Surah አል ነምል

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ነምል - Aya count 93
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
طس ۚ تِلْكَ آيَاتُ الْقُرْآنِ وَكِتَابٍ مُّبِينٍ ( 1 ) አል ነምል - Aya 1
ጠ.ሰ (ጣ ሲን) ይህቺ ከቁርኣኑና ከገላጩ መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡ አል ነምል - Aya 1
هُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ ( 2 ) አል ነምል - Aya 2
ለምእምናን መሪና ብስራት ናት፡፡ አል ነምል - Aya 2
الَّذِينَ يُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَهُم بِالْآخِرَةِ هُمْ يُوقِنُونَ ( 3 ) አል ነምል - Aya 3
ለእነዚያ ሶላትን ለሚሰግዱት ዘካንም ለሚሰጡት እነሱም በመጨረሻይቱ ሕይወት እነሱ የሚያረጋግጡ ለኾኑት፡፡ አል ነምል - Aya 3
إِنَّ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ زَيَّنَّا لَهُمْ أَعْمَالَهُمْ فَهُمْ يَعْمَهُونَ ( 4 ) አል ነምል - Aya 4
እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ለእነሱ (ክፉ) ሥራዎቻቸውን ሸለምንላቸው፡፡ ስለዚህ እነርሱ ይዋልላሉ፡፡ አል ነምል - Aya 4
أُولَٰئِكَ الَّذِينَ لَهُمْ سُوءُ الْعَذَابِ وَهُمْ فِي الْآخِرَةِ هُمُ الْأَخْسَرُونَ ( 5 ) አል ነምል - Aya 5
እነርሱ እነዚያ ክፉ ቅጣት ለእነርሱ ያላቸው ናቸው፡፡ እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ በጣም ከሳሪዎቹ ናቸው፡፡ አል ነምል - Aya 5
وَإِنَّكَ لَتُلَقَّى الْقُرْآنَ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ عَلِيمٍ ( 6 ) አል ነምል - Aya 6
አንተም ቁርኣንን ጥበበኛና ዐዋቂ ከኾነው (ጌታህ) ዘንድ በእርግጥ ትስሰጣለህ፡፡ አል ነምል - Aya 6
إِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِأَهْلِهِ إِنِّي آنَسْتُ نَارًا سَآتِيكُم مِّنْهَا بِخَبَرٍ أَوْ آتِيكُم بِشِهَابٍ قَبَسٍ لَّعَلَّكُمْ تَصْطَلُونَ ( 7 ) አል ነምል - Aya 7
ሙሳ ለቤተሰቦቹ «እኔ እሳትን አየሁ፡፡ ከእርሷ ወሬን አመጣላችኋለሁ፡፡ ወይም ትሞቁ ዘንድ የተለኮሰ ችቦን አመጣላችኋለሁ» ባለ ጊዜ (የኾነውን አውሳላቸው)፡፡ አል ነምል - Aya 7
فَلَمَّا جَاءَهَا نُودِيَ أَن بُورِكَ مَن فِي النَّارِ وَمَنْ حَوْلَهَا وَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ ( 8 ) አል ነምል - Aya 8
በመጣትም ጊዜ እንዲህ በማለት ተጠራ፤ «በእሳቲቱ ያለው ሰውና በዙሪያዋ ያሉም ሁሉ ተባረኩ፡፡ የዐለማትም ጌታ አላህ ጥራት ይገባው፡፡» አል ነምል - Aya 8
يَا مُوسَىٰ إِنَّهُ أَنَا اللَّهُ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ ( 9 ) አል ነምል - Aya 9
«ሙሳ ሆይ! እነሆ እኔ አሸናፊው ጥበበኛው አላህ ነኝ፡፡ አል ነምል - Aya 9
وَأَلْقِ عَصَاكَ ۚ فَلَمَّا رَآهَا تَهْتَزُّ كَأَنَّهَا جَانٌّ وَلَّىٰ مُدْبِرًا وَلَمْ يُعَقِّبْ ۚ يَا مُوسَىٰ لَا تَخَفْ إِنِّي لَا يَخَافُ لَدَيَّ الْمُرْسَلُونَ ( 10 ) አል ነምል - Aya 10
«በትርህንም ጣል» (ተባለ ጣለም)፡፡ እርሷ እንደ ትንሽ እባብ በፍጥነት ስትስለከለክ ባያትም ጊዜ፤ ወደ ኋላ ዞሮ ሸሸ፡፡ አልተመለሰምም፡፡ «ሙሳ ሆይ! አትፈራ፤ እኔ መልክተኞቹ እኔ ዘንድ አይፈሩምና፡፡ አል ነምል - Aya 10
إِلَّا مَن ظَلَمَ ثُمَّ بَدَّلَ حُسْنًا بَعْدَ سُوءٍ فَإِنِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ ( 11 ) አል ነምል - Aya 11
«ግን የበደለ ሰው ከዚያም ከመጥፎ ሥራው በኋላ መልካምን የለወጠ እኔ መሓሪ አዛኝ ነኝ፡፡ አል ነምል - Aya 11
وَأَدْخِلْ يَدَكَ فِي جَيْبِكَ تَخْرُجْ بَيْضَاءَ مِنْ غَيْرِ سُوءٍ ۖ فِي تِسْعِ آيَاتٍ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَقَوْمِهِ ۚ إِنَّهُمْ كَانُوا قَوْمًا فَاسِقِينَ ( 12 ) አል ነምል - Aya 12
«እጅህንም በአንገትጌህ ውስጥ አግባ፡፡ ያለነውር (ያለ ለምጽ) ነጭ ኾና ትወጣለችና፡፡ በዘጠኝ ተዓምራት ወደ ፈርዖንና ወደ ሕዝቦቹ (ኺድ)፡፡ እነርሱ አመጸኞች ሕዝቦች ናቸውና፡፡ አል ነምል - Aya 12
فَلَمَّا جَاءَتْهُمْ آيَاتُنَا مُبْصِرَةً قَالُوا هَٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ ( 13 ) አል ነምል - Aya 13
ተዓምራታችንም ግልጽ ኾና በመጣቻቸው ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡ አል ነምል - Aya 13
وَجَحَدُوا بِهَا وَاسْتَيْقَنَتْهَا أَنفُسُهُمْ ظُلْمًا وَعُلُوًّا ۚ فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُفْسِدِينَ ( 14 ) አል ነምል - Aya 14
ነፍሶቻቸውም ያረጋገጧት ሲኾኑ ለበደልና ለኩራት በእርሷ ካዱ፡፡ የአመጸኞችም ፍጻሜ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት፡፡ አል ነምል - Aya 14
وَلَقَدْ آتَيْنَا دَاوُودَ وَسُلَيْمَانَ عِلْمًا ۖ وَقَالَا الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي فَضَّلَنَا عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّنْ عِبَادِهِ الْمُؤْمِنِينَ ( 15 ) አል ነምል - Aya 15
ለዳውድና ለሱለይማንም ዕውቀትን በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡ አሉም፡- «ምስጋና ለአላህ ለእዚያ ከምእምናን ባሮቹ በብዙዎቹ ላይ ላበለጠን ይገባው፡፡» አል ነምል - Aya 15
وَوَرِثَ سُلَيْمَانُ دَاوُودَ ۖ وَقَالَ يَا أَيُّهَا النَّاسُ عُلِّمْنَا مَنطِقَ الطَّيْرِ وَأُوتِينَا مِن كُلِّ شَيْءٍ ۖ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ الْفَضْلُ الْمُبِينُ ( 16 ) አል ነምል - Aya 16
ሱለይማንም ዳውድን ወረሰ፡፡ አለም «ሰዎች ሆይ! የበራሪን ንግግር (የወፍን ቋንቋ) ተስተማርን፡፡ ከነገሩም ሁሉ ተሰጠን፡፡ ይህ እርሱ በእርግጥ ግልጽ የኾነ ችሮታ ነው፡፡» አል ነምል - Aya 16
وَحُشِرَ لِسُلَيْمَانَ جُنُودُهُ مِنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ وَالطَّيْرِ فَهُمْ يُوزَعُونَ ( 17 ) አል ነምል - Aya 17
ለሱለይማንም ሰራዊቶቹ ከጋኔን፣ ከሰውም፣ ከበራሪም የኾኑት ተሰበሰቡ፡፡ እነሱም ይከመከማሉ፡፡ አል ነምል - Aya 17
حَتَّىٰ إِذَا أَتَوْا عَلَىٰ وَادِ النَّمْلِ قَالَتْ نَمْلَةٌ يَا أَيُّهَا النَّمْلُ ادْخُلُوا مَسَاكِنَكُمْ لَا يَحْطِمَنَّكُمْ سُلَيْمَانُ وَجُنُودُهُ وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ ( 18 ) አል ነምል - Aya 18
በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን «እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ፡፡ ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑ አይሰባብሩዋችሁ» አለች፡፡ አል ነምል - Aya 18
فَتَبَسَّمَ ضَاحِكًا مِّن قَوْلِهَا وَقَالَ رَبِّ أَوْزِعْنِي أَنْ أَشْكُرَ نِعْمَتَكَ الَّتِي أَنْعَمْتَ عَلَيَّ وَعَلَىٰ وَالِدَيَّ وَأَنْ أَعْمَلَ صَالِحًا تَرْضَاهُ وَأَدْخِلْنِي بِرَحْمَتِكَ فِي عِبَادِكَ الصَّالِحِينَ ( 19 ) አል ነምል - Aya 19
ከንግግርዋም እየሳቀ ጥርሱን ፈገግ አደረገ፡፡ «ጌታዬ ሆይ! ያቺን በእኔና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን የምትወደውንም በጎ ሥራ እንድሠራ ምራኝ፡፡ በችሮታህም በመልካሞቹ ባሮችህ ውስጥ አግባኝ» አለ፡፡ አል ነምል - Aya 19
وَتَفَقَّدَ الطَّيْرَ فَقَالَ مَا لِيَ لَا أَرَى الْهُدْهُدَ أَمْ كَانَ مِنَ الْغَائِبِينَ ( 20 ) አል ነምል - Aya 20
በራሪዎቹንም ተመለከተ፤ አለም «ሁድሁድን ለምን አላየውም! በእውነቱ ከራቁት ነበርን፡፡ አል ነምል - Aya 20
لَأُعَذِّبَنَّهُ عَذَابًا شَدِيدًا أَوْ لَأَذْبَحَنَّهُ أَوْ لَيَأْتِيَنِّي بِسُلْطَانٍ مُّبِينٍ ( 21 ) አል ነምል - Aya 21
«ብርቱን ቅጣት በእርግጥ እቀጣዋለሁ፡፡ ወይም በእርግጥ ዐርደዋለሁ፤ ወይም ግልጽ በኾነ አስረጅ ይመጣኛል» (አለ) አል ነምል - Aya 21
فَمَكَثَ غَيْرَ بَعِيدٍ فَقَالَ أَحَطتُ بِمَا لَمْ تُحِطْ بِهِ وَجِئْتُكَ مِن سَبَإٍ بِنَبَإٍ يَقِينٍ ( 22 ) አል ነምል - Aya 22
(ወፉ) ዕሩቅ ያልኾነንም ጊዜ ቆዬ፡፡ አለም «ያላወቅከውን ነገር አወቅኩ፡፡ ከሰበእም እርግጠኛን ወሬ አመጣሁልህ፡፡ አል ነምል - Aya 22
إِنِّي وَجَدتُّ امْرَأَةً تَمْلِكُهُمْ وَأُوتِيَتْ مِن كُلِّ شَيْءٍ وَلَهَا عَرْشٌ عَظِيمٌ ( 23 ) አል ነምል - Aya 23
«እኔ የምትገዛቸው የኾኑችን ሴት ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችኝ አገኘሁ፡፡ ለእርሷም ታላቅ ዙፋን አልላት፡፡ አል ነምል - Aya 23
وَجَدتُّهَا وَقَوْمَهَا يَسْجُدُونَ لِلشَّمْسِ مِن دُونِ اللَّهِ وَزَيَّنَ لَهُمُ الشَّيْطَانُ أَعْمَالَهُمْ فَصَدَّهُمْ عَنِ السَّبِيلِ فَهُمْ لَا يَهْتَدُونَ ( 24 ) አል ነምል - Aya 24
«እርስዋንም ሕዝቦችዋንም ከአላህ ሌላ ለፀሐይ ሲሰግዱ አገኘኋቸው፡፡ ሰይጣንም ለእነሱ ሥራዎቻቸውን ሸልሞላቸዋል፡፡ ከእውነተኛውም መንገድ አግዷቸዋል፡፡ ስለዚህ እነሱ (ወደ እውነት) አይምመሩም፡፡» አል ነምል - Aya 24
أَلَّا يَسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي يُخْرِجُ الْخَبْءَ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَيَعْلَمُ مَا تُخْفُونَ وَمَا تُعْلِنُونَ ( 25 ) አል ነምል - Aya 25
ለዚያ በሰማያትና በምድር የተደበቀውን ለሚያወጣው፣ የምትሸሽጉትንና የምትገ ልጹትንም ሁሉ ለሚያውቀው አላህ እንዳይሰግዱ (ሰይጣን አግዷቸዋል)፡፡ አል ነምል - Aya 25
اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ ۩ ( 26 ) አል ነምል - Aya 26
አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የታላቁ ዐርሽ (ዙፋን) ጌታ ነው፡፡ አል ነምል - Aya 26
قَالَ سَنَنظُرُ أَصَدَقْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ الْكَاذِبِينَ ( 27 ) አል ነምል - Aya 27
(ሱለይማንም) አለ «እውነት እንደ ተናገርክ ወይም ከውሸታሞቹ እንደ ኾንክ ወደፊት እናያለን፡፡ አል ነምል - Aya 27
اذْهَب بِّكِتَابِي هَٰذَا فَأَلْقِهْ إِلَيْهِمْ ثُمَّ تَوَلَّ عَنْهُمْ فَانظُرْ مَاذَا يَرْجِعُونَ ( 28 ) አል ነምል - Aya 28
«ይህንን ደብዳቤዬን ይዘህ ኺድ፡፡ ወደእነርሱም ጣለው፡፡ ከዚያም ከእነሱ ዘወር በል፡፡ ምን አንደሚመልሱም ተመልከት፡፡» አል ነምል - Aya 28
قَالَتْ يَا أَيُّهَا الْمَلَأُ إِنِّي أُلْقِيَ إِلَيَّ كِتَابٌ كَرِيمٌ ( 29 ) አል ነምል - Aya 29
(እርሷም በደረሳት ጊዜ) አለች «እናንተ መማክርቶች ሆይ! እኔ ክብር ያለው ጽሑፍ ወደኔ ተጣለ፡፡ አል ነምል - Aya 29
إِنَّهُ مِن سُلَيْمَانَ وَإِنَّهُ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ ( 30 ) አል ነምል - Aya 30
«እርሱ ከሱለይማን ነው፡፡ እርሱም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡ አል ነምል - Aya 30
أَلَّا تَعْلُوا عَلَيَّ وَأْتُونِي مُسْلِمِينَ ( 31 ) አል ነምል - Aya 31
«በእኔ ላይ አትኩሩ፡፡ ታዛዦችም ኾናችሁ ወደኔ ኑ፤ (የሚል ነው)፡፡ አል ነምል - Aya 31
قَالَتْ يَا أَيُّهَا الْمَلَأُ أَفْتُونِي فِي أَمْرِي مَا كُنتُ قَاطِعَةً أَمْرًا حَتَّىٰ تَشْهَدُونِ ( 32 ) አል ነምል - Aya 32
«እናንተ መማክርቶች ሆይ! በነገሬ (የሚበጀውን) ንገሩኝ፡፡ እስከምትገኙልኝ ድረስ አንድንም ነገር ቆራጭ አይደለሁምና» አለች፡፡ አል ነምል - Aya 32
قَالُوا نَحْنُ أُولُو قُوَّةٍ وَأُولُو بَأْسٍ شَدِيدٍ وَالْأَمْرُ إِلَيْكِ فَانظُرِي مَاذَا تَأْمُرِينَ ( 33 ) አል ነምል - Aya 33
«እኛ የኀይል ባለቤቶች የብርቱ ጦርም ባለቤቶች ነን፡፡ ግን ትዕዛዙ ወደ አንቺ ነው፡፡ ምን እንደምታዢም አስተውዪ፤» አሏት፡፡ አል ነምል - Aya 33
قَالَتْ إِنَّ الْمُلُوكَ إِذَا دَخَلُوا قَرْيَةً أَفْسَدُوهَا وَجَعَلُوا أَعِزَّةَ أَهْلِهَا أَذِلَّةً ۖ وَكَذَٰلِكَ يَفْعَلُونَ ( 34 ) አል ነምል - Aya 34
(እርሷም) አለች «ንጉሦች ከተማን (በኀይል) በገቡባት ጊዜ ያበላሹዋታል፡፡ የተከበሩ ሰዎችዋንም ወራዶች ያደርጋሉ፡፡ እንደዚሁም (እነዚህ) ይሠራሉ፡፡ አል ነምል - Aya 34
وَإِنِّي مُرْسِلَةٌ إِلَيْهِم بِهَدِيَّةٍ فَنَاظِرَةٌ بِمَ يَرْجِعُ الْمُرْسَلُونَ ( 35 ) አል ነምል - Aya 35
«እኔም ወደእነርሱ ገጸ በረከትን የምልክና መልክተኞቹ በምን እንደሚመለሱ የምጠባበቅ ነኝ፡፡» አል ነምል - Aya 35
فَلَمَّا جَاءَ سُلَيْمَانَ قَالَ أَتُمِدُّونَنِ بِمَالٍ فَمَا آتَانِيَ اللَّهُ خَيْرٌ مِّمَّا آتَاكُم بَلْ أَنتُم بِهَدِيَّتِكُمْ تَفْرَحُونَ ( 36 ) አል ነምል - Aya 36
(መልክተኛው) ሱለይማንንም በመጣው ጊዜ አለ «በገንዘብ ትረዱኛላችሁን አላህም የሰጠኝ ከሰጣችሁ የበለጠ ነው፡፡ ይልቁንም እናንተ በገጸ በረከታችሁ ትደሰታላችሁ፡፡» አል ነምል - Aya 36
ارْجِعْ إِلَيْهِمْ فَلَنَأْتِيَنَّهُم بِجُنُودٍ لَّا قِبَلَ لَهُم بِهَا وَلَنُخْرِجَنَّهُم مِّنْهَا أَذِلَّةً وَهُمْ صَاغِرُونَ ( 37 ) አል ነምል - Aya 37
«ወደእነሱ ተመለስ፡፡ ለእነርሱም በእርሷ ችሎታ በሌላቸው ሰራዊት እንመጣባቸዋለን፡፡ ከእርሷም እነርሱ የተዋረዱ ኾነው በእርግጥ እናወጣቸዋለን» (አለ)፡፡ አል ነምል - Aya 37
قَالَ يَا أَيُّهَا الْمَلَأُ أَيُّكُمْ يَأْتِينِي بِعَرْشِهَا قَبْلَ أَن يَأْتُونِي مُسْلِمِينَ ( 38 ) አል ነምል - Aya 38
«እናንተ መኳንንቶች ሆይ! ሙስሊሞች ኾነው ሳይመጡኝ በፊት ዙፋንዋን የሚያመጣልኝ ማንኛችሁ ነው» አለ፡፡ አል ነምል - Aya 38
قَالَ عِفْرِيتٌ مِّنَ الْجِنِّ أَنَا آتِيكَ بِهِ قَبْلَ أَن تَقُومَ مِن مَّقَامِكَ ۖ وَإِنِّي عَلَيْهِ لَقَوِيٌّ أَمِينٌ ( 39 ) አል ነምል - Aya 39
ከጋኔን ኀይለኛው «ከችሎትህ ከመነሳትህ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ፡፡ እኔም በእርሱ ላይ ብርቱ ታማኝ ነኝ» አለ፡፡ አል ነምል - Aya 39
قَالَ الَّذِي عِندَهُ عِلْمٌ مِّنَ الْكِتَابِ أَنَا آتِيكَ بِهِ قَبْلَ أَن يَرْتَدَّ إِلَيْكَ طَرْفُكَ ۚ فَلَمَّا رَآهُ مُسْتَقِرًّا عِندَهُ قَالَ هَٰذَا مِن فَضْلِ رَبِّي لِيَبْلُوَنِي أَأَشْكُرُ أَمْ أَكْفُرُ ۖ وَمَن شَكَرَ فَإِنَّمَا يَشْكُرُ لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ رَبِّي غَنِيٌّ كَرِيمٌ ( 40 ) አል ነምል - Aya 40
ያ እርሱ ዘንድ ከመጽሐፉ ዕውቀት ያለው ሰው (የተገለጸው) «ዓይንህ ወደ አንተ ከመመለሱ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ» አለ፤ (እንደዚሁም አደረገ)፡፡ እርሱ ዘንድ ረግቶ ባየውም ጊዜ «ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው፡፡ የማመሰግን ወይም የምክድ መኾኔን ሊሞክረኝ (ቸረልኝ)፡፡ ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ነው፡፡ የካደም ሰው ጌታዬ ከእርሱ ተብቃቂ ቸር ነው» አለ፡፡ አል ነምል - Aya 40
قَالَ نَكِّرُوا لَهَا عَرْشَهَا نَنظُرْ أَتَهْتَدِي أَمْ تَكُونُ مِنَ الَّذِينَ لَا يَهْتَدُونَ ( 41 ) አል ነምል - Aya 41
«ዙፋንዋን ለእርሷ አሳስቱ፡፡ ታውቀው እንደኾነ ወይም ከእነዚያ ከማያወቁት ትኾን እንደሆነ፤ እናያለን፤» አላቸው፡፡ አል ነምል - Aya 41
فَلَمَّا جَاءَتْ قِيلَ أَهَٰكَذَا عَرْشُكِ ۖ قَالَتْ كَأَنَّهُ هُوَ ۚ وَأُوتِينَا الْعِلْمَ مِن قَبْلِهَا وَكُنَّا مُسْلِمِينَ ( 42 ) አል ነምል - Aya 42
በመጣች ጊዜ፡- «ዙፋንሽ እንደዚህ ነውን» ተባለች፡፡ «እርሱ ልክ እርሱ ነው መሰለኝ» አለች፡፡ (ሱለይማን) «ከእርሷ በፊትም ዕውቀትን ተሰጠን ሙስሊሞችም ነበርን፤» (አለ)፡፡ አል ነምል - Aya 42
وَصَدَّهَا مَا كَانَت تَّعْبُدُ مِن دُونِ اللَّهِ ۖ إِنَّهَا كَانَتْ مِن قَوْمٍ كَافِرِينَ ( 43 ) አል ነምል - Aya 43
ከአላህ ሌላ ትግገዛው የነበረችውንም ከለከላት፡፡ እርሷ ከከሓዲዎች ሕዝቦች ነበረችና፡፡ አል ነምል - Aya 43
قِيلَ لَهَا ادْخُلِي الصَّرْحَ ۖ فَلَمَّا رَأَتْهُ حَسِبَتْهُ لُجَّةً وَكَشَفَتْ عَن سَاقَيْهَا ۚ قَالَ إِنَّهُ صَرْحٌ مُّمَرَّدٌ مِّن قَوَارِيرَ ۗ قَالَتْ رَبِّ إِنِّي ظَلَمْتُ نَفْسِي وَأَسْلَمْتُ مَعَ سُلَيْمَانَ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ ( 44 ) አል ነምል - Aya 44
ሕንጻውን ግቢ ተባለች፡፡ ባየቺውም ጊዜ ባሕር ነው ብላ ጠረጠረችው፡፡ ከባቶችዋም ገለጠች፡፡ «እርሱ ከመስተዋት የተለሰለሰ ሕንጻ ነው» አላት፡፡ «ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ፡፡ ከሱለይማንም ጋር ሆኜ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ታዘዝኩ» አለች፡፡ አል ነምል - Aya 44
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا إِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ فَإِذَا هُمْ فَرِيقَانِ يَخْتَصِمُونَ ( 45 ) አል ነምል - Aya 45
ወደ ሰሙድም ወንድማቸውን ሷሊሕን አላህን ተገዙ በማለት በእርግጥ ላክነው፡፡ ወዲያውም እነሱ የሚነታረኩ ሁለት ጭፍሮች ኾኑ፡፡ አል ነምል - Aya 45
قَالَ يَا قَوْمِ لِمَ تَسْتَعْجِلُونَ بِالسَّيِّئَةِ قَبْلَ الْحَسَنَةِ ۖ لَوْلَا تَسْتَغْفِرُونَ اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ ( 46 ) አል ነምል - Aya 46
«ሕዝቦቼ ሆይ! ከመልካሙ በፊት በክፉው (ቅጣትን አምጣብን በማለት) ለምን ታስቸኩላላችሀ ይታዘንላችሁ ዘንድ አላህን ምሕረትን አትለምኑምን» አላቸው፡፡ አል ነምል - Aya 46
قَالُوا اطَّيَّرْنَا بِكَ وَبِمَن مَّعَكَ ۚ قَالَ طَائِرُكُمْ عِندَ اللَّهِ ۖ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ تُفْتَنُونَ ( 47 ) አል ነምል - Aya 47
«ባንተና ከአንተም ጋር ባሉት ሰዎች ምክንያት ገደቢሶች ኾን» አሉት፡፡ «ገደቢስነታችሁ አላህ ዘንድ ነው፤ ይልቁንም እናንተ የምትፈተኑ ሕዝቦች ናችሁ» አላቸው፡፡ አል ነምል - Aya 47
وَكَانَ فِي الْمَدِينَةِ تِسْعَةُ رَهْطٍ يُفْسِدُونَ فِي الْأَرْضِ وَلَا يُصْلِحُونَ ( 48 ) አል ነምል - Aya 48
በከተማይቱም ውስጥ በምድር ውስጥ የሚያበላሹና የማያሳምሩ ዘጠኝ ሰዎች ነበሩ፡፡ አል ነምል - Aya 48
قَالُوا تَقَاسَمُوا بِاللَّهِ لَنُبَيِّتَنَّهُ وَأَهْلَهُ ثُمَّ لَنَقُولَنَّ لِوَلِيِّهِ مَا شَهِدْنَا مَهْلِكَ أَهْلِهِ وَإِنَّا لَصَادِقُونَ ( 49 ) አል ነምል - Aya 49
«እርሱንና ቤተሰቦቹን ሌሊት ልንገድል ከዚያም ለዘመዱ የቤተሰቦቹን ጥፋት (መገደላቸውን) አላየንም፤ እኛም እውነተኞች ነን ልንል በአላህ ተማማሉ» አሉ፡፡ አል ነምል - Aya 49
وَمَكَرُوا مَكْرًا وَمَكَرْنَا مَكْرًا وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ ( 50 ) አል ነምል - Aya 50
ተንኮልንም መከሩ፡፡ እነርሱም የማያወቁ ሲኾኑ በተንኮላቸው አጠፋናቸው፡፡ አል ነምል - Aya 50
فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ مَكْرِهِمْ أَنَّا دَمَّرْنَاهُمْ وَقَوْمَهُمْ أَجْمَعِينَ ( 51 ) አል ነምል - Aya 51
የተንኮላቸውም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ እኛ እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም በሙሉ እንዴት እንዳጠፋናቸው ተመልከት፡፡ አል ነምል - Aya 51
فَتِلْكَ بُيُوتُهُمْ خَاوِيَةً بِمَا ظَلَمُوا ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَعْلَمُونَ ( 52 ) አል ነምል - Aya 52
እኚህም በበደላቸው ምክንያት ባዶዎች ሲሆኑ ቤቶቻቸው ናቸው፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያወቁ ሕዝቦች አስደናቂ ተዓምር አለበት፡፡ አል ነምል - Aya 52
وَأَنجَيْنَا الَّذِينَ آمَنُوا وَكَانُوا يَتَّقُونَ ( 53 ) አል ነምል - Aya 53
እነዚያንም ያመኑትንና ከክሕደት ይጠነቀቁ የነበሩትን አዳን፡፡ አል ነምል - Aya 53
وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ وَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ ( 54 ) አል ነምል - Aya 54
ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ «እናንተ የምታዩ ስትኾኑ ፀያፍን ነገር ትሠራላችሁን አል ነምል - Aya 54
أَئِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الرِّجَالَ شَهْوَةً مِّن دُونِ النِّسَاءِ ۚ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ ( 55 ) አል ነምል - Aya 55
«እናንተ ከሴቶች አልፋችሁ ወንዶችን ለመከጀል ትመጣላችሁን በእውነቱ እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናቸሁ፡፡» አል ነምል - Aya 55
فَمَا كَانَ جَوَابَ قَوْمِهِ إِلَّا أَن قَالُوا أَخْرِجُوا آلَ لُوطٍ مِّن قَرْيَتِكُمْ ۖ إِنَّهُمْ أُنَاسٌ يَتَطَهَّرُونَ ( 56 ) አል ነምል - Aya 56
የሕዝቦቹም መልስ የሉጥን ቤተሰቦች «ከከተማችሁ አውጡ፡፡ እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና» ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም፡፡ አል ነምል - Aya 56
فَأَنجَيْنَاهُ وَأَهْلَهُ إِلَّا امْرَأَتَهُ قَدَّرْنَاهَا مِنَ الْغَابِرِينَ ( 57 ) አል ነምል - Aya 57
እርሱንና ቤተሰቦቹንም አዳን፡፡ ሚስቱ፤ ብቻ ስትቀር፡፡ (በጥፋቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ አደረግናት፡፡ አል ነምል - Aya 57
وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا ۖ فَسَاءَ مَطَرُ الْمُنذَرِينَ ( 58 ) አል ነምል - Aya 58
በእነርሱም ላይ (የድንጋይ) ዝናብን አዘነብንባቸው፡፡ የተስፈራሪዎቹም ዝናብ ከፋ፡፡ አል ነምል - Aya 58
قُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ وَسَلَامٌ عَلَىٰ عِبَادِهِ الَّذِينَ اصْطَفَىٰ ۗ آللَّهُ خَيْرٌ أَمَّا يُشْرِكُونَ ( 59 ) አል ነምል - Aya 59
(ሙሐመድ ሆይ) በል «ምስጋና ለአላህ ይግባው፡፡ በእነዚያም በመረጣቸው ባሮቹ ላይ ሰላም ይውረድ፡፡ አላህ በላጭ ነውን ወይስ ያ የሚያጋሩት (ጣዖት)፡፡ አል ነምል - Aya 59
أَمَّنْ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَأَنزَلَ لَكُم مِّنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَنبَتْنَا بِهِ حَدَائِقَ ذَاتَ بَهْجَةٍ مَّا كَانَ لَكُمْ أَن تُنبِتُوا شَجَرَهَا ۗ أَإِلَٰهٌ مَّعَ اللَّهِ ۚ بَلْ هُمْ قَوْمٌ يَعْدِلُونَ ( 60 ) አል ነምል - Aya 60
ወይም ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረና ከሰማይም ለእናንተ ውሃን ያወረደው (ይበልጣል ወይስ የሚያጋሩት) በእርሱም ባለውበት የኾኑትን የታጠሩ አትክልቶችን ዛፍዋን ልታበቅሉ ለናንተ ችሎታ ያልነበራችሁን አበቀልን፡፡ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን (የለም)፡፡ ግን እነርሱ (ከእውነት) የሚያዘነብሉ ሕዝቦች ናቸው፡፡ አል ነምል - Aya 60
أَمَّن جَعَلَ الْأَرْضَ قَرَارًا وَجَعَلَ خِلَالَهَا أَنْهَارًا وَجَعَلَ لَهَا رَوَاسِيَ وَجَعَلَ بَيْنَ الْبَحْرَيْنِ حَاجِزًا ۗ أَإِلَٰهٌ مَّعَ اللَّهِ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ ( 61 ) አል ነምል - Aya 61
ወይም ያ ምድርን መርጊያ ያደረገና በመካከሏም ወንዞችን ያደረገ፣ ለእርሷም ጋራዎችን ያደረገ፣ በሁለቱ ባሕሮችም (በጣፋጩና በጨው ባሕር) መካከል ግርዶን ያደረገ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ አል ነምል - Aya 61
أَمَّن يُجِيبُ الْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكْشِفُ السُّوءَ وَيَجْعَلُكُمْ خُلَفَاءَ الْأَرْضِ ۗ أَإِلَٰهٌ مَّعَ اللَّهِ ۚ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ ( 62 ) አል ነምል - Aya 62
ወይም ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደረጋችሁ፤ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን ጥቂትንም አትገሠጹም፡፡ አል ነምል - Aya 62
أَمَّن يَهْدِيكُمْ فِي ظُلُمَاتِ الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَمَن يُرْسِلُ الرِّيَاحَ بُشْرًا بَيْنَ يَدَيْ رَحْمَتِهِ ۗ أَإِلَٰهٌ مَّعَ اللَّهِ ۚ تَعَالَى اللَّهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ ( 63 ) አል ነምል - Aya 63
ወይም ያ በየብስና በባሕር ጨለማዎች ውስጥ የሚመራችሁ ነፋሶችንም ከዝናሙ በፊት አብሳሪ ኾነው የሚልክ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን አላህ (በእርሱ) ከሚያጋሩዋቸው ሁሉ ላቀ፡፡ አል ነምል - Aya 63
أَمَّن يَبْدَأُ الْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُ وَمَن يَرْزُقُكُم مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ ۗ أَإِلَٰهٌ مَّعَ اللَّهِ ۚ قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ ( 64 ) አል ነምል - Aya 64
ወይም ያ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም የሚመልሰው ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አምላክ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን «እውነተኞች እንደኾናችሁ፤ አስረጃችሁን አምጡ» በላቸው፡፡ አል ነምል - Aya 64
قُل لَّا يَعْلَمُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ الْغَيْبَ إِلَّا اللَّهُ ۚ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ ( 65 ) አል ነምል - Aya 65
«በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም፡፡ ግን አላህ (ያውቀዋል)፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም» በላቸው፡፡ አል ነምል - Aya 65
بَلِ ادَّارَكَ عِلْمُهُمْ فِي الْآخِرَةِ ۚ بَلْ هُمْ فِي شَكٍّ مِّنْهَا ۖ بَلْ هُم مِّنْهَا عَمُونَ ( 66 ) አል ነምል - Aya 66
በእውነት የመጨረሻይቱን ዓለም (ኹኔታ) ማወቃቸው ተሟላን አይደለም እነርሱ ከእርሷ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ በእውነትም እነርሱ ከእርሷ ዕውሮች ናቸው፡፡ አል ነምል - Aya 66
وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَإِذَا كُنَّا تُرَابًا وَآبَاؤُنَا أَئِنَّا لَمُخْرَجُونَ ( 67 ) አል ነምል - Aya 67
እነዚያም የካዱት አሉ «እኛም አባቶቻችንም ዐፈር በኾን ጊዜ እኛ (ከመቃብር) የምንወጣ ነን አል ነምል - Aya 67
لَقَدْ وُعِدْنَا هَٰذَا نَحْنُ وَآبَاؤُنَا مِن قَبْلُ إِنْ هَٰذَا إِلَّا أَسَاطِيرُ الْأَوَّلِينَ ( 68 ) አል ነምል - Aya 68
«ይህንን እኛም ከፊት የነበሩት አባቶቻችንም በእርግጥ ተቀጥረንበታል፡፡ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጅ ሌላ አይደለም» (አሉ)፡፡ አል ነምል - Aya 68
قُلْ سِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَانظُرُوا كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُجْرِمِينَ ( 69 ) አል ነምል - Aya 69
«በምድር ላይ ኺዱ፡፡ የአመጸኞችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከቱ» በላቸው፡፡ አል ነምል - Aya 69
وَلَا تَحْزَنْ عَلَيْهِمْ وَلَا تَكُن فِي ضَيْقٍ مِّمَّا يَمْكُرُونَ ( 70 ) አል ነምል - Aya 70
በእነሱም ላይ አትዘን፡፡ ከሚመክሩብህም ነገር በጭንቀት ውስጥ አትኹን፡፡ አል ነምል - Aya 70
وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا الْوَعْدُ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ ( 71 ) አል ነምል - Aya 71
«እውነተኞችም እንደ ኾናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው» ይላሉ፡፡ አል ነምል - Aya 71
قُلْ عَسَىٰ أَن يَكُونَ رَدِفَ لَكُم بَعْضُ الَّذِي تَسْتَعْجِلُونَ ( 72 ) አል ነምል - Aya 72
«የዚያ የምትቻኮሉበት ከፊሉ ለእናንተ የቀረበ መኾኑ ተረጋግጧል» በላቸው፡፡ አል ነምል - Aya 72
وَإِنَّ رَبَّكَ لَذُو فَضْلٍ عَلَى النَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَشْكُرُونَ ( 73 ) አል ነምል - Aya 73
ጌታህም በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቻቸው አያመሰግኑም፡፡ አል ነምል - Aya 73
وَإِنَّ رَبَّكَ لَيَعْلَمُ مَا تُكِنُّ صُدُورُهُمْ وَمَا يُعْلِنُونَ ( 74 ) አል ነምል - Aya 74
ጌታህም ልቦቻቸው የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ያውቃል፡፡ አል ነምል - Aya 74
وَمَا مِنْ غَائِبَةٍ فِي السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ إِلَّا فِي كِتَابٍ مُّبِينٍ ( 75 ) አል ነምል - Aya 75
በሰማይና በምድር ውስጥ ምንም የተደበቀ ነገር የለም ገላጭ በኾነው መጽሐፍ ውስጥ ያለ ቢኾን እንጅ፡፡ አል ነምል - Aya 75
إِنَّ هَٰذَا الْقُرْآنَ يَقُصُّ عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَكْثَرَ الَّذِي هُمْ فِيهِ يَخْتَلِفُونَ ( 76 ) አል ነምል - Aya 76
ይህ ቁርኣን በእስራኤል ልጆች ላይ የእነዚያን እነርሱ በእርሱ የሚለያዩበትን አብዛኛውን ይነግራል፡፡ አል ነምል - Aya 76
وَإِنَّهُ لَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ ( 77 ) አል ነምል - Aya 77
እርሱም ለምእምናን መምሪያና እዝነት ነው፡፡ አል ነምል - Aya 77
إِنَّ رَبَّكَ يَقْضِي بَيْنَهُم بِحُكْمِهِ ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْعَلِيمُ ( 78 ) አል ነምል - Aya 78
ጌታህ በመካከላቸው በትክክል ፍርዱ ይፈርዳል፡፡ እርሱም አሸናፊው ዐዋቂው ነው፡፡ አል ነምል - Aya 78
فَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۖ إِنَّكَ عَلَى الْحَقِّ الْمُبِينِ ( 79 ) አል ነምል - Aya 79
በአላህም ላይ ተጠጋ፡፡ አንተ ግልጽ በኾነው እውነት ላይ ነህና፡፡ አል ነምል - Aya 79
إِنَّكَ لَا تُسْمِعُ الْمَوْتَىٰ وَلَا تُسْمِعُ الصُّمَّ الدُّعَاءَ إِذَا وَلَّوْا مُدْبِرِينَ ( 80 ) አል ነምል - Aya 80
አንተ ሙታንን አታሰማም፡፡ ደንቆሮዎችንም የሚተው ኾነው በዞሩ ጊዜ ጥሪን አታሰማም፡፡ አል ነምል - Aya 80
وَمَا أَنتَ بِهَادِي الْعُمْيِ عَن ضَلَالَتِهِمْ ۖ إِن تُسْمِعُ إِلَّا مَن يُؤْمِنُ بِآيَاتِنَا فَهُم مُّسْلِمُونَ ( 81 ) አል ነምል - Aya 81
አንተም (ልበ) ዕውሮችን ከጥመታቸው አቅኚ አይደለህም፡፡ በአንቀጾቻችን የሚያምኑትን በስተቀር አታሰማም፡፡ እነርሱ ፍጹም ታዛዦች ናቸውና፡፡ አል ነምል - Aya 81
وَإِذَا وَقَعَ الْقَوْلُ عَلَيْهِمْ أَخْرَجْنَا لَهُمْ دَابَّةً مِّنَ الْأَرْضِ تُكَلِّمُهُمْ أَنَّ النَّاسَ كَانُوا بِآيَاتِنَا لَا يُوقِنُونَ ( 82 ) አል ነምል - Aya 82
በእነርሱም ላይ (የቅጣት) ቃሉ በተረጋገጠ ጊዜ ሰዎቹ በአንቀጾቻችን የማያረጋግጡ እንደነበሩ የምትነግራቸውን እንስሳ ለእነርሱ ከምድር እናወጣለን፡፡ አል ነምል - Aya 82
وَيَوْمَ نَحْشُرُ مِن كُلِّ أُمَّةٍ فَوْجًا مِّمَّن يُكَذِّبُ بِآيَاتِنَا فَهُمْ يُوزَعُونَ ( 83 ) አል ነምል - Aya 83
ከሕዝቦቹም ሁሉ ባንቀፆቻችን የሚያስተባብሉትን ጭፍሮች የምንሰበስብበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ እነሱም ይከመከማሉ፡፡ አል ነምል - Aya 83
حَتَّىٰ إِذَا جَاءُوا قَالَ أَكَذَّبْتُم بِآيَاتِي وَلَمْ تُحِيطُوا بِهَا عِلْمًا أَمَّاذَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ ( 84 ) አል ነምል - Aya 84
በመጡም ጊዜ (አላህ) ይላቸዋል «በአንቀጾቼ እርሷን በማወቅ ያላዳረሳችሁ ስትሆኑ አስተባበላችሁን ወይስ ምንን ትሠሩ ነበራችሁ» አል ነምል - Aya 84
وَوَقَعَ الْقَوْلُ عَلَيْهِم بِمَا ظَلَمُوا فَهُمْ لَا يَنطِقُونَ ( 85 ) አል ነምል - Aya 85
በመበደላቸውም በእነርሱ ላይ ቃሉ ይፈጸምባቸዋል፡፡ እነርሱም አይናገሩም፡፡ አል ነምል - Aya 85
أَلَمْ يَرَوْا أَنَّا جَعَلْنَا اللَّيْلَ لِيَسْكُنُوا فِيهِ وَالنَّهَارَ مُبْصِرًا ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ ( 86 ) አል ነምል - Aya 86
እኛ ሌሊትን በእርሱ ውስጥ እንዲያርፉበት ቀንንም የሚያሳይ እንዳደረግን አያዩምን ለሚያምኑ ሕዝቦች በዚህ ውስጥ ተዓምራቶች አሉበት፡፡ አል ነምል - Aya 86
وَيَوْمَ يُنفَخُ فِي الصُّورِ فَفَزِعَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ إِلَّا مَن شَاءَ اللَّهُ ۚ وَكُلٌّ أَتَوْهُ دَاخِرِينَ ( 87 ) አል ነምል - Aya 87
በቀንዱም በሚነፋ ቀን በሰማያት ውስጥ ያሉትና በምድርም ውስጥ ያሉት ሁሉ አላህ የሻው ነገር ብቻ ሲቀር በሚደነግጡ ጊዜ (የሚኾነውን አስታውስ)፡፡ ሁሉም የተናነሱ ኾነውም ወደርሱ ይመጣሉ፡፡ አል ነምል - Aya 87
وَتَرَى الْجِبَالَ تَحْسَبُهَا جَامِدَةً وَهِيَ تَمُرُّ مَرَّ السَّحَابِ ۚ صُنْعَ اللَّهِ الَّذِي أَتْقَنَ كُلَّ شَيْءٍ ۚ إِنَّهُ خَبِيرٌ بِمَا تَفْعَلُونَ ( 88 ) አል ነምል - Aya 88
ጋራዎችንም እርሷ እንደ ደመና አስተላለፍ የምታልፍ ስትኾን የቆመች ናት ብለህ የምታስባት ሆና ታያታለህ፡፡ የዚያን ነገሩን ሁሉ ያጠነከረውን የአላህን ጥበብ (ተመልከት)፡፡ እርሱ በምትሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡ አል ነምል - Aya 88
مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ خَيْرٌ مِّنْهَا وَهُم مِّن فَزَعٍ يَوْمَئِذٍ آمِنُونَ ( 89 ) አል ነምል - Aya 89
በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ከእርስዋ የበለጠ ምንዳ አልለው፡፡ እነርሱም በዚያ ቀን ከድንጋጤ ጸጥተኞች ናቸው፡፡ አል ነምል - Aya 89
وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَكُبَّتْ وُجُوهُهُمْ فِي النَّارِ هَلْ تُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ ( 90 ) አል ነምል - Aya 90
በመጥፎም የመጡ ሰዎች ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ ይደፋሉ፡፡ «ትሠሩት የነበራችሁትን እንጅ አትመነዱም» (ይባላሉ)፡፡ አል ነምል - Aya 90
إِنَّمَا أُمِرْتُ أَنْ أَعْبُدَ رَبَّ هَٰذِهِ الْبَلْدَةِ الَّذِي حَرَّمَهَا وَلَهُ كُلُّ شَيْءٍ ۖ وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ الْمُسْلِمِينَ ( 91 ) አል ነምል - Aya 91
የታዘዝኩት የዚህችን አገር ጌታ ያንን ክልል ያደረጋትን እንድግገዛ ብቻ ነው፡፡ ነገሩንም ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ከሙስሊሞችም እንድኾን ታዝዣለሁ (በላቸው)፡፡ አል ነምል - Aya 91
وَأَنْ أَتْلُوَ الْقُرْآنَ ۖ فَمَنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَقُلْ إِنَّمَا أَنَا مِنَ الْمُنذِرِينَ ( 92 ) አል ነምል - Aya 92
ቁርኣንንም እንዳነብ (ታዝዣለሁ)፡፡ የተመራም ሰው የሚመራው ለእራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው «እኔ ከአስጠንቃቂዎች ነኝ እንጅ ሌላ አይደለሁም» በለው፡፡ አል ነምል - Aya 92
وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ سَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ فَتَعْرِفُونَهَا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ ( 93 ) አል ነምል - Aya 93
ምስጋናም ለአላህ ነው፡፡ ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፡፡ «ታውቋትምአላችሁ» በላቸው፡፡ ጌታህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ አል ነምል - Aya 93
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah