Surah አል ሙደሲር

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ሙደሲር - Aya count 56
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
يَا أَيُّهَا الْمُدَّثِّرُ ( 1 ) አል ሙደሲር - Aya 1
አንተ (ልብስህን) ደራቢው ሆይ! አል ሙደሲር - Aya 1
قُمْ فَأَنذِرْ ( 2 ) አል ሙደሲር - Aya 2
ተነሳ አስጠንቅቅም፡፡ አል ሙደሲር - Aya 2
وَرَبَّكَ فَكَبِّرْ ( 3 ) አል ሙደሲር - Aya 3
ጌታህንም አክብር፡፡ አል ሙደሲር - Aya 3
وَثِيَابَكَ فَطَهِّرْ ( 4 ) አል ሙደሲር - Aya 4
ልብስህንም አጥራ፡፡ አል ሙደሲር - Aya 4
وَالرُّجْزَ فَاهْجُرْ ( 5 ) አል ሙደሲር - Aya 5
ጣዖትንም ራቅ፡፡ አል ሙደሲር - Aya 5
وَلَا تَمْنُن تَسْتَكْثِرُ ( 6 ) አል ሙደሲር - Aya 6
ማብዛትንም የምትፈልግ ኾነህ፤ (በረከትን) አትለግስለለ አል ሙደሲር - Aya 6
وَلِرَبِّكَ فَاصْبِرْ ( 7 ) አል ሙደሲር - Aya 7
ለጌታህም (ትዕዛዝ) ታገሥ፡፡ አል ሙደሲር - Aya 7
فَإِذَا نُقِرَ فِي النَّاقُورِ ( 8 ) አል ሙደሲር - Aya 8
በቀንዱም በተነፋ ጊዜ (ነገሩ ይበረታል)፡፡ አል ሙደሲር - Aya 8
فَذَٰلِكَ يَوْمَئِذٍ يَوْمٌ عَسِيرٌ ( 9 ) አል ሙደሲር - Aya 9
ይህም (ጊዜ) ያ ቀን አስቸጋሪ ቀን ነው፡፡ አል ሙደሲር - Aya 9
عَلَى الْكَافِرِينَ غَيْرُ يَسِيرٍ ( 10 ) አል ሙደሲር - Aya 10
በከሓዲዎች ላይ ገር ያልኾነ ነው፡፡ አል ሙደሲር - Aya 10
ذَرْنِي وَمَنْ خَلَقْتُ وَحِيدًا ( 11 ) አል ሙደሲር - Aya 11
አንድ ኾኖ ከፈጠርኩት ሰው ጋር ተዎኝ (እኔ እበቃሃለሁ)፡፡ አል ሙደሲር - Aya 11
وَجَعَلْتُ لَهُ مَالًا مَّمْدُودًا ( 12 ) አል ሙደሲር - Aya 12
ለእርሱም የተዘረጋን ገንዘብ (በያይነቱ) ያደረግሁለት፡፡ አል ሙደሲር - Aya 12
وَبَنِينَ شُهُودًا ( 13 ) አል ሙደሲር - Aya 13
(በያደባባዩ) ተገኝዎች የኾኑ ወንዶች ልጆችንም፡፡ አል ሙደሲር - Aya 13
وَمَهَّدتُّ لَهُ تَمْهِيدًا ( 14 ) አል ሙደሲር - Aya 14
ለእርሱም (ኑሮውን) መዘርጋትን የዘረጋሁለት (ከኾነ ሰው ገር ተዎኝ)፡፡ አል ሙደሲር - Aya 14
ثُمَّ يَطْمَعُ أَنْ أَزِيدَ ( 15 ) አል ሙደሲር - Aya 15
ከዚያም ልጨምርለት ይከጅላል፡፡ አል ሙደሲር - Aya 15
كَلَّا ۖ إِنَّهُ كَانَ لِآيَاتِنَا عَنِيدًا ( 16 ) አል ሙደሲር - Aya 16
ይከልከል፤ እርሱ ለአንቀጾቻችን በእርግጥ ተቃዋሚ ነበር፡፡ አል ሙደሲር - Aya 16
سَأُرْهِقُهُ صَعُودًا ( 17 ) አል ሙደሲር - Aya 17
በእርግጥ ችግርን አስገድደዋለሁ፡፡ አል ሙደሲር - Aya 17
إِنَّهُ فَكَّرَ وَقَدَّرَ ( 18 ) አል ሙደሲር - Aya 18
እርሱ (በቁርኣን ነገር) ሐሰበ፤ ገመተም፡፡ አል ሙደሲር - Aya 18
فَقُتِلَ كَيْفَ قَدَّرَ ( 19 ) አል ሙደሲር - Aya 19
ተረገመም፤ እንዴት ገመተ! አል ሙደሲር - Aya 19
ثُمَّ قُتِلَ كَيْفَ قَدَّرَ ( 20 ) አል ሙደሲር - Aya 20
ከዚያም (ከሞት በኋላ) ተረገመ፡፡ እንዴት ገመተ! አል ሙደሲር - Aya 20
ثُمَّ نَظَرَ ( 21 ) አል ሙደሲር - Aya 21
ከዚያም እንደ ገና (በቁርኣኑ ነገር) ተመለከተ፡፡ አል ሙደሲር - Aya 21
ثُمَّ عَبَسَ وَبَسَرَ ( 22 ) አል ሙደሲር - Aya 22
ከዚያም ፊቱን አጨፈገገ፤ አኮማተረም፡፡ አል ሙደሲር - Aya 22
ثُمَّ أَدْبَرَ وَاسْتَكْبَرَ ( 23 ) አል ሙደሲር - Aya 23
ከዚያም (ከማመን) ዞረ፤ ኮራም፡፡ አል ሙደሲር - Aya 23
فَقَالَ إِنْ هَٰذَا إِلَّا سِحْرٌ يُؤْثَرُ ( 24 ) አል ሙደሲር - Aya 24
አለም «ይህ (ከሌላ) የሚቀዳ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ አል ሙደሲር - Aya 24
إِنْ هَٰذَا إِلَّا قَوْلُ الْبَشَرِ ( 25 ) አል ሙደሲር - Aya 25
«ይህ የሰው ቃል እንጅ ሌላ አይደለም፡፡» አል ሙደሲር - Aya 25
سَأُصْلِيهِ سَقَرَ ( 26 ) አል ሙደሲር - Aya 26
በሰቀር ውስጥ በእርግጥ አገባዋለሁ፡፡ አል ሙደሲር - Aya 26
وَمَا أَدْرَاكَ مَا سَقَرُ ( 27 ) አል ሙደሲር - Aya 27
ሰቀር ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? አል ሙደሲር - Aya 27
لَا تُبْقِي وَلَا تَذَرُ ( 28 ) አል ሙደሲር - Aya 28
(ያገኘችውን ሁሉ) አታስቀርም አትተውምም፡፡ አል ሙደሲር - Aya 28
لَوَّاحَةٌ لِّلْبَشَرِ ( 29 ) አል ሙደሲር - Aya 29
ቆዳን በጣም አክሳይ ናት፡፡ አል ሙደሲር - Aya 29
عَلَيْهَا تِسْعَةَ عَشَرَ ( 30 ) አል ሙደሲር - Aya 30
በእርሷም ላይ አሥራ ዘጠኝ (ዘበኞች) አሉባት፡፡ አል ሙደሲር - Aya 30
وَمَا جَعَلْنَا أَصْحَابَ النَّارِ إِلَّا مَلَائِكَةً ۙ وَمَا جَعَلْنَا عِدَّتَهُمْ إِلَّا فِتْنَةً لِّلَّذِينَ كَفَرُوا لِيَسْتَيْقِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ وَيَزْدَادَ الَّذِينَ آمَنُوا إِيمَانًا ۙ وَلَا يَرْتَابَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ وَالْمُؤْمِنُونَ ۙ وَلِيَقُولَ الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ وَالْكَافِرُونَ مَاذَا أَرَادَ اللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلًا ۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ اللَّهُ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي مَن يَشَاءُ ۚ وَمَا يَعْلَمُ جُنُودَ رَبِّكَ إِلَّا هُوَ ۚ وَمَا هِيَ إِلَّا ذِكْرَىٰ لِلْبَشَرِ ( 31 ) አል ሙደሲር - Aya 31
የእሳትንም ዘበኞች መላእክት እንጅ ሌላ አላደረግንም፡፡ ቁጥራቸውንም ለእነዚያ ለካዱት መፈተኛ እንጅ አላደረግንም፡፡ እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት እንዲያረጋግጡ፣ እነዚያም ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፣ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምእምናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፣ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው (መናፍቃን)፣ ከሓዲዎችም አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል? እንዲሉ (እንጅ አላደረግንም)፡፡ እንደዚሁ አላህ የሚሻውን ያጠምማል፡፡ የሚሻውንም ያቀናል፡፡ የጌታህንም ሰራዊት (ልክ) ከርሱ በቀር ማንም አያውቅም፡፡ እርሷም (የሰቀር እሳት) ለሰዎች መገሰጫ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ አል ሙደሲር - Aya 31
كَلَّا وَالْقَمَرِ ( 32 ) አል ሙደሲር - Aya 32
(ከክህደት) ይከልከሉ፡፡ በጨረቃ እምላለሁ፡፡ አል ሙደሲር - Aya 32
وَاللَّيْلِ إِذْ أَدْبَرَ ( 33 ) አል ሙደሲር - Aya 33
በሌሊቱም በኼደ ጊዜ፡፡ አል ሙደሲር - Aya 33
وَالصُّبْحِ إِذَا أَسْفَرَ ( 34 ) አል ሙደሲር - Aya 34
በንጋቱም ባበራ ጊዜ፡፡ አል ሙደሲር - Aya 34
إِنَّهَا لَإِحْدَى الْكُبَرِ ( 35 ) አል ሙደሲር - Aya 35
እርሷ (ሰቀር) ከታላላቆቹ (አደጋዎች) አንዷ ናት፡፡ አል ሙደሲር - Aya 35
نَذِيرًا لِّلْبَشَرِ ( 36 ) አል ሙደሲር - Aya 36
ለሰዎች አስፈራሪ ስትኾን፡፡ አል ሙደሲር - Aya 36
لِمَن شَاءَ مِنكُمْ أَن يَتَقَدَّمَ أَوْ يَتَأَخَّرَ ( 37 ) አል ሙደሲር - Aya 37
ከእናንተ (ወደ በጎ ነገር) መቅደምን ወይም ወደ ኋላ መቅረትን ለሻ ሰው (አስፈራሪ ስትኾኑ)፡፡ አል ሙደሲር - Aya 37
كُلُّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ رَهِينَةٌ ( 38 ) አል ሙደሲር - Aya 38
ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት፡፡ አል ሙደሲር - Aya 38
إِلَّا أَصْحَابَ الْيَمِينِ ( 39 ) አል ሙደሲር - Aya 39
የቀኝ ባለቤቶች ብቻ ሲቀሩ፡፡ አል ሙደሲር - Aya 39
فِي جَنَّاتٍ يَتَسَاءَلُونَ ( 40 ) አል ሙደሲር - Aya 40
(እነርሱስ) በገነቶች ውስጥ ይጠያየቃሉ፡፡ አል ሙደሲር - Aya 40
عَنِ الْمُجْرِمِينَ ( 41 ) አል ሙደሲር - Aya 41
ከአመጸኞቹ ኹነታ፡፡ አል ሙደሲር - Aya 41
مَا سَلَكَكُمْ فِي سَقَرَ ( 42 ) አል ሙደሲር - Aya 42
(ይሏቸዋልም) «በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?» አል ሙደሲር - Aya 42
قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّينَ ( 43 ) አል ሙደሲር - Aya 43
(እነርሱም) ይላሉ «ከሰጋጆቹ አልነበርንም፡፡ አል ሙደሲር - Aya 43
وَلَمْ نَكُ نُطْعِمُ الْمِسْكِينَ ( 44 ) አል ሙደሲር - Aya 44
«ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፡፡ አል ሙደሲር - Aya 44
وَكُنَّا نَخُوضُ مَعَ الْخَائِضِينَ ( 45 ) አል ሙደሲር - Aya 45
«ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፡፡ አል ሙደሲር - Aya 45
وَكُنَّا نُكَذِّبُ بِيَوْمِ الدِّينِ ( 46 ) አል ሙደሲር - Aya 46
«በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን፡፡ አል ሙደሲር - Aya 46
حَتَّىٰ أَتَانَا الْيَقِينُ ( 47 ) አል ሙደሲር - Aya 47
«እርግጠኛው (ሞት) እስከ መጣን ድረስ፡፡» አል ሙደሲር - Aya 47
فَمَا تَنفَعُهُمْ شَفَاعَةُ الشَّافِعِينَ ( 48 ) አል ሙደሲር - Aya 48
የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፡፡ አል ሙደሲር - Aya 48
فَمَا لَهُمْ عَنِ التَّذْكِرَةِ مُعْرِضِينَ ( 49 ) አል ሙደሲር - Aya 49
ከግሣጼዬም (ከቁርኣን) የሚያፈገፍጉት ለእነርሱ ምን አልላቸው? አል ሙደሲር - Aya 49
كَأَنَّهُمْ حُمُرٌ مُّسْتَنفِرَةٌ ( 50 ) አል ሙደሲር - Aya 50
እነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ አህዮች ይመስላሉ፡፡ አል ሙደሲር - Aya 50
فَرَّتْ مِن قَسْوَرَةٍ ( 51 ) አል ሙደሲር - Aya 51
ከዐንበሳ የሸሹ፡፡ አል ሙደሲር - Aya 51
بَلْ يُرِيدُ كُلُّ امْرِئٍ مِّنْهُمْ أَن يُؤْتَىٰ صُحُفًا مُّنَشَّرَةً ( 52 ) አል ሙደሲር - Aya 52
ይልቁንም ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው ሁሉ የተዘረጉ ጽሑፎችን እንዲስሰጥ ይፈልጋል፡፡ አል ሙደሲር - Aya 52
كَلَّا ۖ بَل لَّا يَخَافُونَ الْآخِرَةَ ( 53 ) አል ሙደሲር - Aya 53
ይከልከሉ፡፡ ይልቁንም የመጨረሻይቱን ዓለም (ቅጣት) አይፈሩም፡፡ አል ሙደሲር - Aya 53
كَلَّا إِنَّهُ تَذْكِرَةٌ ( 54 ) አል ሙደሲር - Aya 54
ይከልከሉ፡፡ እርሱ (ቁርኣን) መገሠጫ ነው፡፡ አል ሙደሲር - Aya 54
فَمَن شَاءَ ذَكَرَهُ ( 55 ) አል ሙደሲር - Aya 55
ስለዚህ የሻ ሰው ይገሰጽበታል፡፡ አል ሙደሲር - Aya 55
وَمَا يَذْكُرُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ ۚ هُوَ أَهْلُ التَّقْوَىٰ وَأَهْلُ الْمَغْفِرَةِ ( 56 ) አል ሙደሲር - Aya 56
አላህም ካልሻ በስተቀር አይገሠጹም፡፡ እርሱ (አላህ) የመፈራት ባለቤት የምሕረትም ባለቤት ነው፡፡ አል ሙደሲር - Aya 56
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah