Surah አል ቂያማህ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ቂያማህ - Aya count 40
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
لَا أُقْسِمُ بِيَوْمِ الْقِيَامَةِ ( 1 ) አል ቂያማህ - Aya 1
(ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት) አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ፡፡ አል ቂያማህ - Aya 1
وَلَا أُقْسِمُ بِالنَّفْسِ اللَّوَّامَةِ ( 2 ) አል ቂያማህ - Aya 2
(ራሷን) ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡ አል ቂያማህ - Aya 2
أَيَحْسَبُ الْإِنسَانُ أَلَّن نَّجْمَعَ عِظَامَهُ ( 3 ) አል ቂያማህ - Aya 3
ሰው አጥንቶቹን አለመሰብሰባችንን ያስባልን? አል ቂያማህ - Aya 3
بَلَىٰ قَادِرِينَ عَلَىٰ أَن نُّسَوِّيَ بَنَانَهُ ( 4 ) አል ቂያማህ - Aya 4
አይደለም ጣቶቹን (ፊት እንደ ነበሩ) በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንኾን (እንሰበስባቸዋለን)፡፡ አል ቂያማህ - Aya 4
بَلْ يُرِيدُ الْإِنسَانُ لِيَفْجُرَ أَمَامَهُ ( 5 ) አል ቂያማህ - Aya 5
ይልቁንም ሰው በፊቱ ባለው ነገር (በትንሣኤ) ሊያስተባብል ይፈልጋል፡፡ አል ቂያማህ - Aya 5
يَسْأَلُ أَيَّانَ يَوْمُ الْقِيَامَةِ ( 6 ) አል ቂያማህ - Aya 6
«የትንሣኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል፡፡ አል ቂያማህ - Aya 6
فَإِذَا بَرِقَ الْبَصَرُ ( 7 ) አል ቂያማህ - Aya 7
ዓይንም በዋለለ ጊዜ፡፡ አል ቂያማህ - Aya 7
وَخَسَفَ الْقَمَرُ ( 8 ) አል ቂያማህ - Aya 8
ጨረቃም በጨለመ ጊዜ፡፡ አል ቂያማህ - Aya 8
وَجُمِعَ الشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ( 9 ) አል ቂያማህ - Aya 9
ፀሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፡፡ አል ቂያማህ - Aya 9
يَقُولُ الْإِنسَانُ يَوْمَئِذٍ أَيْنَ الْمَفَرُّ ( 10 ) አል ቂያማህ - Aya 10
«ሰው በዚያ ቀን መሸሻው የት ነው?» ይላል፡፡ አል ቂያማህ - Aya 10
كَلَّا لَا وَزَرَ ( 11 ) አል ቂያማህ - Aya 11
ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም፡፡ አል ቂያማህ - Aya 11
إِلَىٰ رَبِّكَ يَوْمَئِذٍ الْمُسْتَقَرُّ ( 12 ) አል ቂያማህ - Aya 12
በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ አል ቂያማህ - Aya 12
يُنَبَّأُ الْإِنسَانُ يَوْمَئِذٍ بِمَا قَدَّمَ وَأَخَّرَ ( 13 ) አል ቂያማህ - Aya 13
ሰው በዚያ ቀን ባስቀደመውና ባስቆየው ሁሉ ይነገራል፡፡ አል ቂያማህ - Aya 13
بَلِ الْإِنسَانُ عَلَىٰ نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ ( 14 ) አል ቂያማህ - Aya 14
በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡ (አካሎቹ ይመሰክሩበታል)፡፡ አል ቂያማህ - Aya 14
وَلَوْ أَلْقَىٰ مَعَاذِيرَهُ ( 15 ) አል ቂያማህ - Aya 15
ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣም እንኳ (አይሰማም)፡፡ አል ቂያማህ - Aya 15
لَا تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ لِتَعْجَلَ بِهِ ( 16 ) አል ቂያማህ - Aya 16
በእርሱ (በቁርኣን ንባብ) ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ፡፡ አል ቂያማህ - Aya 16
إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ ( 17 ) አል ቂያማህ - Aya 17
(በልብህ ውስጥ) መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና፡፡ አል ቂያማህ - Aya 17
فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَهُ ( 18 ) አል ቂያማህ - Aya 18
ባነበብነውም ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል፡፡ አል ቂያማህ - Aya 18
ثُمَّ إِنَّ عَلَيْنَا بَيَانَهُ ( 19 ) አል ቂያማህ - Aya 19
ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው፡፡ አል ቂያማህ - Aya 19
كَلَّا بَلْ تُحِبُّونَ الْعَاجِلَةَ ( 20 ) አል ቂያማህ - Aya 20
(ከመጣደፍ) ተከልከል፡፡ ይልቁንም (ሰዎች) ፈጣኒቱን (ዓለም) ትወዳላችሁ፡፡ አል ቂያማህ - Aya 20
وَتَذَرُونَ الْآخِرَةَ ( 21 ) አል ቂያማህ - Aya 21
መጨረሻይቱንም (ዓለም) ትተዋላችሁ፡፡ (አትዘጋጁላትም)፡፡ አል ቂያማህ - Aya 21
وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاضِرَةٌ ( 22 ) አል ቂያማህ - Aya 22
ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡ አል ቂያማህ - Aya 22
إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ ( 23 ) አል ቂያማህ - Aya 23
ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ አል ቂያማህ - Aya 23
وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ بَاسِرَةٌ ( 24 ) አል ቂያማህ - Aya 24
ፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡ አል ቂያማህ - Aya 24
تَظُنُّ أَن يُفْعَلَ بِهَا فَاقِرَةٌ ( 25 ) አል ቂያማህ - Aya 25
በርሳቸውም ዐደጋ እንደሚሠራባቸው ያረጋግጣሉ፡፡ አል ቂያማህ - Aya 25
كَلَّا إِذَا بَلَغَتِ التَّرَاقِيَ ( 26 ) አል ቂያማህ - Aya 26
ንቁ (ነፍስ) ብሪዎችን በደረሰች ጊዜ፤ አል ቂያማህ - Aya 26
وَقِيلَ مَنْ ۜ رَاقٍ ( 27 ) አል ቂያማህ - Aya 27
«አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፡፡ አል ቂያማህ - Aya 27
وَظَنَّ أَنَّهُ الْفِرَاقُ ( 28 ) አል ቂያማህ - Aya 28
(ሕመምተኛው) እርሱ (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መልለየት መኾኑን ባረጋገጠም ጊዜ፡፡ አል ቂያማህ - Aya 28
وَالْتَفَّتِ السَّاقُ بِالسَّاقِ ( 29 ) አል ቂያማህ - Aya 29
ባትም በባት በተጣበቀች ጊዜ፡፡ አል ቂያማህ - Aya 29
إِلَىٰ رَبِّكَ يَوْمَئِذٍ الْمَسَاقُ ( 30 ) አል ቂያማህ - Aya 30
በዚያ ቀን መነዳቱ ወደ ጌታህ (ፍርድ) ነው፡፡ አል ቂያማህ - Aya 30
فَلَا صَدَّقَ وَلَا صَلَّىٰ ( 31 ) አል ቂያማህ - Aya 31
አላመነምም አልሰገደምም፡፡ አል ቂያማህ - Aya 31
وَلَٰكِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ ( 32 ) አል ቂያማህ - Aya 32
ግን አስተባበለ፤ (ከእምነት) ዞረም፡፡ አል ቂያማህ - Aya 32
ثُمَّ ذَهَبَ إِلَىٰ أَهْلِهِ يَتَمَطَّىٰ ( 33 ) አል ቂያማህ - Aya 33
ከዚያም እየተንጎባለለ ወደ ቤተሰቡ ኼደ፡፡ አል ቂያማህ - Aya 33
أَوْلَىٰ لَكَ فَأَوْلَىٰ ( 34 ) አል ቂያማህ - Aya 34
የምትጠላውን ነገር (አላህ) ያስከትልህ፡፡ ለአንተ ተገቢህም ነው፡፡ አል ቂያማህ - Aya 34
ثُمَّ أَوْلَىٰ لَكَ فَأَوْلَىٰ ( 35 ) አል ቂያማህ - Aya 35
ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ለአንተ የተገባህም ነው፡፡ አል ቂያማህ - Aya 35
أَيَحْسَبُ الْإِنسَانُ أَن يُتْرَكَ سُدًى ( 36 ) አል ቂያማህ - Aya 36
ሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን? አል ቂያማህ - Aya 36
أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِّن مَّنِيٍّ يُمْنَىٰ ( 37 ) አል ቂያማህ - Aya 37
የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን? አል ቂያማህ - Aya 37
ثُمَّ كَانَ عَلَقَةً فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ ( 38 ) አል ቂያማህ - Aya 38
ከዚያም የረጋ ደም ኾነ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም፡፡ አል ቂያማህ - Aya 38
فَجَعَلَ مِنْهُ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ ( 39 ) አል ቂያማህ - Aya 39
ከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ፡፡ አል ቂያማህ - Aya 39
أَلَيْسَ ذَٰلِكَ بِقَادِرٍ عَلَىٰ أَن يُحْيِيَ الْمَوْتَىٰ ( 40 ) አል ቂያማህ - Aya 40
ይህ (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን? አል ቂያማህ - Aya 40
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah