Surah ጣሃ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah ጣሃ - Aya count 135
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
طه ( 1 ) ጣሃ - Aya 1
ጠ.ሀ. (ጣ ሃ) ጣሃ - Aya 1
مَا أَنزَلْنَا عَلَيْكَ الْقُرْآنَ لِتَشْقَىٰ ( 2 ) ጣሃ - Aya 2
ቁርኣንን ባንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም፡፡ ጣሃ - Aya 2
إِلَّا تَذْكِرَةً لِّمَن يَخْشَىٰ ( 3 ) ጣሃ - Aya 3
ግን አላህን ለሚፈራ ሰው መገሰጫ ይኾን ዘንድ (አወረድነው)፡፡ ጣሃ - Aya 3
تَنزِيلًا مِّمَّنْ خَلَقَ الْأَرْضَ وَالسَّمَاوَاتِ الْعُلَى ( 4 ) ጣሃ - Aya 4
ምድርንና የላይኛዎቹን ሰማያት ከፈጠረ አምላክ ተወረደ፡፡ ጣሃ - Aya 4
الرَّحْمَٰنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَىٰ ( 5 ) ጣሃ - Aya 5
(እርሱ) አልረሕማን ነው በዐርሹ ላይ (ስልጣኑ) ተደላደለ፡፡ ጣሃ - Aya 5
لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا وَمَا تَحْتَ الثَّرَىٰ ( 6 ) ጣሃ - Aya 6
በሰማያት ያለው፣ በምድርም ያለው፣ በመካከላቸውም ያለው፣ ከዐፈር በታችም ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ጣሃ - Aya 6
وَإِن تَجْهَرْ بِالْقَوْلِ فَإِنَّهُ يَعْلَمُ السِّرَّ وَأَخْفَى ( 7 ) ጣሃ - Aya 7
በንግግር ብትጮህ (አላህ ከጩኸቱ የተብቃቃ ነው)፡፡ እርሱ ምስጢርን በጣም የተደበቀንም ያውቃልና፡፡ ጣሃ - Aya 7
اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ( 8 ) ጣሃ - Aya 8
አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ለእርሱ መልካሞች የኾኑ ስሞች አልሉት፡፡ ጣሃ - Aya 8
وَهَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ مُوسَىٰ ( 9 ) ጣሃ - Aya 9
የሙሳም ወሬ በእርግጥ መጥቶሃል፡፡ ጣሃ - Aya 9
إِذْ رَأَىٰ نَارًا فَقَالَ لِأَهْلِهِ امْكُثُوا إِنِّي آنَسْتُ نَارًا لَّعَلِّي آتِيكُم مِّنْهَا بِقَبَسٍ أَوْ أَجِدُ عَلَى النَّارِ هُدًى ( 10 ) ጣሃ - Aya 10
እሳትን ባየና ለቤተሰቦቹ፡- (እዚህ) «ቆዩ፤ እኔ እሳትን አየሁ፡፡ ከእርሷ ችቦን ላመጣላችሁ፤ ወይም እሳቲቱ ዘንድ መሪን ላገኝ እከጅላለሁ» ባለጊዜ (አስታውስ)፡፡ ጣሃ - Aya 10
فَلَمَّا أَتَاهَا نُودِيَ يَا مُوسَىٰ ( 11 ) ጣሃ - Aya 11
በመጣትም ጊዜ «ሙሳ ሆይ» በማለት ተጠራ፡፡ ጣሃ - Aya 11
إِنِّي أَنَا رَبُّكَ فَاخْلَعْ نَعْلَيْكَ ۖ إِنَّكَ بِالْوَادِ الْمُقَدَّسِ طُوًى ( 12 ) ጣሃ - Aya 12
«እኔ ጌታህ እኔ ነኝ መጫሚያዎችህንም አውልቅ፡፡ አንተ በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ ነህና፡፡ ጣሃ - Aya 12
وَأَنَا اخْتَرْتُكَ فَاسْتَمِعْ لِمَا يُوحَىٰ ( 13 ) ጣሃ - Aya 13
«እኔም መረጥኩህ፤ የሚወረድልህንም ነገር አዳምጥ፡፡ ጣሃ - Aya 13
إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي ( 14 ) ጣሃ - Aya 14
«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ ጣሃ - Aya 14
إِنَّ السَّاعَةَ آتِيَةٌ أَكَادُ أُخْفِيهَا لِتُجْزَىٰ كُلُّ نَفْسٍ بِمَا تَسْعَىٰ ( 15 ) ጣሃ - Aya 15
«ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪናት፡፡ ልደብቃት እቃረባለሁ፡፡ ነፍስ ሁሉ በምትሠራው ነገር ትመነዳ ዘንድ (መጭ ናት)፡፡ ጣሃ - Aya 15
فَلَا يَصُدَّنَّكَ عَنْهَا مَن لَّا يُؤْمِنُ بِهَا وَاتَّبَعَ هَوَاهُ فَتَرْدَىٰ ( 16 ) ጣሃ - Aya 16
«በእርሷ የማያምነውና ዝንባሌውን የተከተለውም ሰው ከእርሷ አያግድህ ትጠፋለህና፡፤ ጣሃ - Aya 16
وَمَا تِلْكَ بِيَمِينِكَ يَا مُوسَىٰ ( 17 ) ጣሃ - Aya 17
«ሙሳ ሆይ! ይህችም በቀኝ እጅህ ያለችው ምንድን ናት» (ተባለ)፡፡ ጣሃ - Aya 17
قَالَ هِيَ عَصَايَ أَتَوَكَّأُ عَلَيْهَا وَأَهُشُّ بِهَا عَلَىٰ غَنَمِي وَلِيَ فِيهَا مَآرِبُ أُخْرَىٰ ( 18 ) ጣሃ - Aya 18
«እርሷ በትሬ ናት፡፡ በእርሷ ላይ እደገፍባታለሁ፣ በእርሷም ለፍየሎቼ ቅጠልን አረግፍባታለሁ፣ ለእኔም በእርሷ ሌሎች ጉዳዮች አሉኝ» አለ፡፡ ጣሃ - Aya 18
قَالَ أَلْقِهَا يَا مُوسَىٰ ( 19 ) ጣሃ - Aya 19
(አላህም) «ሙሳ ሆይ! ጣላት» አለው፡፡ ጣሃ - Aya 19
فَأَلْقَاهَا فَإِذَا هِيَ حَيَّةٌ تَسْعَىٰ ( 20 ) ጣሃ - Aya 20
ጣላትም፡፡ ወዲያውም እርሷ የምትሮጥ እባብ ኾነች፡፡ ጣሃ - Aya 20
قَالَ خُذْهَا وَلَا تَخَفْ ۖ سَنُعِيدُهَا سِيرَتَهَا الْأُولَىٰ ( 21 ) ጣሃ - Aya 21
«ያዛት፤ አትፍራም፡፡ ወደ መጀመሪያ ጠባይዋ እንመልሳታለን» አለው፡፡ ጣሃ - Aya 21
وَاضْمُمْ يَدَكَ إِلَىٰ جَنَاحِكَ تَخْرُجْ بَيْضَاءَ مِنْ غَيْرِ سُوءٍ آيَةً أُخْرَىٰ ( 22 ) ጣሃ - Aya 22
«እጅህንም ወደ ብብትህ አግባ፡፡ ሌላ ተዓምር ስትኾን ያለነውር ነጭ ኾና ትወጣለችና፡፡ ጣሃ - Aya 22
لِنُرِيَكَ مِنْ آيَاتِنَا الْكُبْرَى ( 23 ) ጣሃ - Aya 23
«ከተዓምራቶቻችን ታላቋን እናሳይህ ዘንድ (ይህን ሠራን)፡፡ ጣሃ - Aya 23
اذْهَبْ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ إِنَّهُ طَغَىٰ ( 24 ) ጣሃ - Aya 24
«ወደ ፈርዖን ኺድ፡፡ እርሱ ወሰን አልፏልና፡፡» ጣሃ - Aya 24
قَالَ رَبِّ اشْرَحْ لِي صَدْرِي ( 25 ) ጣሃ - Aya 25
(ሙሳም) አለ «ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ፡፡ ጣሃ - Aya 25
وَيَسِّرْ لِي أَمْرِي ( 26 ) ጣሃ - Aya 26
«ነገሬንም ለእኔ አግራልኝ፡፡ ጣሃ - Aya 26
وَاحْلُلْ عُقْدَةً مِّن لِّسَانِي ( 27 ) ጣሃ - Aya 27
«ከምላሴም መኮላተፍን ፍታልኝ፡፡ ጣሃ - Aya 27
يَفْقَهُوا قَوْلِي ( 28 ) ጣሃ - Aya 28
«ንግግሬን ያውቃሉና፡፡ ጣሃ - Aya 28
وَاجْعَل لِّي وَزِيرًا مِّنْ أَهْلِي ( 29 ) ጣሃ - Aya 29
«ከቤተሰቦቼም ለእኔ ረዳትን አድርግልኝ፡፡ ጣሃ - Aya 29
هَارُونَ أَخِي ( 30 ) ጣሃ - Aya 30
«ሃሩንን ወንድሜን፡፡ ጣሃ - Aya 30
اشْدُدْ بِهِ أَزْرِي ( 31 ) ጣሃ - Aya 31
«ኅይሌን በእርሱ አበርታልኝ፡፡ ጣሃ - Aya 31
وَأَشْرِكْهُ فِي أَمْرِي ( 32 ) ጣሃ - Aya 32
«በነገሬም አጋራው፡፡ ጣሃ - Aya 32
كَيْ نُسَبِّحَكَ كَثِيرًا ( 33 ) ጣሃ - Aya 33
«በብዙ እናጠራህ ዘንድ፡፡ ጣሃ - Aya 33
وَنَذْكُرَكَ كَثِيرًا ( 34 ) ጣሃ - Aya 34
«በብዙም እንድናወሳህ፡፡ ጣሃ - Aya 34
إِنَّكَ كُنتَ بِنَا بَصِيرًا ( 35 ) ጣሃ - Aya 35
«አንተ በእኛ ነገር ዐዋቂ ነህና፡፡» ጣሃ - Aya 35
قَالَ قَدْ أُوتِيتَ سُؤْلَكَ يَا مُوسَىٰ ( 36 ) ጣሃ - Aya 36
(አላህም) አለ «ሙሳ ሆይ! ልመናህን በእርግጥ ተሰጠህ፡፡ ጣሃ - Aya 36
وَلَقَدْ مَنَنَّا عَلَيْكَ مَرَّةً أُخْرَىٰ ( 37 ) ጣሃ - Aya 37
«በሌላም ጊዜ ባንተ ላይ በእርግጥ ለግሰናል፡፡ ጣሃ - Aya 37
إِذْ أَوْحَيْنَا إِلَىٰ أُمِّكَ مَا يُوحَىٰ ( 38 ) ጣሃ - Aya 38
«ወደናትህ በልብ የሚፈስን ነገር ባሳወቅን ጊዜ፡፡ ጣሃ - Aya 38
أَنِ اقْذِفِيهِ فِي التَّابُوتِ فَاقْذِفِيهِ فِي الْيَمِّ فَلْيُلْقِهِ الْيَمُّ بِالسَّاحِلِ يَأْخُذْهُ عَدُوٌّ لِّي وَعَدُوٌّ لَّهُ ۚ وَأَلْقَيْتُ عَلَيْكَ مَحَبَّةً مِّنِّي وَلِتُصْنَعَ عَلَىٰ عَيْنِي ( 39 ) ጣሃ - Aya 39
«(ሕፃኑን) በሳጥኑ ውስጥ ጣይው፡፡ እርሱንም (ሳጥኑን) በባሕር ላይ ጣይው፡፡ ባሕሩም በዳርቻው ይጣለው፡፡ ለእኔ ጠላት ለእርሱም ጠላት የኾነ ሰው ይይዘዋልና በማለት (ባሳወቅን ጊዜ ለገስንልህ)፡፡ ባንተ ላይም ከእኔ የኾነን መወደድ ጣልኩብህ፡፡ (ልትወደድና) በእኔም ጥበቃ ታድግ ዘንድ፡፡ ጣሃ - Aya 39
إِذْ تَمْشِي أُخْتُكَ فَتَقُولُ هَلْ أَدُلُّكُمْ عَلَىٰ مَن يَكْفُلُهُ ۖ فَرَجَعْنَاكَ إِلَىٰ أُمِّكَ كَيْ تَقَرَّ عَيْنُهَا وَلَا تَحْزَنَ ۚ وَقَتَلْتَ نَفْسًا فَنَجَّيْنَاكَ مِنَ الْغَمِّ وَفَتَنَّاكَ فُتُونًا ۚ فَلَبِثْتَ سِنِينَ فِي أَهْلِ مَدْيَنَ ثُمَّ جِئْتَ عَلَىٰ قَدَرٍ يَا مُوسَىٰ ( 40 ) ጣሃ - Aya 40
«እኅትህም በምትኼድና የሚያሳድገውን ሰው ላመላክታችሁን በምትል ጊዜ (መወደድን ጣልኩብህ)፡፡ ወደ እናትህም ዓይንዋ እንዲረጋ (እርሷ) እንዳታዝንም መለስንህ፡፡ ነፍስንም ገደልክ፡፡ ከጭንቅም አዳንንህ፡፡ ፈተናዎችንም ፈተንህ፡፡ በመድየን ቤተሰቦችም ውስጥ (ብዙ) ዓመታትን ተቀመጥክ፡፡ ከዚያም ሙሳ ሆይ! በተወሰነ ጊዜ ላይ መጣህ፡፡ ጣሃ - Aya 40
وَاصْطَنَعْتُكَ لِنَفْسِي ( 41 ) ጣሃ - Aya 41
«ለነፍሴም (በመልእክቴ) መረጥኩህ፡፡ ጣሃ - Aya 41
اذْهَبْ أَنتَ وَأَخُوكَ بِآيَاتِي وَلَا تَنِيَا فِي ذِكْرِي ( 42 ) ጣሃ - Aya 42
«አንተም ወንድምህም በተዓምራቶቼ ኺዱ፡፡ እኔንም ከማውሳት አትቦዝኑ፡፡ ጣሃ - Aya 42
اذْهَبَا إِلَىٰ فِرْعَوْنَ إِنَّهُ طَغَىٰ ( 43 ) ጣሃ - Aya 43
«ወደ ፈርዖን ኺዱ፡፡ እርሱ ወሰን አልፏልና፡፡ ጣሃ - Aya 43
فَقُولَا لَهُ قَوْلًا لَّيِّنًا لَّعَلَّهُ يَتَذَكَّرُ أَوْ يَخْشَىٰ ( 44 ) ጣሃ - Aya 44
«እርሱም ይገሰጽ ወይም ይፈራ ዘንድ፤ ለእርሱ ልዝብን ቃል ተናገሩት፡፡» ጣሃ - Aya 44
قَالَا رَبَّنَا إِنَّنَا نَخَافُ أَن يَفْرُطَ عَلَيْنَا أَوْ أَن يَطْغَىٰ ( 45 ) ጣሃ - Aya 45
«ጌታችን ሆይ! እኛ በእኛ ላይ ክፋት በመሥራት መቸኮሉን ወይም ኩራትን መጨመሩን እንፈራለን» አሉ፡፡ ጣሃ - Aya 45
قَالَ لَا تَخَافَا ۖ إِنَّنِي مَعَكُمَا أَسْمَعُ وَأَرَىٰ ( 46 ) ጣሃ - Aya 46
(አላህም) አለ «አትፍሩ፡፡ እኔ በእርግጥ ከእናንተ ጋር ነኝና፡፡ እሰማለሁ፤ አያለሁም፡፡ ጣሃ - Aya 46
فَأْتِيَاهُ فَقُولَا إِنَّا رَسُولَا رَبِّكَ فَأَرْسِلْ مَعَنَا بَنِي إِسْرَائِيلَ وَلَا تُعَذِّبْهُمْ ۖ قَدْ جِئْنَاكَ بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكَ ۖ وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ ( 47 ) ጣሃ - Aya 47
«ወደርሱም ኺዱ፤ በሉትም፡- ‹እኛ የጌታህ መልክተኞች ነን፡፡› የእስራኤልንም ልጆች ከኛ ጋር ልቀቅ፡፡ አታሰቃያቸውም፡፡ ከጌታህ በኾነው ተዓምር በእርግጥ መጥተንሃልና፡፡ ሰላምም ቀጥታን በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡ ጣሃ - Aya 47
إِنَّا قَدْ أُوحِيَ إِلَيْنَا أَنَّ الْعَذَابَ عَلَىٰ مَن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ ( 48 ) ጣሃ - Aya 48
«እኛ ቅጣቱ ባስተባበለና እምቢ ባለ ሰው ላይ ነው ማለት በእርግጥ ተወረደልን፡፡» ጣሃ - Aya 48
قَالَ فَمَن رَّبُّكُمَا يَا مُوسَىٰ ( 49 ) ጣሃ - Aya 49
(ፈርዖንም) «ሙሳ ሆይ! ጌታችሁ ማነው» አለ፡፡ ጣሃ - Aya 49
قَالَ رَبُّنَا الَّذِي أَعْطَىٰ كُلَّ شَيْءٍ خَلْقَهُ ثُمَّ هَدَىٰ ( 50 ) ጣሃ - Aya 50
«ጌታችን ያ ለፍጥረቱ ነገርን ሁሉ (የሚያስፈልገውን) የሰጠ ከዚያም የመራው ነው» አለው፡፡ ጣሃ - Aya 50
قَالَ فَمَا بَالُ الْقُرُونِ الْأُولَىٰ ( 51 ) ጣሃ - Aya 51
(ፈርዖንም) «የመጀመሪያይቱ ዘመናት ሕዝቦች ኹኔታ ምንድን ነው» አለ፡፡ ጣሃ - Aya 51
قَالَ عِلْمُهَا عِندَ رَبِّي فِي كِتَابٍ ۖ لَّا يَضِلُّ رَبِّي وَلَا يَنسَى ( 52 ) ጣሃ - Aya 52
(ሙሳም) «ዕውቀትዋ እጌታዬ ዘንድ በመጽሐፍ የተመዘገበ ነው፡፡ ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም» አለው፡፡ ጣሃ - Aya 52
الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ مَهْدًا وَسَلَكَ لَكُمْ فِيهَا سُبُلًا وَأَنزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَخْرَجْنَا بِهِ أَزْوَاجًا مِّن نَّبَاتٍ شَتَّىٰ ( 53 ) ጣሃ - Aya 53
(እርሱ) ያ ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ ያደረገላችሁ፣ በእርሷም ውስጥ ለእናንተ መንገድን ያገራላችሁ፣ ውሃንም ከሰማይ ያወረደ ነው (አለ)፡፡ በርሱም ከተለያየ በቃይ ዓይነቶችን አወጣንላችሁ፡፡ ጣሃ - Aya 53
كُلُوا وَارْعَوْا أَنْعَامَكُمْ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّأُولِي النُّهَىٰ ( 54 ) ጣሃ - Aya 54
ብሉ እንስሳዎቻችሁንም አግጡ፤ (ባዮች ኾነን አወጣንላችሁ)፡፡ በዚህ ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች በእርግጥ ተዓምራት አለበት፡፡ ጣሃ - Aya 54
مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ ( 55 ) ጣሃ - Aya 55
ከእርሷ (ከምድር) ፈጠርናችሁ፡፡ በእርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፡፡ ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን፡፡ ጣሃ - Aya 55
وَلَقَدْ أَرَيْنَاهُ آيَاتِنَا كُلَّهَا فَكَذَّبَ وَأَبَىٰ ( 56 ) ጣሃ - Aya 56
ተዓምራቶቻችንንም ሁሏንም (ለፈርዖን) በእርግጥ አሳየነው፡፡ አስተባበለም፡፡ እምቢም አለ፡፡ ጣሃ - Aya 56
قَالَ أَجِئْتَنَا لِتُخْرِجَنَا مِنْ أَرْضِنَا بِسِحْرِكَ يَا مُوسَىٰ ( 57 ) ጣሃ - Aya 57
«ከምድራችን በድግምትህ ልታወጣን መጣህብን ሙሳ ሆይ!» አለ፡፡ ጣሃ - Aya 57
فَلَنَأْتِيَنَّكَ بِسِحْرٍ مِّثْلِهِ فَاجْعَلْ بَيْنَنَا وَبَيْنَكَ مَوْعِدًا لَّا نُخْلِفُهُ نَحْنُ وَلَا أَنتَ مَكَانًا سُوًى ( 58 ) ጣሃ - Aya 58
«መሰሉንም ድግምት እናመጣብሃለን፡፡ በእኛና ባንተም መካከል እኛም አንተም የማንጥሰው የኾነ ቀጠሮን በመካከለኛ ስፍራ አድርግልን» አለ፡፡ ጣሃ - Aya 58
قَالَ مَوْعِدُكُمْ يَوْمُ الزِّينَةِ وَأَن يُحْشَرَ النَّاسُ ضُحًى ( 59 ) ጣሃ - Aya 59
«ቀጠሯችሁ በማጌጫው ቀን ሰዎቹም በረፋድ በሚሰበሰቡበት ነው» አለ፡፡ ጣሃ - Aya 59
فَتَوَلَّىٰ فِرْعَوْنُ فَجَمَعَ كَيْدَهُ ثُمَّ أَتَىٰ ( 60 ) ጣሃ - Aya 60
ፈርዖንም ዞረ፡፡ ተንኮሉንም ሰበሰበ፡፡ ከዚያም መጣ፡፡ ጣሃ - Aya 60
قَالَ لَهُم مُّوسَىٰ وَيْلَكُمْ لَا تَفْتَرُوا عَلَى اللَّهِ كَذِبًا فَيُسْحِتَكُم بِعَذَابٍ ۖ وَقَدْ خَابَ مَنِ افْتَرَىٰ ( 61 ) ጣሃ - Aya 61
ሙሳ ለእነሱ አላቸው «ወዮላችሁ በአላህ ላይ ውሸትን አትቅጠፉ፡፡ በቅጣት ያጠፋችኋልና፡፡ የቀጠፈም ሰው በእርግጥ አፈረ፡፡» ጣሃ - Aya 61
فَتَنَازَعُوا أَمْرَهُم بَيْنَهُمْ وَأَسَرُّوا النَّجْوَىٰ ( 62 ) ጣሃ - Aya 62
(ድግምተኞቹ) በመካከላቸውም ነገራቸውን ተጨቃጨቁ፡፡ ውይይትንም ደበቁ፡፡ ጣሃ - Aya 62
قَالُوا إِنْ هَٰذَانِ لَسَاحِرَانِ يُرِيدَانِ أَن يُخْرِجَاكُم مِّنْ أَرْضِكُم بِسِحْرِهِمَا وَيَذْهَبَا بِطَرِيقَتِكُمُ الْمُثْلَىٰ ( 63 ) ጣሃ - Aya 63
«እነዚህ በእርግጥ ደጋሚዎች ናቸው፡፡ ከምድራችሁ በድግምታቸው ሊያወጧችሁ በላጪቱንም መንገዳችሁን ሊያስወግዱባችሁ ይሻሉ» አሉ፡፡ ጣሃ - Aya 63
فَأَجْمِعُوا كَيْدَكُمْ ثُمَّ ائْتُوا صَفًّا ۚ وَقَدْ أَفْلَحَ الْيَوْمَ مَنِ اسْتَعْلَىٰ ( 64 ) ጣሃ - Aya 64
«ተንኮላችሁንም አጠንክሩ፡፡ ከዚያም ተሰልፋችሁ ኑ፡፡ ዛሬ ያሸነፈም ሰው ምኞቱን አገኘ» (ተባባሉ)፡፡ ጣሃ - Aya 64
قَالُوا يَا مُوسَىٰ إِمَّا أَن تُلْقِيَ وَإِمَّا أَن نَّكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَلْقَىٰ ( 65 ) ጣሃ - Aya 65
«ሙሳ ሆይ! ወይ ትጥላለህ ወይም በመጀመሪያ የምንጥል እንኾናለን» (ምረጥ) አሉ፡፡ ጣሃ - Aya 65
قَالَ بَلْ أَلْقُوا ۖ فَإِذَا حِبَالُهُمْ وَعِصِيُّهُمْ يُخَيَّلُ إِلَيْهِ مِن سِحْرِهِمْ أَنَّهَا تَسْعَىٰ ( 66 ) ጣሃ - Aya 66
«አይደለም ጣሉ» አላቸው፡፡ ወዲያውም ገመዶቻቸውና ዘንጎቻቸው ከድግምታቸው የተነሳ እነርሱ የሚሮጡ (እባቦች) ኾነው ወደርሱ ተመለሱ፡፡ ጣሃ - Aya 66
فَأَوْجَسَ فِي نَفْسِهِ خِيفَةً مُّوسَىٰ ( 67 ) ጣሃ - Aya 67
ሙሳም በነፍሱ ውስጥ ፍርሃትን አሳደረ፡፡ ጣሃ - Aya 67
قُلْنَا لَا تَخَفْ إِنَّكَ أَنتَ الْأَعْلَىٰ ( 68 ) ጣሃ - Aya 68
«አትፍራ አንተ የበላዩ አንተ ነህና» አልነው፡፡ ጣሃ - Aya 68
وَأَلْقِ مَا فِي يَمِينِكَ تَلْقَفْ مَا صَنَعُوا ۖ إِنَّمَا صَنَعُوا كَيْدُ سَاحِرٍ ۖ وَلَا يُفْلِحُ السَّاحِرُ حَيْثُ أَتَىٰ ( 69 ) ጣሃ - Aya 69
«በቀኝ እጅህ ያለቸውንም በትር ጣል፡፡ ያንን የሠሩትን ትውጣለችና፡፡ ያ የሠሩት ሁሉ የድግምተኛ ተንኮል ነውና፡፡ ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም» (አልን)፡፡ ጣሃ - Aya 69
فَأُلْقِيَ السَّحَرَةُ سُجَّدًا قَالُوا آمَنَّا بِرَبِّ هَارُونَ وَمُوسَىٰ ( 70 ) ጣሃ - Aya 70
ድግምተኞቹም ሰጋጆች ኾነው ወደቁ፡፡ «በሃሩንና በሙሳ ጌታ አመንን» አሉ፡፡ ጣሃ - Aya 70
قَالَ آمَنتُمْ لَهُ قَبْلَ أَنْ آذَنَ لَكُمْ ۖ إِنَّهُ لَكَبِيرُكُمُ الَّذِي عَلَّمَكُمُ السِّحْرَ ۖ فَلَأُقَطِّعَنَّ أَيْدِيَكُمْ وَأَرْجُلَكُم مِّنْ خِلَافٍ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمْ فِي جُذُوعِ النَّخْلِ وَلَتَعْلَمُنَّ أَيُّنَا أَشَدُّ عَذَابًا وَأَبْقَىٰ ( 71 ) ጣሃ - Aya 71
(ፈርዖንም) «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን እርሱ በእርግጥ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ትልቃችሁ ነው፡፡ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማናጋት (ግራናቀኝን በማፈራረቅ) እቆራርጣችኋለሁ፡፡ በዘምባባም ግንዶች ለይ እሰቅላችኋለሁ፡፡ ማንኛችንም ቅጣቱ በጣም ብርቱ የሚቆይም መኾኑን ታውቃላችሁ» አላቸው፡፡ ጣሃ - Aya 71
قَالُوا لَن نُّؤْثِرَكَ عَلَىٰ مَا جَاءَنَا مِنَ الْبَيِّنَاتِ وَالَّذِي فَطَرَنَا ۖ فَاقْضِ مَا أَنتَ قَاضٍ ۖ إِنَّمَا تَقْضِي هَٰذِهِ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا ( 72 ) ጣሃ - Aya 72
ከመጡልን ታምራቶች ከዚያም ከፈጠረን(አምላክ) ፈጽሞ አንመርጥህም፤ አንተም የምትፈርደውን ፍረድ፤ የምትፈርደው በዚች በአነስተኛይቱ ሕይወት ብቻ ነው አሉ፡፡ ጣሃ - Aya 72
إِنَّا آمَنَّا بِرَبِّنَا لِيَغْفِرَ لَنَا خَطَايَانَا وَمَا أَكْرَهْتَنَا عَلَيْهِ مِنَ السِّحْرِ ۗ وَاللَّهُ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ ( 73 ) ጣሃ - Aya 73
«ኃጢአቶቻችንንና ከድግምትም በእርሱ ላይ ያስገደድከንን ለእኛ ይምረን ዘንድ እኛ በጌታችን አምነናል፡፡ አላህም በጣም በላጭ ነው፤ (ቅጣቱም) በጣም የሚዘወትር ነው» አሉ፡፡ ጣሃ - Aya 73
إِنَّهُ مَن يَأْتِ رَبَّهُ مُجْرِمًا فَإِنَّ لَهُ جَهَنَّمَ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحْيَىٰ ( 74 ) ጣሃ - Aya 74
እነሆ ከሓዲ ኾኖ ወደ ጌታው የሚመጣ ሰው ለእርሱ ገሀነም አለችው፡፡ በውስጧም አይሞትም ሕያውም አይኾን፡፡ ጣሃ - Aya 74
وَمَن يَأْتِهِ مُؤْمِنًا قَدْ عَمِلَ الصَّالِحَاتِ فَأُولَٰئِكَ لَهُمُ الدَّرَجَاتُ الْعُلَىٰ ( 75 ) ጣሃ - Aya 75
በጎ ሥራዎችን በእርግጥ የሠራ ምእመን ኾኖ የመጣውም ሰው እነዚያ ለእነሱ ከፍተኛ ደረጃዎች አሏቸው፡፡ ጣሃ - Aya 75
جَنَّاتُ عَدْنٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ وَذَٰلِكَ جَزَاءُ مَن تَزَكَّىٰ ( 76 ) ጣሃ - Aya 76
ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ (አሏቸው)፡፡ ይህም የተጥራራ ሰው ምንዳ ነው፡፡ ጣሃ - Aya 76
وَلَقَدْ أَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ أَنْ أَسْرِ بِعِبَادِي فَاضْرِبْ لَهُمْ طَرِيقًا فِي الْبَحْرِ يَبَسًا لَّا تَخَافُ دَرَكًا وَلَا تَخْشَىٰ ( 77 ) ጣሃ - Aya 77
ወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ በሌሊት ኺድ፡፡ ለእነሱም በባሕር ውስጥ ደረቅ መንገድን አድርግላቸው፡፡ መገኘትን አትፍራ፡፡ (ከመስጠም) አትጨነቅም፡፡» ስንል በእርግጥ ላክንበት፡፡ ጣሃ - Aya 77
فَأَتْبَعَهُمْ فِرْعَوْنُ بِجُنُودِهِ فَغَشِيَهُم مِّنَ الْيَمِّ مَا غَشِيَهُمْ ( 78 ) ጣሃ - Aya 78
ፈርዖንም ከሰራዊቱ ጋር ኾኖ ተከተላቸው፡፡ ከባህሩም የሚሸፍን ሸፈናቸው፡፡ ጣሃ - Aya 78
وَأَضَلَّ فِرْعَوْنُ قَوْمَهُ وَمَا هَدَىٰ ( 79 ) ጣሃ - Aya 79
ፈርዖንም ሕዝቦቹን አሳሳታቸው፡፡ ቅኑንም መንገድ አልመራቸውም፡፡ ጣሃ - Aya 79
يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ قَدْ أَنجَيْنَاكُم مِّنْ عَدُوِّكُمْ وَوَاعَدْنَاكُمْ جَانِبَ الطُّورِ الْأَيْمَنَ وَنَزَّلْنَا عَلَيْكُمُ الْمَنَّ وَالسَّلْوَىٰ ( 80 ) ጣሃ - Aya 80
የእስራኤል ልጆች ሆይ! ከጠላታችሁ በእርግጥ አዳንናችሁ፡፡ በጡርም ቀኝ ጎን ቀጠሮ አደረግንላችሁ፡፡ በእናንተም ላይ መናንና ድርጭትን አወረድንላችሁ፡፡ ጣሃ - Aya 80
كُلُوا مِن طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ وَلَا تَطْغَوْا فِيهِ فَيَحِلَّ عَلَيْكُمْ غَضَبِي ۖ وَمَن يَحْلِلْ عَلَيْهِ غَضَبِي فَقَدْ هَوَىٰ ( 81 ) ጣሃ - Aya 81
ከሰጠናችሁ ሲሳይ፤ ከመልካሙ ብሉ፡፡ በእርሱም ወሰንን አትለፉ፡፡ ቁጣዬ በእናንተ ላይ ይወርድባችኋልና፡፡ በእርሱም ላይ ቁጣዬ የሚወርድበት ሰው በእርግጥ ይጠፋል፡፡ ጣሃ - Aya 81
وَإِنِّي لَغَفَّارٌ لِّمَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ صَالِحًا ثُمَّ اهْتَدَىٰ ( 82 ) ጣሃ - Aya 82
እኔም ለተጸጸተ፣ ላመነም፣ መልካምንም ለሠራ፣ ከዚያም ለተመራ ሰው በእርግጥ መሓሪ ነኝ፡፡ ጣሃ - Aya 82
وَمَا أَعْجَلَكَ عَن قَوْمِكَ يَا مُوسَىٰ ( 83 ) ጣሃ - Aya 83
«ሙሳ ሆይ! ከሕዝቦችህ ምን አስቸኮለህም» (ተባለ)፡፡ ጣሃ - Aya 83
قَالَ هُمْ أُولَاءِ عَلَىٰ أَثَرِي وَعَجِلْتُ إِلَيْكَ رَبِّ لِتَرْضَىٰ ( 84 ) ጣሃ - Aya 84
«እነሱ እነዚህ፤ በዱካዬ ላይ ያሉ ናቸው፡፡ ጌታዬ ሆይ! ትወድልንም ዘንድ ወደ አንተ ቸኮልኩ» አለ፡፡ ጣሃ - Aya 84
قَالَ فَإِنَّا قَدْ فَتَنَّا قَوْمَكَ مِن بَعْدِكَ وَأَضَلَّهُمُ السَّامِرِيُّ ( 85 ) ጣሃ - Aya 85
(አላህ) «እኛም ከአንተ በኋላ ሰዎችህን በእርግጥ ፈትተን፡፡ ሳምራዊውም አሳሳታቸው» አለው፡፡ ጣሃ - Aya 85
فَرَجَعَ مُوسَىٰ إِلَىٰ قَوْمِهِ غَضْبَانَ أَسِفًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ أَلَمْ يَعِدْكُمْ رَبُّكُمْ وَعْدًا حَسَنًا ۚ أَفَطَالَ عَلَيْكُمُ الْعَهْدُ أَمْ أَرَدتُّمْ أَن يَحِلَّ عَلَيْكُمْ غَضَبٌ مِّن رَّبِّكُمْ فَأَخْلَفْتُم مَّوْعِدِي ( 86 ) ጣሃ - Aya 86
ሙሳም ወደ ሰዎቹ የተቆጣ ያዘነ ኾኖ ተመለሰ፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! ጌታችሁ መልካም ተስፋን አልቀጠራችሁምን ቀጠሮው በእናንተ ላይ ረዘመባችሁን» ወይስ በእናንተ ላይ ከጌታችሁ ቅጣት ሊወርድባችሁ ፈለጋችሁና ቀጠሮየን አፈረሳችሁን አላቸው፡፡ ጣሃ - Aya 86
قَالُوا مَا أَخْلَفْنَا مَوْعِدَكَ بِمَلْكِنَا وَلَٰكِنَّا حُمِّلْنَا أَوْزَارًا مِّن زِينَةِ الْقَوْمِ فَقَذَفْنَاهَا فَكَذَٰلِكَ أَلْقَى السَّامِرِيُّ ( 87 ) ጣሃ - Aya 87
«ቀጠሮህን በፈቃዳችን አልጣስንም፡፡ ግን እኛ ከሕዝቦቹ ጌጥ ሸክሞችን ተጫን (በእሳት ላይ) ጣልናትም፡፡ ሳምራዊውም እንደዚሁ ጣለ» አሉት፡፡ ጣሃ - Aya 87
فَأَخْرَجَ لَهُمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ فَقَالُوا هَٰذَا إِلَٰهُكُمْ وَإِلَٰهُ مُوسَىٰ فَنَسِيَ ( 88 ) ጣሃ - Aya 88
ለእነሱም አካል የኾነ ጥጃን ለእርሱ መጓጎር ያለውን አወጣላቸው፡፡ (ተከታዮቹ) «ይህ አምላካችሁ የሙሳም አምላክ ነው ግን ረሳው» አሉም፡፡ ጣሃ - Aya 88
أَفَلَا يَرَوْنَ أَلَّا يَرْجِعُ إِلَيْهِمْ قَوْلًا وَلَا يَمْلِكُ لَهُمْ ضَرًّا وَلَا نَفْعًا ( 89 ) ጣሃ - Aya 89
ወደእነሱ ንግግርን የማይመልስ ለእነሱም ጉዳትንና ጥቅምን የማይችል መኾኑን አያዩምን ጣሃ - Aya 89
وَلَقَدْ قَالَ لَهُمْ هَارُونُ مِن قَبْلُ يَا قَوْمِ إِنَّمَا فُتِنتُم بِهِ ۖ وَإِنَّ رَبَّكُمُ الرَّحْمَٰنُ فَاتَّبِعُونِي وَأَطِيعُوا أَمْرِي ( 90 ) ጣሃ - Aya 90
ሃሩንም ከዚህ በፊት በእርግጥ አላቸው፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! (ይህ) በእርሱ የተሞከራችሁበት ብቻ ነው፡፡ ጌታችሁም አልረሕማን ነው፡፡ ተከተሉኝም፡፡ ትዕዛዜንም ስሙ፡፡» ጣሃ - Aya 90
قَالُوا لَن نَّبْرَحَ عَلَيْهِ عَاكِفِينَ حَتَّىٰ يَرْجِعَ إِلَيْنَا مُوسَىٰ ( 91 ) ጣሃ - Aya 91
«ሙሳ ወደእኛ እስከሚመለስ በእርሱ (መገዛት) ላይ ከመቆየት ፈጽሞ አንወገድም» አሉ፡፡ ጣሃ - Aya 91
قَالَ يَا هَارُونُ مَا مَنَعَكَ إِذْ رَأَيْتَهُمْ ضَلُّوا ( 92 ) ጣሃ - Aya 92
(ሙሳ) አለ፡- «ሃሩን ሆይ! ተሳስተው ባየሃቸው ጊዜ ምን ከለከልህ ጣሃ - Aya 92
أَلَّا تَتَّبِعَنِ ۖ أَفَعَصَيْتَ أَمْرِي ( 93 ) ጣሃ - Aya 93
«እኔን ከመከተል ትዕዛዜን ጣስክን» ጣሃ - Aya 93
قَالَ يَا ابْنَ أُمَّ لَا تَأْخُذْ بِلِحْيَتِي وَلَا بِرَأْسِي ۖ إِنِّي خَشِيتُ أَن تَقُولَ فَرَّقْتَ بَيْنَ بَنِي إِسْرَائِيلَ وَلَمْ تَرْقُبْ قَوْلِي ( 94 ) ጣሃ - Aya 94
«የእናቴ ልጅ ሆይ! ጢሜንም ራሴንም አትያዝ፡፡ እኔ በእስራኤል ልጆች መካከል ለያየህ፤ ቃሌንም አልጠበቅህም ማለትህን ፈራሁ» አለው፡፡ ጣሃ - Aya 94
قَالَ فَمَا خَطْبُكَ يَا سَامِرِيُّ ( 95 ) ጣሃ - Aya 95
(ሙሳ) «ሳምራዊው ሆይ! ነገርህም ምንድን ነው» አለ፡፡ ጣሃ - Aya 95
قَالَ بَصُرْتُ بِمَا لَمْ يَبْصُرُوا بِهِ فَقَبَضْتُ قَبْضَةً مِّنْ أَثَرِ الرَّسُولِ فَنَبَذْتُهَا وَكَذَٰلِكَ سَوَّلَتْ لِي نَفْسِي ( 96 ) ጣሃ - Aya 96
ያላዩትን ነገር አየሁ፡፡ ከመልክተኛው (ከፈረሱ ኮቴ) ዱካም ጭብጥ አፈርን ዘገንኩ፡፡ (በቅርጹ ላይ) ጣልኳትም፡፡ እንደዚሁም ነፍሴ ሸለመችልኝ» አለ፡፡ ጣሃ - Aya 96
قَالَ فَاذْهَبْ فَإِنَّ لَكَ فِي الْحَيَاةِ أَن تَقُولَ لَا مِسَاسَ ۖ وَإِنَّ لَكَ مَوْعِدًا لَّن تُخْلَفَهُ ۖ وَانظُرْ إِلَىٰ إِلَٰهِكَ الَّذِي ظَلْتَ عَلَيْهِ عَاكِفًا ۖ لَّنُحَرِّقَنَّهُ ثُمَّ لَنَنسِفَنَّهُ فِي الْيَمِّ نَسْفًا ( 97 ) ጣሃ - Aya 97
አለው «ኺድ፤ ላንተም በሕይወትህ (ለአየኸው ሰው ሁሉ) መነካካት የለም ማለት አለህ፡፡ ለአንተም ፈጽሞ የማትጣሰው ቀጠሮ አለህ፡፡ ወደዚያም በእርሱ ላይ ተገዢው ኾነህ ወደ ቆየህበት አምላክህ ተመልከት፡፡ በእርግጥ እናቃጥለዋለን፡፡ ከዚያም በባሕሩ ውስጥ መበተንን እንበትነዋለን፡፡» ጣሃ - Aya 97
إِنَّمَا إِلَٰهُكُمُ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ وَسِعَ كُلَّ شَيْءٍ عِلْمًا ( 98 ) ጣሃ - Aya 98
ጌታችሁ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ የኾነው አላህ ብቻ ነው፡፡ እውቀቱ ነገርን ሁሉ አዳረሰ፡፡ ጣሃ - Aya 98
كَذَٰلِكَ نَقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنبَاءِ مَا قَدْ سَبَقَ ۚ وَقَدْ آتَيْنَاكَ مِن لَّدُنَّا ذِكْرًا ( 99 ) ጣሃ - Aya 99
እንደዚሁ በእርግጥ ካለፉት ወሬዎች ባንተ ላይ እንተርካለን፡፡ ከእኛም ዘንድ ቁረኣንን በእርግጥ ሰጠንህ፡፡ ጣሃ - Aya 99
مَّنْ أَعْرَضَ عَنْهُ فَإِنَّهُ يَحْمِلُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وِزْرًا ( 100 ) ጣሃ - Aya 100
ከእርሱ ያፈገፈገ ሰው እርሱ በትንሣኤ ቀን ከባድን ቅጣት ይሸከማል፡፡ ጣሃ - Aya 100
خَالِدِينَ فِيهِ ۖ وَسَاءَ لَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ حِمْلًا ( 101 ) ጣሃ - Aya 101
በእርሱ ውስጥ ዘውታሪዎች ኾነው (ይሸከማሉ)፡፡ በትንሣኤም ቀን ለእነሱ የኾነው ሸክም ከፋ! ጣሃ - Aya 101
يَوْمَ يُنفَخُ فِي الصُّورِ ۚ وَنَحْشُرُ الْمُجْرِمِينَ يَوْمَئِذٍ زُرْقًا ( 102 ) ጣሃ - Aya 102
በቀንዱ በሚነፋ ቀን (ሸክማቸው ከፋ)፤ ከሓዲዎችንም በዚያ ቀን (ዓይኖቻቸው) ሰማያዊዎች ሆነው እንሰበስባቸዋለን፡፡ ጣሃ - Aya 102
يَتَخَافَتُونَ بَيْنَهُمْ إِن لَّبِثْتُمْ إِلَّا عَشْرًا ( 103 ) ጣሃ - Aya 103
«ዐሥርን (ቀን) እንጂ አልቆያችሁም» በመባባል በመካከላቸው ይንሾካሾካሉ፡፡ ጣሃ - Aya 103
نَّحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَقُولُونَ إِذْ يَقُولُ أَمْثَلُهُمْ طَرِيقَةً إِن لَّبِثْتُمْ إِلَّا يَوْمًا ( 104 ) ጣሃ - Aya 104
በሐሳብ ቀጥተኛው «አንድን ቀን እንጅ አልቆያችሁም» በሚል ጊዜ የሚሉትን ነገር እኛ ዐዋቂዎች ነን፡፡ ጣሃ - Aya 104
وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الْجِبَالِ فَقُلْ يَنسِفُهَا رَبِّي نَسْفًا ( 105 ) ጣሃ - Aya 105
ከጋራዎችም ይጠይቁሃል፤ በላቸው «ጌታዬ መበተንን ይበትናቸዋል፡፡ ጣሃ - Aya 105
فَيَذَرُهَا قَاعًا صَفْصَفًا ( 106 ) ጣሃ - Aya 106
«ትክክል ሜዳም ኾና ይተዋታል፡፡ ጣሃ - Aya 106
لَّا تَرَىٰ فِيهَا عِوَجًا وَلَا أَمْتًا ( 107 ) ጣሃ - Aya 107
«በርሷ ዝቅታና ከፍታን አታይም፡፡» ጣሃ - Aya 107
يَوْمَئِذٍ يَتَّبِعُونَ الدَّاعِيَ لَا عِوَجَ لَهُ ۖ وَخَشَعَتِ الْأَصْوَاتُ لِلرَّحْمَٰنِ فَلَا تَسْمَعُ إِلَّا هَمْسًا ( 108 ) ጣሃ - Aya 108
በዚያ ቀን (ለመሰብሰብ) ጠሪውን ለእርሱ መጣመም የሌለውን መከተል ይከተላሉ፡፡ ድምጾችም ለአልረሕማን ጸጥ ይላሉ፡፡ ስለዚህ ሹክሹክታን እንጂ አትሰማም፡፡ ጣሃ - Aya 108
يَوْمَئِذٍ لَّا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ إِلَّا مَنْ أَذِنَ لَهُ الرَّحْمَٰنُ وَرَضِيَ لَهُ قَوْلًا ( 109 ) ጣሃ - Aya 109
በዚያ ቀን ለእርሱ አልረሕማን የፈቀደለትንና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ሰው ቢኾን እንጅ ምልጃ (አንድንም) አትጠቅምም፡፡ ጣሃ - Aya 109
يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يُحِيطُونَ بِهِ عِلْمًا ( 110 ) ጣሃ - Aya 110
በስተፊታቸው ያለውን በስተኋላቸውም ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በእርሱም ዕውቀትን አያካብቡም፤ (አያውቁም)፡፡ ጣሃ - Aya 110
وَعَنَتِ الْوُجُوهُ لِلْحَيِّ الْقَيُّومِ ۖ وَقَدْ خَابَ مَنْ حَمَلَ ظُلْمًا ( 111 ) ጣሃ - Aya 111
ፊቶችም ሁሉ ሕያው አስተናባሪ ለኾነው (አላህ) ተዋረዱ፡፡ በደልንም የተሸከመ ሰው በእርግጥ ከሰረ፡፡ ጣሃ - Aya 111
وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَا يَخَافُ ظُلْمًا وَلَا هَضْمًا ( 112 ) ጣሃ - Aya 112
እርሱ አማኝ ኾኖ ከመልካም ሥራዎችም የሠራ ሰው በደልንም መጉደልንም አይፈራም፡፡ ጣሃ - Aya 112
وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا وَصَرَّفْنَا فِيهِ مِنَ الْوَعِيدِ لَعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ أَوْ يُحْدِثُ لَهُمْ ذِكْرًا ( 113 ) ጣሃ - Aya 113
እንደዚሁም ዐረብኛ ቁርኣን ኾኖ አወረድነው፡፡ አላህንም ይፈሩ ዘንድ ወይም ለእነሱ ግሣጼን ያድስላቸው ዘንድ ከዛቻ ደጋግመን በውስጡ ገለጽን፡፡ ጣሃ - Aya 113
فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ ۗ وَلَا تَعْجَلْ بِالْقُرْآنِ مِن قَبْلِ أَن يُقْضَىٰ إِلَيْكَ وَحْيُهُ ۖ وَقُل رَّبِّ زِدْنِي عِلْمًا ( 114 ) ጣሃ - Aya 114
እውነተኛው ንጉስ አላህም (ከሓዲዎች ከሚሉት) ላቀ፡፡ ወደ አንተ መወረዱም ከመፈጸሙ በፊት በማንበብ አትቸኩል፡፡ «ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ» በል፡፡ ጣሃ - Aya 114
وَلَقَدْ عَهِدْنَا إِلَىٰ آدَمَ مِن قَبْلُ فَنَسِيَ وَلَمْ نَجِدْ لَهُ عَزْمًا ( 115 ) ጣሃ - Aya 115
ወደ አደምም ከዚህ በፊት ኪዳንን በእርግጥ አወረድን፡፡ ረሳም፡፡ ለእርሱም ቆራጥነትን አላገኘንለትም፡፡ ጣሃ - Aya 115
وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ أَبَىٰ ( 116 ) ጣሃ - Aya 116
ለመላእክትም ለአዳም ስገዱ ባልን ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ሰገዱም፤ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር እምቢ አለ፡፡ ጣሃ - Aya 116
فَقُلْنَا يَا آدَمُ إِنَّ هَٰذَا عَدُوٌّ لَّكَ وَلِزَوْجِكَ فَلَا يُخْرِجَنَّكُمَا مِنَ الْجَنَّةِ فَتَشْقَىٰ ( 117 ) ጣሃ - Aya 117
አልንም «አደም ሆይ! ይህ ላንተም ለሚስትህም በእርግጥ ጠላት ነው፡፡ ስለዚህ ከገነት አያውጣችሁ፤ ትለፋለህና፡፡ ጣሃ - Aya 117
إِنَّ لَكَ أَلَّا تَجُوعَ فِيهَا وَلَا تَعْرَىٰ ( 118 ) ጣሃ - Aya 118
ለአንተ በእርሷ ውስጥ አለመራብና አለመታረዝ አለህ፡፡ ጣሃ - Aya 118
وَأَنَّكَ لَا تَظْمَأُ فِيهَا وَلَا تَضْحَىٰ ( 119 ) ጣሃ - Aya 119
አንተም በርሷ ውስጥ አትጠማም፤ ፀሐይም አትተኮስም፡፡ ጣሃ - Aya 119
فَوَسْوَسَ إِلَيْهِ الشَّيْطَانُ قَالَ يَا آدَمُ هَلْ أَدُلُّكَ عَلَىٰ شَجَرَةِ الْخُلْدِ وَمُلْكٍ لَّا يَبْلَىٰ ( 120 ) ጣሃ - Aya 120
ሰይጣንም ወደርሱ ጎተጎተ «አደም ሆይ! በመዘውተሪያ ዛፍ በማይጠፋ ንግሥናም ላይ ላመላክትህን አለው፡፡ ጣሃ - Aya 120
فَأَكَلَا مِنْهَا فَبَدَتْ لَهُمَا سَوْآتُهُمَا وَطَفِقَا يَخْصِفَانِ عَلَيْهِمَا مِن وَرَقِ الْجَنَّةِ ۚ وَعَصَىٰ آدَمُ رَبَّهُ فَغَوَىٰ ( 121 ) ጣሃ - Aya 121
ከእርሷም በልሉ፡፡ ለእነርሱም ኀፍረተ ገላቸው ተገለጸች፡፡ ከገነትም ቅጠል በላያቸው ላይ ይለጥፉ ጀመር፡፡ አደምም የጌታውን ትእዛዝ (ረስቶ) ጣሰ፡፡ (ከፈለገው መዘውተር) ተሳሳተም፡፡ ጣሃ - Aya 121
ثُمَّ اجْتَبَاهُ رَبُّهُ فَتَابَ عَلَيْهِ وَهَدَىٰ ( 122 ) ጣሃ - Aya 122
ከዚያም ጌታው መረጠው ከእርሱም ጸጸቱን ተቀበለው መራውም፡፡ ጣሃ - Aya 122
قَالَ اهْبِطَا مِنْهَا جَمِيعًا ۖ بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ ۖ فَإِمَّا يَأْتِيَنَّكُم مِّنِّي هُدًى فَمَنِ اتَّبَعَ هُدَايَ فَلَا يَضِلُّ وَلَا يَشْقَىٰ ( 123 ) ጣሃ - Aya 123
አላቸው «ከፊላችሁም ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ሁላችሁም ከእርሷ ውረዱ ከእኔም የኾነ መሪ ቢመጣላችሁ መሪየን የተከተለ አይሳሳትም አይቸገርምም፡፡ ጣሃ - Aya 123
وَمَنْ أَعْرَضَ عَن ذِكْرِي فَإِنَّ لَهُ مَعِيشَةً ضَنكًا وَنَحْشُرُهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَعْمَىٰ ( 124 ) ጣሃ - Aya 124
«ከግሣጼዬም የዞረ ሰው ለእርሱ ጠባብ ኑሮ አለው፡፡ በትንሣኤም ቀን ዕውር ኾኖ እንቀሰቅሰዋለን፡፡ ጣሃ - Aya 124
قَالَ رَبِّ لِمَ حَشَرْتَنِي أَعْمَىٰ وَقَدْ كُنتُ بَصِيرًا ( 125 ) ጣሃ - Aya 125
«ጌታዬ ሆይ! ለምን ዕውር አድርገህ አስነሳኸኝ በእርግጥ የማይ የነበርኩ ስኾን» ይላል፡፡ ጣሃ - Aya 125
قَالَ كَذَٰلِكَ أَتَتْكَ آيَاتُنَا فَنَسِيتَهَا ۖ وَكَذَٰلِكَ الْيَوْمَ تُنسَىٰ ( 126 ) ጣሃ - Aya 126
(ነገሩ) እንደዚሁ ነው፡፡ «ታምራታችን መጣችልህ፡፡ ተውካትም፡፡ እንደዚሁም ዛሬ ትተዋለህ» ይለዋል፡፡ ጣሃ - Aya 126
وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي مَنْ أَسْرَفَ وَلَمْ يُؤْمِن بِآيَاتِ رَبِّهِ ۚ وَلَعَذَابُ الْآخِرَةِ أَشَدُّ وَأَبْقَىٰ ( 127 ) ጣሃ - Aya 127
እንደዚሁም ያጋራንና በጌታው አንቀጾች ያላመነን ሰው እንቀጣዋለን፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት በጣም ብርቱ ሁልጊዜ ዘውታሪም ነው፡፡ ጣሃ - Aya 127
أَفَلَمْ يَهْدِ لَهُمْ كَمْ أَهْلَكْنَا قَبْلَهُم مِّنَ الْقُرُونِ يَمْشُونَ فِي مَسَاكِنِهِمْ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّأُولِي النُّهَىٰ ( 128 ) ጣሃ - Aya 128
(ቁረይሾች) ከእነሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን ያጠፋን መኾናችን በመኖሪያዎቻቸው የሚኼዱ ኾነው ሳሉ ለእነርሱ አልተገለጸላቸውምን በዚህ ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች በእርግጥ መልክቶች አሉበት፡፡ ጣሃ - Aya 128
وَلَوْلَا كَلِمَةٌ سَبَقَتْ مِن رَّبِّكَ لَكَانَ لِزَامًا وَأَجَلٌ مُّسَمًّى ( 129 ) ጣሃ - Aya 129
ከጌታህ ያለፈች ቃልና የተወሰነ ጊዜ ባልነበረ ኖሮ (ቅጣቱ አሁኑኑ) የሚይዛቸው ይኾን ነበር፡፡ ጣሃ - Aya 129
فَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ قَبْلَ طُلُوعِ الشَّمْسِ وَقَبْلَ غُرُوبِهَا ۖ وَمِنْ آنَاءِ اللَّيْلِ فَسَبِّحْ وَأَطْرَافَ النَّهَارِ لَعَلَّكَ تَرْضَىٰ ( 130 ) ጣሃ - Aya 130
በሚሉትም ላይ ታገስ፡፡ ጌታህንም ፀሐይ ከመውጣትዋ በፊት ከመግባትዋም በፊት የምታመሰግን ኾነህ አጥራው፤ (ስገድ)፡፡ ከሌሊት ሰዓቶችም በቀን ጫፎችም አጥራው፡፡ (በሚሰጥህ ምንዳ) ልትወድ ይከጀላልና፡፡ ጣሃ - Aya 130
وَلَا تَمُدَّنَّ عَيْنَيْكَ إِلَىٰ مَا مَتَّعْنَا بِهِ أَزْوَاجًا مِّنْهُمْ زَهْرَةَ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا لِنَفْتِنَهُمْ فِيهِ ۚ وَرِزْقُ رَبِّكَ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ ( 131 ) ጣሃ - Aya 131
ዓይኖችህንም ከእነርሱ (ከሰዎቹ) ክፍሎችን በእርሱ ልንፈትናቸው ወደ አጣቀምንበት፤ ወደ ቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች አትዘርጋ፡፡ የጌታህ ሲሳይም በጣም በላጭ ዘውታሪም ነው፡፡ ጣሃ - Aya 131
وَأْمُرْ أَهْلَكَ بِالصَّلَاةِ وَاصْطَبِرْ عَلَيْهَا ۖ لَا نَسْأَلُكَ رِزْقًا ۖ نَّحْنُ نَرْزُقُكَ ۗ وَالْعَاقِبَةُ لِلتَّقْوَىٰ ( 132 ) ጣሃ - Aya 132
ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፡፡ በእርሷም ላይ ዘውትር፤(ጽና)፡፡ ሲሳይን አንጠይቅህም፡፡ እኛ እንሰጥሃለን፡፡ መልካሚቱ መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት፡፡ ጣሃ - Aya 132
وَقَالُوا لَوْلَا يَأْتِينَا بِآيَةٍ مِّن رَّبِّهِ ۚ أَوَلَمْ تَأْتِهِم بَيِّنَةُ مَا فِي الصُّحُفِ الْأُولَىٰ ( 133 ) ጣሃ - Aya 133
«ከጌታውም በኾነ ተዓምር አይመጣንምን» አሉ በመጀመሪያዎቹ ጽሑፎች ውስጥ ያለችው ማስረጃ አልመጣቻቸውምን ጣሃ - Aya 133
وَلَوْ أَنَّا أَهْلَكْنَاهُم بِعَذَابٍ مِّن قَبْلِهِ لَقَالُوا رَبَّنَا لَوْلَا أَرْسَلْتَ إِلَيْنَا رَسُولًا فَنَتَّبِعَ آيَاتِكَ مِن قَبْلِ أَن نَّذِلَّ وَنَخْزَىٰ ( 134 ) ጣሃ - Aya 134
እኛም ከእርሱ (ከሙሐመድ መላክ) በፊት በቅጣት ባጠፋናቸው ኖሮ «ጌታችን ሆይ! ከመዋረዳችንና ከማፈራችን በፊት አንቀጾችህን እንከተል ዘንድ ወደኛ መልከተኛን አትልክም ነበርን» ባሉ ነበር፡፡ ጣሃ - Aya 134
قُلْ كُلٌّ مُّتَرَبِّصٌ فَتَرَبَّصُوا ۖ فَسَتَعْلَمُونَ مَنْ أَصْحَابُ الصِّرَاطِ السَّوِيِّ وَمَنِ اهْتَدَىٰ ( 135 ) ጣሃ - Aya 135
«ሁሉም ተጠባባቂ ነው፡፡ ተጠባበቁም፡፡ የቀጥታውም መንገድ ባለቤቶች እነማን እንደሆኑ እነማንም እንደ ተመሩ ወደ ፊት ታውቃላችሁ» በላቸው፡፡ ጣሃ - Aya 135
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah