Surah አል ሹራ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ሹራ - Aya count 53
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
حم ( 1 ) አል ሹራ - Aya 1
ሐ.መ (ሐ፡ ሚም)፡፡ አል ሹራ - Aya 1
عسق ( 2 ) አል ሹራ - Aya 2
ዐ.ሰ.ቀ (ዓይን ሲን ቃፍ)፤ አል ሹራ - Aya 2
كَذَٰلِكَ يُوحِي إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكَ اللَّهُ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ ( 3 ) አል ሹራ - Aya 3
እንደዚሁ (በዚህች ሱራ ውስጥ እንዳለው) አሸናፊው ጥበበኛው አላህ ወዳንተ ያወርዳል፡፡ ወደእነዚያም ከአንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች (አውርዷል)፡፡ አል ሹራ - Aya 3
لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ ( 4 ) አል ሹራ - Aya 4
በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ እርሱም የበላዩ ታላቁ ነው፡፡ አል ሹራ - Aya 4
تَكَادُ السَّمَاوَاتُ يَتَفَطَّرْنَ مِن فَوْقِهِنَّ ۚ وَالْمَلَائِكَةُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيَسْتَغْفِرُونَ لِمَن فِي الْأَرْضِ ۗ أَلَا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ ( 5 ) አል ሹራ - Aya 5
(ከአላህ ፍራቻ) ሰማያት ከበላያቸው ሊቀደዱ ይቀርባሉ፡፡ መላእክትም ጌታቸውን እያመሰገኑ ያወድሳሉ፡፡ በምድርም ላለው ፍጡር ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ ንቁ! አላህ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነው፡፡ አል ሹራ - Aya 5
وَالَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ اللَّهُ حَفِيظٌ عَلَيْهِمْ وَمَا أَنتَ عَلَيْهِم بِوَكِيلٍ ( 6 ) አል ሹራ - Aya 6
እነዚያም ከእርሱ ሌላ (የጣዖታት) ረዳቶችን የያዙ፤ አላህ በእነርሱ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ አንተም በእነርሱ ላይ ኀላፊ አይደለህም፡፡ አል ሹራ - Aya 6
وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّتُنذِرَ أُمَّ الْقُرَىٰ وَمَنْ حَوْلَهَا وَتُنذِرَ يَوْمَ الْجَمْعِ لَا رَيْبَ فِيهِ ۚ فَرِيقٌ فِي الْجَنَّةِ وَفَرِيقٌ فِي السَّعِيرِ ( 7 ) አል ሹራ - Aya 7
እንደዚሁም የከተሞች እናት የኾነችውን (የመካን ሰዎች) በአካባቢዋ ያሉትንም ልታስፈራራ የመሰብሰቢያውንም ቀን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲኾን ልታስጠነቅቅ ዐረብኛ የኾነን ቁርኣን ወደ አንተ አወረድን፡፡ (ከእነርሱም) ከፊሉ በገነት ውሰጥ ከፊሉም በእሳት ውስጥ ነው፡፡ አል ሹራ - Aya 7
وَلَوْ شَاءَ اللَّهُ لَجَعَلَهُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَلَٰكِن يُدْخِلُ مَن يَشَاءُ فِي رَحْمَتِهِ ۚ وَالظَّالِمُونَ مَا لَهُم مِّن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ ( 8 ) አል ሹራ - Aya 8
አላህም በሻ ኖሮ (ባንድ ሃይማኖት ላይ) አንድ ሕዝብ ባደረጋቸው ነበር፡፡ ግን የሚሻውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባል፡፡ በዳዮችም ለእነርሱ ወዳጅና ረዳት ምንም የላቸውም፡፡ አል ሹራ - Aya 8
أَمِ اتَّخَذُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ ۖ فَاللَّهُ هُوَ الْوَلِيُّ وَهُوَ يُحْيِي الْمَوْتَىٰ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ( 9 ) አል ሹራ - Aya 9
ከእርሱ ሌላ ረዳቶችን ያዙን? (ረዳቶች አይደሉም)፡፡ አላህም ረዳት እርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ሙታንን ሕያው ያደርጋል፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ አል ሹራ - Aya 9
وَمَا اخْتَلَفْتُمْ فِيهِ مِن شَيْءٍ فَحُكْمُهُ إِلَى اللَّهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبِّي عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ أُنِيبُ ( 10 ) አል ሹራ - Aya 10
ከምንም ነገር ያ በእርሱ የተለያዩበት ፍርዱ ወደ አላህ ነው፡፡ «እርሱ አላህ ጌታዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተጠጋሁ፣ ወደርሱም እመለሳለሁ» (በላቸው)፡፡ አል ሹራ - Aya 10
فَاطِرُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ جَعَلَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا وَمِنَ الْأَنْعَامِ أَزْوَاجًا ۖ يَذْرَؤُكُمْ فِيهِ ۚ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ ( 11 ) አል ሹራ - Aya 11
ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ነው፡፡ ከነፍሶቻችሁ ሴቶችን ከቤት እንስሳዎችም ዓይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ አደረገላችሁ፡፡ በእርሱ ያበዛችኋል፡፡ የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ አል ሹራ - Aya 11
لَهُ مَقَالِيدُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ يَبْسُطُ الرِّزْقَ لِمَن يَشَاءُ وَيَقْدِرُ ۚ إِنَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ ( 12 ) አል ሹራ - Aya 12
የሰማያትና የምድር (ድልቦች) መከፈቻዎች የእርሱ ናቸው፡፡ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ያጠባልም፡፡ እርሱ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡ አል ሹራ - Aya 12
شَرَعَ لَكُم مِّنَ الدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِ نُوحًا وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰ ۖ أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ ۚ كَبُرَ عَلَى الْمُشْرِكِينَ مَا تَدْعُوهُمْ إِلَيْهِ ۚ اللَّهُ يَجْتَبِي إِلَيْهِ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَن يُنِيبُ ( 13 ) አል ሹራ - Aya 13
ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን)፡፡ በአጋሪዎቹ ላይ ያ ወደርሱ የምትጠራቸው ነገር ከበዳቸው፡፡ አላህ የሚሻውን ሰው ወደእርሱ (እምነት) ይመርጣል፡፡ የሚመለስንም ሰው ወደርሱ ይመራል፡፡ አል ሹራ - Aya 13
وَمَا تَفَرَّقُوا إِلَّا مِن بَعْدِ مَا جَاءَهُمُ الْعِلْمُ بَغْيًا بَيْنَهُمْ ۚ وَلَوْلَا كَلِمَةٌ سَبَقَتْ مِن رَّبِّكَ إِلَىٰ أَجَلٍ مُّسَمًّى لَّقُضِيَ بَيْنَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ أُورِثُوا الْكِتَابَ مِن بَعْدِهِمْ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ مُرِيبٍ ( 14 ) አል ሹራ - Aya 14
(የሃይማኖት ሰዎች) ዕውቀቱም ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ለምቀኝነት እንጅ ለሌላ አልተለያዩም፡፡ እስከ ተወሰነም ጊዜ (በማቆየት) ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በእነርሱ መካከል (አሁን) በተፈረደ ነበር፡፡ እነዚያም ከኋላቸው መጽሐፉን እንዲወርሱ የተደረጉት ከእርሱ በእርግጥ በአወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው፡፡ አል ሹራ - Aya 14
فَلِذَٰلِكَ فَادْعُ ۖ وَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُمْ ۖ وَقُلْ آمَنتُ بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ مِن كِتَابٍ ۖ وَأُمِرْتُ لِأَعْدِلَ بَيْنَكُمُ ۖ اللَّهُ رَبُّنَا وَرَبُّكُمْ ۖ لَنَا أَعْمَالُنَا وَلَكُمْ أَعْمَالُكُمْ ۖ لَا حُجَّةَ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمُ ۖ اللَّهُ يَجْمَعُ بَيْنَنَا ۖ وَإِلَيْهِ الْمَصِيرُ ( 15 ) አል ሹራ - Aya 15
ለዚህም (ድንጋጌ ሰዎችን) ጥራ፡፡ እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ዝንባሌዎቻቸውንም አትከተል፡፡ «በላቸውም ከመጽሐፍ አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ፡፡ በመካከላችሁም ላስተካክል ታዘዝኩ፡፡ አላህ ጌታችን ጌታችሁም ነው፡፡ ለእኛ ሥራዎቻችን አልሉን፡፡ ለእናንተም ሥራዎቻችሁ አልሏችሁ፡፡ በእኛና በእናንተ መካከል ክርክር የለም፡፡ አላህ በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ መመለሻም ወደእርሱ ብቻ ነው፡፡» አል ሹራ - Aya 15
وَالَّذِينَ يُحَاجُّونَ فِي اللَّهِ مِن بَعْدِ مَا اسْتُجِيبَ لَهُ حُجَّتُهُمْ دَاحِضَةٌ عِندَ رَبِّهِمْ وَعَلَيْهِمْ غَضَبٌ وَلَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ ( 16 ) አል ሹራ - Aya 16
እነዚያም በአላህ (ሃይማኖት) ለእርሱ ተቀባይ ካገኘ በኋላ የሚከራከሩት ማስረጃቸው በጌታቸው ዘንድ ብልሹ ናት፡፡ በእነርሱም ላይ ቁጣ አልለባቸው፡፡ ለእነርሱም ብርቱ ቅጣት አልላቸው፡፡ አል ሹራ - Aya 16
اللَّهُ الَّذِي أَنزَلَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ وَالْمِيزَانَ ۗ وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّ السَّاعَةَ قَرِيبٌ ( 17 ) አል ሹራ - Aya 17
አላህ ያ መጽሐፉን በእውነት ያወረደ ነው፡፡ ሚዛንንም (እንደዚሁ)፡፡ ሰዓቲቱ ምንአልባት ቅርብ መኾንዋን ምን ያሳውቅሃል? አል ሹራ - Aya 17
يَسْتَعْجِلُ بِهَا الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِهَا ۖ وَالَّذِينَ آمَنُوا مُشْفِقُونَ مِنْهَا وَيَعْلَمُونَ أَنَّهَا الْحَقُّ ۗ أَلَا إِنَّ الَّذِينَ يُمَارُونَ فِي السَّاعَةِ لَفِي ضَلَالٍ بَعِيدٍ ( 18 ) አል ሹራ - Aya 18
እነዚያ በእርሷ የማያምኑት በእርሷ ያቻኩላሉ፡፡ እነዚያም ያመኑት ከእርሷ ፈሪዎች ናቸው፡፡ እርሷም እውነት መኾንዋን ያውቃሉ፡፡ ንቁ! እነዚያ በሰዓቲቱ የሚከራከሩት በእርግጥ (ከእውነት) በራቀ ስሕተት ውስጥ ናቸው፡፡ አል ሹራ - Aya 18
اللَّهُ لَطِيفٌ بِعِبَادِهِ يَرْزُقُ مَن يَشَاءُ ۖ وَهُوَ الْقَوِيُّ الْعَزِيزُ ( 19 ) አል ሹራ - Aya 19
አላህ በባሮቹ ሩህሩህ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው (በሰፊው) ሲሳይን ይሰጣል፡፡ እርሱም ብርቱው አሸናፊው ነው፡፡ አል ሹራ - Aya 19
مَن كَانَ يُرِيدُ حَرْثَ الْآخِرَةِ نَزِدْ لَهُ فِي حَرْثِهِ ۖ وَمَن كَانَ يُرِيدُ حَرْثَ الدُّنْيَا نُؤْتِهِ مِنْهَا وَمَا لَهُ فِي الْآخِرَةِ مِن نَّصِيبٍ ( 20 ) አል ሹራ - Aya 20
(በሥራው) የኋለኛይቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ የኾነ ሰው ለእርሱ በአዝመራው ላይ እንጨምርለታለን፡፡ የቅርቢቱንም ዓለም አዝመራ የሚፈልግ የኾነ ሰው ከእርሷ (የተወሰነለትን ብቻ) እንሰጠዋለን፡፡ ለእርሱም በኋለኛይቱ ዓለም ምንም ፋንታ የለውም፡፡ አል ሹራ - Aya 20
أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُم مِّنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَن بِهِ اللَّهُ ۚ وَلَوْلَا كَلِمَةُ الْفَصْلِ لَقُضِيَ بَيْنَهُمْ ۗ وَإِنَّ الظَّالِمِينَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ ( 21 ) አል ሹራ - Aya 21
ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አልሏቸውን? የፍርዱ ቃል ባልነበረ ኖሮ በመካከላቸው (አሁን) በተፈረደ ነበር፡፡ በደለኞችም ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ አልላቸው፡፡ አል ሹራ - Aya 21
تَرَى الظَّالِمِينَ مُشْفِقِينَ مِمَّا كَسَبُوا وَهُوَ وَاقِعٌ بِهِمْ ۗ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فِي رَوْضَاتِ الْجَنَّاتِ ۖ لَهُم مَّا يَشَاءُونَ عِندَ رَبِّهِمْ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَضْلُ الْكَبِيرُ ( 22 ) አል ሹራ - Aya 22
በደለኞችን ከሠሩት ሥራ (ዋጋ በትንሣኤ ቀን) ፈሪዎች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ እርሱም በእነርሱ ላይ ወዳቂ ነው፡፡ እነዚያም ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት በገነቶች ጨፌዎች ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አልላቸው፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው፡፡ አል ሹራ - Aya 22
ذَٰلِكَ الَّذِي يُبَشِّرُ اللَّهُ عِبَادَهُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ ۗ قُل لَّا أَسْأَلُكُمْ عَلَيْهِ أَجْرًا إِلَّا الْمَوَدَّةَ فِي الْقُرْبَىٰ ۗ وَمَن يَقْتَرِفْ حَسَنَةً نَّزِدْ لَهُ فِيهَا حُسْنًا ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ شَكُورٌ ( 23 ) አል ሹራ - Aya 23
ይህ (ታላቅ ችሮታ) ያ አላህ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ባሮቹን የሚያበስርበት ነው፡፡ «በእርሱ (መልክቴን በማድረሴ) ላይ በዝምድና ውዴታን እንጅ ዋጋን አልጠይቃችሁም» በላቸው፡፡ መልካሚቱንም ሥራ የሚሠራ ሰው ለእርሱ በእርሷ መልካምን ነገር እንጨምርለታለን፡፡ አላህ መሓሪ አመስጋኝ ነውና፡፡ አል ሹራ - Aya 23
أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا ۖ فَإِن يَشَإِ اللَّهُ يَخْتِمْ عَلَىٰ قَلْبِكَ ۗ وَيَمْحُ اللَّهُ الْبَاطِلَ وَيُحِقُّ الْحَقَّ بِكَلِمَاتِهِ ۚ إِنَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ ( 24 ) አል ሹራ - Aya 24
ይልቁንም «በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈ» ይላሉን? አላህም ቢሻ በልብህ ላይ ያትማል፡፡ አላህም ውሸቱን ያብብሳል፡፡ እውነቱንም በቃላቱ ያረጋግጣል፡፡ እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡ አል ሹራ - Aya 24
وَهُوَ الَّذِي يَقْبَلُ التَّوْبَةَ عَنْ عِبَادِهِ وَيَعْفُو عَنِ السَّيِّئَاتِ وَيَعْلَمُ مَا تَفْعَلُونَ ( 25 ) አል ሹራ - Aya 25
እርሱም ያ ከባሮቹ ንስሓን የሚቀበል፣ ከኃጢአቶችም ይቅር የሚል፣ የምትሠሩትንም ሁሉ የሚያውቅ ነው፡፡ አል ሹራ - Aya 25
وَيَسْتَجِيبُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَيَزِيدُهُم مِّن فَضْلِهِ ۚ وَالْكَافِرُونَ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ ( 26 ) አል ሹራ - Aya 26
እነዚያንም ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ልመናቸውን ይቀበላል፡፡ ከችሮታውም ይጨምርላቸዋል፡፡ ከሓዲዎቹም ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አልላቸው፡፡ አል ሹራ - Aya 26
وَلَوْ بَسَطَ اللَّهُ الرِّزْقَ لِعِبَادِهِ لَبَغَوْا فِي الْأَرْضِ وَلَٰكِن يُنَزِّلُ بِقَدَرٍ مَّا يَشَاءُ ۚ إِنَّهُ بِعِبَادِهِ خَبِيرٌ بَصِيرٌ ( 27 ) አል ሹራ - Aya 27
አላህም ለባሮቹ (ሁሉ) ሲሳይን በዘረጋ ኖሮ በምድር ውስጥ (ሁሉም) ወሰን ባለፉ ነበር፡፡ ግን የሚሻውን በልክ ያወርዳል፡፡ እርሱ በባሮቹ ውስጥ ዐዋቂ ተመልካች ነውና፡፡ አል ሹራ - Aya 27
وَهُوَ الَّذِي يُنَزِّلُ الْغَيْثَ مِن بَعْدِ مَا قَنَطُوا وَيَنشُرُ رَحْمَتَهُ ۚ وَهُوَ الْوَلِيُّ الْحَمِيدُ ( 28 ) አል ሹራ - Aya 28
እርሱም ያ ተስፋ ከቆረጡ በኋላ ዝናምን የሚያወርድ ችሮታውንም የሚዘረጋ ነው፡፡ እርሱም ረዳቱ ምስጉኑ ነው፡፡ አል ሹራ - Aya 28
وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَثَّ فِيهِمَا مِن دَابَّةٍ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ جَمْعِهِمْ إِذَا يَشَاءُ قَدِيرٌ ( 29 ) አል ሹራ - Aya 29
ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ ከተንቀሳቃሽም በሁለቱ ውስጥ የበተነውን (መፍጠሩ) ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ እርሱም በሚሻ ጊዜ እነርሱን በመሰብሰብ ላይ ቻይ ነው፡፡ አል ሹራ - Aya 29
وَمَا أَصَابَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ ( 30 ) አል ሹራ - Aya 30
ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት (ኃጢኣት) ምክንያት ነው፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል፡፡ አል ሹራ - Aya 30
وَمَا أَنتُم بِمُعْجِزِينَ فِي الْأَرْضِ ۖ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ ( 31 ) አል ሹራ - Aya 31
እናንተም በምድር ውስጥ የምታቅቱ አይደላችሁም፡፡ ለእናንተም ከአላህ ሌላ ከዘመድም ከረዳትም ምንም የላችሁም፡፡ አል ሹራ - Aya 31
وَمِنْ آيَاتِهِ الْجَوَارِ فِي الْبَحْرِ كَالْأَعْلَامِ ( 32 ) አል ሹራ - Aya 32
በባሕር ላይ እንደ ጋራዎች ኾነው ተንሻላዮቹም (መርከቦች) ከአስደናቂ ምልክቶቹ ናቸው፡፡ አል ሹራ - Aya 32
إِن يَشَأْ يُسْكِنِ الرِّيحَ فَيَظْلَلْنَ رَوَاكِدَ عَلَىٰ ظَهْرِهِ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّكُلِّ صَبَّارٍ شَكُورٍ ( 33 ) አል ሹራ - Aya 33
ቢሻ ነፋሱን የረጋ ያደርገዋል፡፡ በባሕሩም ጀርባ ላይ ረጊዎች ይኾናሉ፡፡ በዚህ ውሰጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለኾነ ሁሉ በእርግጥ ምልክቶች አልሉ፡፡ አል ሹራ - Aya 33
أَوْ يُوبِقْهُنَّ بِمَا كَسَبُوا وَيَعْفُ عَن كَثِيرٍ ( 34 ) አል ሹራ - Aya 34
ወይም በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት (በማስጠም) ያጠፋቸዋል፡፡ ከብዙም ይቅርታ ያደርጋል፡፡ አል ሹራ - Aya 34
وَيَعْلَمَ الَّذِينَ يُجَادِلُونَ فِي آيَاتِنَا مَا لَهُم مِّن مَّحِيصٍ ( 35 ) አል ሹራ - Aya 35
(ከእነርሱ ለመበቀል)፤ እነዚያንም በአንቀጾቻችን የሚከራከሩትን ለማወቅ (ያጠፋቸዋል)፡፡ ለእነርሱ ምንም መሸሻ የላቸውም፡፡ አል ሹራ - Aya 35
فَمَا أُوتِيتُم مِّن شَيْءٍ فَمَتَاعُ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۖ وَمَا عِندَ اللَّهِ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ لِلَّذِينَ آمَنُوا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ ( 36 ) አል ሹራ - Aya 36
ከምንም ነገር የተሰጣችሁት የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው፡፡ አላህ ዘንድ ያለውም ምንዳ ለእነዚያ ለአመኑትና በጌታቸው ላይ ለሚጠጉት በላጭና ሁል ጊዜ ነዋሪ ነው፡፡ አል ሹራ - Aya 36
وَالَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَائِرَ الْإِثْمِ وَالْفَوَاحِشَ وَإِذَا مَا غَضِبُوا هُمْ يَغْفِرُونَ ( 37 ) አል ሹራ - Aya 37
ለእነዚያም የኀጢኣትን ታላላቆችና ጠያፎችን የሚርቁ በተቆጡም ጊዜ እነሱ የሚምሩት ለኾኑት፡፡ አል ሹራ - Aya 37
وَالَّذِينَ اسْتَجَابُوا لِرَبِّهِمْ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَمْرُهُمْ شُورَىٰ بَيْنَهُمْ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُونَ ( 38 ) አል ሹራ - Aya 38
ለእነዚያም የጌታቸውን ጥሪ ለተቀበሉት፣ ሶላትንም ላዘወተሩት፣ ነገራቸውም በመካከላቸው መመካከር ለኾነው ከሰጠናቸውም ሲሳይ ለሚለግሱት፡፡ አል ሹራ - Aya 38
وَالَّذِينَ إِذَا أَصَابَهُمُ الْبَغْيُ هُمْ يَنتَصِرُونَ ( 39 ) አል ሹራ - Aya 39
ለእነዚያም በደል በደረሰባቸው ጊዜ እነርሱ (በመሰሉ) የሚመልሱ ለኾኑት (በላጭና ኗሪ ነው)፡፡ አል ሹራ - Aya 39
وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا ۖ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ ( 40 ) አል ሹራ - Aya 40
የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም፡፡ አል ሹራ - Aya 40
وَلَمَنِ انتَصَرَ بَعْدَ ظُلْمِهِ فَأُولَٰئِكَ مَا عَلَيْهِم مِّن سَبِيلٍ ( 41 ) አል ሹራ - Aya 41
ከተበደሉም በኋላ (በመሰሉ) የተበቀሉ እነዚያ በነርሱ ላይ ምንም (የወቀሳ) መንገድ የለባቸውም፡፡ አል ሹራ - Aya 41
إِنَّمَا السَّبِيلُ عَلَى الَّذِينَ يَظْلِمُونَ النَّاسَ وَيَبْغُونَ فِي الْأَرْضِ بِغَيْرِ الْحَقِّ ۚ أُولَٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ ( 42 ) አል ሹራ - Aya 42
(የወቀሳ) መንገዱ በእነዚያ ሰዎችን በሚበድሉት፣ በምድርም ውስጥ ያለ ሕግ ወሰን በሚያልፉት፣ ላይ ብቻ ነው፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አልላቸው፡፡ አል ሹራ - Aya 42
وَلَمَن صَبَرَ وَغَفَرَ إِنَّ ذَٰلِكَ لَمِنْ عَزْمِ الْأُمُورِ ( 43 ) አል ሹራ - Aya 43
የታገስና ምሕረት ያደረገም ሰው ይህ ከምርሮቹ (ከተፈላጊዎቹ) ነገሮች ነው፡፡ አል ሹራ - Aya 43
وَمَن يُضْلِلِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِن وَلِيٍّ مِّن بَعْدِهِ ۗ وَتَرَى الظَّالِمِينَ لَمَّا رَأَوُا الْعَذَابَ يَقُولُونَ هَلْ إِلَىٰ مَرَدٍّ مِّن سَبِيلٍ ( 44 ) አል ሹራ - Aya 44
አላህ የሚያጠመውም ሰው ከእርሱ በኋለ ለእርሱ ምንም ረዳት የለውም፡፡ በደለኞችንም ቅጣቱን ባዩ ጊዜ ወደ መመለስ መንገድ አልለን? የሚሉ ሲኾኑ ታያቸዋለህ፡፡ አል ሹራ - Aya 44
وَتَرَاهُمْ يُعْرَضُونَ عَلَيْهَا خَاشِعِينَ مِنَ الذُّلِّ يَنظُرُونَ مِن طَرْفٍ خَفِيٍّ ۗ وَقَالَ الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ الْخَاسِرِينَ الَّذِينَ خَسِرُوا أَنفُسَهُمْ وَأَهْلِيهِمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ أَلَا إِنَّ الظَّالِمِينَ فِي عَذَابٍ مُّقِيمٍ ( 45 ) አል ሹራ - Aya 45
ከውርደት የተነሳ ፈሪዎች ኾነው በዓይን ስርቆት ወደእርሷ (ወደ እሳት) እያስተዋሉ በእርሷ ላይ የሚቀረቡ ሲኾኑ ታያቸዋለህ፡፡ እነዚያም ያመኑት፡- «በእርግጥ ከሳሪዎቹ እነዚያ ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በትንሣኤ ቀን ያከሰሩት ናቸው» ይላሉ፡፡ አል ሹራ - Aya 45
وَمَا كَانَ لَهُم مِّنْ أَوْلِيَاءَ يَنصُرُونَهُم مِّن دُونِ اللَّهِ ۗ وَمَن يُضْلِلِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِن سَبِيلٍ ( 46 ) አል ሹራ - Aya 46
ንቁ! በደለኞች በእርግጥ በዘውታሪ ስቃይ ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዷቸው ዘመዶች ምንም አልነበሩዋቸውም፡፡ አላህም የሚያጠመው ሰው ለእርሱ (ወደ እውነት) ምንም መንገድ የለውም፡፡ አል ሹራ - Aya 46
اسْتَجِيبُوا لِرَبِّكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَ يَوْمٌ لَّا مَرَدَّ لَهُ مِنَ اللَّهِ ۚ مَا لَكُم مِّن مَّلْجَإٍ يَوْمَئِذٍ وَمَا لَكُم مِّن نَّكِيرٍ ( 47 ) አል ሹራ - Aya 47
ለእርሱ መመለስ የሌለው ቀን ከአላህ ከመምጣቱ በፊት ለጌታችሁ ታዘዙ፡፡ በዚያ ቀን ለእናንተ ምንም መጠጊያ የላችሁም፡፡ ለእናንተም ምንም መካድ የላችሁም፡፡ አል ሹራ - Aya 47
فَإِنْ أَعْرَضُوا فَمَا أَرْسَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا ۖ إِنْ عَلَيْكَ إِلَّا الْبَلَاغُ ۗ وَإِنَّا إِذَا أَذَقْنَا الْإِنسَانَ مِنَّا رَحْمَةً فَرِحَ بِهَا ۖ وَإِن تُصِبْهُمْ سَيِّئَةٌ بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيهِمْ فَإِنَّ الْإِنسَانَ كَفُورٌ ( 48 ) አል ሹራ - Aya 48
ቢዞሩም (ወቀሳ የለብህም)፡፡ በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፡፡ ባንተ ላይ ማድረስ እንጅ ሌላ የለብህም፡፡ እኛም ሰውን ከእኛ የኾነን ጸጋ ባቀመስነው ጊዜ በርሷ ይደሰታል፡፡ እጆቻቸው ባስቀደሙትም ኀጢአት ምክንያት መከራ ብትደርስባቸው (ተስፋ ይቆርጣሉ)፡፡ ሰው (ውለታን) በጣም ከሐዲ ነውና፡፡ አል ሹራ - Aya 48
لِّلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ ( 49 ) አል ሹራ - Aya 49
የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡ አል ሹራ - Aya 49
أَوْ يُزَوِّجُهُمْ ذُكْرَانًا وَإِنَاثًا ۖ وَيَجْعَلُ مَن يَشَاءُ عَقِيمًا ۚ إِنَّهُ عَلِيمٌ قَدِيرٌ ( 50 ) አል ሹራ - Aya 50
ወይም ወንዶችና ሴቶች አድርጎ ያጠናዳቸዋል፡፡ የሚሻውንም ሰው መካን ያደርገዋል፡፡ እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና፡፡ አል ሹራ - Aya 50
وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ اللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَاءِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًا فَيُوحِيَ بِإِذْنِهِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّهُ عَلِيٌّ حَكِيمٌ ( 51 ) አል ሹራ - Aya 51
ለሰውም አላህ በራእይ፣ ወይም ከግርዶ ወዲያ፣ ወይም መልክተኛን (መልአክን) የሚልክና በፈቃዱ የሚሻውን ነገር የሚያወርድለት ቢኾን እንጅ (በገሃድ) ሊያናግረው ተገቢው አይደለም፡፡ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና፡፡ አል ሹራ - Aya 51
وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَٰكِن جَعَلْنَاهُ نُورًا نَّهْدِي بِهِ مَن نَّشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ وَإِنَّكَ لَتَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ ( 52 ) አል ሹራ - Aya 52
እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ ግን (መንፈሱን) ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡ አል ሹራ - Aya 52
صِرَاطِ اللَّهِ الَّذِي لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ أَلَا إِلَى اللَّهِ تَصِيرُ الْأُمُورُ ( 53 ) አል ሹራ - Aya 53
ወደዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ወደ ኾነው አላህ መንገድ (ትመራለህ)፡፡ ንቁ! ነገሮቹ ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ፡፡ አል ሹራ - Aya 53
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah