Surah አል ቡሩጅ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ቡሩጅ - Aya count 22
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الْبُرُوجِ ( 1 ) አል ቡሩጅ - Aya 1
የቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 1
وَالْيَوْمِ الْمَوْعُودِ ( 2 ) አል ቡሩጅ - Aya 2
በተቀጠረው ቀንም፤ አል ቡሩጅ - Aya 2
وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ ( 3 ) አል ቡሩጅ - Aya 3
በተጣጅና በሚጣዱትም፤ (እምላለሁ)፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 3
قُتِلَ أَصْحَابُ الْأُخْدُودِ ( 4 ) አል ቡሩጅ - Aya 4
የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 4
النَّارِ ذَاتِ الْوَقُودِ ( 5 ) አል ቡሩጅ - Aya 5
የማገዶ ባለቤት የኾነቺው እሳት (ባለቤቶች)፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 5
إِذْ هُمْ عَلَيْهَا قُعُودٌ ( 6 ) አል ቡሩጅ - Aya 6
እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በኾኑ ጊዜ፤ (ተረገሙ)፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 6
وَهُمْ عَلَىٰ مَا يَفْعَلُونَ بِالْمُؤْمِنِينَ شُهُودٌ ( 7 ) አል ቡሩጅ - Aya 7
እነርሱም በምእምናኖቹ በሚሠሩት (ማሰቃየት) ላይ መስካሪዎች ናቸው፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 7
وَمَا نَقَمُوا مِنْهُمْ إِلَّا أَن يُؤْمِنُوا بِاللَّهِ الْعَزِيزِ الْحَمِيدِ ( 8 ) አል ቡሩጅ - Aya 8
ከእነርሱም በአላህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በኾነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 8
الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ ( 9 ) አል ቡሩጅ - Aya 9
በእዚያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ በኾነው (አላህ ማመናቸውን)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 9
إِنَّ الَّذِينَ فَتَنُوا الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَتُوبُوا فَلَهُمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمْ عَذَابُ الْحَرِيقِ ( 10 ) አል ቡሩጅ - Aya 10
እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 10
إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْكَبِيرُ ( 11 ) አል ቡሩጅ - Aya 11
እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 11
إِنَّ بَطْشَ رَبِّكَ لَشَدِيدٌ ( 12 ) አል ቡሩጅ - Aya 12
የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 12
إِنَّهُ هُوَ يُبْدِئُ وَيُعِيدُ ( 13 ) አል ቡሩጅ - Aya 13
እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 13
وَهُوَ الْغَفُورُ الْوَدُودُ ( 14 ) አል ቡሩጅ - Aya 14
እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 14
ذُو الْعَرْشِ الْمَجِيدُ ( 15 ) አል ቡሩጅ - Aya 15
የዙፋኑ ባለቤት የላቀው ነው፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 15
فَعَّالٌ لِّمَا يُرِيدُ ( 16 ) አል ቡሩጅ - Aya 16
የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 16
هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ الْجُنُودِ ( 17 ) አል ቡሩጅ - Aya 17
የሰራዊቶቹ ወሬ መጣልህን? አል ቡሩጅ - Aya 17
فِرْعَوْنَ وَثَمُودَ ( 18 ) አል ቡሩጅ - Aya 18
የፈርዖንና የሰሙድ፤ (ወሬ)፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 18
بَلِ الَّذِينَ كَفَرُوا فِي تَكْذِيبٍ ( 19 ) አል ቡሩጅ - Aya 19
በእውነቱ እነዚያ የካዱት በማስተባበል ውስጥ ናቸው፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 19
وَاللَّهُ مِن وَرَائِهِم مُّحِيطٌ ( 20 ) አል ቡሩጅ - Aya 20
አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 20
بَلْ هُوَ قُرْآنٌ مَّجِيدٌ ( 21 ) አል ቡሩጅ - Aya 21
ይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 21
فِي لَوْحٍ مَّحْفُوظٍ ( 22 ) አል ቡሩጅ - Aya 22
የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡ አል ቡሩጅ - Aya 22
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah