Surah አል ጋሺያህ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ጋሺያህ - Aya count 26
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ الْغَاشِيَةِ ( 1 ) አል ጋሺያህ - Aya 1
የሸፋኝቱ (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን? አል ጋሺያህ - Aya 1
وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ خَاشِعَةٌ ( 2 ) አል ጋሺያህ - Aya 2
ፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 2
عَامِلَةٌ نَّاصِبَةٌ ( 3 ) አል ጋሺያህ - Aya 3
ሠሪዎች ለፊዎች ናቸው፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 3
تَصْلَىٰ نَارًا حَامِيَةً ( 4 ) አል ጋሺያህ - Aya 4
ተኳሳን እሳት ይገባሉ፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 4
تُسْقَىٰ مِنْ عَيْنٍ آنِيَةٍ ( 5 ) አል ጋሺያህ - Aya 5
በጣም ከፈላች ምንጭ ይጋታሉ፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 5
لَّيْسَ لَهُمْ طَعَامٌ إِلَّا مِن ضَرِيعٍ ( 6 ) አል ጋሺያህ - Aya 6
ለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 6
لَّا يُسْمِنُ وَلَا يُغْنِي مِن جُوعٍ ( 7 ) አል ጋሺያህ - Aya 7
የማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 7
وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاعِمَةٌ ( 8 ) አል ጋሺያህ - Aya 8
ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 8
لِّسَعْيِهَا رَاضِيَةٌ ( 9 ) አል ጋሺያህ - Aya 9
ለሥራቸው ተደሳቾች ናቸው፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 9
فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ ( 10 ) አል ጋሺያህ - Aya 10
በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 10
لَّا تَسْمَعُ فِيهَا لَاغِيَةً ( 11 ) አል ጋሺያህ - Aya 11
በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 11
فِيهَا عَيْنٌ جَارِيَةٌ ( 12 ) አል ጋሺያህ - Aya 12
በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አልሉ፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 12
فِيهَا سُرُرٌ مَّرْفُوعَةٌ ( 13 ) አል ጋሺያህ - Aya 13
በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አልሉ፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 13
وَأَكْوَابٌ مَّوْضُوعَةٌ ( 14 ) አል ጋሺያህ - Aya 14
በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 14
وَنَمَارِقُ مَصْفُوفَةٌ ( 15 ) አል ጋሺያህ - Aya 15
የተደረደሩ መከዳዎችም፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 15
وَزَرَابِيُّ مَبْثُوثَةٌ ( 16 ) አል ጋሺያህ - Aya 16
የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አልሉ)፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 16
أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى الْإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ ( 17 ) አል ጋሺያህ - Aya 17
(ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች! አል ጋሺያህ - Aya 17
وَإِلَى السَّمَاءِ كَيْفَ رُفِعَتْ ( 18 ) አል ጋሺያህ - Aya 18
ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች! አል ጋሺያህ - Aya 18
وَإِلَى الْجِبَالِ كَيْفَ نُصِبَتْ ( 19 ) አል ጋሺያህ - Aya 19
ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ! አል ጋሺያህ - Aya 19
وَإِلَى الْأَرْضِ كَيْفَ سُطِحَتْ ( 20 ) አል ጋሺያህ - Aya 20
ወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?) አል ጋሺያህ - Aya 20
فَذَكِّرْ إِنَّمَا أَنتَ مُذَكِّرٌ ( 21 ) አል ጋሺያህ - Aya 21
አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 21
لَّسْتَ عَلَيْهِم بِمُصَيْطِرٍ ( 22 ) አል ጋሺያህ - Aya 22
በእነርሱ ላይ ተሿሚ (አስገዳጅ) አይደለህም፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 22
إِلَّا مَن تَوَلَّىٰ وَكَفَرَ ( 23 ) አል ጋሺያህ - Aya 23
ግን (ከእውነት) የዞረና የካደ ሰው፤ አል ጋሺያህ - Aya 23
فَيُعَذِّبُهُ اللَّهُ الْعَذَابَ الْأَكْبَرَ ( 24 ) አል ጋሺያህ - Aya 24
አላህ ታላቁን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 24
إِنَّ إِلَيْنَا إِيَابَهُمْ ( 25 ) አል ጋሺያህ - Aya 25
መመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 25
ثُمَّ إِنَّ عَلَيْنَا حِسَابَهُم ( 26 ) አል ጋሺያህ - Aya 26
ከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡ አል ጋሺያህ - Aya 26
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah