Surah ሰበእ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah ሰበእ - Aya count 54
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَلَهُ الْحَمْدُ فِي الْآخِرَةِ ۚ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْخَبِيرُ ( 1 ) ሰበእ - Aya 1
ምስጋና ለዚያ በሰማያትም ያለ በምድርም ያለ ሁሉ የርሱ ለኾነው ለአላህ ይገባው፡፡ በመጨረሻይቱም ዓለም ምስጋና ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ብልሃተኛው ውስጠ ዐዋቂው ነው፡፡ ሰበእ - Aya 1
يَعْلَمُ مَا يَلِجُ فِي الْأَرْضِ وَمَا يَخْرُجُ مِنْهَا وَمَا يَنزِلُ مِنَ السَّمَاءِ وَمَا يَعْرُجُ فِيهَا ۚ وَهُوَ الرَّحِيمُ الْغَفُورُ ( 2 ) ሰበእ - Aya 2
በምድር ውስጥ የሚገባውን ሁሉ ከእርሷም የሚወጣውን ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን ሁሉ ያውቃል፡፡ እርሱም አዛኙ መሓሪው ነው፡፡ ሰበእ - Aya 2
وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَا تَأْتِينَا السَّاعَةُ ۖ قُلْ بَلَىٰ وَرَبِّي لَتَأْتِيَنَّكُمْ عَالِمِ الْغَيْبِ ۖ لَا يَعْزُبُ عَنْهُ مِثْقَالُ ذَرَّةٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ وَلَا أَصْغَرُ مِن ذَٰلِكَ وَلَا أَكْبَرُ إِلَّا فِي كِتَابٍ مُّبِينٍ ( 3 ) ሰበእ - Aya 3
እነዚያ የካዱትም «ሰዓቲቱ አትመጣብንም» አሉ፡፡ በላቸው «አይደለም፤ ሩቁን ሁሉ ዐዋቂ በኾነው ጌታዬ እምላለሁ፡፡ በእርግጥ ትመጣባችኋለች፡፡ የብናኝ ክብደት ያክል እንኳ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከእርሱ አይርቅም፡፡ ከዚህ ያነሰም ኾነ የበለጠ የለም በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢኾን እንጅ፡፡» ሰበእ - Aya 3
لِّيَجْزِيَ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ ۚ أُولَٰئِكَ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ ( 4 ) ሰበእ - Aya 4
እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ሊመነዳ (ሰዓቲቱ ትመጣባችኋለች)፤ እነዚያ ለእነርሱ ምህረትና የከበረ ሲሳይ አላቸው፡፡ ሰበእ - Aya 4
وَالَّذِينَ سَعَوْا فِي آيَاتِنَا مُعَاجِزِينَ أُولَٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مِّن رِّجْزٍ أَلِيمٌ ( 5 ) ሰበእ - Aya 5
እነዚያም የሚያመልጡ መስሏቸው አንቀጾቻችንን ለማፍረስ የጣሩ እነዚያ ለእነርሱ ከመጥፎ ቅጣት የኾነ አሳማሚ ስቃይ አላቸው፡፡ ሰበእ - Aya 5
وَيَرَى الَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ الَّذِي أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ هُوَ الْحَقَّ وَيَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطِ الْعَزِيزِ الْحَمِيدِ ( 6 ) ሰበእ - Aya 6
እነዚያም ዕውቀትን የተሰጡት ያንን ከጌታህ ወዳንተ የተወረደውን እርሱ እውነትና አሸናፊ ምስጉን ወደ ኾነው አላህ መንገድ የሚመራ መኾኑን ያውቃሉ፡፡ ሰበእ - Aya 6
وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا هَلْ نَدُلُّكُمْ عَلَىٰ رَجُلٍ يُنَبِّئُكُمْ إِذَا مُزِّقْتُمْ كُلَّ مُمَزَّقٍ إِنَّكُمْ لَفِي خَلْقٍ جَدِيدٍ ( 7 ) ሰበእ - Aya 7
እነዚያም የካዱት «(ሙታችሁ) መበጣጠስን ሁሉ በተበጣጠሳችሁ ጊዜ እናንተ በአዲስ መፈጠር ውስጥ ትኾናላችሁ ብሎ የሚነግራችሁን ሰው እናሳያችሁን?» አሉ፡፡ ሰበእ - Aya 7
أَفْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا أَم بِهِ جِنَّةٌ ۗ بَلِ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ فِي الْعَذَابِ وَالضَّلَالِ الْبَعِيدِ ( 8 ) ሰበእ - Aya 8
በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈን? ወይስ በእርሱ ዕብደት አለበትን? (አሉ)፡፡ እንዳሉት አይደለም፡፡ እነዚያ በመጨረሻይቱ (ዓለም) የሚያምኑት (በእርሷ) በቅጣት ውስጥ (አሁን) በራቀ ስህተትም ውስጥ ናቸው፡፡ ሰበእ - Aya 8
أَفَلَمْ يَرَوْا إِلَىٰ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُم مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ ۚ إِن نَّشَأْ نَخْسِفْ بِهِمُ الْأَرْضَ أَوْ نُسْقِطْ عَلَيْهِمْ كِسَفًا مِّنَ السَّمَاءِ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّكُلِّ عَبْدٍ مُّنِيبٍ ( 9 ) ሰበእ - Aya 9
ከሰማይና ከምድር በፊታቸውና በኋላቸው ወዳለው ሁሉ አይመለከቱምን? ብንሻ በእነርሱ ምድርን እንደረባባቸዋለን፡፡ ወይም በእነርሱ ላይ ከሰማይ ቁራጭን እንጥልባቸዋለን፤ በዚህ ውስጥ (ወደ ጌታው) ተመላሽ ለኾነ ባሪያ ሁሉ ምልክት አለበት፡፡ ሰበእ - Aya 9
وَلَقَدْ آتَيْنَا دَاوُودَ مِنَّا فَضْلًا ۖ يَا جِبَالُ أَوِّبِي مَعَهُ وَالطَّيْرَ ۖ وَأَلَنَّا لَهُ الْحَدِيدَ ( 10 ) ሰበእ - Aya 10
ለዳውድም ከእኛ የኾነን ችሮታ በእርግጥ ሰጠነው፡፡ (አልንም)፡-«ተራራዎች ሆይ! ከእርሱ ጋር ውዳሴን መላልሱ፡፡ በራሪዎችንም (ገራንለት)፡፡ ብረትንም ለእርሱ አለዘብንለት፡፡» ሰበእ - Aya 10
أَنِ اعْمَلْ سَابِغَاتٍ وَقَدِّرْ فِي السَّرْدِ ۖ وَاعْمَلُوا صَالِحًا ۖ إِنِّي بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ ( 11 ) ሰበእ - Aya 11
ሰፋፊዎችን ጥሩሮች ሥራ፡፡ በአሠራርዋም መጥን፡፡ መልካምንም ሥራ ሥሩ፡፡ እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና (አልነው)፡፡ ሰበእ - Aya 11
وَلِسُلَيْمَانَ الرِّيحَ غُدُوُّهَا شَهْرٌ وَرَوَاحُهَا شَهْرٌ ۖ وَأَسَلْنَا لَهُ عَيْنَ الْقِطْرِ ۖ وَمِنَ الْجِنِّ مَن يَعْمَلُ بَيْنَ يَدَيْهِ بِإِذْنِ رَبِّهِ ۖ وَمَن يَزِغْ مِنْهُمْ عَنْ أَمْرِنَا نُذِقْهُ مِنْ عَذَابِ السَّعِيرِ ( 12 ) ሰበእ - Aya 12
ለሱለይማንም ነፋስን የቀትር በፊት ጉዞዋ የወር መንገድ የቀትር በኋላ ጉዞዋም የወር መንገድ ሲኾን ገራንለት፡፡ የነሐስንም ምንጭ ለእርሱ አፈሰስንለት፡፡ ከጋኔኖችም በጌታው ፈቃድ በፊቱ የሚሠሩን (አደረግንለት)፡፡ ከነርሱም ውስጥ ከትእዛዛችን ዝንፍ የሚል ከነዲድ እሳት ቅጣት እናቀምሰዋለን፡፡ ሰበእ - Aya 12
يَعْمَلُونَ لَهُ مَا يَشَاءُ مِن مَّحَارِيبَ وَتَمَاثِيلَ وَجِفَانٍ كَالْجَوَابِ وَقُدُورٍ رَّاسِيَاتٍ ۚ اعْمَلُوا آلَ دَاوُودَ شُكْرًا ۚ وَقَلِيلٌ مِّنْ عِبَادِيَ الشَّكُورُ ( 13 ) ሰበእ - Aya 13
ከምኩራቦች፣ ከምስሎችም እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል፡፡ (አልናቸውም) «የዳውድ ቤተሰቦች ሆይ! አመስጋኞች ኾናችሁ (ለጌታችሁ) ሥሩ፡፡» ከባሮቼ በጣም አመስጋኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ሰበእ - Aya 13
فَلَمَّا قَضَيْنَا عَلَيْهِ الْمَوْتَ مَا دَلَّهُمْ عَلَىٰ مَوْتِهِ إِلَّا دَابَّةُ الْأَرْضِ تَأْكُلُ مِنسَأَتَهُ ۖ فَلَمَّا خَرَّ تَبَيَّنَتِ الْجِنُّ أَن لَّوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ الْغَيْبَ مَا لَبِثُوا فِي الْعَذَابِ الْمُهِينِ ( 14 ) ሰበእ - Aya 14
በእርሱም ላይ ሞትን በፈጸምንበት ጊዜ መሞቱን በትሩን የምትበላ ተንቀሳቃሽ ምስጥ እንጂ ሌላ አላመለከታቸውም፡፡ በወደቀ ጊዜም ጋኔኖች ሩቅን ምስጢር የሚያወቁ በኾኑ ኖሮ በአዋራጅ ስቃይ ውስጥ የማይቆይ እንደነበሩ ተረዱ፡፡ ሰበእ - Aya 14
لَقَدْ كَانَ لِسَبَإٍ فِي مَسْكَنِهِمْ آيَةٌ ۖ جَنَّتَانِ عَن يَمِينٍ وَشِمَالٍ ۖ كُلُوا مِن رِّزْقِ رَبِّكُمْ وَاشْكُرُوا لَهُ ۚ بَلْدَةٌ طَيِّبَةٌ وَرَبٌّ غَفُورٌ ( 15 ) ሰበእ - Aya 15
ለሰበእ በመኖሪያቸው በእውነት አስደናቂ ምልክት ነበራቸው፡፡ ከግራና ከቀኝ ሁለት አትክልቶች (ነበሯቸው)፡፡ «ከጌታችሁ ሲሳይ ብሉ፡፡ ለእርሱም አመስግኑ፡፡ (አገራችሁ) ውብ አገር ናት፡፡ (ጌታችሁ) መሓሪ ጌታም ነው» (ተባሉ)፡፡ ሰበእ - Aya 15
فَأَعْرَضُوا فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ سَيْلَ الْعَرِمِ وَبَدَّلْنَاهُم بِجَنَّتَيْهِمْ جَنَّتَيْنِ ذَوَاتَيْ أُكُلٍ خَمْطٍ وَأَثْلٍ وَشَيْءٍ مِّن سِدْرٍ قَلِيلٍ ( 16 ) ሰበእ - Aya 16
(ከማመስገን) ዞሩም፡፡ በእነርሱም ላይ የግድቡን ጎርፍ ለቀቅንባቸው፡፡ በአትክልቶቻቸውም ሁለት አትክልቶች፣ ባለመርጋጋ ፍሬዎችን፣ ባለጠደቻና ከቁርቁራም ባለጥቂት ዛፎችን ለወጥናቸው፡፡ ሰበእ - Aya 16
ذَٰلِكَ جَزَيْنَاهُم بِمَا كَفَرُوا ۖ وَهَلْ نُجَازِي إِلَّا الْكَفُورَ ( 17 ) ሰበእ - Aya 17
በመካዳቸው ይህንን መነዳናቸው፤ (እንዲህ ያለውን ቅጣት) በጣም ከሓዲን እንጂ ሌላውን እንቀጣለን? ሰበእ - Aya 17
وَجَعَلْنَا بَيْنَهُمْ وَبَيْنَ الْقُرَى الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا قُرًى ظَاهِرَةً وَقَدَّرْنَا فِيهَا السَّيْرَ ۖ سِيرُوا فِيهَا لَيَالِيَ وَأَيَّامًا آمِنِينَ ( 18 ) ሰበእ - Aya 18
በእነርሱና በዚያች በውስጧ በረከትን ባደረግንባት አገር (በሻም) መካከልም ቅጥልጥል ከተሞችን አደረግን፡፡ በእርሷም ጉዞን ወሰንን፡፡ «ጸጥተኞች ኾናችሁ በሌሊቶችም በቀኖችም ተጓዙ፤» (አልን)፡፡ ሰበእ - Aya 18
فَقَالُوا رَبَّنَا بَاعِدْ بَيْنَ أَسْفَارِنَا وَظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ فَجَعَلْنَاهُمْ أَحَادِيثَ وَمَزَّقْنَاهُمْ كُلَّ مُمَزَّقٍ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّكُلِّ صَبَّارٍ شَكُورٍ ( 19 ) ሰበእ - Aya 19
«ጌታችን ሆይ! በጉዞዎቻችን መካከል አራርቅልን» አሉም፡፡ ነፍሶቻቸውንም በደሉ፡፡ (መገረሚያ) ወሬዎችም አደረግናቸው፡፡ መበታተንንም ሁሉ በታተንናቸው፡፡ በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለሆነ ሁሉ መገሰጫዎች አሉበት፡፡ ሰበእ - Aya 19
وَلَقَدْ صَدَّقَ عَلَيْهِمْ إِبْلِيسُ ظَنَّهُ فَاتَّبَعُوهُ إِلَّا فَرِيقًا مِّنَ الْمُؤْمِنِينَ ( 20 ) ሰበእ - Aya 20
ኢብሊስም በእነርሱ ላይ ምኞቱን በእርግጥ ፈጸመ፤ ከአመኑትም የሆኑት ጭፍሮች በስተቀር ተከተሉት፡፡ ሰበእ - Aya 20
وَمَا كَانَ لَهُ عَلَيْهِم مِّن سُلْطَانٍ إِلَّا لِنَعْلَمَ مَن يُؤْمِنُ بِالْآخِرَةِ مِمَّنْ هُوَ مِنْهَا فِي شَكٍّ ۗ وَرَبُّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ حَفِيظٌ ( 21 ) ሰበእ - Aya 21
በመጨረሻይቱም ዓለም የሚያምነውን ከዚያ እርሱ ከእርሷ በመጠራጠር ውስጥ ከሆነው ሰው ለይተን እንድናውቅ እንጅ በእነርሱ ላይ ለእርሱ ምንም ስልጣን አልነበረውም፡፡ ጌታህም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ ሰበእ - Aya 21
قُلِ ادْعُوا الَّذِينَ زَعَمْتُم مِّن دُونِ اللَّهِ ۖ لَا يَمْلِكُونَ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ وَمَا لَهُمْ فِيهِمَا مِن شِرْكٍ وَمَا لَهُ مِنْهُم مِّن ظَهِيرٍ ( 22 ) ሰበእ - Aya 22
«እነዚያን ከአላህ ሌላ (አማልክት ብላችሁ) የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም፡፡ ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸውም፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለውም፤» በላቸው፡፡ ሰበእ - Aya 22
وَلَا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ عِندَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ ۚ حَتَّىٰ إِذَا فُزِّعَ عَن قُلُوبِهِمْ قَالُوا مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ ۖ قَالُوا الْحَقَّ ۖ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ ( 23 ) ሰበእ - Aya 23
ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም፡፡ ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጸም ጊዜ (ተማላጆቹ) «ጌታችሁ ምን አለ?» ይላሉ፡፡ (አማላጆቹ) «እውነትን አለ፤ እርሱም ከፍተኛው ታላቁ ጌታ ነው» ይላሉ፡፡ ሰበእ - Aya 23
قُلْ مَن يَرْزُقُكُم مِّنَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ قُلِ اللَّهُ ۖ وَإِنَّا أَوْ إِيَّاكُمْ لَعَلَىٰ هُدًى أَوْ فِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ ( 24 ) ሰበእ - Aya 24
«ከሰማያትና ከምድር (ዝናብንና በቃይን) የሚሰጣችሁ ማነው?» በላቸው፡፡ «አላህ ነው፡፡ እኛ ወይም እናንተ በትክክለኛው መንገድ ላይ ወይም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነን» በላቸው፡፡ ሰበእ - Aya 24
قُل لَّا تُسْأَلُونَ عَمَّا أَجْرَمْنَا وَلَا نُسْأَلُ عَمَّا تَعْمَلُونَ ( 25 ) ሰበእ - Aya 25
«ከአጠፋነው ጥፋት አትጠየቁም፡፡ ከምትሠሩትም ሥራ አንጠየቅም» በላቸው፡፡ ሰበእ - Aya 25
قُلْ يَجْمَعُ بَيْنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفْتَحُ بَيْنَنَا بِالْحَقِّ وَهُوَ الْفَتَّاحُ الْعَلِيمُ ( 26 ) ሰበእ - Aya 26
«ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል፡፡ እርሱም በትክክል ፈራጁ ዐዋቂው ነው» በላቸው፡፡ ሰበእ - Aya 26
قُلْ أَرُونِيَ الَّذِينَ أَلْحَقْتُم بِهِ شُرَكَاءَ ۖ كَلَّا ۚ بَلْ هُوَ اللَّهُ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ ( 27 ) ሰበእ - Aya 27
«እነዚያን ተጋሪዎች አድርጋችሁ በእርሱ ያስጠጋችኋቸውን (ጣዖታት) አሳዩኝ፡፡ ተዉ (አታጋሩ)፤ በእውነቱ እርሱ አሸናፊው ብልሃተኛው አላህ ነው» በላቸው፡፡ ሰበእ - Aya 27
وَمَا أَرْسَلْنَاكَ إِلَّا كَافَّةً لِّلنَّاسِ بَشِيرًا وَنَذِيرًا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ ( 28 ) ሰበእ - Aya 28
አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አላክንህም፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ ሰበእ - Aya 28
وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا الْوَعْدُ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ ( 29 ) ሰበእ - Aya 29
«እውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ፡፡ ሰበእ - Aya 29
قُل لَّكُم مِّيعَادُ يَوْمٍ لَّا تَسْتَأْخِرُونَ عَنْهُ سَاعَةً وَلَا تَسْتَقْدِمُونَ ( 30 ) ሰበእ - Aya 30
«ለእናንተ ከእርሱ አንዲትንም ሰዓት የማትዘገዩበት የማትቀድሙበትም የቀጠሮ ቀን አላችሁ» በላቸው፡፡ ሰበእ - Aya 30
وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَن نُّؤْمِنَ بِهَٰذَا الْقُرْآنِ وَلَا بِالَّذِي بَيْنَ يَدَيْهِ ۗ وَلَوْ تَرَىٰ إِذِ الظَّالِمُونَ مَوْقُوفُونَ عِندَ رَبِّهِمْ يَرْجِعُ بَعْضُهُمْ إِلَىٰ بَعْضٍ الْقَوْلَ يَقُولُ الَّذِينَ اسْتُضْعِفُوا لِلَّذِينَ اسْتَكْبَرُوا لَوْلَا أَنتُمْ لَكُنَّا مُؤْمِنِينَ ( 31 ) ሰበእ - Aya 31
እነዚያ የካዱትም በዚህ ቁርኣን በዚያ ከበፊቱ ባለውም (መጽሐፍ) በጭራሽ አናምንም አሉ፡፡ በዳዮችም ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ንግግርን የሚመላለሱ ሆነው በጌታቸው ዘንድ በሚቆሙ ጊዜ ብታይ ኖሮ፤ (አስደናቂን ነገር ታይ ነበር)፡፡ እነዚያ የተዋረዱት ለእነዚያ ለኮሩት «እናንተ ባልነበራችሁ ኖሮ አማኞች በኾን ነበር» ይላሉ፡፡ ሰበእ - Aya 31
قَالَ الَّذِينَ اسْتَكْبَرُوا لِلَّذِينَ اسْتُضْعِفُوا أَنَحْنُ صَدَدْنَاكُمْ عَنِ الْهُدَىٰ بَعْدَ إِذْ جَاءَكُم ۖ بَلْ كُنتُم مُّجْرِمِينَ ( 32 ) ሰበእ - Aya 32
እነዚያ የኮሩት ለእነዚያ ለተዋረዱት «ከትክክለኛው እምነት ከመጣላችሁ በኋላ እኛ ከለከልናችሁን? አይደለም (እናንተው) ከሓዲዎች ነበራችሁ» ይሏቸዋል፡፡ ሰበእ - Aya 32
وَقَالَ الَّذِينَ اسْتُضْعِفُوا لِلَّذِينَ اسْتَكْبَرُوا بَلْ مَكْرُ اللَّيْلِ وَالنَّهَارِ إِذْ تَأْمُرُونَنَا أَن نَّكْفُرَ بِاللَّهِ وَنَجْعَلَ لَهُ أَندَادًا ۚ وَأَسَرُّوا النَّدَامَةَ لَمَّا رَأَوُا الْعَذَابَ وَجَعَلْنَا الْأَغْلَالَ فِي أَعْنَاقِ الَّذِينَ كَفَرُوا ۚ هَلْ يُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ ( 33 ) ሰበእ - Aya 33
እነዚያም የተዋረዱት ለእነዚያ ለኮሩት «አይደለም፤ በአላህ እንድንክድና ለእርሱ ባላንጣዎችን እንድናደርግ ስታዙን (የከለከለን) የሌሊትና የቀን ዱለታችሁ ነው» ይላሉ፡፡ ቅጣቱንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይገልጻሉ፡፡ በእነዚያም በካዱት አንገቶች ላይ እንዛዝሎችን እናደርጋለን፡፡ ይሠሩት የነበሩትን እንጂ ሌላን ይመነዳሉን? ሰበእ - Aya 33
وَمَا أَرْسَلْنَا فِي قَرْيَةٍ مِّن نَّذِيرٍ إِلَّا قَالَ مُتْرَفُوهَا إِنَّا بِمَا أُرْسِلْتُم بِهِ كَافِرُونَ ( 34 ) ሰበእ - Aya 34
በከተማም አስፈራሪን አልላክንም፡፡ ነዋሪዎችዋ «እኛ በዚያ በርሱ በተላካችሁበት ከሓዲዎች ነን» ያሉ ቢኾኑ እንጂ፡፡ ሰበእ - Aya 34
وَقَالُوا نَحْنُ أَكْثَرُ أَمْوَالًا وَأَوْلَادًا وَمَا نَحْنُ بِمُعَذَّبِينَ ( 35 ) ሰበእ - Aya 35
«እኛም በገንዘቦችና በልጆች ይበልጥ የበዛን ነን፡፡ እኛም የምንቀጣ አይደለንም» አሉ፡፡ ሰበእ - Aya 35
قُلْ إِنَّ رَبِّي يَبْسُطُ الرِّزْقَ لِمَن يَشَاءُ وَيَقْدِرُ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ ( 36 ) ሰበእ - Aya 36
በላቸው «ጌታዬ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ያጠባልም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡» ሰበእ - Aya 36
وَمَا أَمْوَالُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُم بِالَّتِي تُقَرِّبُكُمْ عِندَنَا زُلْفَىٰ إِلَّا مَنْ آمَنَ وَعَمِلَ صَالِحًا فَأُولَٰئِكَ لَهُمْ جَزَاءُ الضِّعْفِ بِمَا عَمِلُوا وَهُمْ فِي الْغُرُفَاتِ آمِنُونَ ( 37 ) ሰበእ - Aya 37
ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁም ያች እኛ ዘንድ መቅረብን የምታቀርባችሁ አይደለችም፡፡ ያመነና መልካምን የሠራ ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያ ለእነርሱ በሠሩት መልካም ሥራ እጥፍ ምንዳ አልላቸው፡፡ እነርሱም በገነት ሰገነቶች ውስጥ ጸጥተኞች ናቸው፡፡ ሰበእ - Aya 37
وَالَّذِينَ يَسْعَوْنَ فِي آيَاتِنَا مُعَاجِزِينَ أُولَٰئِكَ فِي الْعَذَابِ مُحْضَرُونَ ( 38 ) ሰበእ - Aya 38
እነዚያም የሚያቅቱ መስሏቸው አንቀጾቻችንን ለማበላሸት የሚጥሩት እነዚያ በቅጣቱ ውስጥ የሚጣዱ ናቸው፡፡ ሰበእ - Aya 38
قُلْ إِنَّ رَبِّي يَبْسُطُ الرِّزْقَ لِمَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ وَيَقْدِرُ لَهُ ۚ وَمَا أَنفَقْتُم مِّن شَيْءٍ فَهُوَ يُخْلِفُهُ ۖ وَهُوَ خَيْرُ الرَّازِقِينَ ( 39 ) ሰበእ - Aya 39
«ጌታዬ ሲሳይን ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ያሰፋል፡፡ ለእርሱም ያጠብባል፡፡ ከማንኛውም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል፡፡ እርሱም ከሲሳይ ሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው» በላቸው፡፡ ሰበእ - Aya 39
وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا ثُمَّ يَقُولُ لِلْمَلَائِكَةِ أَهَٰؤُلَاءِ إِيَّاكُمْ كَانُوا يَعْبُدُونَ ( 40 ) ሰበእ - Aya 40
ሁሉንም በሚሰበስባቸውና ከዚያም ለመላእክቶቹ «እነዚህ እናንተን ይግገዙ ነበሩን?» በሚላቸው ቀን (የሚኾነውን አስታውስ)፡፡ ሰበእ - Aya 40
قَالُوا سُبْحَانَكَ أَنتَ وَلِيُّنَا مِن دُونِهِم ۖ بَلْ كَانُوا يَعْبُدُونَ الْجِنَّ ۖ أَكْثَرُهُم بِهِم مُّؤْمِنُونَ ( 41 ) ሰበእ - Aya 41
(መላእክቶቹም) «ጥራት ይገባህ ከእነርሱ ሌላ ረዳታችን አንተ ብቻ ነህ፡፡ (እንደሚሉት) አይደለም ይልቁንም ጋኔንን ይግገዙ ነበሩ፡፡ አብዛኞቻቸው በእነርሱ አማኞች ናቸው» ይላሉ፡፡ ሰበእ - Aya 41
فَالْيَوْمَ لَا يَمْلِكُ بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ نَّفْعًا وَلَا ضَرًّا وَنَقُولُ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا ذُوقُوا عَذَابَ النَّارِ الَّتِي كُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ ( 42 ) ሰበእ - Aya 42
ዛሬም ከፊላችሁ ለከፊሉ መጥቀምንም ኾነ መጉዳትን አይችሉም፡፡ ለእነዚያም ለበደሉት «ያችን በእርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁትን የእሳት ቅጣት ቅመሱ» እንላቸዋለን፡፡ ሰበእ - Aya 42
وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ قَالُوا مَا هَٰذَا إِلَّا رَجُلٌ يُرِيدُ أَن يَصُدَّكُمْ عَمَّا كَانَ يَعْبُدُ آبَاؤُكُمْ وَقَالُوا مَا هَٰذَا إِلَّا إِفْكٌ مُّفْتَرًى ۚ وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِلْحَقِّ لَمَّا جَاءَهُمْ إِنْ هَٰذَا إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ ( 43 ) ሰበእ - Aya 43
በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጽ ኾነው በተነበቡላቸው ጊዜ «ይህ አባቶቻችሁ ይግገዙት ከነበሩት ነገር ሊከለክላችሁ የሚፈልግ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም» አሉ፡፡ «ይህም (ቁርኣን) የተቀጣጠፈ ውሸት ነው እንጂ ሌላ አይደለም» አሉ፡፡ እነዚያም የካዱት እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው እንጂ ሌላ አይደለም» አሉ፡፡ ሰበእ - Aya 43
وَمَا آتَيْنَاهُم مِّن كُتُبٍ يَدْرُسُونَهَا ۖ وَمَا أَرْسَلْنَا إِلَيْهِمْ قَبْلَكَ مِن نَّذِيرٍ ( 44 ) ሰበእ - Aya 44
የሚያጠኑዋቸው የኾኑ መጽሐፍቶችንም ምንም አልሰጠናቸውም፡፡ ከአንተ በፊትም አስፈራሪ ነቢይን ወደእነርሱ አልላክንም፡፡ ሰበእ - Aya 44
وَكَذَّبَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ وَمَا بَلَغُوا مِعْشَارَ مَا آتَيْنَاهُمْ فَكَذَّبُوا رُسُلِي ۖ فَكَيْفَ كَانَ نَكِيرِ ( 45 ) ሰበእ - Aya 45
እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል፡፡ የሰጠናቸውንም ከዐስር አንዱን (እነዚህ) አልደረሱም፡፡ መልክተኞቼንም አስተባበሉ፤ (ነቀፍኳቸውም)፡፡ መንቀፌም እንዴት ነበር! ሰበእ - Aya 45
قُلْ إِنَّمَا أَعِظُكُم بِوَاحِدَةٍ ۖ أَن تَقُومُوا لِلَّهِ مَثْنَىٰ وَفُرَادَىٰ ثُمَّ تَتَفَكَّرُوا ۚ مَا بِصَاحِبِكُم مِّن جِنَّةٍ ۚ إِنْ هُوَ إِلَّا نَذِيرٌ لَّكُم بَيْنَ يَدَيْ عَذَابٍ شَدِيدٍ ( 46 ) ሰበእ - Aya 46
«የምገስጻችሁ ባንዲት ነገር ብቻ ነው፡፡ (እርሷም) ሁለት ሁለት አንድ አንድም ኾናችሁ ለአላህ እንድትነሱ ከዚያም በጓደኛችሁ (በሙሐመድ) ምንም ዕብደት የሌለበት መኾኑን መርምራችሁ እንድትርረዱ ነው፡፡ እርሱ ለእናንተ ከብርቱ ቅጣት በስተፊት አስጠንቃቂ ነው እንጂ ሌላ አይደለም» በላቸው፡፡ ሰበእ - Aya 46
قُلْ مَا سَأَلْتُكُم مِّنْ أَجْرٍ فَهُوَ لَكُمْ ۖ إِنْ أَجْرِيَ إِلَّا عَلَى اللَّهِ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ ( 47 ) ሰበእ - Aya 47
«ከዋጋ ማንኛውም የጠየቅኋችሁ ቢኖር እርሱ ለእናንተው ነው፤ ዋጋዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡ ሰበእ - Aya 47
قُلْ إِنَّ رَبِّي يَقْذِفُ بِالْحَقِّ عَلَّامُ الْغُيُوبِ ( 48 ) ሰበእ - Aya 48
«ጌታዬ እውነትን ያወርዳል፡፡ ሩቅ የኾኑትን ምስጢሮች ሁሉ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡ ሰበእ - Aya 48
قُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ ( 49 ) ሰበእ - Aya 49
«እውነቱ መጣ፡፡ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም (ተወገደ)» በላቸው፡፡ ሰበእ - Aya 49
قُلْ إِن ضَلَلْتُ فَإِنَّمَا أَضِلُّ عَلَىٰ نَفْسِي ۖ وَإِنِ اهْتَدَيْتُ فَبِمَا يُوحِي إِلَيَّ رَبِّي ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ قَرِيبٌ ( 50 ) ሰበእ - Aya 50
«ብሳሳት የምሳሳተው በራሴ ላይ ብቻ ነው፡፡ ብመራም ጌታዬ ወደኔ በሚያወርደው ነው፡፡ እርሱ ሰሚ ቅርብ ነውና» በላቸው፡፡ ሰበእ - Aya 50
وَلَوْ تَرَىٰ إِذْ فَزِعُوا فَلَا فَوْتَ وَأُخِذُوا مِن مَّكَانٍ قَرِيبٍ ( 51 ) ሰበእ - Aya 51
በደነገጡና ማምለጫ በሌላቸው ጊዜ ከቅርብ ስፍራም በተያዙ ጊዜ (ኹኔታቸውን) ብታይ ኖሮ (አስደናቂን ነገር ባየህ ነበር)፡፡ ሰበእ - Aya 51
وَقَالُوا آمَنَّا بِهِ وَأَنَّىٰ لَهُمُ التَّنَاوُشُ مِن مَّكَانٍ بَعِيدٍ ( 52 ) ሰበእ - Aya 52
«በእርሱም (አሁን) አመንን» ይላሉ፡፡ ለእነርሱም ከሩቅ ስፍራ (እምነትን) በቀላል ማግኘት ከየታቸው? ሰበእ - Aya 52
وَقَدْ كَفَرُوا بِهِ مِن قَبْلُ ۖ وَيَقْذِفُونَ بِالْغَيْبِ مِن مَّكَانٍ بَعِيدٍ ( 53 ) ሰበእ - Aya 53
በፊትም በእርሱ በእርግጥ ክደዋል፡፡ ከሩቅ ስፍራም በግምት ንግግርን ይጥላሉ፡፡ ሰበእ - Aya 53
وَحِيلَ بَيْنَهُمْ وَبَيْنَ مَا يَشْتَهُونَ كَمَا فُعِلَ بِأَشْيَاعِهِم مِّن قَبْلُ ۚ إِنَّهُمْ كَانُوا فِي شَكٍّ مُّرِيبٍ ( 54 ) ሰበእ - Aya 54
ከዚህ ቀደም በመሰሎቻቸው እንደ ተሠራውም ብጤ በእነርሱና በሚፈልጉት መካከል ተጋረደ፡፡ እነርሱ በእርግጥ በአወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ነበሩና፡፡ ሰበእ - Aya 54
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah