Surah አል ሙጃደላ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ሙጃደላ - Aya count 22
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
قَدْ سَمِعَ اللَّهُ قَوْلَ الَّتِي تُجَادِلُكَ فِي زَوْجِهَا وَتَشْتَكِي إِلَى اللَّهِ وَاللَّهُ يَسْمَعُ تَحَاوُرَكُمَا ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ ( 1 ) አል ሙጃደላ - Aya 1
አላህ የዚያችን በባሏ (ነገር) የምተከራከርህንና ወደ አላህ የምታሰሙተውን (ሴት) ቃል በእርግጥ ሰማ፡፡ አላህም (በንግግር) መመላለሳችሁን ይሰማል፡፡ አላህ ሰሚ ተመልካች ነውና፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 1
الَّذِينَ يُظَاهِرُونَ مِنكُم مِّن نِّسَائِهِم مَّا هُنَّ أُمَّهَاتِهِمْ ۖ إِنْ أُمَّهَاتُهُمْ إِلَّا اللَّائِي وَلَدْنَهُمْ ۚ وَإِنَّهُمْ لَيَقُولُونَ مُنكَرًا مِّنَ الْقَوْلِ وَزُورًا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ لَعَفُوٌّ غَفُورٌ ( 2 ) አል ሙጃደላ - Aya 2
እነዚያ ከእናንተ ውስጥ ከሚስቶቻቸው እንደናቶቻችን ጀርባዎች ይኹኑብን በማለት የሚምሉ እነርሱ እናቶቻቸው አይደሉም፡፡ እናቶቻቸው እኒያ የወለዱዋቸው ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱም (በዚህ ቃል) ከንግግር የተጠላንና ውሸትን በእርግጥ ይናገራሉ፡፡ አላህም (ለሚጸጸት) ይቅር ባይ መሓሪ ነው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 2
وَالَّذِينَ يُظَاهِرُونَ مِن نِّسَائِهِمْ ثُمَّ يَعُودُونَ لِمَا قَالُوا فَتَحْرِيرُ رَقَبَةٍ مِّن قَبْلِ أَن يَتَمَاسَّا ۚ ذَٰلِكُمْ تُوعَظُونَ بِهِ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ ( 3 ) አል ሙጃደላ - Aya 3
እነዚያም ከሚስቶቻቸው እንደናቶቻችን ጀርባዎች ኹኑብን በማለት የሚምሉ ከዚያም ወደ ተናገሩት የሚመለሱ ሳይነካኩ በፊት ጫንቃን ነጻ ማውጣት በነርሱ ላይ አለባቸው፡፡ እነሆ በእርሱ ትገሰጹበታለችሁ፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጥ ዓዋቂ ነው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 3
فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ شَهْرَيْنِ مُتَتَابِعَيْنِ مِن قَبْلِ أَن يَتَمَاسَّا ۖ فَمَن لَّمْ يَسْتَطِعْ فَإِطْعَامُ سِتِّينَ مِسْكِينًا ۚ ذَٰلِكَ لِتُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ۚ وَتِلْكَ حُدُودُ اللَّهِ ۗ وَلِلْكَافِرِينَ عَذَابٌ أَلِيمٌ ( 4 ) አል ሙጃደላ - Aya 4
ያላገኘም ሰው ከመነካከታቸው በፊት ሁለት የተከታተሉ ወሮችን መጾም አለበት፡፡ ያልቻለም ሰው ስድሳ ድኾችን ማብላት (አለበት)፡፡ ይህ በአላህና በመልክተኛው እንድታምኑ ነው፡፡ ይህችም የአላህ ሕግጋት ናት፡፡ ለከሓዲዎችም አሳማሚ ቅጣት አልላቸው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 4
إِنَّ الَّذِينَ يُحَادُّونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ كُبِتُوا كَمَا كُبِتَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ ۚ وَقَدْ أَنزَلْنَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ ۚ وَلِلْكَافِرِينَ عَذَابٌ مُّهِينٌ ( 5 ) አል ሙጃደላ - Aya 5
ግልጾች ማስረጃዎችን ያወረድን ስንኾን እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት እንደተዋረዱ ይዋረዳሉ፡፡ ለከሓዲዎችም አዋራጅ ቅጣት አልላቸው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 5
يَوْمَ يَبْعَثُهُمُ اللَّهُ جَمِيعًا فَيُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوا ۚ أَحْصَاهُ اللَّهُ وَنَسُوهُ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ ( 6 ) አል ሙጃደላ - Aya 6
አላህ ሁላቸውንም በሚቀስቃሳቸው ቀን (ይቀጣቸዋል)፡፡ የሠሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡ የረሱት ሲኾኑ አላህ ዐውቆታል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 6
أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۖ مَا يَكُونُ مِن نَّجْوَىٰ ثَلَاثَةٍ إِلَّا هُوَ رَابِعُهُمْ وَلَا خَمْسَةٍ إِلَّا هُوَ سَادِسُهُمْ وَلَا أَدْنَىٰ مِن ذَٰلِكَ وَلَا أَكْثَرَ إِلَّا هُوَ مَعَهُمْ أَيْنَ مَا كَانُوا ۖ ثُمَّ يُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوا يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ ( 7 ) አል ሙጃደላ - Aya 7
አላህ በሰማያት ውስጥ ያለውን በምድርም ውሰጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ መኾኑን አታይምን? ከሦስት ሰዎች መሾካሾክ አይኖርም እርሱ አራተኛቸው ቢኾን እንጅ፡፡ ከአምስትም (አይኖርም) እርሱ ስድስተኛቸው ቢኾን እንጅ፡፡ ከዚያ ያነሰም የበዛም (አይኖርም) እርሱ የትም ቢኾኑ እንጂ፡፡ ከዚያም በትንሣኤ ቀን የሠሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡ አላህ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 7
أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ نُهُوا عَنِ النَّجْوَىٰ ثُمَّ يَعُودُونَ لِمَا نُهُوا عَنْهُ وَيَتَنَاجَوْنَ بِالْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ وَمَعْصِيَتِ الرَّسُولِ وَإِذَا جَاءُوكَ حَيَّوْكَ بِمَا لَمْ يُحَيِّكَ بِهِ اللَّهُ وَيَقُولُونَ فِي أَنفُسِهِمْ لَوْلَا يُعَذِّبُنَا اللَّهُ بِمَا نَقُولُ ۚ حَسْبُهُمْ جَهَنَّمُ يَصْلَوْنَهَا ۖ فَبِئْسَ الْمَصِيرُ ( 8 ) አል ሙጃደላ - Aya 8
ወደእነዚያ (በመጥፎ) ከመሾካሾክ ወደ ተከለከሉት፣ ከዚያም ከእርሱ ወደ ተከለከሉት ነገር ወደሚመለሱት፣ በኃጢአትና ድንበር በማለፍ መልክተኛውን በመቃወም ወደሚንሾካሾኩት አላየህምን? (ሰላም ሊሉ) በመጡህም ጊዜ አላህ በእርሱ ባላናገረህ ቃል ያናግሩሃል፡፡ በነፍሶቻቸውም ውስጥ (ነቢይ ከኾንክ) «በምንለው ነገር አላህ አይቀጣንም ኖሮአልን?» ይላሉ፡፡ ገሀነም የሚገቧት ሲኾኑ በቂያቸው ናት፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ! አል ሙጃደላ - Aya 8
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا تَنَاجَيْتُمْ فَلَا تَتَنَاجَوْا بِالْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ وَمَعْصِيَتِ الرَّسُولِ وَتَنَاجَوْا بِالْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ ( 9 ) አል ሙጃደላ - Aya 9
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተንሾካሾካችሁ ጊዜ በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ፣ መልክተኛውንም በመቃወም አትንሾካሾኩ፡፡ ግን በበጎ ሥራና አላህን በመፍራት ተወያዩ፡፡ ያንንም ወደእርሱ የምትሰበሰቡበትን አላህን ፍሩ፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 9
إِنَّمَا النَّجْوَىٰ مِنَ الشَّيْطَانِ لِيَحْزُنَ الَّذِينَ آمَنُوا وَلَيْسَ بِضَارِّهِمْ شَيْئًا إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ وَعَلَى اللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ الْمُؤْمِنُونَ ( 10 ) አል ሙጃደላ - Aya 10
(በመጥፎ) መንሾካሾክ ከሰይጣን ብቻ ነው፡፡ እነዚያ ያመኑት ያዝኑ ዘንድ (ይቀሰቅሰዋል)፡፡ በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በቀር በምንም አይጎዳቸውም፡፡ በአላህ ላይም አማኞች ይጠጉ፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 10
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا قِيلَ لَكُمْ تَفَسَّحُوا فِي الْمَجَالِسِ فَافْسَحُوا يَفْسَحِ اللَّهُ لَكُمْ ۖ وَإِذَا قِيلَ انشُزُوا فَانشُزُوا يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ ( 11 ) አል ሙጃደላ - Aya 11
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ በመቀመጫዎች ስፍራ ተስፋፉ በተባላችሁ ጊዜ (ስፍራን) አስፉ፡፡ አላህ ያሰፋላችኋልና፡፡ ተነሱ በተባላችሁም ጊዜ ተነሱ፡፡ አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም ዕውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል፡፡ አላህም በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 11
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نَاجَيْتُمُ الرَّسُولَ فَقَدِّمُوا بَيْنَ يَدَيْ نَجْوَاكُمْ صَدَقَةً ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ لَّكُمْ وَأَطْهَرُ ۚ فَإِن لَّمْ تَجِدُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ( 12 ) አል ሙጃደላ - Aya 12
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! መልክተኛውን በተወያያችሁ ጊዜ ከመወያየታችሁ በፊት ምጽዋትን አስቀድሙ፡፡ ይህ ለእናንተ መልካም ነው፡፡ አጥሪም ነው፡፡ ባታገኙም አላህ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 12
أَأَشْفَقْتُمْ أَن تُقَدِّمُوا بَيْنَ يَدَيْ نَجْوَاكُمْ صَدَقَاتٍ ۚ فَإِذْ لَمْ تَفْعَلُوا وَتَابَ اللَّهُ عَلَيْكُمْ فَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَأَطِيعُوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ وَاللَّهُ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ ( 13 ) አል ሙጃደላ - Aya 13
ከውይይታችሁ በፊት ምጽዋቶችን ከማስቀደም (ድህነትን) ፈራችሁን? ባልሠራችሁም ጊዜ አላህ ከእናንተ ጸጸትን የተቀበለ ሲኾን ሶላትን ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ አላህም ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 13
أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ تَوَلَّوْا قَوْمًا غَضِبَ اللَّهُ عَلَيْهِم مَّا هُم مِّنكُمْ وَلَا مِنْهُمْ وَيَحْلِفُونَ عَلَى الْكَذِبِ وَهُمْ يَعْلَمُونَ ( 14 ) አል ሙጃደላ - Aya 14
ወደእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ የተቆጣባቸውን ሕዝቦች ወደ ተወዳጁት (መናፍቃን) አላየኽምን? እነርሱ ከእናንተ አይደሉም፡፡ ከእነርሱም አይደሉም፡፡ እነርሱም የሚያውቁ ሲኾኑ በውሸት ላይ ይምላሉ፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 14
أَعَدَّ اللَّهُ لَهُمْ عَذَابًا شَدِيدًا ۖ إِنَّهُمْ سَاءَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ ( 15 ) አል ሙጃደላ - Aya 15
አላህ ለእነርሱ ብርቱን ቅጣት አዘጋጀ፡፡ እነርሱ ይሠሩት የነበሩት ሥራ ምንኛ ከፋ! አል ሙጃደላ - Aya 15
اتَّخَذُوا أَيْمَانَهُمْ جُنَّةً فَصَدُّوا عَن سَبِيلِ اللَّهِ فَلَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ ( 16 ) አል ሙጃደላ - Aya 16
መሓሎቻቸውን ጋሻ አድርገው ያዙ፡፡ ከአላህም መንገድ አገዱ፡፡ ስለዚህ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አልላቸው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 16
لَّن تُغْنِيَ عَنْهُمْ أَمْوَالُهُمْ وَلَا أَوْلَادُهُم مِّنَ اللَّهِ شَيْئًا ۚ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ ( 17 ) አል ሙጃደላ - Aya 17
ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው ከአላህ (ቅጣት) ምንንም ከእነርሱ አያድኗቸውም፡፡ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 17
يَوْمَ يَبْعَثُهُمُ اللَّهُ جَمِيعًا فَيَحْلِفُونَ لَهُ كَمَا يَحْلِفُونَ لَكُمْ ۖ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُمْ عَلَىٰ شَيْءٍ ۚ أَلَا إِنَّهُمْ هُمُ الْكَاذِبُونَ ( 18 ) አል ሙጃደላ - Aya 18
አላህ የተሰበሰቡ ኾነው በሚያስነሳቸው ቀን ለእናንተ እንደሚምሉላችሁም እነርሱ (በሚጠቅም) ነገር ላይ መኾናቸውን የሚያስቡ ኾነው ለእርሱ በሚምሉበት ቀን (አዋራጅ ቅጣት አልላቸው)፡፡ ንቁ! እነርሱ ውሸታሞቹ እነርሱ ናቸው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 18
اسْتَحْوَذَ عَلَيْهِمُ الشَّيْطَانُ فَأَنسَاهُمْ ذِكْرَ اللَّهِ ۚ أُولَٰئِكَ حِزْبُ الشَّيْطَانِ ۚ أَلَا إِنَّ حِزْبَ الشَّيْطَانِ هُمُ الْخَاسِرُونَ ( 19 ) አል ሙጃደላ - Aya 19
በእነርሱ ላይ ሰይጣን ተሾመባቸው፡፡ አላህንም ማስታወስን አስረሳቸው፡፡ እነዚያ የሰይጣን ጭፍሮች ናቸው፡፡ ንቁ! የሰይጣን ጭፍሮች ከሳሪዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 19
إِنَّ الَّذِينَ يُحَادُّونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ أُولَٰئِكَ فِي الْأَذَلِّينَ ( 20 ) አል ሙጃደላ - Aya 20
እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩት እነዚያ በጣም በወራዶቹ ውስጥ ናቸው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 20
كَتَبَ اللَّهُ لَأَغْلِبَنَّ أَنَا وَرُسُلِي ۚ إِنَّ اللَّهَ قَوِيٌّ عَزِيزٌ ( 21 ) አል ሙጃደላ - Aya 21
አላህ፡- «እኔ በእርግጥ አሸንፋለሁ፣ መልክተኞቼም (ያሸንፋሉ)» ሲል፤ ጽፏል፡፡ አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 21
لَّا تَجِدُ قَوْمًا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ يُوَادُّونَ مَنْ حَادَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَوْ كَانُوا آبَاءَهُمْ أَوْ أَبْنَاءَهُمْ أَوْ إِخْوَانَهُمْ أَوْ عَشِيرَتَهُمْ ۚ أُولَٰئِكَ كَتَبَ فِي قُلُوبِهِمُ الْإِيمَانَ وَأَيَّدَهُم بِرُوحٍ مِّنْهُ ۖ وَيُدْخِلُهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ ۚ أُولَٰئِكَ حِزْبُ اللَّهِ ۚ أَلَا إِنَّ حِزْبَ اللَّهِ هُمُ الْمُفْلِحُونَ ( 22 ) አል ሙጃደላ - Aya 22
በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው፣ ወይም ልጆቻቸው፣ ወይም ወንድሞቻቸው፣ ወይም ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም፡፡ እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል፡፡ ከእርሱም በኾነ መንፈስ ደግፏቸዋል፡፡ ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባቸዋል፡፡ አላህ ከእነርሱ ወዷል፡፡ ከእርሱም ወደዋል፡፡ እነዚያ የአላህ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ንቁ! የአላህ ሕዝቦቸ እነርሱ ምኞታቸውን የሚያገኙ ናቸው፡፡ አል ሙጃደላ - Aya 22
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah