Surah አል ዱኻን

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ዱኻን - Aya count 59
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
حم ( 1 ) አል ዱኻን - Aya 1
ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡ አል ዱኻን - Aya 1
وَالْكِتَابِ الْمُبِينِ ( 2 ) አል ዱኻን - Aya 2
አብራሪ በኾነው መጽሐፍ እንምላለን፡፡ አል ዱኻን - Aya 2
إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَةٍ ۚ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينَ ( 3 ) አል ዱኻን - Aya 3
እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡ አል ዱኻን - Aya 3
فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٍ ( 4 ) አል ዱኻን - Aya 4
በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡ አል ዱኻን - Aya 4
أَمْرًا مِّنْ عِندِنَا ۚ إِنَّا كُنَّا مُرْسِلِينَ ( 5 ) አል ዱኻን - Aya 5
ከእኛ ዘንድ የኾነ ትእዛዝ ሲኾን (አወረድነው)፡፡ እኛ (መልክተኞችን) ላኪዎች ነበርን፡፡ አል ዱኻን - Aya 5
رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ ( 6 ) አል ዱኻን - Aya 6
ከጌታህ በኾነው ችሮታ (ተላኩ)፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡ አል ዱኻን - Aya 6
رَبِّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا ۖ إِن كُنتُم مُّوقِنِينَ ( 7 ) አል ዱኻን - Aya 7
የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ከኾነው (ተላኩ)፡፡ የምታረጋግጡ እንደኾናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መኾኑን እወቁ)፡፡ አል ዱኻን - Aya 7
لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ يُحْيِي وَيُمِيتُ ۖ رَبُّكُمْ وَرَبُّ آبَائِكُمُ الْأَوَّلِينَ ( 8 ) አል ዱኻን - Aya 8
ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ ጌታችሁ የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው፡፡ አል ዱኻን - Aya 8
بَلْ هُمْ فِي شَكٍّ يَلْعَبُونَ ( 9 ) አል ዱኻን - Aya 9
በእውነቱ እነርሱ የሚጫወቱ ሲኾኑ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ አል ዱኻን - Aya 9
فَارْتَقِبْ يَوْمَ تَأْتِي السَّمَاءُ بِدُخَانٍ مُّبِينٍ ( 10 ) አል ዱኻን - Aya 10
ሰማይም በግልጽ ጭስ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ፡፡ አል ዱኻን - Aya 10
يَغْشَى النَّاسَ ۖ هَٰذَا عَذَابٌ أَلِيمٌ ( 11 ) አል ዱኻን - Aya 11
ሰዎችን የሚሸፍን (በኾነ ጭስ) ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው፡፡ አል ዱኻን - Aya 11
رَّبَّنَا اكْشِفْ عَنَّا الْعَذَابَ إِنَّا مُؤْمِنُونَ ( 12 ) አል ዱኻን - Aya 12
«ጌታችን ሆይ! ከእኛ ላይ ቅጣቱን ግለጥልን፡፡ እኛ አማኞች እንኾናለንና» (ይላሉም)፡፡ አል ዱኻን - Aya 12
أَنَّىٰ لَهُمُ الذِّكْرَىٰ وَقَدْ جَاءَهُمْ رَسُولٌ مُّبِينٌ ( 13 ) አል ዱኻን - Aya 13
(ቅጣቱ በወረደ ጊዜ) ለእነርሱ መግገሰጽ እንዴት ይኖራቸዋል? አስረጅ መልክተኛ የመጣቸው ሲኾን (የካዱም ሲኾኑ)፡፡ አል ዱኻን - Aya 13
ثُمَّ تَوَلَّوْا عَنْهُ وَقَالُوا مُعَلَّمٌ مَّجْنُونٌ ( 14 ) አል ዱኻን - Aya 14
ከዚያም ከእርሱ የዞሩ፤ (ከሰው) «የተሰተማረ ዕብድ ነው» ያሉም ሲኾኑ፡፡ አል ዱኻን - Aya 14
إِنَّا كَاشِفُو الْعَذَابِ قَلِيلًا ۚ إِنَّكُمْ عَائِدُونَ ( 15 ) አል ዱኻን - Aya 15
እኛ ቅጣቱን ለጥቂት ጊዜ ገላጮች ነን፡፡ እናንተ (ወደ ክህደታችሁ) በእርግጥ ተመላሾች ናችሁ፡፡ አል ዱኻን - Aya 15
يَوْمَ نَبْطِشُ الْبَطْشَةَ الْكُبْرَىٰ إِنَّا مُنتَقِمُونَ ( 16 ) አል ዱኻን - Aya 16
ታላቂቱን ብርቱ አያያዝ በምንይዝበት ቀን፤ እኛ ተበቃዮች ነን፡፡ አል ዱኻን - Aya 16
وَلَقَدْ فَتَنَّا قَبْلَهُمْ قَوْمَ فِرْعَوْنَ وَجَاءَهُمْ رَسُولٌ كَرِيمٌ ( 17 ) አል ዱኻን - Aya 17
ከእነርሱም በፊት የፈርዖንን ሕዝቦች በእርግጥ ሞከርን፡፡ ክቡር መልእክተኛም መጣላቸው፡፡ አል ዱኻን - Aya 17
أَنْ أَدُّوا إِلَيَّ عِبَادَ اللَّهِ ۖ إِنِّي لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌ ( 18 ) አል ዱኻን - Aya 18
«የአላህን ባሮች ወደኔ አድርሱ፡፡ እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝና፡፡ አል ዱኻን - Aya 18
وَأَن لَّا تَعْلُوا عَلَى اللَّهِ ۖ إِنِّي آتِيكُم بِسُلْطَانٍ مُّبِينٍ ( 19 ) አል ዱኻን - Aya 19
«በአላህም ላይ አትኩሩ፡፡ እኔ ግልጽ የኾነን አስረጅ ያመጣሁላችሁ ነኝና (በማለት መጣላቸው)፡፡ አል ዱኻን - Aya 19
وَإِنِّي عُذْتُ بِرَبِّي وَرَبِّكُمْ أَن تَرْجُمُونِ ( 20 ) አል ዱኻን - Aya 20
«እኔም እንዳትወግሩኝ በጌታየና በጌታችሁ ተጠብቂያለሁ፡፡ አል ዱኻን - Aya 20
وَإِن لَّمْ تُؤْمِنُوا لِي فَاعْتَزِلُونِ ( 21 ) አል ዱኻን - Aya 21
«በእኔም ባታምኑ ራቁኝ» (ተዉኝ አለ)፡፡ አል ዱኻን - Aya 21
فَدَعَا رَبَّهُ أَنَّ هَٰؤُلَاءِ قَوْمٌ مُّجْرِمُونَ ( 22 ) አል ዱኻን - Aya 22
ቀጥሎም (ስለ ዛቱበት) «እነዚህ አመጸኞች ሕዝቦች ናቸው» (አጥፋቸው) ሲል ጌታውን ለመነ፡፡ አል ዱኻን - Aya 22
فَأَسْرِ بِعِبَادِي لَيْلًا إِنَّكُم مُّتَّبَعُونَ ( 23 ) አል ዱኻን - Aya 23
(ጌታው) «ባሮቼንም ይዘህ በሌሊት ኺድ፡፡ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና፡፡ አል ዱኻን - Aya 23
وَاتْرُكِ الْبَحْرَ رَهْوًا ۖ إِنَّهُمْ جُندٌ مُّغْرَقُونَ ( 24 ) አል ዱኻን - Aya 24
«ባሕሩንም የተከፈተ ኾኖ ተወው፡፡ እነርሱ የሚሰጥጠሙ ሰራዊት ናቸውና» (አለው)፡፡ አል ዱኻን - Aya 24
كَمْ تَرَكُوا مِن جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ ( 25 ) አል ዱኻን - Aya 25
ከአትክልቶችና ከምንጮችም ብዙ ነገሮችን ተዉ፡፡ አል ዱኻን - Aya 25
وَزُرُوعٍ وَمَقَامٍ كَرِيمٍ ( 26 ) አል ዱኻን - Aya 26
ከአዝመራዎችም ከመልካም መቀመጫም፡፡ አል ዱኻን - Aya 26
وَنَعْمَةٍ كَانُوا فِيهَا فَاكِهِينَ ( 27 ) አል ዱኻን - Aya 27
በእርሷ ተደሳቾች ከነበሩባትም ድሎት (ብዙን ነገር ተዉ)፡፡ አል ዱኻን - Aya 27
كَذَٰلِكَ ۖ وَأَوْرَثْنَاهَا قَوْمًا آخَرِينَ ( 28 ) አል ዱኻን - Aya 28
(ነገሩ) እንደዚሁ ኾነ፡፡ ሌሎችንም ሕዝቦች አወረስናት፡፡ አል ዱኻን - Aya 28
فَمَا بَكَتْ عَلَيْهِمُ السَّمَاءُ وَالْأَرْضُ وَمَا كَانُوا مُنظَرِينَ ( 29 ) አል ዱኻን - Aya 29
ሰማይና ምድርም በእነርሱ ላይ አላለቀሱም፡፡ የሚቆዩም አልነበሩም፡፡ አል ዱኻን - Aya 29
وَلَقَدْ نَجَّيْنَا بَنِي إِسْرَائِيلَ مِنَ الْعَذَابِ الْمُهِينِ ( 30 ) አል ዱኻን - Aya 30
የእስራኤልንም ልጆች አዋራጅ ከኾነ ስቃይ በእርግጥ አዳንናቸው፡፡ አል ዱኻን - Aya 30
مِن فِرْعَوْنَ ۚ إِنَّهُ كَانَ عَالِيًا مِّنَ الْمُسْرِفِينَ ( 31 ) አል ዱኻን - Aya 31
ከፈርዖን፤ እርሱ የኮራ ከወሰን አላፊዎቹ ነበርና፡፡ አል ዱኻን - Aya 31
وَلَقَدِ اخْتَرْنَاهُمْ عَلَىٰ عِلْمٍ عَلَى الْعَالَمِينَ ( 32 ) አል ዱኻን - Aya 32
ከማወቅም ጋር በዓለማት ላይ በእርግጥ መረጥናቸው፡፡ አል ዱኻን - Aya 32
وَآتَيْنَاهُم مِّنَ الْآيَاتِ مَا فِيهِ بَلَاءٌ مُّبِينٌ ( 33 ) አል ዱኻን - Aya 33
ከታምራቶችም በውስጡ ግልጽ የኾነ ፈተና ያለበትን ሰጠናቸው፡፡ አል ዱኻን - Aya 33
إِنَّ هَٰؤُلَاءِ لَيَقُولُونَ ( 34 ) አል ዱኻን - Aya 34
እነዚህ (የመካ ከሓዲዎች) በእርግጥ ይላሉ፡- አል ዱኻን - Aya 34
إِنْ هِيَ إِلَّا مَوْتَتُنَا الْأُولَىٰ وَمَا نَحْنُ بِمُنشَرِينَ ( 35 ) አል ዱኻን - Aya 35
እርሷ የፊተኛይቱ ሞታችን እንጅ አይደለችም፡፡ እኛም የምንቀሰቀስ አይደለንም፡፡ አል ዱኻን - Aya 35
فَأْتُوا بِآبَائِنَا إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ ( 36 ) አል ዱኻን - Aya 36
እውነተኞችም እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡልን፡፡ አል ዱኻን - Aya 36
أَهُمْ خَيْرٌ أَمْ قَوْمُ تُبَّعٍ وَالَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ ۚ أَهْلَكْنَاهُمْ ۖ إِنَّهُمْ كَانُوا مُجْرِمِينَ ( 37 ) አል ዱኻን - Aya 37
እነርሱ በላጮች ናቸውን ወይስ የቱብበዕ ሕዝቦችና እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት? አጠፋናቸው፡፡ እነርሱ አመጸኞች ነበሩና፡፡ አል ዱኻን - Aya 37
وَمَا خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا لَاعِبِينَ ( 38 ) አል ዱኻን - Aya 38
ሰማያትንና ምድርንም በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ኾነን አልፈጠርንም፡፡ አል ዱኻን - Aya 38
مَا خَلَقْنَاهُمَا إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ ( 39 ) አል ዱኻን - Aya 39
ሁለቱንም በምር እንጅ አልፈጠርናቸውም፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ አል ዱኻን - Aya 39
إِنَّ يَوْمَ الْفَصْلِ مِيقَاتُهُمْ أَجْمَعِينَ ( 40 ) አል ዱኻን - Aya 40
የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው፡፡ አል ዱኻን - Aya 40
يَوْمَ لَا يُغْنِي مَوْلًى عَن مَّوْلًى شَيْئًا وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ ( 41 ) አል ዱኻን - Aya 41
ዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት እነርሱም የማይርረዱበት ቀን ነው፡፡ አል ዱኻን - Aya 41
إِلَّا مَن رَّحِمَ اللَّهُ ۚ إِنَّهُ هُوَ الْعَزِيزُ الرَّحِيمُ ( 42 ) አል ዱኻን - Aya 42
አላህ ያዘነለት ሰውና ያመነ ብቻ ሲቀር፡፡ (እርሱስ ይርረዳል)፡፡ እርሱ አሸናፊው አዛኙ ነውና፡፡ አል ዱኻን - Aya 42
إِنَّ شَجَرَتَ الزَّقُّومِ ( 43 ) አል ዱኻን - Aya 43
የዘቁመ ዛፍ አል ዱኻን - Aya 43
طَعَامُ الْأَثِيمِ ( 44 ) አል ዱኻን - Aya 44
የኀጢኣተኛው ምግብ ነው፡፡ አል ዱኻን - Aya 44
كَالْمُهْلِ يَغْلِي فِي الْبُطُونِ ( 45 ) አል ዱኻን - Aya 45
እንደ ዘይት አተላ ነው፡፡ በሆዶች ውስጥ የሚፈላ ሲኾን፡፡ አል ዱኻን - Aya 45
كَغَلْيِ الْحَمِيمِ ( 46 ) አል ዱኻን - Aya 46
እንደ ገነፈለ ውሃ አፈላል (የሚፈላ ሲኾን)፡፡ አል ዱኻን - Aya 46
خُذُوهُ فَاعْتِلُوهُ إِلَىٰ سَوَاءِ الْجَحِيمِ ( 47 ) አል ዱኻን - Aya 47
ያዙት፤ ወደ ገሀነም መካከልም በኀይል ጎትቱት፡፡ አል ዱኻን - Aya 47
ثُمَّ صُبُّوا فَوْقَ رَأْسِهِ مِنْ عَذَابِ الْحَمِيمِ ( 48 ) አል ዱኻን - Aya 48
ከዚያም «ከራሱ በላይ ከፈላ ውሃ ስቃይ አንቧቡበት፡፡» አል ዱኻን - Aya 48
ذُقْ إِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْكَرِيمُ ( 49 ) አል ዱኻን - Aya 49
«ቅመስ፤ አንተ አሸናፊው ክብሩ ነህና» (ይባላል)፡፡ አል ዱኻን - Aya 49
إِنَّ هَٰذَا مَا كُنتُم بِهِ تَمْتَرُونَ ( 50 ) አል ዱኻን - Aya 50
«ይህ ያ በእርሱ ትጠራጠሩበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)፡፡ አል ዱኻን - Aya 50
إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي مَقَامٍ أَمِينٍ ( 51 ) አል ዱኻን - Aya 51
ጥንቁቆቹ በእርግጥ በጸጥተኛ መኖሪያ ውስጥ ናቸው፡፡ አል ዱኻን - Aya 51
فِي جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ ( 52 ) አል ዱኻን - Aya 52
በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ አል ዱኻን - Aya 52
يَلْبَسُونَ مِن سُندُسٍ وَإِسْتَبْرَقٍ مُّتَقَابِلِينَ ( 53 ) አል ዱኻን - Aya 53
ፊት ለፊት የተቅጣጩ ኾነው ከስስ ሐርና ከወፍራም ሐር ይለብሳሉ፡፡ አል ዱኻን - Aya 53
كَذَٰلِكَ وَزَوَّجْنَاهُم بِحُورٍ عِينٍ ( 54 ) አል ዱኻን - Aya 54
(ነገሩ) እንደዚሁ ነው፤ ዓይናማዎች የኾኑን ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡ አል ዱኻን - Aya 54
يَدْعُونَ فِيهَا بِكُلِّ فَاكِهَةٍ آمِنِينَ ( 55 ) አል ዱኻን - Aya 55
በእርሷም ውስጥ የተማመኑ ኾነው፤ ከፍራፍሬ ሁሉ ያዝዛሉ፡፡ አል ዱኻን - Aya 55
لَا يَذُوقُونَ فِيهَا الْمَوْتَ إِلَّا الْمَوْتَةَ الْأُولَىٰ ۖ وَوَقَاهُمْ عَذَابَ الْجَحِيمِ ( 56 ) አል ዱኻን - Aya 56
የፊተኛይቱን ሞት እንጅ (ዳግመኛ) በእርሷ ውስጥ ሞትን አይቀምሱም፡፡ የገሀነምንም ቅጣት (አላህ) ጠበቃቸው፡፡ አል ዱኻን - Aya 56
فَضْلًا مِّن رَّبِّكَ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ ( 57 ) አል ዱኻን - Aya 57
ከጌታህ በኾነ ችሮታ (ጠበቃቸው)፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ አል ዱኻን - Aya 57
فَإِنَّمَا يَسَّرْنَاهُ بِلِسَانِكَ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ ( 58 ) አል ዱኻን - Aya 58
(ቁርኣኑን) በቋንቋህም ያገራነው (ሕዝቦችህ) ይገነዘቡ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ አል ዱኻን - Aya 58
فَارْتَقِبْ إِنَّهُم مُّرْتَقِبُونَ ( 59 ) አል ዱኻን - Aya 59
ተጠባበቅም እነርሱ ተጠባባቂዎች ናቸውና፡፡ አል ዱኻን - Aya 59
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah