Surah አል ሙዘሚል

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ሙዘሚል - Aya count 20
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
يَا أَيُّهَا الْمُزَّمِّلُ ( 1 ) አል ሙዘሚል - Aya 1
አንተ ተከናናቢው ሆይ፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 1
قُمِ اللَّيْلَ إِلَّا قَلِيلًا ( 2 ) አል ሙዘሚል - Aya 2
ሌሊቱን ሁሉ ጥቂት ሲቀር ቁም፤ (ስገደ)፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 2
نِّصْفَهُ أَوِ انقُصْ مِنْهُ قَلِيلًا ( 3 ) አል ሙዘሚል - Aya 3
ግማሹን (ቁም)፤ ወይም ከርሱ ጥቂትን ቀንስ፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 3
أَوْ زِدْ عَلَيْهِ وَرَتِّلِ الْقُرْآنَ تَرْتِيلًا ( 4 ) አል ሙዘሚል - Aya 4
ወይም በእርሱ ላይ ጨምር፡፡ ቁርኣንንም በዝግታ ማንበብን አንብብ፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 4
إِنَّا سَنُلْقِي عَلَيْكَ قَوْلًا ثَقِيلًا ( 5 ) አል ሙዘሚል - Aya 5
እኛ ባንተ ላይ ከባድ ቃልን እንጥላለንና፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 5
إِنَّ نَاشِئَةَ اللَّيْلِ هِيَ أَشَدُّ وَطْئًا وَأَقْوَمُ قِيلًا ( 6 ) አል ሙዘሚል - Aya 6
የሌሊት መነሳት እርሷ (ሕዋሳትንና ልብን) ለማስማማት በጣም ብርቱ ናት፡፡ ለማንበብም ትክክለኛ ናት፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 6
إِنَّ لَكَ فِي النَّهَارِ سَبْحًا طَوِيلًا ( 7 ) አል ሙዘሚል - Aya 7
ላንተ በቀን ውስጥ ረዥም መዘዋወር አልለህ፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 7
وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ وَتَبَتَّلْ إِلَيْهِ تَبْتِيلًا ( 8 ) አል ሙዘሚል - Aya 8
የጌታህንም ስም አውሳ፤ ወደእርሱም (መግገዛት) መቋረጥን ተቋረጥ ፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 8
رَّبُّ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ فَاتَّخِذْهُ وَكِيلًا ( 9 ) አል ሙዘሚል - Aya 9
(እርሱም) የምሥራቅና የምዕራብ ጌታ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ መጠጊያ አድርገህም ያዘው፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 9
وَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَاهْجُرْهُمْ هَجْرًا جَمِيلًا ( 10 ) አል ሙዘሚል - Aya 10
(ከሓዲዎች) በሚሉትም ላይ ታገሥ፡፡ መልካምንም መተው ተዋቸው፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 10
وَذَرْنِي وَالْمُكَذِّبِينَ أُولِي النَّعْمَةِ وَمَهِّلْهُمْ قَلِيلًا ( 11 ) አል ሙዘሚል - Aya 11
የድሎት ባለቤቶችም ከኾኑት አስተባባዮች ጋር ተዎኝ፡፡ ጥቂትንም ጊዜ አቆያቸው፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 11
إِنَّ لَدَيْنَا أَنكَالًا وَجَحِيمًا ( 12 ) አል ሙዘሚል - Aya 12
እኛ ዘንድ ከባድ ማሰሪያዎች እሳትም አልለና፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 12
وَطَعَامًا ذَا غُصَّةٍ وَعَذَابًا أَلِيمًا ( 13 ) አል ሙዘሚል - Aya 13
የሚያንቅ ምግብም፤ አሳማሚ ቅጣትም (አልለ) አል ሙዘሚል - Aya 13
يَوْمَ تَرْجُفُ الْأَرْضُ وَالْجِبَالُ وَكَانَتِ الْجِبَالُ كَثِيبًا مَّهِيلًا ( 14 ) አል ሙዘሚል - Aya 14
ምድርና ገራዎች በሚርገፈገፉበት፣ ጋራዎችም ፈሳሽ የአሸዋ ክምር በሚኾኑበት ቀን፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 14
إِنَّا أَرْسَلْنَا إِلَيْكُمْ رَسُولًا شَاهِدًا عَلَيْكُمْ كَمَا أَرْسَلْنَا إِلَىٰ فِرْعَوْنَ رَسُولًا ( 15 ) አል ሙዘሚል - Aya 15
እኛ በእናንተ ላይ መስካሪ መልክተኛን ወደእናንተ ላክን፡፡ ወደ ፈርዖን መልክተኛን እንደላክን፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 15
فَعَصَىٰ فِرْعَوْنُ الرَّسُولَ فَأَخَذْنَاهُ أَخْذًا وَبِيلًا ( 16 ) አል ሙዘሚል - Aya 16
ፈርዖንም መልክተኛውን አመጸ፤ ብርቱ መያዝንም ያዝነው፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 16
فَكَيْفَ تَتَّقُونَ إِن كَفَرْتُمْ يَوْمًا يَجْعَلُ الْوِلْدَانَ شِيبًا ( 17 ) አል ሙዘሚል - Aya 17
ብትክዱ ልጆችን ሸበቶዎች የሚያደርገውን ቀን (ቅጣት) እንዴት ትጠበቃላችሁ፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 17
السَّمَاءُ مُنفَطِرٌ بِهِ ۚ كَانَ وَعْدُهُ مَفْعُولًا ( 18 ) አል ሙዘሚል - Aya 18
ሰማዩ በርሱ (በዚያ ቀን) ተሰንጣቂ ነው፡፡ ቀጠሮው ተፈጻሚ ነው፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 18
إِنَّ هَٰذِهِ تَذْكِرَةٌ ۖ فَمَن شَاءَ اتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِ سَبِيلًا ( 19 ) አል ሙዘሚል - Aya 19
ይህቺ መገሠጫ ናት፡፡ (መዳንን) የሻም ሰው ወደ ጌታው መንገድን ይይዛል፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 19
إِنَّ رَبَّكَ يَعْلَمُ أَنَّكَ تَقُومُ أَدْنَىٰ مِن ثُلُثَيِ اللَّيْلِ وَنِصْفَهُ وَثُلُثَهُ وَطَائِفَةٌ مِّنَ الَّذِينَ مَعَكَ ۚ وَاللَّهُ يُقَدِّرُ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ ۚ عَلِمَ أَن لَّن تُحْصُوهُ فَتَابَ عَلَيْكُمْ ۖ فَاقْرَءُوا مَا تَيَسَّرَ مِنَ الْقُرْآنِ ۚ عَلِمَ أَن سَيَكُونُ مِنكُم مَّرْضَىٰ ۙ وَآخَرُونَ يَضْرِبُونَ فِي الْأَرْضِ يَبْتَغُونَ مِن فَضْلِ اللَّهِ ۙ وَآخَرُونَ يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۖ فَاقْرَءُوا مَا تَيَسَّرَ مِنْهُ ۚ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَأَقْرِضُوا اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا ۚ وَمَا تُقَدِّمُوا لِأَنفُسِكُم مِّنْ خَيْرٍ تَجِدُوهُ عِندَ اللَّهِ هُوَ خَيْرًا وَأَعْظَمَ أَجْرًا ۚ وَاسْتَغْفِرُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ( 20 ) አል ሙዘሚል - Aya 20
አንተ ከሌሊቱ ሁለት እጅ ያነሰን ግማሹንም ሲሶውንም የምትቆም መኾንህን ጌታህ በእርግጥ ያውቃል፡፡ ከእነዚያም አብረውህ ካሉት ከፊሎች (የሚቆሙ መኾናቸውን ያውቃል)፡፡ አላህም ሌሊትንና ቀንን ይለክካል፡፡ (ሌሊቱን) የማታዳርሱት መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ በእናንተ ላይም (ወደ ማቃለል) ተመለሰላችሁ፡፡ ስለዚህ ከቁርኣን (በስግደት) የተቻላችሁን አንብቡ፡፡ ከእናንተ ውስጥ በሽተኞች፣ ሌሎችም ከአላህ ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ የሚጓዙ፣ ሌሎችም በአላህ መንገድ (ሃይማኖት) የሚጋደሉ እንደሚኖሩ ዐወቀ፡፡ (አቃለለላቸውም)፡፡ ከእርሱም የተቻለችሁን አንብቡ፡፡ ሶላትንም ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ ለአላህም መልካም ብደርን አበድሩ፡፡ ከመልካም ሥራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ እርሱ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ኾኖ አላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ፡፡ አላህንም ምሕረትን ለምኑት፡፡ አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ አል ሙዘሚል - Aya 20
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah