Surah አል ሙምተሒናህ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ሙምተሒናህ - Aya count 13
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا عَدُوِّي وَعَدُوَّكُمْ أَوْلِيَاءَ تُلْقُونَ إِلَيْهِم بِالْمَوَدَّةِ وَقَدْ كَفَرُوا بِمَا جَاءَكُم مِّنَ الْحَقِّ يُخْرِجُونَ الرَّسُولَ وَإِيَّاكُمْ ۙ أَن تُؤْمِنُوا بِاللَّهِ رَبِّكُمْ إِن كُنتُمْ خَرَجْتُمْ جِهَادًا فِي سَبِيلِي وَابْتِغَاءَ مَرْضَاتِي ۚ تُسِرُّونَ إِلَيْهِم بِالْمَوَدَّةِ وَأَنَا أَعْلَمُ بِمَا أَخْفَيْتُمْ وَمَا أَعْلَنتُمْ ۚ وَمَن يَفْعَلْهُ مِنكُمْ فَقَدْ ضَلَّ سَوَاءَ السَّبِيلِ ( 1 ) አል ሙምተሒናህ - Aya 1
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጠላቶቼንና ጠላቶቻችሁን ወዳጆች አድርገችሁ አትያዙ፡፡ ከእውነቱ የመጣላችሁን ሃይማኖት በእርግጥ የካዱ ሲኾኑ ውዴታን ወደእነርሱ ታደርሳላችሁ፡፡ መልክተኛውንና እናንተን በአላህ በጌታችሁ ስላመናችሁ (ከመካ) ያወጣሉ፡፡ በመንገዴ ለመታገልና ውዴታዬን ለመፈለግ የወጣችሁ እንደኾናችሁ (ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙዋቸው)፡፡ እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን ሁሉ የማውቅ ስኾን ወደእነርሱ በፍቅር ትመሳጠራላችሁ፡፡ ከእናንተም (ይህንን) የሚሠራ ሰው ቀጥተኛውን መንገድ በእርግጥ ተሳሳተ፡፡ አል ሙምተሒናህ - Aya 1
إِن يَثْقَفُوكُمْ يَكُونُوا لَكُمْ أَعْدَاءً وَيَبْسُطُوا إِلَيْكُمْ أَيْدِيَهُمْ وَأَلْسِنَتَهُم بِالسُّوءِ وَوَدُّوا لَوْ تَكْفُرُونَ ( 2 ) አል ሙምተሒናህ - Aya 2
ቢያሸንፏችሁ ለእናንተ ጠላቶች ይኾናሉ፡፡ እጆቻቸውንና ምላሶቻቸውንም ወደእናንተ በክፉ ይዘረጋሉ፡፡ ብትክዱም ተመኙ፡፡ አል ሙምተሒናህ - Aya 2
لَن تَنفَعَكُمْ أَرْحَامُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُمْ ۚ يَوْمَ الْقِيَامَةِ يَفْصِلُ بَيْنَكُمْ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ ( 3 ) አል ሙምተሒናህ - Aya 3
ዘመዶቻችሁም፣ ልጆቻችሁም በትንሣኤ ቀን አይጠቅሟችሁም፤ (አላህ) በመካከላችሁ ይለያል፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ አል ሙምተሒናህ - Aya 3
قَدْ كَانَتْ لَكُمْ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ فِي إِبْرَاهِيمَ وَالَّذِينَ مَعَهُ إِذْ قَالُوا لِقَوْمِهِمْ إِنَّا بُرَآءُ مِنكُمْ وَمِمَّا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ كَفَرْنَا بِكُمْ وَبَدَا بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمُ الْعَدَاوَةُ وَالْبَغْضَاءُ أَبَدًا حَتَّىٰ تُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَحْدَهُ إِلَّا قَوْلَ إِبْرَاهِيمَ لِأَبِيهِ لَأَسْتَغْفِرَنَّ لَكَ وَمَا أَمْلِكُ لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن شَيْءٍ ۖ رَّبَّنَا عَلَيْكَ تَوَكَّلْنَا وَإِلَيْكَ أَنَبْنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ ( 4 ) አል ሙምተሒናህ - Aya 4
በኢብራሂምና በእነዚያ ከእርሱ ጋር በነበሩት (ምእምናን) መልካም መከተል አለቻችሁ፡፡ ለሕዝቦቻቸው «እኛ ከእናንተ ከአላህ ሌላ ከምትግገዙትም ንጹሖች ነን፡፡ በእናንተ ካድን፡፡ በአላህ አንድ ብቻ ሲኾን እስከምታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ፡፡» ባሉ ጊዜ (መልካም መከተል አለቻችሁ)፡፡ ኢብራሂም ለአባቱ «እኔ ለአንተ ከአላህ (ቅጣት) ምንም የማልጠቅም ስኾን ለአንተ በእርግጥ ምሕረትን እለምንልኻለሁ» ማለቱ ብቻ ሲቀር፡፡ «ጌታችን ሆይ! በአንተ ላይ ተመካን፡፡ ወደ አንተም ተመለስን መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው፤» (ባለው ተከተሉት)፡፡ አል ሙምተሒናህ - Aya 4
رَبَّنَا لَا تَجْعَلْنَا فِتْنَةً لِّلَّذِينَ كَفَرُوا وَاغْفِرْ لَنَا رَبَّنَا ۖ إِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ ( 5 ) አል ሙምተሒናህ - Aya 5
ጌታችን ሆይ! ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች መሞከሪያ አታድርገን፡፡ ለእኛም ምሕረት አድርግልን፡፡ ጌታችን ሆይ! አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህ፡፡ አል ሙምተሒናህ - Aya 5
لَقَدْ كَانَ لَكُمْ فِيهِمْ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ ۚ وَمَن يَتَوَلَّ فَإِنَّ اللَّهَ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ ( 6 ) አል ሙምተሒናህ - Aya 6
ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን ለሚፈራ ሰው በእነርሱ መልካም መከተል አልላችሁ፡፡ የሚዞርም ሰው (ራሱን ይጎዳል)፡፡ አላህ ተብቃቂው ምስጉኑ እርሱ ብቻ ነውና፡፡ አል ሙምተሒናህ - Aya 6
عَسَى اللَّهُ أَن يَجْعَلَ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَ الَّذِينَ عَادَيْتُم مِّنْهُم مَّوَدَّةً ۚ وَاللَّهُ قَدِيرٌ ۚ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ( 7 ) አል ሙምተሒናህ - Aya 7
በናንተና በእነዚያ ከእነርሱ ጋር በተጣላችሁት ሰዎች መካከል አላህ መፋቀርን ሊያደርግ ይቻላል፡፡ አላህም ቻይ ነው፡፡ አላህም በጣም አዛኝ ነው፡፡ አል ሙምተሒናህ - Aya 7
لَّا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ أَن تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ ( 8 ) አል ሙምተሒናህ - Aya 8
ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ (ከሓዲዎች) መልካም ብትውሉላቸውና ወደእነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና፡፡ አል ሙምተሒናህ - Aya 8
إِنَّمَا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ قَاتَلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَأَخْرَجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ وَظَاهَرُوا عَلَىٰ إِخْرَاجِكُمْ أَن تَوَلَّوْهُمْ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُمْ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ ( 9 ) አል ሙምተሒናህ - Aya 9
አላህ የሚከለክላችሁ ከእነዚያ በሃይማኖት ከተጋደሉዋችሁ፣ ከቤቶቻችሁም ካወጡዋችሁ፣ እናንተም በማውጣት ላይ ከረዱት (ከሓዲዎች) እንዳትወዳጁዋቸው ብቻ ነው፡፡ ወዳጅ የሚያደርጓቸውም ሰዎች እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው፡፡ አል ሙምተሒናህ - Aya 9
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا جَاءَكُمُ الْمُؤْمِنَاتُ مُهَاجِرَاتٍ فَامْتَحِنُوهُنَّ ۖ اللَّهُ أَعْلَمُ بِإِيمَانِهِنَّ ۖ فَإِنْ عَلِمْتُمُوهُنَّ مُؤْمِنَاتٍ فَلَا تَرْجِعُوهُنَّ إِلَى الْكُفَّارِ ۖ لَا هُنَّ حِلٌّ لَّهُمْ وَلَا هُمْ يَحِلُّونَ لَهُنَّ ۖ وَآتُوهُم مَّا أَنفَقُوا ۚ وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ أَن تَنكِحُوهُنَّ إِذَا آتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ ۚ وَلَا تُمْسِكُوا بِعِصَمِ الْكَوَافِرِ وَاسْأَلُوا مَا أَنفَقْتُمْ وَلْيَسْأَلُوا مَا أَنفَقُوا ۚ ذَٰلِكُمْ حُكْمُ اللَّهِ ۖ يَحْكُمُ بَيْنَكُمْ ۚ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ ( 10 ) አል ሙምተሒናህ - Aya 10
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ምእምናት ስደተኞች ኾነው በመጧችሁ ጊዜ (ለሃይማኖት መሰደዳቸውን) ፈትኑዋቸው፡፡ አላህ በእምነታቸው ይበልጥ ዐዋቂ ነው፡፡ አማኞችም መኾናቸውን ብትውቁ ወደ ከሓዲዎቹ አትመልሱዋቸው፡፡ እነርሱ (ሴቶቹ) ለእነርሱ የተፈቀዱ አይደሉምና፡፡ እነርሱም (ወንዶቹ) ለእነርሱ አይፈቀዱምና፡፡ ያወጡትንም ገንዘብ ስጧቸው፡፡ መህራቸውንም በሰጣችኋቸው ጊዜ ብታገቡዋቸው በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም፡፡ የከሓዲዎቹንም ሴቶች የጋብቻ ቃል ኪዳኖች አትያዙ፤ ያወጣችሁትንም ገንዘብ ጠይቁ፡፡ ያወጡትንም ይጠይቁ፡፡ ይህ የአላህ ፍርድ ነው፡፡ በመካከላችሁ ይፈርዳል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ አል ሙምተሒናህ - Aya 10
وَإِن فَاتَكُمْ شَيْءٌ مِّنْ أَزْوَاجِكُمْ إِلَى الْكُفَّارِ فَعَاقَبْتُمْ فَآتُوا الَّذِينَ ذَهَبَتْ أَزْوَاجُهُم مِّثْلَ مَا أَنفَقُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي أَنتُم بِهِ مُؤْمِنُونَ ( 11 ) አል ሙምተሒናህ - Aya 11
ከሚስቶቻችሁም ወደ ከሓዲዎቹ አንዳቸው ቢያመልጧችሁ ቀጥሎም ብትዘምቱባቸው ለእነዚያ ሚስቶቻቸው ለኼዱባቸው (ሰዎች) ያወጡትን ብጤ ስጧቸው፡፡ ያንንም እናንተ በርሱ ያመናችሁበትን አላህን ፍሩ፡፡ አል ሙምተሒናህ - Aya 11
يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِذَا جَاءَكَ الْمُؤْمِنَاتُ يُبَايِعْنَكَ عَلَىٰ أَن لَّا يُشْرِكْنَ بِاللَّهِ شَيْئًا وَلَا يَسْرِقْنَ وَلَا يَزْنِينَ وَلَا يَقْتُلْنَ أَوْلَادَهُنَّ وَلَا يَأْتِينَ بِبُهْتَانٍ يَفْتَرِينَهُ بَيْنَ أَيْدِيهِنَّ وَأَرْجُلِهِنَّ وَلَا يَعْصِينَكَ فِي مَعْرُوفٍ ۙ فَبَايِعْهُنَّ وَاسْتَغْفِرْ لَهُنَّ اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ( 12 ) አል ሙምተሒናህ - Aya 12
አንተ ነቢዩ ሆይ! ምእምናቶቹ በአላህ ምንንም ላያጋሩ፣ ላይሰርቁም ላያመነዝሩም፣ ልጆቻቸውን ላይገድሉም፣ በእጆቻቸውና በእግሮቻቸው መካከልም የሚቀጣጥፉት የኾነን ኃጢኣት ላያመጡ (ላይሠሩ) በበጎም ሥራ ትዕዛዝህን ላይጥሱ ቃል ኪዳን ሊገቡልህ በመጡህ ጊዜ ኪዳን ተጋባቸው፡፡ ለእነርሱም አላህን ምሕረት ለምንላቸው፡፡ አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ አል ሙምተሒናህ - Aya 12
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَوَلَّوْا قَوْمًا غَضِبَ اللَّهُ عَلَيْهِمْ قَدْ يَئِسُوا مِنَ الْآخِرَةِ كَمَا يَئِسَ الْكُفَّارُ مِنْ أَصْحَابِ الْقُبُورِ ( 13 ) አል ሙምተሒናህ - Aya 13
እላንተ ያመናቸሁ ሆይ! አላህ በእነርሱ ላይ የተቆጣባቸውን ሕዝቦች አትወዳጁ፡፡ ከሓዲዎች ከመቃብር ሰዎች ተስፋ እንደቆረጡ ከመጨረሻይቱ ዓለም (ምንዳ) በእርግጥ ተስፋ ቆርጠዋል፡፡ አል ሙምተሒናህ - Aya 13
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah