Surah አል ሸምስ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ሸምስ - Aya count 15
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
وَالشَّمْسِ وَضُحَاهَا ( 1 ) አል ሸምስ - Aya 1
በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡ አል ሸምስ - Aya 1
وَالْقَمَرِ إِذَا تَلَاهَا ( 2 ) አል ሸምስ - Aya 2
በጨረቃም በተከተላት ጊዜ፤ አል ሸምስ - Aya 2
وَالنَّهَارِ إِذَا جَلَّاهَا ( 3 ) አል ሸምስ - Aya 3
በቀኑም (ፀሐይን) በገለጻት ጊዜ፤ አል ሸምስ - Aya 3
وَاللَّيْلِ إِذَا يَغْشَاهَا ( 4 ) አል ሸምስ - Aya 4
በሌሊቱም በሸፈናት ጊዜ፤ አል ሸምስ - Aya 4
وَالسَّمَاءِ وَمَا بَنَاهَا ( 5 ) አል ሸምስ - Aya 5
በሰማይቱም በገነባትም (ጌታ)፤ አል ሸምስ - Aya 5
وَالْأَرْضِ وَمَا طَحَاهَا ( 6 ) አል ሸምስ - Aya 6
በምድሪቱም በዘረጋትም፤ አል ሸምስ - Aya 6
وَنَفْسٍ وَمَا سَوَّاهَا ( 7 ) አል ሸምስ - Aya 7
በነፍስም ባስተካከላትም፤ አል ሸምስ - Aya 7
فَأَلْهَمَهَا فُجُورَهَا وَتَقْوَاهَا ( 8 ) አል ሸምስ - Aya 8
አመጽዋንና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት (አምላክ እምላለሁ)፡፡ አል ሸምስ - Aya 8
قَدْ أَفْلَحَ مَن زَكَّاهَا ( 9 ) አል ሸምስ - Aya 9
(ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡ አል ሸምስ - Aya 9
وَقَدْ خَابَ مَن دَسَّاهَا ( 10 ) አል ሸምስ - Aya 10
(በኀጢኣት) የሸፈናትም ሰው በእውነት አፈረ፡፡ አል ሸምስ - Aya 10
كَذَّبَتْ ثَمُودُ بِطَغْوَاهَا ( 11 ) አል ሸምስ - Aya 11
ሠሙድ ወሰን በማለፍዋ አስተባበለች፡፡ አል ሸምስ - Aya 11
إِذِ انبَعَثَ أَشْقَاهَا ( 12 ) አል ሸምስ - Aya 12
ጠማማዋ በተንቀሳቀሰ ጊዜ፡፡ አል ሸምስ - Aya 12
فَقَالَ لَهُمْ رَسُولُ اللَّهِ نَاقَةَ اللَّهِ وَسُقْيَاهَا ( 13 ) አል ሸምስ - Aya 13
ለእነርሱም የአላህ መልክተኛ (ሷሊህ) «የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም (ተጠንቀቁ)» አላቸው፡፡ አል ሸምስ - Aya 13
فَكَذَّبُوهُ فَعَقَرُوهَا فَدَمْدَمَ عَلَيْهِمْ رَبُّهُم بِذَنبِهِمْ فَسَوَّاهَا ( 14 ) አል ሸምስ - Aya 14
አስተባበሉትም፡፡ (ቋንጃዋን) ወጓትም፡፡ በኀጢኣታቸውም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም፡፡ አል ሸምስ - Aya 14
وَلَا يَخَافُ عُقْبَاهَا ( 15 ) አል ሸምስ - Aya 15
ፍጻሜዋንም (የምታስከትለውን) አያፈራም፡፡ አል ሸምስ - Aya 15
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah