Surah አል ሷፋት

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ሷፋት - Aya count 182
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
وَالصَّافَّاتِ صَفًّا ( 1 ) አል ሷፋት - Aya 1
መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡ አል ሷፋት - Aya 1
فَالزَّاجِرَاتِ زَجْرًا ( 2 ) አል ሷፋት - Aya 2
መገሠጽንም በሚገሥጹት፤ አል ሷፋት - Aya 2
فَالتَّالِيَاتِ ذِكْرًا ( 3 ) አል ሷፋት - Aya 3
ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡ አል ሷፋት - Aya 3
إِنَّ إِلَٰهَكُمْ لَوَاحِدٌ ( 4 ) አል ሷፋት - Aya 4
አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡ አል ሷፋት - Aya 4
رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا وَرَبُّ الْمَشَارِقِ ( 5 ) አል ሷፋት - Aya 5
የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡ አል ሷፋት - Aya 5
إِنَّا زَيَّنَّا السَّمَاءَ الدُّنْيَا بِزِينَةٍ الْكَوَاكِبِ ( 6 ) አል ሷፋት - Aya 6
እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡ አል ሷፋት - Aya 6
وَحِفْظًا مِّن كُلِّ شَيْطَانٍ مَّارِدٍ ( 7 ) አል ሷፋት - Aya 7
አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት፡፡ አል ሷፋት - Aya 7
لَّا يَسَّمَّعُونَ إِلَى الْمَلَإِ الْأَعْلَىٰ وَيُقْذَفُونَ مِن كُلِّ جَانِبٍ ( 8 ) አል ሷፋት - Aya 8
ወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም፡፡ ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፡፡ አል ሷፋት - Aya 8
دُحُورًا ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ وَاصِبٌ ( 9 ) አል ሷፋት - Aya 9
የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፡፡ ለእነሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 9
إِلَّا مَنْ خَطِفَ الْخَطْفَةَ فَأَتْبَعَهُ شِهَابٌ ثَاقِبٌ ( 10 ) አል ሷፋት - Aya 10
ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር፤ (እርሱ ይሰማዋል)፡፡ አል ሷፋት - Aya 10
فَاسْتَفْتِهِمْ أَهُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَم مَّنْ خَلَقْنَا ۚ إِنَّا خَلَقْنَاهُم مِّن طِينٍ لَّازِبٍ ( 11 ) አል ሷፋት - Aya 11
ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነው? (ፍጡር) እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 11
بَلْ عَجِبْتَ وَيَسْخَرُونَ ( 12 ) አል ሷፋት - Aya 12
ይልቁንም (በማስተባበላቸው) ተደነቅህ፤(ከመደነቅህ) ይሳለቃሉም፡፡ አል ሷፋት - Aya 12
وَإِذَا ذُكِّرُوا لَا يَذْكُرُونَ ( 13 ) አል ሷፋት - Aya 13
በተገሠጹም ጊዜ አይመለሱም፡፡ አል ሷፋት - Aya 13
وَإِذَا رَأَوْا آيَةً يَسْتَسْخِرُونَ ( 14 ) አል ሷፋት - Aya 14
ተዓምርን ባዩም ጊዜ ለመሳለቅ ይጠራራሉ፡፡ አል ሷፋት - Aya 14
وَقَالُوا إِنْ هَٰذَا إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ ( 15 ) አል ሷፋት - Aya 15
ይላሉም «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ አል ሷፋት - Aya 15
أَإِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَامًا أَإِنَّا لَمَبْعُوثُونَ ( 16 ) አል ሷፋት - Aya 16
«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን? አል ሷፋት - Aya 16
أَوَآبَاؤُنَا الْأَوَّلُونَ ( 17 ) አል ሷፋት - Aya 17
«የቀድሞዎቹ አባቶችንም? (ይላሉ)፡፡ አል ሷፋት - Aya 17
قُلْ نَعَمْ وَأَنتُمْ دَاخِرُونَ ( 18 ) አል ሷፋት - Aya 18
«አዎን እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)» በላቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 18
فَإِنَّمَا هِيَ زَجْرَةٌ وَاحِدَةٌ فَإِذَا هُمْ يَنظُرُونَ ( 19 ) አል ሷፋት - Aya 19
እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ እነርሱም ወዲያውኑ (ምን እንደሚፈጸምባቸው) ያያሉ፡፡ አል ሷፋት - Aya 19
وَقَالُوا يَا وَيْلَنَا هَٰذَا يَوْمُ الدِّينِ ( 20 ) አል ሷፋት - Aya 20
«ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው» ይላሉም፡፡ አል ሷፋት - Aya 20
هَٰذَا يَوْمُ الْفَصْلِ الَّذِي كُنتُم بِهِ تُكَذِّبُونَ ( 21 ) አል ሷፋት - Aya 21
«ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት መለያው ቀን ነው» (ይባላሉ)፡፡ አል ሷፋት - Aya 21
احْشُرُوا الَّذِينَ ظَلَمُوا وَأَزْوَاجَهُمْ وَمَا كَانُوا يَعْبُدُونَ ( 22 ) አል ሷፋት - Aya 22
(ለመላእክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ይግገዟቸው የነበሩትንም (ጣዖታት) ሰብስቡ፡፡ አል ሷፋት - Aya 22
مِن دُونِ اللَّهِ فَاهْدُوهُمْ إِلَىٰ صِرَاطِ الْجَحِيمِ ( 23 ) አል ሷፋት - Aya 23
«ከአላህ ሌላ (የሚገዙዋቸውን ሰብስቧቸው) ወደ እሳት መንገድም ምሩዋቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 23
وَقِفُوهُمْ ۖ إِنَّهُم مَّسْئُولُونَ ( 24 ) አል ሷፋት - Aya 24
«አቁሟቸውም፡፡ እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና» (ይባላል)፡፡ አል ሷፋት - Aya 24
مَا لَكُمْ لَا تَنَاصَرُونَ ( 25 ) አል ሷፋት - Aya 25
(ለእነርሱም) «የማትረዳዱት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ይባላሉ)፡፡ አል ሷፋት - Aya 25
بَلْ هُمُ الْيَوْمَ مُسْتَسْلِمُونَ ( 26 ) አል ሷፋት - Aya 26
በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ወራዳዎች ናቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 26
وَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ يَتَسَاءَلُونَ ( 27 ) አል ሷፋት - Aya 27
የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይመጣሉ፡፡ አል ሷፋት - Aya 27
قَالُوا إِنَّكُمْ كُنتُمْ تَأْتُونَنَا عَنِ الْيَمِينِ ( 28 ) አል ሷፋት - Aya 28
(ለአስከታዮቹ) እናንተ ከስተቀኝ ትመጡብን ነበር ይላሉ፡፡ አል ሷፋት - Aya 28
قَالُوا بَل لَّمْ تَكُونُوا مُؤْمِنِينَ ( 29 ) አል ሷፋት - Aya 29
(አስከታዮቹም) ይላሉ «አይደለም ፈጽሞ ምእምናን አልነበራችሁም፡፡ አል ሷፋት - Aya 29
وَمَا كَانَ لَنَا عَلَيْكُم مِّن سُلْطَانٍ ۖ بَلْ كُنتُمْ قَوْمًا طَاغِينَ ( 30 ) አል ሷፋት - Aya 30
«ለእኛም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም፡፡ በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ሕዝቦች ነበራችሁ፡፡ አል ሷፋት - Aya 30
فَحَقَّ عَلَيْنَا قَوْلُ رَبِّنَا ۖ إِنَّا لَذَائِقُونَ ( 31 ) አል ሷፋት - Aya 31
«በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠብን፤ እኛ (ሁላችንም ቅጣቱን) ቀማሾች ነን፡፡ አል ሷፋት - Aya 31
فَأَغْوَيْنَاكُمْ إِنَّا كُنَّا غَاوِينَ ( 32 ) አል ሷፋት - Aya 32
«ወደ ጥምመት ጠራናችሁም፡፡ እኛ ጠማሞች ነበርንና» (ይላሉ)፡፡ አል ሷፋት - Aya 32
فَإِنَّهُمْ يَوْمَئِذٍ فِي الْعَذَابِ مُشْتَرِكُونَ ( 33 ) አል ሷፋት - Aya 33
ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ነጋሪዎች ናቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 33
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَفْعَلُ بِالْمُجْرِمِينَ ( 34 ) አል ሷፋት - Aya 34
እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡ አል ሷፋት - Aya 34
إِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ ( 35 ) አል ሷፋት - Aya 35
እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፡፡ አል ሷፋት - Aya 35
وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُو آلِهَتِنَا لِشَاعِرٍ مَّجْنُونٍ ( 36 ) አል ሷፋት - Aya 36
እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን? ይሉም ነበር፡፡ አል ሷፋት - Aya 36
بَلْ جَاءَ بِالْحَقِّ وَصَدَّقَ الْمُرْسَلِينَ ( 37 ) አል ሷፋት - Aya 37
አይደለም እውነቱን (ሃይማኖት) አመጣ፡፡ መልክተኞቹንም እውነተኛነታቸውን አረጋገጠ፡፡ አል ሷፋት - Aya 37
إِنَّكُمْ لَذَائِقُو الْعَذَابِ الْأَلِيمِ ( 38 ) አል ሷፋት - Aya 38
እናንተ አሳማሚውን ቅጣት በእርግጥ ቀማሾች ናችሁ፡፡ አል ሷፋት - Aya 38
وَمَا تُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ ( 39 ) አል ሷፋት - Aya 39
ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም፡፡ አል ሷፋት - Aya 39
إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ ( 40 ) አል ሷፋት - Aya 40
ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች (ቅጣትን አይቀምሱም)፡፡ አል ሷፋት - Aya 40
أُولَٰئِكَ لَهُمْ رِزْقٌ مَّعْلُومٌ ( 41 ) አል ሷፋት - Aya 41
እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አላቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 41
فَوَاكِهُ ۖ وَهُم مُّكْرَمُونَ ( 42 ) አል ሷፋት - Aya 42
ፍራፍሬዎች (አሏቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው፤ አል ሷፋት - Aya 42
فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ ( 43 ) አል ሷፋት - Aya 43
በድሎት ገነቶች ውስጥ፡፡ አል ሷፋት - Aya 43
عَلَىٰ سُرُرٍ مُّتَقَابِلِينَ ( 44 ) አል ሷፋት - Aya 44
ፊት ለፊት የሚታያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ አል ሷፋት - Aya 44
يُطَافُ عَلَيْهِم بِكَأْسٍ مِّن مَّعِينٍ ( 45 ) አል ሷፋት - Aya 45
ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡ አል ሷፋት - Aya 45
بَيْضَاءَ لَذَّةٍ لِّلشَّارِبِينَ ( 46 ) አል ሷፋት - Aya 46
ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከኾነች፡፡ አል ሷፋት - Aya 46
لَا فِيهَا غَوْلٌ وَلَا هُمْ عَنْهَا يُنزَفُونَ ( 47 ) አል ሷፋት - Aya 47
በእርሷ ውስጥም ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡ አል ሷፋት - Aya 47
وَعِندَهُمْ قَاصِرَاتُ الطَّرْفِ عِينٌ ( 48 ) አል ሷፋት - Aya 48
እነርሱም ዘንድ ዓይናቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ ዓይናማዎች አልሉ፡፡ አል ሷፋት - Aya 48
كَأَنَّهُنَّ بَيْضٌ مَّكْنُونٌ ( 49 ) አል ሷፋት - Aya 49
እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) ዕንቁላል ይመስላሉ፡፡ አል ሷፋት - Aya 49
فَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ يَتَسَاءَلُونَ ( 50 ) አል ሷፋት - Aya 50
የሚጠያየቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ፡፡ አል ሷፋት - Aya 50
قَالَ قَائِلٌ مِّنْهُمْ إِنِّي كَانَ لِي قَرِينٌ ( 51 ) አል ሷፋት - Aya 51
ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል «እኔ ጓደኛ ነበረኝ፡፡ አል ሷፋት - Aya 51
يَقُولُ أَإِنَّكَ لَمِنَ الْمُصَدِّقِينَ ( 52 ) አል ሷፋት - Aya 52
«በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን? የሚል፡፡ አል ሷፋት - Aya 52
أَإِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَامًا أَإِنَّا لَمَدِينُونَ ( 53 ) አል ሷፋት - Aya 53
«በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?» (የሚል)፡፡ አል ሷፋት - Aya 53
قَالَ هَلْ أَنتُم مُّطَّلِعُونَ ( 54 ) አል ሷፋት - Aya 54
እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል፡፡ አል ሷፋት - Aya 54
فَاطَّلَعَ فَرَآهُ فِي سَوَاءِ الْجَحِيمِ ( 55 ) አል ሷፋት - Aya 55
ይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛውን) ያየዋል፡፡ አል ሷፋት - Aya 55
قَالَ تَاللَّهِ إِن كِدتَّ لَتُرْدِينِ ( 56 ) አል ሷፋት - Aya 56
ይላል «በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር፡፡ አል ሷፋት - Aya 56
وَلَوْلَا نِعْمَةُ رَبِّي لَكُنتُ مِنَ الْمُحْضَرِينَ ( 57 ) አል ሷፋት - Aya 57
«የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር፡፡» አል ሷፋት - Aya 57
أَفَمَا نَحْنُ بِمَيِّتِينَ ( 58 ) አል ሷፋት - Aya 58
(የገነት ሰዎች ይላሉ) «እኛ የምንሞት አይደለንምን? አል ሷፋት - Aya 58
إِلَّا مَوْتَتَنَا الْأُولَىٰ وَمَا نَحْنُ بِمُعَذَّبِينَ ( 59 ) አል ሷፋት - Aya 59
«የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር፡፡ እኛም የምንቅቀጣ አይደለንምን?» (ይላሉ)፡፡ አል ሷፋት - Aya 59
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ ( 60 ) አል ሷፋት - Aya 60
ይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳው) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ አል ሷፋት - Aya 60
لِمِثْلِ هَٰذَا فَلْيَعْمَلِ الْعَامِلُونَ ( 61 ) አል ሷፋት - Aya 61
ለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ፡፡ አል ሷፋት - Aya 61
أَذَٰلِكَ خَيْرٌ نُّزُلًا أَمْ شَجَرَةُ الزَّقُّومِ ( 62 ) አል ሷፋት - Aya 62
በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ? አል ሷፋት - Aya 62
إِنَّا جَعَلْنَاهَا فِتْنَةً لِّلظَّالِمِينَ ( 63 ) አል ሷፋት - Aya 63
እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል፡፡ አል ሷፋት - Aya 63
إِنَّهَا شَجَرَةٌ تَخْرُجُ فِي أَصْلِ الْجَحِيمِ ( 64 ) አል ሷፋት - Aya 64
እርሷ በገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፡፡ አል ሷፋት - Aya 64
طَلْعُهَا كَأَنَّهُ رُءُوسُ الشَّيَاطِينِ ( 65 ) አል ሷፋት - Aya 65
እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል፡፡ አል ሷፋት - Aya 65
فَإِنَّهُمْ لَآكِلُونَ مِنْهَا فَمَالِئُونَ مِنْهَا الْبُطُونَ ( 66 ) አል ሷፋት - Aya 66
እነርሱም ከእርሷ በይዎች ናቸው፤ ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 66
ثُمَّ إِنَّ لَهُمْ عَلَيْهَا لَشَوْبًا مِّنْ حَمِيمٍ ( 67 ) አል ሷፋት - Aya 67
ከዚያም ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅል (መጠጥ) አልላቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 67
ثُمَّ إِنَّ مَرْجِعَهُمْ لَإِلَى الْجَحِيمِ ( 68 ) አል ሷፋት - Aya 68
ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው፡፡ አል ሷፋት - Aya 68
إِنَّهُمْ أَلْفَوْا آبَاءَهُمْ ضَالِّينَ ( 69 ) አል ሷፋት - Aya 69
እነሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋልና፡፡ አል ሷፋት - Aya 69
فَهُمْ عَلَىٰ آثَارِهِمْ يُهْرَعُونَ ( 70 ) አል ሷፋት - Aya 70
እነሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና፡፡ አል ሷፋት - Aya 70
وَلَقَدْ ضَلَّ قَبْلَهُمْ أَكْثَرُ الْأَوَّلِينَ ( 71 ) አል ሷፋት - Aya 71
ከእነርሱ በፊትም የቀድሞዎቹ (ሕዝቦች) አብዛኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል፡፡ አል ሷፋት - Aya 71
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا فِيهِم مُّنذِرِينَ ( 72 ) አል ሷፋት - Aya 72
በውስጣቸውም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል፡፡ አል ሷፋት - Aya 72
فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُنذَرِينَ ( 73 ) አል ሷፋት - Aya 73
የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡ አል ሷፋት - Aya 73
إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ ( 74 ) አል ሷፋት - Aya 74
ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡ አል ሷፋት - Aya 74
وَلَقَدْ نَادَانَا نُوحٌ فَلَنِعْمَ الْمُجِيبُونَ ( 75 ) አል ሷፋት - Aya 75
ኑሕም በእርግጥ ጠራን፡፡ ጥሪውን ተቀባዮቹም ምንኛ አማርን! አል ሷፋት - Aya 75
وَنَجَّيْنَاهُ وَأَهْلَهُ مِنَ الْكَرْبِ الْعَظِيمِ ( 76 ) አል ሷፋት - Aya 76
እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን፡፡ አል ሷፋት - Aya 76
وَجَعَلْنَا ذُرِّيَّتَهُ هُمُ الْبَاقِينَ ( 77 ) አል ሷፋት - Aya 77
ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን፤ አል ሷፋት - Aya 77
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الْآخِرِينَ ( 78 ) አል ሷፋት - Aya 78
በርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልካም ዝናን) ተውን፡፡ አል ሷፋት - Aya 78
سَلَامٌ عَلَىٰ نُوحٍ فِي الْعَالَمِينَ ( 79 ) አል ሷፋት - Aya 79
«በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑሕ ላይ ይኹን፡፡» አል ሷፋት - Aya 79
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ ( 80 ) አል ሷፋት - Aya 80
እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ አል ሷፋት - Aya 80
إِنَّهُ مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ ( 81 ) አል ሷፋት - Aya 81
እርሱ ከምእምናን ባሮቻችን ነውና፡፡ አል ሷፋት - Aya 81
ثُمَّ أَغْرَقْنَا الْآخَرِينَ ( 82 ) አል ሷፋት - Aya 82
ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡ አል ሷፋት - Aya 82
وَإِنَّ مِن شِيعَتِهِ لَإِبْرَاهِيمَ ( 83 ) አል ሷፋት - Aya 83
ኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው፡፡ አል ሷፋት - Aya 83
إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ ( 84 ) አል ሷፋት - Aya 84
ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡፡ አል ሷፋት - Aya 84
إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِ مَاذَا تَعْبُدُونَ ( 85 ) አል ሷፋት - Aya 85
«ለአባቱና ለሕዝቦቹ ምንን ትግገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ፡፡ አል ሷፋት - Aya 85
أَئِفْكًا آلِهَةً دُونَ اللَّهِ تُرِيدُونَ ( 86 ) አል ሷፋት - Aya 86
«ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን? አል ሷፋት - Aya 86
فَمَا ظَنُّكُم بِرَبِّ الْعَالَمِينَ ( 87 ) አል ሷፋት - Aya 87
«በዓለማትም ጌታ ሃሳባችሁ ምንድን ነው?» አለ፡፡ አል ሷፋት - Aya 87
فَنَظَرَ نَظْرَةً فِي النُّجُومِ ( 88 ) አል ሷፋት - Aya 88
በከዋክብትም መመልከትን ተመለከተ፡፡ አል ሷፋት - Aya 88
فَقَالَ إِنِّي سَقِيمٌ ( 89 ) አል ሷፋት - Aya 89
«እኔ በሽተኛ ነኝም» አለ፡፡ አል ሷፋት - Aya 89
فَتَوَلَّوْا عَنْهُ مُدْبِرِينَ ( 90 ) አል ሷፋት - Aya 90
ከእርሱም የሸሹ ሆነው ኼዱ፡፡ አል ሷፋት - Aya 90
فَرَاغَ إِلَىٰ آلِهَتِهِمْ فَقَالَ أَلَا تَأْكُلُونَ ( 91 ) አል ሷፋት - Aya 91
ወደ አማልክቶቻቸውም ተዘነበለ፡፡ አለም፡- «አትበሉምን?» አል ሷፋት - Aya 91
مَا لَكُمْ لَا تَنطِقُونَ ( 92 ) አል ሷፋት - Aya 92
«የማትናገሩት ለናንተ ምን አላችሁ?» አል ሷፋት - Aya 92
فَرَاغَ عَلَيْهِمْ ضَرْبًا بِالْيَمِينِ ( 93 ) አል ሷፋት - Aya 93
በኀይል የሚመታቸውም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ፡፡ አል ሷፋት - Aya 93
فَأَقْبَلُوا إِلَيْهِ يَزِفُّونَ ( 94 ) አል ሷፋት - Aya 94
ወደእርሱም (ሰዎቹ) እየሮጡ መጡ፡፡ አል ሷፋት - Aya 94
قَالَ أَتَعْبُدُونَ مَا تَنْحِتُونَ ( 95 ) አል ሷፋት - Aya 95
አላቸው «የምትጠርቡትን ትግገዛላችሁን?» አል ሷፋት - Aya 95
وَاللَّهُ خَلَقَكُمْ وَمَا تَعْمَلُونَ ( 96 ) አል ሷፋት - Aya 96
«አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን፡፡» አል ሷፋት - Aya 96
قَالُوا ابْنُوا لَهُ بُنْيَانًا فَأَلْقُوهُ فِي الْجَحِيمِ ( 97 ) አል ሷፋት - Aya 97
«ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም» አሉ፡፡ አል ሷፋት - Aya 97
فَأَرَادُوا بِهِ كَيْدًا فَجَعَلْنَاهُمُ الْأَسْفَلِينَ ( 98 ) አል ሷፋት - Aya 98
በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 98
وَقَالَ إِنِّي ذَاهِبٌ إِلَىٰ رَبِّي سَيَهْدِينِ ( 99 ) አል ሷፋት - Aya 99
አለም «እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡» አል ሷፋት - Aya 99
رَبِّ هَبْ لِي مِنَ الصَّالِحِينَ ( 100 ) አል ሷፋት - Aya 100
ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡ አል ሷፋት - Aya 100
فَبَشَّرْنَاهُ بِغُلَامٍ حَلِيمٍ ( 101 ) አል ሷፋት - Aya 101
ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡ አል ሷፋት - Aya 101
فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ السَّعْيَ قَالَ يَا بُنَيَّ إِنِّي أَرَىٰ فِي الْمَنَامِ أَنِّي أَذْبَحُكَ فَانظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَا أَبَتِ افْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِي إِن شَاءَ اللَّهُ مِنَ الصَّابِرِينَ ( 102 ) አል ሷፋት - Aya 102
ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ አል ሷፋት - Aya 102
فَلَمَّا أَسْلَمَا وَتَلَّهُ لِلْجَبِينِ ( 103 ) አል ሷፋት - Aya 103
ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡ አል ሷፋት - Aya 103
وَنَادَيْنَاهُ أَن يَا إِبْرَاهِيمُ ( 104 ) አል ሷፋት - Aya 104
ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ! አል ሷፋት - Aya 104
قَدْ صَدَّقْتَ الرُّؤْيَا ۚ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ ( 105 ) አል ሷፋት - Aya 105
ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ አል ሷፋት - Aya 105
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ الْبَلَاءُ الْمُبِينُ ( 106 ) አል ሷፋት - Aya 106
ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ አል ሷፋት - Aya 106
وَفَدَيْنَاهُ بِذِبْحٍ عَظِيمٍ ( 107 ) አል ሷፋት - Aya 107
በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡ አል ሷፋት - Aya 107
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الْآخِرِينَ ( 108 ) አል ሷፋት - Aya 108
በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡ አል ሷፋት - Aya 108
سَلَامٌ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ ( 109 ) አል ሷፋት - Aya 109
ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡ አል ሷፋት - Aya 109
كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ ( 110 ) አል ሷፋት - Aya 110
እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ አል ሷፋት - Aya 110
إِنَّهُ مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ ( 111 ) አል ሷፋት - Aya 111
እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡ አል ሷፋት - Aya 111
وَبَشَّرْنَاهُ بِإِسْحَاقَ نَبِيًّا مِّنَ الصَّالِحِينَ ( 112 ) አል ሷፋት - Aya 112
በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡ አል ሷፋት - Aya 112
وَبَارَكْنَا عَلَيْهِ وَعَلَىٰ إِسْحَاقَ ۚ وَمِن ذُرِّيَّتِهِمَا مُحْسِنٌ وَظَالِمٌ لِّنَفْسِهِ مُبِينٌ ( 113 ) አል ሷፋት - Aya 113
በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን፡፡ ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሠሪ አልለ፡፡ ለነፍሱ ግልጽ በዳይም አለ፡፡ አል ሷፋት - Aya 113
وَلَقَدْ مَنَنَّا عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَارُونَ ( 114 ) አል ሷፋት - Aya 114
በሙሳና በሃሩን ላይም በእርግጥ ለገስን፡፡ አል ሷፋት - Aya 114
وَنَجَّيْنَاهُمَا وَقَوْمَهُمَا مِنَ الْكَرْبِ الْعَظِيمِ ( 115 ) አል ሷፋት - Aya 115
እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን፡፡ አል ሷፋት - Aya 115
وَنَصَرْنَاهُمْ فَكَانُوا هُمُ الْغَالِبِينَ ( 116 ) አል ሷፋት - Aya 116
ረዳናቸውም፡፡ እነርሱም አሸናፊዎች ነበሩ፡፡ አል ሷፋት - Aya 116
وَآتَيْنَاهُمَا الْكِتَابَ الْمُسْتَبِينَ ( 117 ) አል ሷፋት - Aya 117
በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 117
وَهَدَيْنَاهُمَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ ( 118 ) አል ሷፋት - Aya 118
ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 118
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِمَا فِي الْآخِرِينَ ( 119 ) አል ሷፋት - Aya 119
በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንላቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 119
سَلَامٌ عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَارُونَ ( 120 ) አል ሷፋት - Aya 120
ሰላም በሙሳና በሃሩን ላይ ይሁን፡፡ አል ሷፋት - Aya 120
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ ( 121 ) አል ሷፋት - Aya 121
እኛ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ አል ሷፋት - Aya 121
إِنَّهُمَا مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ ( 122 ) አል ሷፋት - Aya 122
ሁለቱም በእርግጥ ከአመኑት ባሮቻችን ናቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 122
وَإِنَّ إِلْيَاسَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ ( 123 ) አል ሷፋት - Aya 123
ኢልያስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ አል ሷፋት - Aya 123
إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَلَا تَتَّقُونَ ( 124 ) አል ሷፋት - Aya 124
ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ አላህን አትፈሩምን? አል ሷፋት - Aya 124
أَتَدْعُونَ بَعْلًا وَتَذَرُونَ أَحْسَنَ الْخَالِقِينَ ( 125 ) አል ሷፋት - Aya 125
በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን? አል ሷፋት - Aya 125
اللَّهَ رَبَّكُمْ وَرَبَّ آبَائِكُمُ الْأَوَّلِينَ ( 126 ) አል ሷፋት - Aya 126
አላህን ጌታችሁንና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ (ትተዋላችሁን)? አል ሷፋት - Aya 126
فَكَذَّبُوهُ فَإِنَّهُمْ لَمُحْضَرُونَ ( 127 ) አል ሷፋት - Aya 127
አስተባበሉትም፡፡ ስለዚህ እነርሱ (ለቅጣት) የሚጣዱ ናቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 127
إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ ( 128 ) አል ሷፋት - Aya 128
ንጹሕ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡ አል ሷፋት - Aya 128
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الْآخِرِينَ ( 129 ) አል ሷፋት - Aya 129
በእርሱ ላይም በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት፡፡ አል ሷፋት - Aya 129
سَلَامٌ عَلَىٰ إِلْ يَاسِينَ ( 130 ) አል ሷፋት - Aya 130
ሰላም በኢልያሲን ላይ ይሁን፡፡ አል ሷፋት - Aya 130
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ ( 131 ) አል ሷፋት - Aya 131
እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ አል ሷፋት - Aya 131
إِنَّهُ مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ ( 132 ) አል ሷፋት - Aya 132
እርሱ በእርግጥ ከምእመናን ባሮቻችን ነው፡፡ አል ሷፋት - Aya 132
وَإِنَّ لُوطًا لَّمِنَ الْمُرْسَلِينَ ( 133 ) አል ሷፋት - Aya 133
ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ አል ሷፋት - Aya 133
إِذْ نَجَّيْنَاهُ وَأَهْلَهُ أَجْمَعِينَ ( 134 ) አል ሷፋት - Aya 134
እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳንናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ አል ሷፋት - Aya 134
إِلَّا عَجُوزًا فِي الْغَابِرِينَ ( 135 ) አል ሷፋት - Aya 135
(በቅጣቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር፡፡ አል ሷፋት - Aya 135
ثُمَّ دَمَّرْنَا الْآخَرِينَ ( 136 ) አል ሷፋት - Aya 136
ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡ አል ሷፋት - Aya 136
وَإِنَّكُمْ لَتَمُرُّونَ عَلَيْهِم مُّصْبِحِينَ ( 137 ) አል ሷፋት - Aya 137
እናንተም ያነጋችሁ ስትሆኑ በእነርሱ (መኖሪያዎች) ላይ (በቀን) ታልፋላችሁ፡፡ አል ሷፋት - Aya 137
وَبِاللَّيْلِ ۗ أَفَلَا تَعْقِلُونَ ( 138 ) አል ሷፋት - Aya 138
በሌሊትም (ታልፋላችሁ)፤ ልብም አታደርጉምን? አል ሷፋት - Aya 138
وَإِنَّ يُونُسَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ ( 139 ) አል ሷፋት - Aya 139
ዩኑስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ አል ሷፋት - Aya 139
إِذْ أَبَقَ إِلَى الْفُلْكِ الْمَشْحُونِ ( 140 ) አል ሷፋት - Aya 140
ወደ ተመላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ አል ሷፋት - Aya 140
فَسَاهَمَ فَكَانَ مِنَ الْمُدْحَضِينَ ( 141 ) አል ሷፋት - Aya 141
ዕጣም ተጣጣለ፡፡ ከተሸነፉትም ሆነ፡፡ አል ሷፋት - Aya 141
فَالْتَقَمَهُ الْحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٌ ( 142 ) አል ሷፋት - Aya 142
እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳው ዋጠው፡፡ አል ሷፋት - Aya 142
فَلَوْلَا أَنَّهُ كَانَ مِنَ الْمُسَبِّحِينَ ( 143 ) አል ሷፋት - Aya 143
እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነም ኖሮ፤ አል ሷፋት - Aya 143
لَلَبِثَ فِي بَطْنِهِ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ ( 144 ) አል ሷፋት - Aya 144
እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር፡፡ አል ሷፋት - Aya 144
فَنَبَذْنَاهُ بِالْعَرَاءِ وَهُوَ سَقِيمٌ ( 145 ) አል ሷፋት - Aya 145
እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው (በባሕር) ዳርቻ ላይ ጣልነውም፡፡ አል ሷፋት - Aya 145
وَأَنبَتْنَا عَلَيْهِ شَجَرَةً مِّن يَقْطِينٍ ( 146 ) አል ሷፋት - Aya 146
በእርሱም ላይ (በአጠገቡ) ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን፡፡ አል ሷፋት - Aya 146
وَأَرْسَلْنَاهُ إِلَىٰ مِائَةِ أَلْفٍ أَوْ يَزِيدُونَ ( 147 ) አል ሷፋት - Aya 147
ወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም (ዳግመኛ) ላክነው፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ፡፡ አል ሷፋት - Aya 147
فَآمَنُوا فَمَتَّعْنَاهُمْ إِلَىٰ حِينٍ ( 148 ) አል ሷፋት - Aya 148
አመኑም፡፡ እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 148
فَاسْتَفْتِهِمْ أَلِرَبِّكَ الْبَنَاتُ وَلَهُمُ الْبَنُونَ ( 149 ) አል ሷፋት - Aya 149
(የመካን ሰዎች) ጠይቃቸውም፡፡ «ለጌታህ ሴቶች ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራልን?» አል ሷፋት - Aya 149
أَمْ خَلَقْنَا الْمَلَائِكَةَ إِنَاثًا وَهُمْ شَاهِدُونَ ( 150 ) አል ሷፋት - Aya 150
ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን? አል ሷፋት - Aya 150
أَلَا إِنَّهُم مِّنْ إِفْكِهِمْ لَيَقُولُونَ ( 151 ) አል ሷፋት - Aya 151
ንቁ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው (የተነሳ) ይላሉ፡- አል ሷፋት - Aya 151
وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ ( 152 ) አል ሷፋት - Aya 152
«አላህ (መላእክትን) ወለደ፡፡» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 152
أَصْطَفَى الْبَنَاتِ عَلَى الْبَنِينَ ( 153 ) አል ሷፋት - Aya 153
በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጥን? አል ሷፋት - Aya 153
مَا لَكُمْ كَيْفَ تَحْكُمُونَ ( 154 ) አል ሷፋት - Aya 154
ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ! አል ሷፋት - Aya 154
أَفَلَا تَذَكَّرُونَ ( 155 ) አል ሷፋት - Aya 155
አትገነዘቡምን? አል ሷፋት - Aya 155
أَمْ لَكُمْ سُلْطَانٌ مُّبِينٌ ( 156 ) አል ሷፋት - Aya 156
ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጅ አላችሁን? አል ሷፋት - Aya 156
فَأْتُوا بِكِتَابِكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ ( 157 ) አል ሷፋት - Aya 157
«እውነተኞች እንደ ሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» (በላቸው)፡፡ አል ሷፋት - Aya 157
وَجَعَلُوا بَيْنَهُ وَبَيْنَ الْجِنَّةِ نَسَبًا ۚ وَلَقَدْ عَلِمَتِ الْجِنَّةُ إِنَّهُمْ لَمُحْضَرُونَ ( 158 ) አል ሷፋት - Aya 158
በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ፡፡ አጋንንትም እነርሱ (ይህን ባዮች በእሳት) የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ ዐውቀዋል፡፡ አል ሷፋት - Aya 158
سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ ( 159 ) አል ሷፋት - Aya 159
አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡ አል ሷፋት - Aya 159
إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ ( 160 ) አል ሷፋት - Aya 160
ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች (በአላህ ላይ አይዋሹም)፡፡ አል ሷፋት - Aya 160
فَإِنَّكُمْ وَمَا تَعْبُدُونَ ( 161 ) አል ሷፋት - Aya 161
እናንተም የምትገዟቸውም ሁሉ፤ አል ሷፋት - Aya 161
مَا أَنتُمْ عَلَيْهِ بِفَاتِنِينَ ( 162 ) አል ሷፋት - Aya 162
በእርሱ (በአላህ) ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም፡፡ አል ሷፋት - Aya 162
إِلَّا مَنْ هُوَ صَالِ الْجَحِيمِ ( 163 ) አል ሷፋት - Aya 163
ያንን እርሱ ገሀነምን ገቢ የሆነውን ሰው ቢሆን እንጅ፡፡ አል ሷፋት - Aya 163
وَمَا مِنَّا إِلَّا لَهُ مَقَامٌ مَّعْلُومٌ ( 164 ) አል ሷፋት - Aya 164
(ጂብሪል አለ) ከእኛም አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ፡፡ አል ሷፋት - Aya 164
وَإِنَّا لَنَحْنُ الصَّافُّونَ ( 165 ) አል ሷፋት - Aya 165
እኛም (ጌታን ለመግገዛት) ተሰላፊዎቹ እኛ ነን፡፡ አል ሷፋት - Aya 165
وَإِنَّا لَنَحْنُ الْمُسَبِّحُونَ ( 166 ) አል ሷፋት - Aya 166
እኛም (አላህን) አጥሪዎቹ እኛ ነን፡፡ አል ሷፋት - Aya 166
وَإِن كَانُوا لَيَقُولُونَ ( 167 ) አል ሷፋት - Aya 167
እነርሱም (ከሓዲዎቹ) በእርግጥ ይሉ ነበሩ፡- አል ሷፋት - Aya 167
لَوْ أَنَّ عِندَنَا ذِكْرًا مِّنَ الْأَوَّلِينَ ( 168 ) አል ሷፋት - Aya 168
«ከቀድሞዎቹ (መጻሕፍት) ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረን ኖሮ፤ አል ሷፋት - Aya 168
لَكُنَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ ( 169 ) አል ሷፋት - Aya 169
«የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር፡፡» አል ሷፋት - Aya 169
فَكَفَرُوا بِهِ ۖ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ ( 170 ) አል ሷፋት - Aya 170
ግን (ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ) በእርሱ ካዱ፡፡ ወደፊትም በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ አል ሷፋት - Aya 170
وَلَقَدْ سَبَقَتْ كَلِمَتُنَا لِعِبَادِنَا الْمُرْسَلِينَ ( 171 ) አል ሷፋት - Aya 171
(የእርዳታ) ቃላችንም መልክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች፡፡ አል ሷፋት - Aya 171
إِنَّهُمْ لَهُمُ الْمَنصُورُونَ ( 172 ) አል ሷፋት - Aya 172
እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 172
وَإِنَّ جُندَنَا لَهُمُ الْغَالِبُونَ ( 173 ) አል ሷፋት - Aya 173
ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 173
فَتَوَلَّ عَنْهُمْ حَتَّىٰ حِينٍ ( 174 ) አል ሷፋት - Aya 174
ከእነርሱም (ከመካ ከሓዲዎች) እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር (ተዋቸው)፡፡ አል ሷፋት - Aya 174
وَأَبْصِرْهُمْ فَسَوْفَ يُبْصِرُونَ ( 175 ) አል ሷፋት - Aya 175
እያቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያያሉ፡፡ አል ሷፋት - Aya 175
أَفَبِعَذَابِنَا يَسْتَعْجِلُونَ ( 176 ) አል ሷፋት - Aya 176
በቅጣታችንም ያቻኩላሉን? አል ሷፋት - Aya 176
فَإِذَا نَزَلَ بِسَاحَتِهِمْ فَسَاءَ صَبَاحُ الْمُنذَرِينَ ( 177 ) አል ሷፋት - Aya 177
በቀያቸውም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ! አል ሷፋት - Aya 177
وَتَوَلَّ عَنْهُمْ حَتَّىٰ حِينٍ ( 178 ) አል ሷፋት - Aya 178
እነርሱንም እስከ (ጥቂት) ጊዜ ድረስ ተዋቸው፡፡ አል ሷፋት - Aya 178
وَأَبْصِرْ فَسَوْفَ يُبْصِرُونَ ( 179 ) አል ሷፋት - Aya 179
ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ፡፡ አል ሷፋት - Aya 179
سُبْحَانَ رَبِّكَ رَبِّ الْعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ ( 180 ) አል ሷፋት - Aya 180
የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ አል ሷፋት - Aya 180
وَسَلَامٌ عَلَى الْمُرْسَلِينَ ( 181 ) አል ሷፋት - Aya 181
በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹኑ፤ አል ሷፋት - Aya 181
وَالْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ ( 182 ) አል ሷፋት - Aya 182
ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡ አል ሷፋት - Aya 182
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah