مِنكُمْ أَحَدٌ إِلَّا امْرَأَتَكَ ۖ إِنَّهُ مُصِيبُهَا مَا أَصَابَهُمْ ۚ إِنَّ مَوْعِدَهُمُ الصُّبْحُ ۚ أَلَيْسَ الصُّبْحُ بِقَرِيبٍ ( 81 ) ሁድ - Aya 81
«ሉጥ ሆይ! እኛ የጌታህ መልክተኞች ነን፡፡ (ሕዝቦችህ) ወደ አንተ (በክፉ) አይደርሱብህም፡፡ ቤተሰብህንም ይዘህ ከሌሊቱ በከፊሉ ውስጥ ሊድ፡፡ ከእናንተም አንድም (ወደኋላው) አይገላመጥ፡፡ ሚስትህ ብቻ ስትቀር፡፡ እነሆ እርሷን (እነሱን) የሚያገኛቸው ስቃይ ያገኛታልና፡፡ ቀጠሯቸው እንጋቱ ላይ ነው፡፡ ንጋቱ ቅርብ አይደለምን» አሉት፡፡ ሁድ - Aya 81
فَلَمَّا جَاءَ أَمْرُنَا جَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهَا حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ مَّنضُودٍ ( 82 ) ሁድ - Aya 82
82 ሁድ - Aya 82
مُّسَوَّمَةً عِندَ رَبِّكَ ۖ وَمَا هِيَ مِنَ الظَّالِمِينَ بِبَعِيدٍ ( 83 ) ሁድ - Aya 83
ከጌታህ ዘንድ ምልክት የተደረገባት ስትሆን (አዘነብናት)፡፡ እርሷም ከበደለኞቹ ሩቅ አይደለችም፡፡ ሁድ - Aya 83
وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ وَلَا تَنقُصُوا الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ ۚ إِنِّي أَرَاكُم بِخَيْرٍ وَإِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ مُّحِيطٍ ( 84 ) ሁድ - Aya 84
ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን (ላክን)፡፡ አላቸው «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ ስፍርንና ሚዛንንም አታጉድሉ፤ እኔ በጸጋ ላይ ሆናችሁ አያችኋለሁ፡፡ እኔም በእናንተ ላይ የከባቢን ቀን ቅጣት እፈራለሁ፡፡ ሁድ - Aya 84
وَيَا قَوْمِ أَوْفُوا الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا تَبْخَسُوا النَّاسَ أَشْيَاءَهُمْ وَلَا تَعْثَوْا فِي الْأَرْضِ مُفْسِدِينَ ( 85 ) ሁድ - Aya 85
«ሕዝቦቼም ሆይ! ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ፡፡ ሰዎችንም ምንም ነገራቸውን አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ፡፡ ሁድ - Aya 85
بَقِيَّتُ اللَّهِ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ ۚ وَمَا أَنَا عَلَيْكُم بِحَفِيظٍ ( 86 ) ሁድ - Aya 86
አላህ ያስቀረላችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ ምእመናን እንደሆናችሁ (አላህ በሰጣችሁ ውደዱ)፡፡ እኔም (መካሪ እንጅ) በናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም፡፡» ሁድ - Aya 86
قَالُوا يَا شُعَيْبُ أَصَلَاتُكَ تَأْمُرُكَ أَن نَّتْرُكَ مَا يَعْبُدُ آبَاؤُنَا أَوْ أَن نَّفْعَلَ فِي أَمْوَالِنَا مَا نَشَاءُ ۖ إِنَّكَ لَأَنتَ الْحَلِيمُ الرَّشِيدُ ( 87 ) ሁድ - Aya 87
«ሹዐይብ ሆይ! ስግደትህ አባቶቻችን የሚገዙትን ጣዖታት እንድንተው ወይም በገንዘቦቻችን የምንሻውን መሥራትን (እንድንተው) ታዝሃለችን አንተ በእርግጥ ታጋሹ ቅኑ አንተ ነህና» አሉት፡፡ ሁድ - Aya 87
قَالَ يَا قَوْمِ أَرَأَيْتُمْ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّي وَرَزَقَنِي مِنْهُ رِزْقًا حَسَنًا ۚ وَمَا أُرِيدُ أَنْ أُخَالِفَكُمْ إِلَىٰ مَا أَنْهَاكُمْ عَنْهُ ۚ إِنْ أُرِيدُ إِلَّا الْإِصْلَاحَ مَا اسْتَطَعْتُ ۚ وَمَا تَوْفِيقِي إِلَّا بِاللَّهِ ۚ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ أُنِيبُ ( 88 ) ሁድ - Aya 88
«ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ፤ ከጌታዬ በሆነ አስረጅ ላይ ብሆንና ከእርሱም የሆነን መልካም ሲሳይ ቢሰጠኝ (በቅጥፈት ልቀላቅለው ይገባልን) ከእርሱ ወደ ከለከልኳችሁም ነገር ልለያችሁ አልሻም፡፡ በተቻለኝ ያክል ማበጀትን እንጂ አልሻም (ለደግ ሥራ) መገጠሜም በአላህ እንጂ በሌላ አይደለም፡፡ በእርሱ ላይ ተመካሁ፡፡ ወደእርሱም እመለሳለሁ፤» አላቸው፡፡ ሁድ - Aya 88
وَيَا قَوْمِ لَا يَجْرِمَنَّكُمْ شِقَاقِي أَن يُصِيبَكُم مِّثْلُ مَا أَصَابَ قَوْمَ نُوحٍ أَوْ قَوْمَ هُودٍ أَوْ قَوْمَ صَالِحٍ ۚ وَمَا قَوْمُ لُوطٍ مِّنكُم بِبَعِيدٍ ( 89 ) ሁድ - Aya 89
«ወገኖቼም ሆይ! እኔን መከራከራችሁ የኑሕን ሕዝቦች ወይም የሁድን ሕዝቦች ወይም የሷሊሕን ሕዝቦች ያገኛቸው (ቅጣት) ብጤ እንዲያገኛችሁ አይገፋፋችሁ፡፡ የሉጥም ሕዝቦች ከእናንተ ሩቅ አይደሉም፡፡ ሁድ - Aya 89
وَاسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي رَحِيمٌ وَدُودٌ ( 90 ) ሁድ - Aya 90
«ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት፡፡ ከዚያም ወደርሱ ተመለሱ፡፡ ጌታዬ አዛኝ ወዳድ ነውና (አላቸው)፡፡ ሁድ - Aya 90
قَالُوا يَا شُعَيْبُ مَا نَفْقَهُ كَثِيرًا مِّمَّا تَقُولُ وَإِنَّا لَنَرَاكَ فِينَا ضَعِيفًا ۖ وَلَوْلَا رَهْطُكَ لَرَجَمْنَاكَ ۖ وَمَا أَنتَ عَلَيْنَا بِعَزِيزٍ ( 91 ) ሁድ - Aya 91
«ሹዐይብ ሆይ! ከምትለው ነገር ብዙውን አናውቀውም፡፡ እኛም አንተን በእኛ ውስጥ ደካማ ሆነህ እናይሃለን፡፡ ጎሳዎችህም ባልኖሩ ኖሮ በወገርንህ ነበር፤ አንተም በእኛ ላይ የተከበርክ አይደለህም» አሉት፡፡ ሁድ - Aya 91
قَالَ يَا قَوْمِ أَرَهْطِي أَعَزُّ عَلَيْكُم مِّنَ اللَّهِ وَاتَّخَذْتُمُوهُ وَرَاءَكُمْ ظِهْرِيًّا ۖ إِنَّ رَبِّي بِمَا تَعْمَلُونَ مُحِيطٌ ( 92 ) ሁድ - Aya 92
«ሕዝቦቼ ሆይ! ጎሳዎቼ በእናንተ ላይ ከአላህ ይልቅ የከበሩ ናቸውን (አላህን) ከኋላችሁ ወደ ጀርባ አድርጋችሁም ያዛችሁት፡፡ ጌታዬ በምትሠሩት ሁሉ ከባቢ ነው» አላቸው፡፡ ሁድ - Aya 92
وَيَا قَوْمِ اعْمَلُوا عَلَىٰ مَكَانَتِكُمْ إِنِّي عَامِلٌ ۖ سَوْفَ تَعْلَمُونَ مَن يَأْتِيهِ عَذَابٌ يُخْزِيهِ وَمَنْ هُوَ كَاذِبٌ ۖ وَارْتَقِبُوا إِنِّي مَعَكُمْ رَقِيبٌ ( 93 ) ሁድ - Aya 93
«ሕዝቦቼም ሆይ! በችሎታችሁ ልክ ሥሩ፡፡ እኔ ሠሪ ነኝና፡፡ የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትና እርሱ ውሸታም የሆነው ማን እንደኾነ ወደ ፊት ታውቃላችሁ፡፡ ጠብቁም እኔ ከናንተ ጋር ተጠባባቂ ነኝና»(አላቸው)፡፡ ሁድ - Aya 93
وَلَمَّا جَاءَ أَمْرُنَا نَجَّيْنَا شُعَيْبًا وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ بِرَحْمَةٍ مِّنَّا وَأَخَذَتِ الَّذِينَ ظَلَمُوا الصَّيْحَةُ فَأَصْبَحُوا فِي دِيَارِهِمْ جَاثِمِينَ ( 94 ) ሁድ - Aya 94
ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሹዐይብንና እነዚያን ከርሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን፡፡ እነዚያን የበደሉትንም (የጂብሪል) ጩኸት ያዘቻቸው፡፡ በቤቶቻቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አደሩ፡፡ ሁድ - Aya 94
كَأَن لَّمْ يَغْنَوْا فِيهَا ۗ أَلَا بُعْدًا لِّمَدْيَنَ كَمَا بَعِدَتْ ثَمُودُ ( 95 ) ሁድ - Aya 95
በእርሷ ውስጥ እንዳልነበሩ ሆኑ፡፡ ንቁ! ሰሙድ (ከአላህ እዝነት) እንደ ራቀች መድየንም ትራቅ፡፡ ሁድ - Aya 95
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِآيَاتِنَا وَسُلْطَانٍ مُّبِينٍ ( 96 ) ሁድ - Aya 96
ሙሳንም በተዓምራታችንና በግልጽ ብርሃን በእርግጥ ላክነው፡፡ ሁድ - Aya 96
إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَئِهِ فَاتَّبَعُوا أَمْرَ فِرْعَوْنَ ۖ وَمَا أَمْرُ فِرْعَوْنَ بِرَشِيدٍ ( 97 ) ሁድ - Aya 97
ወደ ፈርዖንና ወደ ሰዎቹ (ላክነው)፡፡ የፈርዖንንም ነገር (ሕዝቦቹ) ተከተሉ፡፡ የፈርዖን ነገርም ቀጥተኛ አልነበረም፡፡ ሁድ - Aya 97
يَقْدُمُ قَوْمَهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فَأَوْرَدَهُمُ النَّارَ ۖ وَبِئْسَ الْوِرْدُ الْمَوْرُودُ ( 98 ) ሁድ - Aya 98
በትንሣኤ ቀን ሕዝቦቹን ይቀድማል፡፡ ወደ እሳትም ያወርዳቸዋል፡፡ የሚገቡትም አገባብ ምንኛ ከፋ! ሁድ - Aya 98
وَأُتْبِعُوا فِي هَٰذِهِ لَعْنَةً وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ ۚ بِئْسَ الرِّفْدُ الْمَرْفُودُ ( 99 ) ሁድ - Aya 99
በዚችም (በቅርቢቱ ዓለም) እርግማንን አስከተልናቸው፡፡ በትንሣኤም ቀን (እንደዚሁ)፡፡ የተሰጡት ስጦታ ምንኛ ከፋ! ሁድ - Aya 99
ذَٰلِكَ مِنْ أَنبَاءِ الْقُرَىٰ نَقُصُّهُ عَلَيْكَ ۖ مِنْهَا قَائِمٌ وَحَصِيدٌ ( 100 ) ሁድ - Aya 100
ይህ (የተነገረው) ከከተሞቹ ወሬዎች ነው፡፡ ባንተ ላይ እንተርከዋለን፡፡ ከእርሷ ፋናው የቀረና ሙሉ በሙሉ የተደመሰሰ አለ፡፡ ሁድ - Aya 100
وَمَا ظَلَمْنَاهُمْ وَلَٰكِن ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ۖ فَمَا أَغْنَتْ عَنْهُمْ آلِهَتُهُمُ الَّتِي يَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مِن شَيْءٍ لَّمَّا جَاءَ أَمْرُ رَبِّكَ ۖ وَمَا زَادُوهُمْ غَيْرَ تَتْبِيبٍ ( 101 ) ሁድ - Aya 101
እኛም አልበደልናቸውም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን በደሉ፡፡ የአላህም ትእዛዝ በመጣ ጊዜ እነዚያ ከአላህ ሌላ የሚገዙዋቸው አማልክቶቻቸው በምንም አላዳኗቸውም፡፡ ከማክሰርም በቀር ምንም አልጨመሩላቸውም፡፡ ሁድ - Aya 101
وَكَذَٰلِكَ أَخْذُ رَبِّكَ إِذَا أَخَذَ الْقُرَىٰ وَهِيَ ظَالِمَةٌ ۚ إِنَّ أَخْذَهُ أَلِيمٌ شَدِيدٌ ( 102 ) ሁድ - Aya 102
የጌታህም ቅጣት የከተሞችን ሰዎች እነሱ በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ እንደዚህ ነው፡፡ ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው፡፡ ሁድ - Aya 102
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّمَنْ خَافَ عَذَابَ الْآخِرَةِ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمٌ مَّجْمُوعٌ لَّهُ النَّاسُ وَذَٰلِكَ يَوْمٌ مَّشْهُودٌ ( 103 ) ሁድ - Aya 103
በዚህ ውስጥ የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ለሚፈሩ ሁሉ መገሰጫ አለ፡፡ ይህ (የትንሣኤ ቀን) ሰዎች በርሱ የሚሰበሰቡበት ቀን ነው፡፡ ይህም የሚጣዱት ቀን ነው፡፡ ሁድ - Aya 103
وَمَا نُؤَخِّرُهُ إِلَّا لِأَجَلٍ مَّعْدُودٍ ( 104 ) ሁድ - Aya 104
(ይህንን ቀን) ለተቆጠረም ጊዜ እንጂ አናቆየውም፡፡ ሁድ - Aya 104
يَوْمَ يَأْتِ لَا تَكَلَّمُ نَفْسٌ إِلَّا بِإِذْنِهِ ۚ فَمِنْهُمْ شَقِيٌّ وَسَعِيدٌ ( 105 ) ሁድ - Aya 105
በሚመጣ ቀን ማንኛዋም ነፍስ በእርሱ ፈቃድ ቢሆን እንጂ አትናገርም፡፡ ከነሱም መናጢና ዕድለኛም አልለ፡፡ ሁድ - Aya 105
فَأَمَّا الَّذِينَ شَقُوا فَفِي النَّارِ لَهُمْ فِيهَا زَفِيرٌ وَشَهِيقٌ ( 106 ) ሁድ - Aya 106
እነዚያ መናጢ የሆኑትማ፡ በእሳት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በእርሷ ውስጥ ማናፋትና መንሰቅሰቅ አላቸው፡፡ ሁድ - Aya 106
خَالِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ إِلَّا مَا شَاءَ رَبُّكَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ فَعَّالٌ لِّمَا يُرِيدُ ( 107 ) ሁድ - Aya 107
ጌታህ ከሻው (ጭማሬ) ሌላ ሰማያትና ምድር እስከ ዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውተሪዎች ሲኾኑ (በእሳት ይኖራሉ)፡፡ ጌታህ የሚሻውን ሠሪ ነውና፡፡ ሁድ - Aya 107
وَأَمَّا الَّذِينَ سُعِدُوا فَفِي الْجَنَّةِ خَالِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ إِلَّا مَا شَاءَ رَبُّكَ ۖ عَطَاءً غَيْرَ مَجْذُوذٍ ( 108 ) ሁድ - Aya 108
እነዚያም ዕድለኞቹማ ጌታህ ከሻው (ጭማሬ) ሌላ ሰማያትና ምድር እስከ ዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውታሪዎች ኾነው በገነት ውስጥ ይኖራሉ፡፡ የማይቋረጥ ስጦታን ተሰጡ፡፡ ሁድ - Aya 108
فَلَا تَكُ فِي مِرْيَةٍ مِّمَّا يَعْبُدُ هَٰؤُلَاءِ ۚ مَا يَعْبُدُونَ إِلَّا كَمَا يَعْبُدُ آبَاؤُهُم مِّن قَبْلُ ۚ وَإِنَّا لَمُوَفُّوهُمْ نَصِيبَهُمْ غَيْرَ مَنقُوصٍ ( 109 ) ሁድ - Aya 109
እነዚህ (ከሓዲዎች) ከሚገዙት ጣዖት በመጠራጠር ውስጥ አትሁን፤ አባቶቻቸው ከዚህ በፊት እንደሚግገዙት እንጂ አይግገዙም፡፡ እኛም (እነዚህን) ፈንታቸውን የማይጓደል ሲሆን የምንሞላላቸው ነን፡፡ ሁድ - Aya 109
وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ فَاخْتُلِفَ فِيهِ ۚ وَلَوْلَا كَلِمَةٌ سَبَقَتْ مِن رَّبِّكَ لَقُضِيَ بَيْنَهُمْ ۚ وَإِنَّهُمْ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ مُرِيبٍ ( 110 ) ሁድ - Aya 110
ለሙሳም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ በእርሱም ተለያዩበት፡፡ ከጌታህም ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው (አሁን) ይፈረድ ነበር፡፡ እነሱም ከእርሱ (ከቁርኣን) አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ሁድ - Aya 110
وَإِنَّ كُلًّا لَّمَّا لَيُوَفِّيَنَّهُمْ رَبُّكَ أَعْمَالَهُمْ ۚ إِنَّهُ بِمَا يَعْمَلُونَ خَبِيرٌ ( 111 ) ሁድ - Aya 111
ሁሉንም ጌታህ ሥራዎቻቸውን (ምንዳቸውን) በእርግጥ ይሞላላቸዋል፡፡ እርሱ በሚሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነውና፡፡ ሁድ - Aya 111
فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا ۚ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ ( 112 ) ሁድ - Aya 112
እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ከአንተ ጋር ያመኑትም (ቀጥ ይበሉ)፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና፡፡ ሁድ - Aya 112
وَلَا تَرْكَنُوا إِلَى الَّذِينَ ظَلَمُوا فَتَمَسَّكُمُ النَّارُ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِنْ أَوْلِيَاءَ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ ( 113 ) ሁድ - Aya 113
ወደእነዚያም ወደ በደሉት አትጠጉ፡፡ እሳት ትነካችኋለችና፡፡ ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም፡፡ ከዚያም አትረድዱም፡፡ ሁድ - Aya 113
وَأَقِمِ الصَّلَاةَ طَرَفَيِ النَّهَارِ وَزُلَفًا مِّنَ اللَّيْلِ ۚ إِنَّ الْحَسَنَاتِ يُذْهِبْنَ السَّيِّئَاتِ ۚ ذَٰلِكَ ذِكْرَىٰ لِلذَّاكِرِينَ ( 114 ) ሁድ - Aya 114
ሶላትንም በቀን ጫፎች ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም፡፡ መልካም ሥራዎች ኀጢአቶችን ያስወገድዳሉና፡፡ ይህ ለተገሳጮች ግሳጼ ነው፡፡ ሁድ - Aya 114
وَاصْبِرْ فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجْرَ الْمُحْسِنِينَ ( 115 ) ሁድ - Aya 115
ታገስም፤ አላህ የበጎ ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና፡፡ ሁድ - Aya 115
فَلَوْلَا كَانَ مِنَ الْقُرُونِ مِن قَبْلِكُمْ أُولُو بَقِيَّةٍ يَنْهَوْنَ عَنِ الْفَسَادِ فِي الْأَرْضِ إِلَّا قَلِيلًا مِّمَّنْ أَنجَيْنَا مِنْهُمْ ۗ وَاتَّبَعَ الَّذِينَ ظَلَمُوا مَا أُتْرِفُوا فِيهِ وَكَانُوا مُجْرِمِينَ ( 116 ) ሁድ - Aya 116
ከእናንተም በፊት ከነበሩት ከክፍለ ዘመናት ሰዎች ውስጥ በምድር ላይ ከማበላሸት የሚከለክሉ የመልካም ቀሪ ሥራዎች ባለቤቶች ለምን አልነበሩም ግን ከእነሱ ያዳንናቸው ጥቂቶቹ (ከለከሉና ዳኑ)፡፡ እነዚያም የበደሉት ሰዎች (አልከለከሉም)፡፡ በእርሱ የተቀማጠሉበትን ተድላ ተከተሉ፡፡ አመጸኞችም ነበሩ፡፡ ሁድ - Aya 116
وَمَا كَانَ رَبُّكَ لِيُهْلِكَ الْقُرَىٰ بِظُلْمٍ وَأَهْلُهَا مُصْلِحُونَ ( 117 ) ሁድ - Aya 117
ጌታህም ከተሞችን ባለቤቶቻቸው መልካም ሠሪዎች ሆነው ሳሉ በመበደል የሚያጠፋቸው አልነበረም፡፡ ሁድ - Aya 117
وَلَوْ شَاءَ رَبُّكَ لَجَعَلَ النَّاسَ أُمَّةً وَاحِدَةً ۖ وَلَا يَزَالُونَ مُخْتَلِفِينَ ( 118 ) ሁድ - Aya 118
ጌታህም በሻ ኖሮ ሰዎችን ሁሉ አንድ ሕዝብ ባደረጋቸው ነበር፡፡ የተለያዩም ከመሆን አይወገዱም፡፡ ሁድ - Aya 118
إِلَّا مَن رَّحِمَ رَبُّكَ ۚ وَلِذَٰلِكَ خَلَقَهُمْ ۗ وَتَمَّتْ كَلِمَةُ رَبِّكَ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ ( 119 ) ሁድ - Aya 119
ጌታህ ያዘነለት ብቻ ሲቀር፤ (ከመለያየት አይወገዱም)፡፡ ለዚሁም ፈጠራቸው፡፡ የጌታህም ቃል ገሀነምን ከአጋንንትና ከሰዎች ከሁሉም በእርግጥ እሞላታለሁ በማለት ተፈጸመች፡፡ ሁድ - Aya 119
وَكُلًّا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنبَاءِ الرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِ فُؤَادَكَ ۚ وَجَاءَكَ فِي هَٰذِهِ الْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ ( 120 ) ሁድ - Aya 120
ከመልክተኞቹም ዜናዎች (ተፈላጊውን) ሁሉንም ልብህን በርሱ የምናረካበትን እንተርክልሃለን፡፡ በዚህችም (ሱራ) እውነቱ ነገር ለምእምናን ግሳጼና ማስታወሻ መጥቶልሃል፡፡ ሁድ - Aya 120
وَقُل لِّلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ اعْمَلُوا عَلَىٰ مَكَانَتِكُمْ إِنَّا عَامِلُونَ ( 121 ) ሁድ - Aya 121
ለእነዚያም ለማያምኑት ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ሥሩ፤ እኛ ሠሪዎች ነንና በላቸው፡፡ ሁድ - Aya 121
وَانتَظِرُوا إِنَّا مُنتَظِرُونَ ( 122 ) ሁድ - Aya 122
ተጠባበቁም እኛ ተጠባባቂዎች ነንና (በላቸው)፡፡ ሁድ - Aya 122
وَلِلَّهِ غَيْبُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَإِلَيْهِ يُرْجَعُ الْأَمْرُ كُلُّهُ فَاعْبُدْهُ وَتَوَكَّلْ عَلَيْهِ ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ ( 123 ) ሁድ - Aya 123
በሰማያትና በምድርም ያለው ምስጢር ሁሉ የአላህ ነው፡፡ ነገሩ ሁሉም ወደርሱ ይመለሳል፡፡ ስለዚህ ተገዛው፡፡ በእርሱም ላይ ተጠጋ፡፡ ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ ሁድ - Aya 123
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah