Surah አል-ተውባህ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል-ተውባህ - Aya count 129
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
بَرَاءَةٌ مِّنَ اللَّهِ وَرَسُولِهِ إِلَى الَّذِينَ عَاهَدتُّم مِّنَ الْمُشْرِكِينَ ( 1 ) አል-ተውባህ - Aya 1
(ይህች) ከአላህና ከመልክተኛው ወደእነዚያ ቃል ኪዳን ወደ ተጋባችኋቸው አጋሪዎች የምትደርስ ንጽሕና ናት፡፡ አል-ተውባህ - Aya 1
فَسِيحُوا فِي الْأَرْضِ أَرْبَعَةَ أَشْهُرٍ وَاعْلَمُوا أَنَّكُمْ غَيْرُ مُعْجِزِي اللَّهِ ۙ وَأَنَّ اللَّهَ مُخْزِي الْكَافِرِينَ ( 2 ) አል-ተውባህ - Aya 2
በምድር ላይም አራት ወሮችን (ጸጥተኞች ስትኾኑ) ኺዱ፡፡ እናንተም ከአላህ (ቅጣት) የማታመልጡ መኾናችሁንና አላህም ከሓዲዎችን አዋራጅ መኾኑን ዕወቁ፤ (በሏቸው)፡፡ አል-ተውባህ - Aya 2
وَأَذَانٌ مِّنَ اللَّهِ وَرَسُولِهِ إِلَى النَّاسِ يَوْمَ الْحَجِّ الْأَكْبَرِ أَنَّ اللَّهَ بَرِيءٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ ۙ وَرَسُولُهُ ۚ فَإِن تُبْتُمْ فَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ ۖ وَإِن تَوَلَّيْتُمْ فَاعْلَمُوا أَنَّكُمْ غَيْرُ مُعْجِزِي اللَّهِ ۗ وَبَشِّرِ الَّذِينَ كَفَرُوا بِعَذَابٍ أَلِيمٍ ( 3 ) አል-ተውባህ - Aya 3
(ይህ) ከአላህና ከመልክተኛው በታላቁ ሐጅ ቀን የወጣ አላህ ከአጋሪዎቹ ንጹሕ ነው መልክተኛውም (እንደዚሁ)፡፡ (ከክህደት) ብትጸጸቱም እርሱ ለእናንተ በላጭ ነው፡፡ (ከእምነት) ብትሸሹም እናንተ አላህን የማታቅቱት መኾናችሁን ዕወቁ በማለት ወደ ሰዎች የሚደርስ ማስታወቂያ ነው፡፡ እነዚያን የካዱትንም በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 3
إِلَّا الَّذِينَ عَاهَدتُّم مِّنَ الْمُشْرِكِينَ ثُمَّ لَمْ يَنقُصُوكُمْ شَيْئًا وَلَمْ يُظَاهِرُوا عَلَيْكُمْ أَحَدًا فَأَتِمُّوا إِلَيْهِمْ عَهْدَهُمْ إِلَىٰ مُدَّتِهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُتَّقِينَ ( 4 ) አል-ተውባህ - Aya 4
ከአጋሪዎቹ እነዚያ ቃል ኪዳን የተጋባችኋቸውና ከዚያም ምንም ያላጎደሉባችሁ በናንተ ላይም አንድንም ያልረዱባችሁ ሲቀሩ፤ (እነዚህን) ቃል ኪዳናቸውን እስከጊዜያታቸው (መጨረሻ) ሙሉላቸው፡፡ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 4
فَإِذَا انسَلَخَ الْأَشْهُرُ الْحُرُمُ فَاقْتُلُوا الْمُشْرِكِينَ حَيْثُ وَجَدتُّمُوهُمْ وَخُذُوهُمْ وَاحْصُرُوهُمْ وَاقْعُدُوا لَهُمْ كُلَّ مَرْصَدٍ ۚ فَإِن تَابُوا وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ فَخَلُّوا سَبِيلَهُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ( 5 ) አል-ተውባህ - Aya 5
የተከበሩትም ወሮች ባለቁ ጊዜ አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸው፡፡ ያዙዋቸውም፣ ክበቡዋቸውም፣ ለእነሱም (መጠባበቅ) በየመንገዱ ተቀመጡ፡፡ ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ፣ ግዴታ ምጽዋትንም ቢሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 5
وَإِنْ أَحَدٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ أَبْلِغْهُ مَأْمَنَهُ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْلَمُونَ ( 6 ) አል-ተውባህ - Aya 6
ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው፡፡ ከዚያም ወደ መጠበቂያው ስፍራ አድርሰው፡፡ ይህ እነሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 6
كَيْفَ يَكُونُ لِلْمُشْرِكِينَ عَهْدٌ عِندَ اللَّهِ وَعِندَ رَسُولِهِ إِلَّا الَّذِينَ عَاهَدتُّمْ عِندَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ۖ فَمَا اسْتَقَامُوا لَكُمْ فَاسْتَقِيمُوا لَهُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُتَّقِينَ ( 7 ) አል-ተውባህ - Aya 7
ለአጋሪዎቹ አላህ ዘንድና እመልክተኛው ዘንድ ቃል ኪዳን እንዴት ይኖራቸዋል እነዚያ በተከበረው መስጊድ ዘንድ ቃል ኪዳን የተጋባችኋቸው ብቻ ሲቀሩ፡፡ (እነዚህ) በቃል ኪዳናቸው ለእናንተ ቀጥ እስካሉላችሁ ድረስ ለነርሱም ቀጥ በሉላቸው፡፡ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 7
كَيْفَ وَإِن يَظْهَرُوا عَلَيْكُمْ لَا يَرْقُبُوا فِيكُمْ إِلًّا وَلَا ذِمَّةً ۚ يُرْضُونَكُم بِأَفْوَاهِهِمْ وَتَأْبَىٰ قُلُوبُهُمْ وَأَكْثَرُهُمْ فَاسِقُونَ ( 8 ) አል-ተውባህ - Aya 8
በእናንተ ላይ ቢያይሉም በእናንተ ውስጥ ዝምድናንና ቃል ኪዳንን የማይጠብቁ ሲኾኑ እንዴት (ቃል ኪዳን ይኖራቸዋል)፡፡ በአፎቻቸው ያስወድዷችኋል፡፡ ልቦቻቸውም እንቢ ይላሉ፡፡ አብዛኞቻቸውም አመጸኞች ናቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 8
اشْتَرَوْا بِآيَاتِ اللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا فَصَدُّوا عَن سَبِيلِهِ ۚ إِنَّهُمْ سَاءَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ ( 9 ) አል-ተውባህ - Aya 9
በአላህ አንቀጾች ጥቂትን ዋጋ ገዙ፡፡ ከመንገዱም አገዱ፡፡ እነርሱ ይሠሩት የነበሩት ሥራ ከፋ! አል-ተውባህ - Aya 9
لَا يَرْقُبُونَ فِي مُؤْمِنٍ إِلًّا وَلَا ذِمَّةً ۚ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُعْتَدُونَ ( 10 ) አል-ተውባህ - Aya 10
በምእምን ነገር ዝምድናንም ኪዳንንም አይጠብቁም፤ እነዚያም እነሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 10
فَإِن تَابُوا وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ فَإِخْوَانُكُمْ فِي الدِّينِ ۗ وَنُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ ( 11 ) አል-ተውባህ - Aya 11
ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም ቢሰግዱ፣ ዘካንም ቢሰጡ የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦችም አንቀጾችን እናብራራለን፡፡ አል-ተውባህ - Aya 11
وَإِن نَّكَثُوا أَيْمَانَهُم مِّن بَعْدِ عَهْدِهِمْ وَطَعَنُوا فِي دِينِكُمْ فَقَاتِلُوا أَئِمَّةَ الْكُفْرِ ۙ إِنَّهُمْ لَا أَيْمَانَ لَهُمْ لَعَلَّهُمْ يَنتَهُونَ ( 12 ) አል-ተውባህ - Aya 12
ከቃል ኪዳናቸው በኋላ መሓላዎቻቸውን ቢያፈርሱ፣ ሃይማኖታችሁንም ቢያነውሩ፣ የክህደት መሪዎችን (ከክህደት) ይከለከሉ ዘንድ ተዋጉዋቸው፡፡ እነርሱ ቃል ኪዳን የላቸውምና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 12
أَلَا تُقَاتِلُونَ قَوْمًا نَّكَثُوا أَيْمَانَهُمْ وَهَمُّوا بِإِخْرَاجِ الرَّسُولِ وَهُم بَدَءُوكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍ ۚ أَتَخْشَوْنَهُمْ ۚ فَاللَّهُ أَحَقُّ أَن تَخْشَوْهُ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ ( 13 ) አል-ተውባህ - Aya 13
መሓላዎቻቸውን ያፈረሱትን መልክተኛውንም ለማውጣት ያሰቡትን ሕዝቦች እነሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመሩዋችሁ ሲኾኑ ለምን አትዋጉዋቸውም ትፈሩዋቸዋላችሁን ምእምናን እንደ ኾናችሁም አላህ ይበልጥ ልትፈሩት የተገባው ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 13
قَاتِلُوهُمْ يُعَذِّبْهُمُ اللَّهُ بِأَيْدِيكُمْ وَيُخْزِهِمْ وَيَنصُرْكُمْ عَلَيْهِمْ وَيَشْفِ صُدُورَ قَوْمٍ مُّؤْمِنِينَ ( 14 ) አል-ተውባህ - Aya 14
ተጋደሉዋቸው፡፡ አላህ በእጆቻችሁ ያሰቃያቸዋል፡፡ ያዋርዳቸዋልም፡፡ በእነሱም ላይ ይረዳችኋል፡፡ የምእምናን ሕዝቦችንም ልቦች ያሽራል፡፡ አል-ተውባህ - Aya 14
وَيُذْهِبْ غَيْظَ قُلُوبِهِمْ ۗ وَيَتُوبُ اللَّهُ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ ( 15 ) አል-ተውባህ - Aya 15
የልቦቻችሁንም ቁጭት ያስወግዳል፡፡ አላህም ከሚሻው ሰው ላይ ጸጸትን ይቀበላል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 15
أَمْ حَسِبْتُمْ أَن تُتْرَكُوا وَلَمَّا يَعْلَمِ اللَّهُ الَّذِينَ جَاهَدُوا مِنكُمْ وَلَمْ يَتَّخِذُوا مِن دُونِ اللَّهِ وَلَا رَسُولِهِ وَلَا الْمُؤْمِنِينَ وَلِيجَةً ۚ وَاللَّهُ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ ( 16 ) አል-ተውባህ - Aya 16
እነዚያን ከእናንተ ውስጥ የታገሉትንና ከአላህም ከመልክተኛውም ከምእመናንም ሌላ ምስጢረኛ ወዳጅ ያልያዙትን አላህ ሳይገልጽ ልትተው ታስባላችሁን አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 16
مَا كَانَ لِلْمُشْرِكِينَ أَن يَعْمُرُوا مَسَاجِدَ اللَّهِ شَاهِدِينَ عَلَىٰ أَنفُسِهِم بِالْكُفْرِ ۚ أُولَٰئِكَ حَبِطَتْ أَعْمَالُهُمْ وَفِي النَّارِ هُمْ خَالِدُونَ ( 17 ) አል-ተውባህ - Aya 17
ለከሓዲዎች በነፍሶቻቸው ላይ በክህደት የሚመሰክሩ ሲኾኑ የአላህን መስጊዶች ሊሠሩ አይገባቸውም፡፡ እነዚያ ሥራዎቻቸው ተበላሹ፡፡ እነሱም በእሳት ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 17
إِنَّمَا يَعْمُرُ مَسَاجِدَ اللَّهِ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَأَقَامَ الصَّلَاةَ وَآتَى الزَّكَاةَ وَلَمْ يَخْشَ إِلَّا اللَّهَ ۖ فَعَسَىٰ أُولَٰئِكَ أَن يَكُونُوا مِنَ الْمُهْتَدِينَ ( 18 ) አል-ተውባህ - Aya 18
የአላህን መስጊዶች የሚሠራው በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ፣ ሶላትንም በደንቡ የሰገደ፣ ግዴታ ምጽዋትንም የሰጠ ከአላህም ሌላ (ማንንም) ያልፈራ ሰው ብቻ ነው፡፡ እነዚያም ከተመሩት ጭምር መኾናቸው ተረጋገጠ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 18
أَجَعَلْتُمْ سِقَايَةَ الْحَاجِّ وَعِمَارَةَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ كَمَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَجَاهَدَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ لَا يَسْتَوُونَ عِندَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ ( 19 ) አል-ተውባህ - Aya 19
ካዕባን ጎብኝዎችን ማጠጣትንና የተከበረውን መስጊድ መሥራትን በአላህና በመጨረሻው ቀን እንዳመነና በአላህ መንገድ እንደታገለ ሰው (እምነትና ትግል) አደረጋችሁን አላህ ዘንድ አይተካከሉም፡፡ አላህም በዳዮች ሕዝቦችን አይመራም፡፡ አል-ተውባህ - Aya 19
الَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ أَعْظَمُ دَرَجَةً عِندَ اللَّهِ ۚ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْفَائِزُونَ ( 20 ) አል-ተውባህ - Aya 20
እነዚያ ያመኑት፣ ከአገራቸውም የተሰደዱት፣ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት አላህ ዘንድ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው፡፡ እነዚያም እነሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 20
يُبَشِّرُهُمْ رَبُّهُم بِرَحْمَةٍ مِّنْهُ وَرِضْوَانٍ وَجَنَّاتٍ لَّهُمْ فِيهَا نَعِيمٌ مُّقِيمٌ ( 21 ) አል-ተውባህ - Aya 21
ጌታቸው ከርሱ በኾነው እዝነትና ውዴታ በገነቶችም ለነሱ በውስጥዋ የማያቋርጥ መጠቀሚያ ያለባት ስትኾን ያበስራቸዋል፡፡ አል-ተውባህ - Aya 21
خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ إِنَّ اللَّهَ عِندَهُ أَجْرٌ عَظِيمٌ ( 22 ) አል-ተውባህ - Aya 22
በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ (ያበስራቸዋል)፡፡ አላህ እርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አለና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 22
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا آبَاءَكُمْ وَإِخْوَانَكُمْ أَوْلِيَاءَ إِنِ اسْتَحَبُّوا الْكُفْرَ عَلَى الْإِيمَانِ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ ( 23 ) አል-ተውባህ - Aya 23
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አባቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ክህደትን ከእምነት አብልጠው ቢወዱ ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ወዳጅ የሚያደርጋቸው እነዚያ እነሱ በዳዮች ናቸው፤ አል-ተውባህ - Aya 23
قُلْ إِن كَانَ آبَاؤُكُمْ وَأَبْنَاؤُكُمْ وَإِخْوَانُكُمْ وَأَزْوَاجُكُمْ وَعَشِيرَتُكُمْ وَأَمْوَالٌ اقْتَرَفْتُمُوهَا وَتِجَارَةٌ تَخْشَوْنَ كَسَادَهَا وَمَسَاكِنُ تَرْضَوْنَهَا أَحَبَّ إِلَيْكُم مِّنَ اللَّهِ وَرَسُولِهِ وَجِهَادٍ فِي سَبِيلِهِ فَتَرَبَّصُوا حَتَّىٰ يَأْتِيَ اللَّهُ بِأَمْرِهِ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْفَاسِقِينَ ( 24 ) አል-ተውባህ - Aya 24
«አባቶቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁም፣ ሚስቶቻችሁም፣ ዘመዶቻችሁም፣ የሰበሰባችኋቸው ሀብቶችም፣ መክሰሩዋን የምትፈሩዋት ንግድም፣ የምትወዷቸው መኖሪያዎችም እናንተ ዘንድ ከአላህና ከመልክተኛው በርሱ መንገድም ከመታገል ይበልጥ የተወደዱ እንደኾኑ አላህ ትእዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ» በላቸው፡፡ አላህም አመጸኞች ሕዝቦችን አይመራም፡፡ አል-ተውባህ - Aya 24
لَقَدْ نَصَرَكُمُ اللَّهُ فِي مَوَاطِنَ كَثِيرَةٍ ۙ وَيَوْمَ حُنَيْنٍ ۙ إِذْ أَعْجَبَتْكُمْ كَثْرَتُكُمْ فَلَمْ تُغْنِ عَنكُمْ شَيْئًا وَضَاقَتْ عَلَيْكُمُ الْأَرْضُ بِمَا رَحُبَتْ ثُمَّ وَلَّيْتُم مُّدْبِرِينَ ( 25 ) አል-ተውባህ - Aya 25
አላህም በብዙ ስፍራዎች በእርግጥ ረዳችሁ፤ የሑነይንም ቀን ብዛታችሁ በአስደነቀቻችሁና ከእናንተም ምንም ባልጠቀመቻችሁ ጊዜ ምድርም ከስፋቷ ጋር በጠበበቻችሁና ከዚያም ተሸናፊዎች ኾናችሁ በዞራችሁ ጊዜ (ረዳችሁ)፡፡ አል-ተውባህ - Aya 25
ثُمَّ أَنزَلَ اللَّهُ سَكِينَتَهُ عَلَىٰ رَسُولِهِ وَعَلَى الْمُؤْمِنِينَ وَأَنزَلَ جُنُودًا لَّمْ تَرَوْهَا وَعَذَّبَ الَّذِينَ كَفَرُوا ۚ وَذَٰلِكَ جَزَاءُ الْكَافِرِينَ ( 26 ) አል-ተውባህ - Aya 26
ከዚያም አላህ እርጋታውን በመልክተኛውና በምእምናኖቹ ላይ አወረደ፡፡ ያላያችኋቸውንም ሰራዊት አወረደ፡፡ እነዚያን የካዱትንም በመገደልና በመማረክ አሰቃየ፡፡ ይህም የከሓዲያን ፍዳ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 26
ثُمَّ يَتُوبُ اللَّهُ مِن بَعْدِ ذَٰلِكَ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ( 27 ) አል-ተውባህ - Aya 27
ከዚያም ከዚህ በኋላ አላህ በሚሻው ሰው ላይ ጸጸትን ይቀበላል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 27
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْمُشْرِكُونَ نَجَسٌ فَلَا يَقْرَبُوا الْمَسْجِدَ الْحَرَامَ بَعْدَ عَامِهِمْ هَٰذَا ۚ وَإِنْ خِفْتُمْ عَيْلَةً فَسَوْفَ يُغْنِيكُمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ إِن شَاءَ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ حَكِيمٌ ( 28 ) አል-ተውባህ - Aya 28
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህም ዓመታቸው በኋላ የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ፡፡ ድኽነትንም ብትፈሩ አላህ ቢሻ ከችሮታው በእርግጥ ያከብራችኋል፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 28
قَاتِلُوا الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَلَا بِالْيَوْمِ الْآخِرِ وَلَا يُحَرِّمُونَ مَا حَرَّمَ اللَّهُ وَرَسُولُهُ وَلَا يَدِينُونَ دِينَ الْحَقِّ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ حَتَّىٰ يُعْطُوا الْجِزْيَةَ عَن يَدٍ وَهُمْ صَاغِرُونَ ( 29 ) አል-ተውባህ - Aya 29
ከእነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡት ሰዎች እነዚያን በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑትን፣ አላህና መልክተኛው እርም ያደረጉትንም እርም የማያደርጉትንና እውነተኛውንም ሃይማኖት የማይቀበሉትን እነርሱ የተዋረዱ ኾነው ግብርን በእጆቻቸው እስከሚሰጡ ድረስ ተዋጉዋቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 29
وَقَالَتِ الْيَهُودُ عُزَيْرٌ ابْنُ اللَّهِ وَقَالَتِ النَّصَارَى الْمَسِيحُ ابْنُ اللَّهِ ۖ ذَٰلِكَ قَوْلُهُم بِأَفْوَاهِهِمْ ۖ يُضَاهِئُونَ قَوْلَ الَّذِينَ كَفَرُوا مِن قَبْلُ ۚ قَاتَلَهُمُ اللَّهُ ۚ أَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ ( 30 ) አል-ተውባህ - Aya 30
አይሁድ ዑዘይር የአላህ ልጅ ነው አለች፡፡ ክርስቲያኖችም አልመሲሕ የአላህ ልጅ ነው አሉ፡፡ ይህ በአፎቻቸው (የሚናገሩት) ቃላቸው ነው፡፡ የእነዚያን ከነሱ በፊት የካዱትን ሰዎች ቃል ያመሳስላሉ፡፡ አላህ ያጥፋቸው፡፡ (ከእውነት) እንዴት ይመለሳሉ! አል-ተውባህ - Aya 30
اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَٰهًا وَاحِدًا ۖ لَّا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ ( 31 ) አል-ተውባህ - Aya 31
ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 31
يُرِيدُونَ أَن يُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَيَأْبَى اللَّهُ إِلَّا أَن يُتِمَّ نُورَهُ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ ( 32 ) አል-ተውባህ - Aya 32
የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አይሻም፡፡ አል-ተውባህ - Aya 32
هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَىٰ وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُشْرِكُونَ ( 33 ) አል-ተውባህ - Aya 33
እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን (ሙሐመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 33
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ كَثِيرًا مِّنَ الْأَحْبَارِ وَالرُّهْبَانِ لَيَأْكُلُونَ أَمْوَالَ النَّاسِ بِالْبَاطِلِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۗ وَالَّذِينَ يَكْنِزُونَ الذَّهَبَ وَالْفِضَّةَ وَلَا يُنفِقُونَهَا فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَبَشِّرْهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ ( 34 ) አል-ተውባህ - Aya 34
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሊቃውንትና ከመነኮሳት ብዙዎቹ የሰዎችን ገንዘቦች በውሸት በእርግጥ ይበላሉ፡፡ ከአላህም መንገድ ያግዳሉ፡፡ እነዚያንም ወርቅንና ብርን የሚያደልቡትን በአላህም መንገድ ላይ የማያወጧትን በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 34
يَوْمَ يُحْمَىٰ عَلَيْهَا فِي نَارِ جَهَنَّمَ فَتُكْوَىٰ بِهَا جِبَاهُهُمْ وَجُنُوبُهُمْ وَظُهُورُهُمْ ۖ هَٰذَا مَا كَنَزْتُمْ لِأَنفُسِكُمْ فَذُوقُوا مَا كُنتُمْ تَكْنِزُونَ ( 35 ) አል-ተውባህ - Aya 35
በርሷ ላይ በገሀነም እሳት ውስጥ በሚጋልባትና ግንባሮቻቸውም፣ ጎኖቻቸውም፣ ጀርባዎቻቸውም በርሷ በሚተኮሱ ቀን (አሳማሚ በኾነ ቅጣት አብስራቸው)፡፡ ይህ ለነፍሶቻችሁ ያደለባችሁት ነው፡፡ ታደልቡት የነበራችሁትንም ቅመሱ (ይባላሉ)፡፡ አል-ተውባህ - Aya 35
إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ ۚ فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ ۚ وَقَاتِلُوا الْمُشْرِكِينَ كَافَّةً كَمَا يُقَاتِلُونَكُمْ كَافَّةً ۚ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ مَعَ الْمُتَّقِينَ ( 36 ) አል-ተውባህ - Aya 36
የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡ አጋሪዎችንም በአንድ ላይ ኾነው እንደሚዋጉዋችሁ በአንድ ላይ ኾናችሁ ተጋደሉዋቸው፡፡ አላህም ከሚፈሩት ጋር መኾኑን ዕወቁ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 36
إِنَّمَا النَّسِيءُ زِيَادَةٌ فِي الْكُفْرِ ۖ يُضَلُّ بِهِ الَّذِينَ كَفَرُوا يُحِلُّونَهُ عَامًا وَيُحَرِّمُونَهُ عَامًا لِّيُوَاطِئُوا عِدَّةَ مَا حَرَّمَ اللَّهُ فَيُحِلُّوا مَا حَرَّمَ اللَّهُ ۚ زُيِّنَ لَهُمْ سُوءُ أَعْمَالِهِمْ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْكَافِرِينَ ( 37 ) አል-ተውባህ - Aya 37
የአንዱን ወር ክብር ወደ ሌላው ማዘግየት በክህደት ላይ (ክህደትን) መጨመር ብቻ ነው፡፡ በእርሱ እነዚያ የካዱት ሰዎች ይሳሳቱበታል፡፡ በአንድ ዓመት የተፈቀደ ያደርጉታል፡፡ በሌላው ዓመትም ያወግዙታል፡፡ (ይህ) አላህ ያከበራቸውን ወሮች ቁጥር ሊያስተካክሉ፣ አላህም እርም ያደረገውን የተፈቀደ ሊያደርጉ ነው፡፡ የሥራዎቻቸው መጥፎው ለነርሱ ተዋበላቸው፡፡ አላህም ከሓዲያን ሕዝቦችን አይመራም፡፡ አል-ተውባህ - Aya 37
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا مَا لَكُمْ إِذَا قِيلَ لَكُمُ انفِرُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ اثَّاقَلْتُمْ إِلَى الْأَرْضِ ۚ أَرَضِيتُم بِالْحَيَاةِ الدُّنْيَا مِنَ الْآخِرَةِ ۚ فَمَا مَتَاعُ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا فِي الْآخِرَةِ إِلَّا قَلِيلٌ ( 38 ) አል-ተውባህ - Aya 38
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ መንገድ (ለመታገል) ውጡ በተባላችሁ ጊዜ ወደ ምድር የምትወዘፉት ለእናንተ ምን አላችሁ የቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ ይበልጥ ወደዳችሁን የቅርቢቱም ሕይወት ጥቅም በመጨረሻይቱ (አንጻር) ጥቂት እንጂ አይደለም፡፡ አል-ተውባህ - Aya 38
إِلَّا تَنفِرُوا يُعَذِّبْكُمْ عَذَابًا أَلِيمًا وَيَسْتَبْدِلْ قَوْمًا غَيْرَكُمْ وَلَا تَضُرُّوهُ شَيْئًا ۗ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ( 39 ) አል-ተውባህ - Aya 39
ለዘመቻ ባትወጡ (አላህ) አሳማሚን ቅጣት ይቀጣችኋል፡፡ ከእናንተ ሌላ የኾኑንም ሕዝቦች ይለውጣል፡፡ በምንም አትጎዱትምም፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 39
إِلَّا تَنصُرُوهُ فَقَدْ نَصَرَهُ اللَّهُ إِذْ أَخْرَجَهُ الَّذِينَ كَفَرُوا ثَانِيَ اثْنَيْنِ إِذْ هُمَا فِي الْغَارِ إِذْ يَقُولُ لِصَاحِبِهِ لَا تَحْزَنْ إِنَّ اللَّهَ مَعَنَا ۖ فَأَنزَلَ اللَّهُ سَكِينَتَهُ عَلَيْهِ وَأَيَّدَهُ بِجُنُودٍ لَّمْ تَرَوْهَا وَجَعَلَ كَلِمَةَ الَّذِينَ كَفَرُوا السُّفْلَىٰ ۗ وَكَلِمَةُ اللَّهِ هِيَ الْعُلْيَا ۗ وَاللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ ( 40 ) አል-ተውባህ - Aya 40
(ነቢዩን) ባትረዱት እነዚያ የካዱት ሕዝቦች የሁለት (ሰዎች) ሁለተኛ ኾኖ (ከመካ) ባወጡት ጊዜ አላህ በእርግጥ ረድቶታል፡፡ ሁለቱም በዋሻው ሳሉ ለጓደኛው አትዘን አላህ ከእኛ ጋር ነውና ባለ ጊዜ አላህም መረጋጋትን በእርሱ ላይ አወረደ፡፡ ባላያችኋቸውም ሰራዊት አበረታው፡፡ የእነዚያንም የካዱትን ሰዎች ቃል ዝቅተኛ አደረገ፡፡ የአላህም ቃል ለእርሷ ከፍተኛ ናት፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 40
انفِرُوا خِفَافًا وَثِقَالًا وَجَاهِدُوا بِأَمْوَالِكُمْ وَأَنفُسِكُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ ( 41 ) አል-ተውባህ - Aya 41
ቀላሎችም ከባዶችም ኾናችሁ ዝመቱ፡፡ በአላህም መንገድ በገንዘቦቻችሁ በነፍሶቻችሁም ታገሉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለናንተ በጣም የተሻለ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 41
لَوْ كَانَ عَرَضًا قَرِيبًا وَسَفَرًا قَاصِدًا لَّاتَّبَعُوكَ وَلَٰكِن بَعُدَتْ عَلَيْهِمُ الشُّقَّةُ ۚ وَسَيَحْلِفُونَ بِاللَّهِ لَوِ اسْتَطَعْنَا لَخَرَجْنَا مَعَكُمْ يُهْلِكُونَ أَنفُسَهُمْ وَاللَّهُ يَعْلَمُ إِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ ( 42 ) አል-ተውባህ - Aya 42
(የጠራህባቸው ነገር) ቅርብ ጥቅምና መካከለኛ ጉዞ በኾነ ኖሮ በተከተሉህ ነበር፡፡ ግን በነሱ ላይ መንገዲቱ ራቀችባቸው፡፡ «በቻልንም ኖሮ ከእናንተ ጋር በወጣን ነበር» ሲሉ በአላህ ይምላሉ፡፡ ነፍሶቻቸውን ያጠፋሉ፡፡ አላህም እነሱ ውሸታሞች መኾናቸውን በእርግጥ ያውቃል፡፡ አል-ተውባህ - Aya 42
عَفَا اللَّهُ عَنكَ لِمَ أَذِنتَ لَهُمْ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَكَ الَّذِينَ صَدَقُوا وَتَعْلَمَ الْكَاذِبِينَ ( 43 ) አል-ተውባህ - Aya 43
አላህ ከአንተ ይቅር አለ፡፡ እነዚያ እውነተኛዎቹ ላንተ እስከሚገለጹልህና ውሸታሞቹንም እስከምታውቅ ድረስ ለነርሱ (እንዲቀሩ) ለምን ፈቀድክላቸው አል-ተውባህ - Aya 43
لَا يَسْتَأْذِنُكَ الَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ أَن يُجَاهِدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِالْمُتَّقِينَ ( 44 ) አል-ተውባህ - Aya 44
እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው ከመታገላቸው (ለመቅረት) ፈቃድን አይጠይቁህም፡፡ አላህም የሚፈሩትን ዐዋቂ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 44
إِنَّمَا يَسْتَأْذِنُكَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَارْتَابَتْ قُلُوبُهُمْ فَهُمْ فِي رَيْبِهِمْ يَتَرَدَّدُونَ ( 45 ) አል-ተውባህ - Aya 45
ፈቃድን የሚጠይቁህ እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑት ልቦቻቸውም የተጠራጠሩት ብቻ ናቸው፡፡ እነሱም በጥርጣሬያቸው ውስጥ ይዋልላሉ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 45
وَلَوْ أَرَادُوا الْخُرُوجَ لَأَعَدُّوا لَهُ عُدَّةً وَلَٰكِن كَرِهَ اللَّهُ انبِعَاثَهُمْ فَثَبَّطَهُمْ وَقِيلَ اقْعُدُوا مَعَ الْقَاعِدِينَ ( 46 ) አል-ተውባህ - Aya 46
መውጣትንም ባሰቡ ኖሮ ለርሱ ዝግጅትን ባሰናዱ ነበር፡፡ ግን አላህ (ለመውጣት) እንቅስቃሴያቸውን ጠላ (አልሻውም)፡፡ አሰነፋቸውም፡፡ ከተቀማጮቹም ጋር ተቀመጡ ተባሉ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 46
لَوْ خَرَجُوا فِيكُم مَّا زَادُوكُمْ إِلَّا خَبَالًا وَلَأَوْضَعُوا خِلَالَكُمْ يَبْغُونَكُمُ الْفِتْنَةَ وَفِيكُمْ سَمَّاعُونَ لَهُمْ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِالظَّالِمِينَ ( 47 ) አል-ተውባህ - Aya 47
ከእናንተ ጋር በወጡ ኖሮ ጥፋትን እንጂ አይጨምሩላችሁም ነበር፡፡ ሁከትንም የሚፈልጉላችሁ ሲኾኑ በመካከላችሁ (በማሳበቅ) ይቻኮሉ ነበር፡፡ በናንተም ውስጥ ለነሱ አዳማጮች አሏቸው፡፡ አላህም በዳዮችን ዐዋቂ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 47
لَقَدِ ابْتَغَوُا الْفِتْنَةَ مِن قَبْلُ وَقَلَّبُوا لَكَ الْأُمُورَ حَتَّىٰ جَاءَ الْحَقُّ وَظَهَرَ أَمْرُ اللَّهِ وَهُمْ كَارِهُونَ ( 48 ) አል-ተውባህ - Aya 48
እነርሱ ጠይዎች ሲኾኑ እውነቱ እስከመጣና የአላህም ትዕዛዝ እስከተገለጸ ድረስ ከዚህ በፊት ሁከትን በእርግጥ ፈለጉ፡፡ ነገሮችንም ሁሉ አገላበጡልህ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 48
وَمِنْهُم مَّن يَقُولُ ائْذَن لِّي وَلَا تَفْتِنِّي ۚ أَلَا فِي الْفِتْنَةِ سَقَطُوا ۗ وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمُحِيطَةٌ بِالْكَافِرِينَ ( 49 ) አል-ተውባህ - Aya 49
ከነሱም ውስጥ «ለእኔ ፍቀድልኝ አትሞክረኝም» የሚል ሰው አልለ፡፡ ንቁ! በመከራ ውስጥ ወደቁ፡፡ ገሀነምም ከሓዲዎችን በእርግጥ ከባቢ ናት፡፡ አል-ተውባህ - Aya 49
إِن تُصِبْكَ حَسَنَةٌ تَسُؤْهُمْ ۖ وَإِن تُصِبْكَ مُصِيبَةٌ يَقُولُوا قَدْ أَخَذْنَا أَمْرَنَا مِن قَبْلُ وَيَتَوَلَّوا وَّهُمْ فَرِحُونَ ( 50 ) አል-ተውባህ - Aya 50
መልካም ነገር ብታገኝህ ታስከፋቸዋለች፡፡ መከራም ብታገኝህ «ከዚህ በፊት በእርግጥ ጥንቃቄያችንን ይዘናል» ይላሉ፡፡ እነርሱም ተደሳቾች ኾነው ይሸሻሉ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 50
قُل لَّن يُصِيبَنَا إِلَّا مَا كَتَبَ اللَّهُ لَنَا هُوَ مَوْلَانَا ۚ وَعَلَى اللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ الْمُؤْمِنُونَ ( 51 ) አል-ተውባህ - Aya 51
«አላህ ለኛ የጻፈልን (ጥቅም) እንጂ ሌላ አይነካንም፡፡ እርሱ ረዳታችን ነው፡፡ በአላህ ላይም ምእመናን ይመኩ» በላቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 51
قُلْ هَلْ تَرَبَّصُونَ بِنَا إِلَّا إِحْدَى الْحُسْنَيَيْنِ ۖ وَنَحْنُ نَتَرَبَّصُ بِكُمْ أَن يُصِيبَكُمُ اللَّهُ بِعَذَابٍ مِّنْ عِندِهِ أَوْ بِأَيْدِينَا ۖ فَتَرَبَّصُوا إِنَّا مَعَكُم مُّتَرَبِّصُونَ ( 52 ) አል-ተውባህ - Aya 52
«በእኛ ላይ ከሁለቱ መልካሞች አንደኛዋን እንጂ ሌላን ትጠባበቃላችሁን እኛም አላህ ከእርሱ በኾነው ቅጣት ወይም በእጆቻችን የሚያጠፋችሁ መኾኑን በናንተ ላይ እንጠባበቃለን፡፡ ተጠባበቁም እኛ ከእናንተ ጋር ተጠባባቂዎች ነንና» በላቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 52
قُلْ أَنفِقُوا طَوْعًا أَوْ كَرْهًا لَّن يُتَقَبَّلَ مِنكُمْ ۖ إِنَّكُمْ كُنتُمْ قَوْمًا فَاسِقِينَ ( 53 ) አል-ተውባህ - Aya 53
«ወዳችሁም ኾነ ጠልታችሁ ለግሱ፡፡ ከእናንተ ተቀባይ የላችሁም፡፡ እናንተ አመጸኞች ሕዝቦች ናችሁና» በላቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 53
وَمَا مَنَعَهُمْ أَن تُقْبَلَ مِنْهُمْ نَفَقَاتُهُمْ إِلَّا أَنَّهُمْ كَفَرُوا بِاللَّهِ وَبِرَسُولِهِ وَلَا يَأْتُونَ الصَّلَاةَ إِلَّا وَهُمْ كُسَالَىٰ وَلَا يُنفِقُونَ إِلَّا وَهُمْ كَارِهُونَ ( 54 ) አል-ተውባህ - Aya 54
ልግስናዎቻቸውን ከነሱ ተቀባይ የሚያገኙ ከመኾን እነሱ በአላህና በመልክተኛው የካዱ፣ ሶላትንም እነሱ ታካቾች ኾነው በስተቀር የማይሰግዱ፣ እነሱም ጠይዎች ኾነው በስተቀር የማይሰጡ መኾናቸው እንጂ ሌላ አልከለከላቸውም፡፡ አል-ተውባህ - Aya 54
فَلَا تُعْجِبْكَ أَمْوَالُهُمْ وَلَا أَوْلَادُهُمْ ۚ إِنَّمَا يُرِيدُ اللَّهُ لِيُعَذِّبَهُم بِهَا فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَتَزْهَقَ أَنفُسُهُمْ وَهُمْ كَافِرُونَ ( 55 ) አል-ተውባህ - Aya 55
ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸውም አይድነቁህ፡፡ አላህ የሚሻው በቅርቢቱ ሕይወት በነርሱ (በገንዘቦቻቸውና በልጆቻቸው) ሊቀጣቸው ነፍሶቻቸውም እነሱ ከሓዲዎች ኾነው ሊወጡ ብቻ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 55
وَيَحْلِفُونَ بِاللَّهِ إِنَّهُمْ لَمِنكُمْ وَمَا هُم مِّنكُمْ وَلَٰكِنَّهُمْ قَوْمٌ يَفْرَقُونَ ( 56 ) አል-ተውባህ - Aya 56
እነሱም በእርግጥ ከእናንተ ለመኾናቸው በአላህ ይምላሉ፡፡ እነርሱም ከናንተ አይደሉም፡፡ ግን እነሱ (አጋሪዎችን ያገኘ እንዳያገኛቸው) የሚፈሩ ሕዝቦች ናቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 56
لَوْ يَجِدُونَ مَلْجَأً أَوْ مَغَارَاتٍ أَوْ مُدَّخَلًا لَّوَلَّوْا إِلَيْهِ وَهُمْ يَجْمَحُونَ ( 57 ) አል-ተውባህ - Aya 57
መጠጊያን ወይም ዋሻዎችን ወይም መግቢያን (ቀዳዳ) ባገኙ ኖሮ እነርሱ እየገሰገሱ ወደርሱ በሸሹ ነበር፡፡ አል-ተውባህ - Aya 57
وَمِنْهُم مَّن يَلْمِزُكَ فِي الصَّدَقَاتِ فَإِنْ أُعْطُوا مِنْهَا رَضُوا وَإِن لَّمْ يُعْطَوْا مِنْهَا إِذَا هُمْ يَسْخَطُونَ ( 58 ) አል-ተውባህ - Aya 58
ከነሱም ውስጥ በምጽዋቶች የሚዘልፉህ ሰዎች አሉ፡፡ ከርሷም (የሚሹትን) ቢስሰጡ ይደሰታሉ፡፡ ከርሷም ባይስሰጡ እነሱ ያን ጊዜ ይጠላሉ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 58
وَلَوْ أَنَّهُمْ رَضُوا مَا آتَاهُمُ اللَّهُ وَرَسُولُهُ وَقَالُوا حَسْبُنَا اللَّهُ سَيُؤْتِينَا اللَّهُ مِن فَضْلِهِ وَرَسُولُهُ إِنَّا إِلَى اللَّهِ رَاغِبُونَ ( 59 ) አል-ተውባህ - Aya 59
እነሱም አላህና መልክተኛው የሰጣቸውን በወደዱ፣ «አላህም በቂያችን ነው፤ አላህ ከችሮታው በእርግጥ ይሰጠናል፣ መልክተኛውም (ይሰጠናል)፣ እኛ ወደ አላህ ከጃዮች ነን» ባሉ ኖሮ (ለነሱ በተሻላቸው ነበር)፡፡ አል-ተውባህ - Aya 59
إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۖ فَرِيضَةً مِّنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ ( 60 ) አል-ተውባህ - Aya 60
ግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድኾች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱት፣ ጫንቃዎችንም (በባርነት ተገዢዎችን) ነጻ በማውጣት፣ በባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሠሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 60
وَمِنْهُمُ الَّذِينَ يُؤْذُونَ النَّبِيَّ وَيَقُولُونَ هُوَ أُذُنٌ ۚ قُلْ أُذُنُ خَيْرٍ لَّكُمْ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَيُؤْمِنُ لِلْمُؤْمِنِينَ وَرَحْمَةٌ لِّلَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ ۚ وَالَّذِينَ يُؤْذُونَ رَسُولَ اللَّهِ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ ( 61 ) አል-ተውባህ - Aya 61
ከእነሱም (ከመናፍቃን) እነዚያ ነቢዩን የሚያሰቃዩ «እርሱም ጆሮ ነው» (ወሬ ሰሚ ነው) የሚሉ አልሉ በላቸው፡፡ ለእናንተ የበጎ (ወሬ) ሰሚ ነው፡፡ በአላህ ያምናል፣ ምእምናንንም ያምናቸዋል፣ ከእናንተም ውስጥ ለነዚያ ላመኑት እዝነት ነው፡፡ እነዚያም የአላህን መልክተኛ የሚያሰቃዩ ለነሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 61
يَحْلِفُونَ بِاللَّهِ لَكُمْ لِيُرْضُوكُمْ وَاللَّهُ وَرَسُولُهُ أَحَقُّ أَن يُرْضُوهُ إِن كَانُوا مُؤْمِنِينَ ( 62 ) አል-ተውባህ - Aya 62
አላህንና መልክተኛውን ሊያስወድዱ ተገቢያቸው ሲኾን እናንተን ያስወደዷችሁ ዘንድ በአላህ ይምሉላችኋል፡፡ ምእምናኖች ቢኾኑ (አላህንና መልክተኛውን ያስወድዱ)፡፡ አል-ተውባህ - Aya 62
أَلَمْ يَعْلَمُوا أَنَّهُ مَن يُحَادِدِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ فَأَنَّ لَهُ نَارَ جَهَنَّمَ خَالِدًا فِيهَا ۚ ذَٰلِكَ الْخِزْيُ الْعَظِيمُ ( 63 ) አል-ተውባህ - Aya 63
አላህንና መልክተኛውን የሚከራከር ሰው ለእርሱ የገሀነም እሳት በውስጧ ዘውታሪ ሲኾን የተገባቺው መኾኑን አያውቁምን ይህ ታላቅ ውርደት ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 63
يَحْذَرُ الْمُنَافِقُونَ أَن تُنَزَّلَ عَلَيْهِمْ سُورَةٌ تُنَبِّئُهُم بِمَا فِي قُلُوبِهِمْ ۚ قُلِ اسْتَهْزِئُوا إِنَّ اللَّهَ مُخْرِجٌ مَّا تَحْذَرُونَ ( 64 ) አል-ተውባህ - Aya 64
መናፍቃን በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር የምትነግራቸው ሱራ በእነርሱ ላይ መውረዷን ይፈራሉ፡፡ «አላግጡ አላህ የምትፈሩትን ሁሉ ገላጭ ነው» በላቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 64
وَلَئِن سَأَلْتَهُمْ لَيَقُولُنَّ إِنَّمَا كُنَّا نَخُوضُ وَنَلْعَبُ ۚ قُلْ أَبِاللَّهِ وَآيَاتِهِ وَرَسُولِهِ كُنتُمْ تَسْتَهْزِئُونَ ( 65 ) አል-ተውባህ - Aya 65
በእርግጥ ብትጠይቃቸው «እኛ የምንዘባርቅና የምንጫወት ብቻ ነበርን» ይላሉ፡፡ «በአላህና በአንቀጾቹ፣ በመልክተኛውም ታላግጡ ነበራችሁን» በላቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 65
لَا تَعْتَذِرُوا قَدْ كَفَرْتُم بَعْدَ إِيمَانِكُمْ ۚ إِن نَّعْفُ عَن طَائِفَةٍ مِّنكُمْ نُعَذِّبْ طَائِفَةً بِأَنَّهُمْ كَانُوا مُجْرِمِينَ ( 66 ) አል-ተውባህ - Aya 66
አታመካኙ፤ ከእምነታችሁ በኋላ በእርግጥ ካዳችሁ፡፡ ከእናንተ አንዷን ጭፍራ ብንምር (ሌላዋን) ጭፍራ እነሱ ኃጢአተኞች በመኾናቸው እንቀጣለን፡፡ አል-ተውባህ - Aya 66
الْمُنَافِقُونَ وَالْمُنَافِقَاتُ بَعْضُهُم مِّن بَعْضٍ ۚ يَأْمُرُونَ بِالْمُنكَرِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمَعْرُوفِ وَيَقْبِضُونَ أَيْدِيَهُمْ ۚ نَسُوا اللَّهَ فَنَسِيَهُمْ ۗ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ هُمُ الْفَاسِقُونَ ( 67 ) አል-ተውባህ - Aya 67
መናፍቃንና መናፍቃት ከፊሎቻቸው ከከፊሉ ናቸው፡፡ በመጥፎ ነገር ያዛሉ ከደግም ነገር ይከለክላሉ፡፡ እጆቻቸውንም (ከልግስና) ይሰበስባሉ፡፡ አላህን ረሱ፡፡፤ ስለዚህ (እርሱ) ዋቸው፡፡ መናፍቃን አመጸኞቹ እነሱ ናቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 67
وَعَدَ اللَّهُ الْمُنَافِقِينَ وَالْمُنَافِقَاتِ وَالْكُفَّارَ نَارَ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ هِيَ حَسْبُهُمْ ۚ وَلَعَنَهُمُ اللَّهُ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ مُّقِيمٌ ( 68 ) አል-ተውባህ - Aya 68
መናፍቃንንና መናፍቃትን፣ ከሓዲዎችንም አላህ የገሀነምን እሳት በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ እርሷ በቂያቸው ናት፡፡ አላህም ረግሟቸዋል፡፡ ለእነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 68
كَالَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ كَانُوا أَشَدَّ مِنكُمْ قُوَّةً وَأَكْثَرَ أَمْوَالًا وَأَوْلَادًا فَاسْتَمْتَعُوا بِخَلَاقِهِمْ فَاسْتَمْتَعْتُم بِخَلَاقِكُمْ كَمَا اسْتَمْتَعَ الَّذِينَ مِن قَبْلِكُم بِخَلَاقِهِمْ وَخُضْتُمْ كَالَّذِي خَاضُوا ۚ أُولَٰئِكَ حَبِطَتْ أَعْمَالُهُمْ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ۖ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ ( 69 ) አል-ተውባህ - Aya 69
እንደነዚያ ከናንተ በፊት እንደ ነበሩት ናችሁ፡፡ ከእናንተ ይበልጥ በኃይል የበረቱ በገንዘቦችም በልጆችም ይበልጥ የበዙ ነበሩ፡፡ በዕድላቸውም ተጠቀሙ፡፡ እነዚያም ከእናንተ በፊት የነበሩት በዕድላቸው እንደተጠቀሙ በዕድላችሁ ተጠቀማችሁ፡፡ እንደነዚያም እንደዘባረቁት ዘባረቃችሁ፡፡ እነዚያ ሥራዎቻቸው በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም ተበላሹ፡፡ እነዚያም ከሳሪዎቹ እነሱ ናቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 69
أَلَمْ يَأْتِهِمْ نَبَأُ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ قَوْمِ نُوحٍ وَعَادٍ وَثَمُودَ وَقَوْمِ إِبْرَاهِيمَ وَأَصْحَابِ مَدْيَنَ وَالْمُؤْتَفِكَاتِ ۚ أَتَتْهُمْ رُسُلُهُم بِالْبَيِّنَاتِ ۖ فَمَا كَانَ اللَّهُ لِيَظْلِمَهُمْ وَلَٰكِن كَانُوا أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ ( 70 ) አል-ተውባህ - Aya 70
የእነዚያ ከእናንተ በፊት የነበሩት የኑሕ ሕዝቦች፣ የዓድና የሰሙድም፣ የኢብራሂምም ሕዝቦች የመድየን ባለቤቶችና የተገልባጮቹም ከተሞች ወሬ አልመጣላቸውምን መልክተኞቻቸው በተዓምራት መጧቸው፡፡ አላህም የሚበድላቸው አልነበረም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 70
وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَيُطِيعُونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ أُولَٰئِكَ سَيَرْحَمُهُمُ اللَّهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ ( 71 ) አል-ተውባህ - Aya 71
ምእምንና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ፡፡ ሶላትንም ይሰግዳሉ፡፡ ዘካንም ይሰጣሉ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ይታዘዛሉ፡፡ እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 71
وَعَدَ اللَّهُ الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَمَسَاكِنَ طَيِّبَةً فِي جَنَّاتِ عَدْنٍ ۚ وَرِضْوَانٌ مِّنَ اللَّهِ أَكْبَرُ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ ( 72 ) አል-ተውባህ - Aya 72
አላህ ምእምናንንና ምእምናትን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በመኖሪያ ገነቶችም ውስጥ መልካም መኖሪያ ቤቶችን ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ ከአላህም የኾነው ውዴታ ከሁሉ የበለጠ ነው፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ እድል ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 72
يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ جَاهِدِ الْكُفَّارَ وَالْمُنَافِقِينَ وَاغْلُظْ عَلَيْهِمْ ۚ وَمَأْوَاهُمْ جَهَنَّمُ ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ ( 73 ) አል-ተውባህ - Aya 73
አንተ ነቢዩ ሆይ! ከሓዲዎችንና መናፍቃንን ታገል፡፡ በእነሱም ላይ ጨክን፡፡ መኖሪያቸውም ገሀነም ናት፡፡ መመለሻይቱም ከፋች፡፡ አል-ተውባህ - Aya 73
يَحْلِفُونَ بِاللَّهِ مَا قَالُوا وَلَقَدْ قَالُوا كَلِمَةَ الْكُفْرِ وَكَفَرُوا بَعْدَ إِسْلَامِهِمْ وَهَمُّوا بِمَا لَمْ يَنَالُوا ۚ وَمَا نَقَمُوا إِلَّا أَنْ أَغْنَاهُمُ اللَّهُ وَرَسُولُهُ مِن فَضْلِهِ ۚ فَإِن يَتُوبُوا يَكُ خَيْرًا لَّهُمْ ۖ وَإِن يَتَوَلَّوْا يُعَذِّبْهُمُ اللَّهُ عَذَابًا أَلِيمًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ۚ وَمَا لَهُمْ فِي الْأَرْضِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ ( 74 ) አል-ተውባህ - Aya 74
ምንም ያላሉ ለመኾናቸው በአላህ ይምላሉ፡፡ የክህደትንም ቃል በእርግጥ አሉ፡፡ ከእስልምናቸውም በኋላ ካዱ፡፡ ያላገኙትንም ነገር አሰቡ፡፡ አላህም ከችሮታው መልክተኛውም (እንደዚሁ) ያከበራቸው መኾኑን እንጂ ሌላን አልጠሉም፡፡ ቢጸጸቱም ለእነሱ የተሻለ ይኾናል፡፡ ቢሸሹም አላህ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም አሳማሚን ቅጣት ይቀጣቸዋል፡፡ ለእነሱም በምድር ውስጥ ምንም ወዳጅና ረዳት የላቸውም፡፡ አል-ተውባህ - Aya 74
وَمِنْهُم مَّنْ عَاهَدَ اللَّهَ لَئِنْ آتَانَا مِن فَضْلِهِ لَنَصَّدَّقَنَّ وَلَنَكُونَنَّ مِنَ الصَّالِحِينَ ( 75 ) አል-ተውባህ - Aya 75
ከእነሱም «አላህን ከችሮታው ቢሰጠን በእርግጥ እንመጸውታለን ከመልካሞቹም በእርግጥ እንኾናለን» ሲል ቃል የተጋባ አልለ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 75
فَلَمَّا آتَاهُم مِّن فَضْلِهِ بَخِلُوا بِهِ وَتَوَلَّوا وَّهُم مُّعْرِضُونَ ( 76 ) አል-ተውባህ - Aya 76
ከችሮታውም በሰጣቸው ጊዜ በእርሱ ሰሰቱ፡፡ እነሱ (ኪዳናቸውን) የተዉ ኾነውም ዞሩ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 76
فَأَعْقَبَهُمْ نِفَاقًا فِي قُلُوبِهِمْ إِلَىٰ يَوْمِ يَلْقَوْنَهُ بِمَا أَخْلَفُوا اللَّهَ مَا وَعَدُوهُ وَبِمَا كَانُوا يَكْذِبُونَ ( 77 ) አል-ተውባህ - Aya 77
አላህንም ቃል የገቡለትን በማፍረሳቸውና ይዋሹትም በነበሩት ምክንያት እስከሚገናኙት ቀን ድረስ ንፍቅናን አስከተላቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 77
أَلَمْ يَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ سِرَّهُمْ وَنَجْوَاهُمْ وَأَنَّ اللَّهَ عَلَّامُ الْغُيُوبِ ( 78 ) አል-ተውባህ - Aya 78
አላህ ምስጢራቸውንና ውይይታቸውን የሚያውቅ መኾኑን አላህም ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ መኾኑን አያውቁምን አል-ተውባህ - Aya 78
الَّذِينَ يَلْمِزُونَ الْمُطَّوِّعِينَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ فِي الصَّدَقَاتِ وَالَّذِينَ لَا يَجِدُونَ إِلَّا جُهْدَهُمْ فَيَسْخَرُونَ مِنْهُمْ ۙ سَخِرَ اللَّهُ مِنْهُمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ ( 79 ) አል-ተውባህ - Aya 79
እነዚያ ከምእምናን በምጽዋቶች ፈቃደኛ የኾኑትን፣ እነዚያንም የችሎታቸውን ያክል እንጅ የማያገኙትን ሰዎች የሚያነውሩ፣ ከእነሱም የሚስቁ አላህ ከነሱ ይሳለቅባቸዋል፤ (ይቀጣቸዋል)፡፡ ለእነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 79
اسْتَغْفِرْ لَهُمْ أَوْ لَا تَسْتَغْفِرْ لَهُمْ إِن تَسْتَغْفِرْ لَهُمْ سَبْعِينَ مَرَّةً فَلَن يَغْفِرَ اللَّهُ لَهُمْ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَفَرُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْفَاسِقِينَ ( 80 ) አል-ተውባህ - Aya 80
ለእነርሱ ምሕረትን ለምንላቸው፤ ወይም ለእነሱ ምሕረትን አትለምንላቸው (እኩል ነው)፡፡ ለእነሱ ሰባ ጊዜ ምሕረትን ብትለምንላቸው አላህ ለነሱ በፍጹም አይምርም፡፡ ይህ እነርሱ አላህና መልክተኛውን በመካዳቸው ነው፡፡ አላህም አመጸኞች ሕዝቦችን አያቀናም፡፡ አል-ተውባህ - Aya 80
فَرِحَ الْمُخَلَّفُونَ بِمَقْعَدِهِمْ خِلَافَ رَسُولِ اللَّهِ وَكَرِهُوا أَن يُجَاهِدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَقَالُوا لَا تَنفِرُوا فِي الْحَرِّ ۗ قُلْ نَارُ جَهَنَّمَ أَشَدُّ حَرًّا ۚ لَّوْ كَانُوا يَفْقَهُونَ ( 81 ) አል-ተውባህ - Aya 81
እነዚያ ከዘመቻ የቀሩት ከአላህ መልክተኛ በኋላ በመቀመጣቸው ተደሰቱ፡፡ በአላህም መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው መታገልን ጠሉ፡፡ «በሐሩር አትኺዱ» አሉም፡፡ «የገሀነም እሳት ተኳሳነቱ በጣም የበረታ ነው» በላቸው፡፡ የሚያውቁ ቢኾኑ ኖሮ (አይቀሩም ነበር)፡፡ አል-ተውባህ - Aya 81
فَلْيَضْحَكُوا قَلِيلًا وَلْيَبْكُوا كَثِيرًا جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ ( 82 ) አል-ተውባህ - Aya 82
ጥቂትንም ይሳቁ፡፡ ይሠሩት በነበሩት ዋጋ ብዙን ያለቅሳሉ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 82
فَإِن رَّجَعَكَ اللَّهُ إِلَىٰ طَائِفَةٍ مِّنْهُمْ فَاسْتَأْذَنُوكَ لِلْخُرُوجِ فَقُل لَّن تَخْرُجُوا مَعِيَ أَبَدًا وَلَن تُقَاتِلُوا مَعِيَ عَدُوًّا ۖ إِنَّكُمْ رَضِيتُم بِالْقُعُودِ أَوَّلَ مَرَّةٍ فَاقْعُدُوا مَعَ الْخَالِفِينَ ( 83 ) አል-ተውባህ - Aya 83
ከእነሱም ወደ ኾነችው ጭፍራ አላህ ቢመልስህ (ከአንተ ጋር) ለመውጣትም ቢያስፈቅዱህ፡-«ከኔ ጋር በፍጹም አትወጡም፡፡ ከእኔም ጋር ጠላትን አትዋጉም፡፡ እናንተ በመጀመሪያ ጊዜ መቀመጥን ወዳችኋልና፡፡ ከተቀማጮቹ ጋርም ተቀመጡ» በላቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 83
وَلَا تُصَلِّ عَلَىٰ أَحَدٍ مِّنْهُم مَّاتَ أَبَدًا وَلَا تَقُمْ عَلَىٰ قَبْرِهِ ۖ إِنَّهُمْ كَفَرُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَمَاتُوا وَهُمْ فَاسِقُونَ ( 84 ) አል-ተውባህ - Aya 84
ከእነሱም በአንድም በሞተ ሰው ላይ ፈጽሞ አትስገድ፡፡ በመቃብሩም ላይ አትቁም፡፡ እነሱ አላህንና መልክተኛውን ክደዋልና፡፡ እነሱም አመጸኞች ኾነው ሞተዋልና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 84
وَلَا تُعْجِبْكَ أَمْوَالُهُمْ وَأَوْلَادُهُمْ ۚ إِنَّمَا يُرِيدُ اللَّهُ أَن يُعَذِّبَهُم بِهَا فِي الدُّنْيَا وَتَزْهَقَ أَنفُسُهُمْ وَهُمْ كَافِرُونَ ( 85 ) አል-ተውባህ - Aya 85
ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸውም አይድነቁህ፡፡ አላህ የሚሻው በቅርቢቱ ዓለም በነሱ ሊቀጣቸውና ከሓዲዎችም ኾነው ነፍሶቻቸው እንዲወጡ ብቻ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 85
وَإِذَا أُنزِلَتْ سُورَةٌ أَنْ آمِنُوا بِاللَّهِ وَجَاهِدُوا مَعَ رَسُولِهِ اسْتَأْذَنَكَ أُولُو الطَّوْلِ مِنْهُمْ وَقَالُوا ذَرْنَا نَكُن مَّعَ الْقَاعِدِينَ ( 86 ) አል-ተውባህ - Aya 86
በአላህ እመኑ፡፡ ከመልክተኛውም ጋር ኾናችሁ ታገሉ፤ በማለት ምዕራፍ በተወረደች ጊዜ ከነሱ የሰፊ ሀብት ባለቤቶች የኾኑት (ለመቅረት) ፈቃድ ይጠይቁሃል፡፡ «ከተቀማጮቹ ጋርም እንኹን ተወን» ይሉሃል፡፡ አል-ተውባህ - Aya 86
رَضُوا بِأَن يَكُونُوا مَعَ الْخَوَالِفِ وَطُبِعَ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَهُمْ لَا يَفْقَهُونَ ( 87 ) አል-ተውባህ - Aya 87
በቤት ከሚቀሩት ጋር መኾናቸውን ወደዱ፡፡ በልቦቻቸውም ላይ (ዝገት) ታተመባቸው፡፡ ስለዚህ እነሱ አያውቁም፡፡ አል-ተውባህ - Aya 87
لَٰكِنِ الرَّسُولُ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ جَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ ۚ وَأُولَٰئِكَ لَهُمُ الْخَيْرَاتُ ۖ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ ( 88 ) አል-ተውባህ - Aya 88
ግን መልክተኛው እነዚያም ከርሱ ጋር ያመኑት በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸውም ታገሉ፡፡ እነዚያም መልካሞች ሁሉ ለነሱ ናቸው፡፡ እነዚያም እነሱ ምኞታቸውን ያገኙ ናቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 88
أَعَدَّ اللَّهُ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ ( 89 ) አል-ተውባህ - Aya 89
ለእነሱም ገነቶችን በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ አላህ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 89
وَجَاءَ الْمُعَذِّرُونَ مِنَ الْأَعْرَابِ لِيُؤْذَنَ لَهُمْ وَقَعَدَ الَّذِينَ كَذَبُوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ سَيُصِيبُ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ ( 90 ) አል-ተውባህ - Aya 90
ከአዕራቦችም ይቅርታ ፈላጊዎቹ ለእነሱ እንዲፈቀድላቸው መጡ፡፡ እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የዋሹትም ተቀመጡ፡፡ ከነሱ እነዚያን የካዱትን አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል፡፡ አል-ተውባህ - Aya 90
لَّيْسَ عَلَى الضُّعَفَاءِ وَلَا عَلَى الْمَرْضَىٰ وَلَا عَلَى الَّذِينَ لَا يَجِدُونَ مَا يُنفِقُونَ حَرَجٌ إِذَا نَصَحُوا لِلَّهِ وَرَسُولِهِ ۚ مَا عَلَى الْمُحْسِنِينَ مِن سَبِيلٍ ۚ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ( 91 ) አል-ተውባህ - Aya 91
በደካሞች ላይ በበሽተኞችም ላይ በነዚያም የሚያወጡት ገንዘብ በማያገኙት ላይ ለአላህና ለመልክተኛው ፍጹም ታዛዦች ከኾኑ (ባይወጡም) ኃጢኣት የለባቸውም፡፡ በበጎ አድራጊዎች ላይ (የወቀሳ) መንገድ ምንም የለባቸውም፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 91
وَلَا عَلَى الَّذِينَ إِذَا مَا أَتَوْكَ لِتَحْمِلَهُمْ قُلْتَ لَا أَجِدُ مَا أَحْمِلُكُمْ عَلَيْهِ تَوَلَّوا وَّأَعْيُنُهُمْ تَفِيضُ مِنَ الدَّمْعِ حَزَنًا أَلَّا يَجِدُوا مَا يُنفِقُونَ ( 92 ) አል-ተውባህ - Aya 92
በእነዚያም ልትጭናቸው በመጡህ ጊዜ «በርሱ ላይ የምጭናችሁ (አጋሰስ) አላገኝም፤» ያልካቸው ስትኾን የሚያወጡት ገንዘብ ባለማግኘታቸው ለማዘናቸው ዓይኖቻቸው እንባን እያፈሰሱ በዞሩት ላይ (የወቀሳ መንገድ የለባቸውም)፡፡ አል-ተውባህ - Aya 92
إِنَّمَا السَّبِيلُ عَلَى الَّذِينَ يَسْتَأْذِنُونَكَ وَهُمْ أَغْنِيَاءُ ۚ رَضُوا بِأَن يَكُونُوا مَعَ الْخَوَالِفِ وَطَبَعَ اللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ ( 93 ) አል-ተውባህ - Aya 93
(የወቀሳ) መንገዱ በእነዚያ እነሱ ባለጸጋዎች ኾነው ሳሉ ለመቅረት ፈቃድ በሚጠይቁህ ሰዎች ላይ ብቻ ነው፡፡ ከቀሪዎቹ ጋር መኾናቸውን ወደዱ፡፡ አላህም በልቦቻቸው ላይ አተመባቸው፤ ስለዚህ እነሱ አያውቁም፡፡ አል-ተውባህ - Aya 93
يَعْتَذِرُونَ إِلَيْكُمْ إِذَا رَجَعْتُمْ إِلَيْهِمْ ۚ قُل لَّا تَعْتَذِرُوا لَن نُّؤْمِنَ لَكُمْ قَدْ نَبَّأَنَا اللَّهُ مِنْ أَخْبَارِكُمْ ۚ وَسَيَرَى اللَّهُ عَمَلَكُمْ وَرَسُولُهُ ثُمَّ تُرَدُّونَ إِلَىٰ عَالِمِ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ ( 94 ) አል-ተውባህ - Aya 94
ወደእነሱ በተመለሳችሁ ጊዜ ምክንያታቸውን ያቀርቡላችኋል፡፡ አታመካኙ፤ እናንተን ፈጽሞ አናምንም፡፡ አላህ ከወሬዎቻችሁ በእርግጥ ነግሮናልና፡፡ አላህም ሥራችሁን በእርግጥ ያያል፡፡ መልክተኛውም (እንደዚሁ)፤ ከዚያም ሩቅንና ቅርብን ሁሉ ዐዋቂ ወደ ኾነው (አላህ) ትመለሳላችሁ ወዲያውም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል በላቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 94
سَيَحْلِفُونَ بِاللَّهِ لَكُمْ إِذَا انقَلَبْتُمْ إِلَيْهِمْ لِتُعْرِضُوا عَنْهُمْ ۖ فَأَعْرِضُوا عَنْهُمْ ۖ إِنَّهُمْ رِجْسٌ ۖ وَمَأْوَاهُمْ جَهَنَّمُ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ ( 95 ) አል-ተውባህ - Aya 95
ወደእነሱ በተመለሳችሁ ጊዜ እንድትተውዋቸው ለእናንተ በእርግጥ በአላህ ይምላሉ፡፡ እነሱንም ተዋቸው፡፡ እነሱ እርኩሶች ናቸውና፡፡ ይሠሩትም በነበሩት ዋጋ መኖሪያቸው ገሀነም ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 95
يَحْلِفُونَ لَكُمْ لِتَرْضَوْا عَنْهُمْ ۖ فَإِن تَرْضَوْا عَنْهُمْ فَإِنَّ اللَّهَ لَا يَرْضَىٰ عَنِ الْقَوْمِ الْفَاسِقِينَ ( 96 ) አል-ተውባህ - Aya 96
ከእነሱ ትወዱላቸው ዘንድ ለናንተ ይምሉላችኋል፡፡ ከእነሱ ብትወዱም አላህ አመጸኞች ሕዝቦችን አይወድም፡፡ አል-ተውባህ - Aya 96
الْأَعْرَابُ أَشَدُّ كُفْرًا وَنِفَاقًا وَأَجْدَرُ أَلَّا يَعْلَمُوا حُدُودَ مَا أَنزَلَ اللَّهُ عَلَىٰ رَسُولِهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ ( 97 ) አል-ተውባህ - Aya 97
አዕራቦች በክህደትና በንፍቅና በጣም የበረቱ፤ አላህም በመልክተኛው ላይ ያወረደውን ሕግጋት ባለማወቅ የተገቡ ናቸው፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 97
وَمِنَ الْأَعْرَابِ مَن يَتَّخِذُ مَا يُنفِقُ مَغْرَمًا وَيَتَرَبَّصُ بِكُمُ الدَّوَائِرَ ۚ عَلَيْهِمْ دَائِرَةُ السَّوْءِ ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ ( 98 ) አል-ተውባህ - Aya 98
ከአዕራቦችም (በአላህ መንገድ) የሚወጣውን (ገንዘብ) ዕዳ አድርጎ የሚይዝ በእናንተም ላይ የጊዜን መገለባበጥ የሚጠባበቅ ሰው አልለ፡፡ በእነሱ ላይ ጥፋቱ ይዙርባቸው፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 98
وَمِنَ الْأَعْرَابِ مَن يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَيَتَّخِذُ مَا يُنفِقُ قُرُبَاتٍ عِندَ اللَّهِ وَصَلَوَاتِ الرَّسُولِ ۚ أَلَا إِنَّهَا قُرْبَةٌ لَّهُمْ ۚ سَيُدْخِلُهُمُ اللَّهُ فِي رَحْمَتِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ( 99 ) አል-ተውባህ - Aya 99
ከአዕራቦችም በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሚሰጣቸውንም (ምጽዋቶች) አላህ ዘንድ መቃረቢያዎችና ወደ መልክተኛው ጸሎቶች መዳረሻ አድርጎ የሚይዝ ሰው አልለ፡፡ ንቁ! እርሷ ለእነሱ በእርግጥ አቃራቢ ናት፡፡ አላህ በችሮታው ውስጥ (በገነቱ) በእርግጥ ያስገባቸዋል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 99
وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ ( 100 ) አል-ተውባህ - Aya 100
ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 100
وَمِمَّنْ حَوْلَكُم مِّنَ الْأَعْرَابِ مُنَافِقُونَ ۖ وَمِنْ أَهْلِ الْمَدِينَةِ ۖ مَرَدُوا عَلَى النِّفَاقِ لَا تَعْلَمُهُمْ ۖ نَحْنُ نَعْلَمُهُمْ ۚ سَنُعَذِّبُهُم مَّرَّتَيْنِ ثُمَّ يُرَدُّونَ إِلَىٰ عَذَابٍ عَظِيمٍ ( 101 ) አል-ተውባህ - Aya 101
በዙሪያችሁም ካሉት ከዐረብ ዘላኖች መናፍቃን አልሉ፡፡ ከመዲና ሰዎችም በንፍቅና ላይ በማመጽ የዘወተሩ አልሉ፡፡ አታውቃቸውም፡፡ እኛ እናውቃቸዋለን፡፡ ሁለት ጊዜ እንቀጣቸዋለን፡፡ ከዚያም ወደታላቅ ቅጣት ይመለሳሉ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 101
وَآخَرُونَ اعْتَرَفُوا بِذُنُوبِهِمْ خَلَطُوا عَمَلًا صَالِحًا وَآخَرَ سَيِّئًا عَسَى اللَّهُ أَن يَتُوبَ عَلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ( 102 ) አል-ተውባህ - Aya 102
ሌሎችም በኃጢአቶቻቸው የተናዘዙ መልካም ሥራንና ሌላን መጥፎ ሥራ የቀላቀሉ አልሉ፡፡ አላህ ከእነሱ ጸጸታቸውን ሊቀበል ይከጀላል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 102
خُذْ مِنْ أَمْوَالِهِمْ صَدَقَةً تُطَهِّرُهُمْ وَتُزَكِّيهِم بِهَا وَصَلِّ عَلَيْهِمْ ۖ إِنَّ صَلَاتَكَ سَكَنٌ لَّهُمْ ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ ( 103 ) አል-ተውባህ - Aya 103
ከገንዘቦቻቸው ስትኾን በእርሷ የምታጠራቸውና የምታፋፋቸው የኾነችን ምጽዋት ያዝ፡፡ ለነሱም ጸልይላቸው፡፡ ጸሎትህ ለእነሱ እርጋታ ነውና አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 103
أَلَمْ يَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ هُوَ يَقْبَلُ التَّوْبَةَ عَنْ عِبَادِهِ وَيَأْخُذُ الصَّدَقَاتِ وَأَنَّ اللَّهَ هُوَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ ( 104 ) አል-ተውባህ - Aya 104
አላህ እርሱ ከባሮቹ ንስሓን የሚቀበል ምጽዋቶችንም የሚወስድ መኾኑን አላህም እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ መኾኑን አያውቁም አል-ተውባህ - Aya 104
وَقُلِ اعْمَلُوا فَسَيَرَى اللَّهُ عَمَلَكُمْ وَرَسُولُهُ وَالْمُؤْمِنُونَ ۖ وَسَتُرَدُّونَ إِلَىٰ عَالِمِ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ ( 105 ) አል-ተውባህ - Aya 105
በላቸውም ሥሩ አላህ ሠራችሁን በእርግጥ ያያልና፡፡ መልክተኛውና ምእምናንም (እንደዚሁ ያያሉ)፡፡ ሩቁንና ቅርቡን ሁሉ ዐዋቂ ወደ ኾነውም (አላህ) በእርግጥ ትመለሳላችሁ፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡ አል-ተውባህ - Aya 105
وَآخَرُونَ مُرْجَوْنَ لِأَمْرِ اللَّهِ إِمَّا يُعَذِّبُهُمْ وَإِمَّا يَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ ( 106 ) አል-ተውባህ - Aya 106
ሌሎችም ለአላህ ትዕዛዝ የተቆዩ ሕዝቦች አልሉ፡፡ ወይ ይቀጣቸዋል ወይም ከነሱ ላይ ጸጸትን ይቀበላል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 106
وَالَّذِينَ اتَّخَذُوا مَسْجِدًا ضِرَارًا وَكُفْرًا وَتَفْرِيقًا بَيْنَ الْمُؤْمِنِينَ وَإِرْصَادًا لِّمَنْ حَارَبَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ مِن قَبْلُ ۚ وَلَيَحْلِفُنَّ إِنْ أَرَدْنَا إِلَّا الْحُسْنَىٰ ۖ وَاللَّهُ يَشْهَدُ إِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ ( 107 ) አል-ተውባህ - Aya 107
እነዚያም (ምእምናንን) ለመጉዳት፣ ክህደትንም ለማበርታት፣ በምእምናንም መካከል ለመለያየት፣ ከአሁን በፊት አላህንና መልክተኛውን የተዋጋውንም ሰው ለመጠባበቅ መስጊድን የሠሩት (ከነሱ ናቸው)፡፡ መልካምን ሥራ እንጂ ሌላ አልሻንም ሲሉም በእርግጥ ይምላሉ፡፡ አላህም እነሱ በእርግጥ ውሸታሞች መኾናቸውን ይመሰክራል፡፡ አል-ተውባህ - Aya 107
لَا تَقُمْ فِيهِ أَبَدًا ۚ لَّمَسْجِدٌ أُسِّسَ عَلَى التَّقْوَىٰ مِنْ أَوَّلِ يَوْمٍ أَحَقُّ أَن تَقُومَ فِيهِ ۚ فِيهِ رِجَالٌ يُحِبُّونَ أَن يَتَطَهَّرُوا ۚ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُطَّهِّرِينَ ( 108 ) አል-ተውባህ - Aya 108
በእርሱ ውስጥ በፍጹም አትስገድ፡፡ ከመጀመሪያ ቀን ይዞ በአላህ ፍራቻ ላይ የተመሠረተው (የቁባ) መስጊድ በውስጡ ልትሰግድበት ይልቅ የተገባው ነው፡፡ በእሱ ውስጥ መጥራራትን የሚወዱ ወንዶች አልሉ፡፡ አላህም ተጥራሪዎችን ይወዳል፡፡ አል-ተውባህ - Aya 108
أَفَمَنْ أَسَّسَ بُنْيَانَهُ عَلَىٰ تَقْوَىٰ مِنَ اللَّهِ وَرِضْوَانٍ خَيْرٌ أَم مَّنْ أَسَّسَ بُنْيَانَهُ عَلَىٰ شَفَا جُرُفٍ هَارٍ فَانْهَارَ بِهِ فِي نَارِ جَهَنَّمَ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ ( 109 ) አል-ተውባህ - Aya 109
አላህን በመፍራትና ውዴታውን በመፈለግ ላይ ግንቡን የመሠረተው ሰው ይበልጣልን ወይስ ጎርፍ በሸረሸረው ለመናድ በተቃረበ ገደል አፋፍ ላይ ግንቡን የመሠረተውና በርሱ (ይዞት) በገሀነም እሳት ውስጥ የወደቀ (ይበልጣል)፡፡ አላህም በደለኞች ሕዝቦችን አይመራም፡፡ አል-ተውባህ - Aya 109
لَا يَزَالُ بُنْيَانُهُمُ الَّذِي بَنَوْا رِيبَةً فِي قُلُوبِهِمْ إِلَّا أَن تَقَطَّعَ قُلُوبُهُمْ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ ( 110 ) አል-ተውባህ - Aya 110
ያ የካቡት ግንባቸው ልቦቻቸው (በሞት) ካልተቆራረጡ በቀር በልቦቻቸው ውስጥ የመጠራጠር ምክንያት ከመኾን አይወገድም፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 110
إِنَّ اللَّهَ اشْتَرَىٰ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ أَنفُسَهُمْ وَأَمْوَالَهُم بِأَنَّ لَهُمُ الْجَنَّةَ ۚ يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَيَقْتُلُونَ وَيُقْتَلُونَ ۖ وَعْدًا عَلَيْهِ حَقًّا فِي التَّوْرَاةِ وَالْإِنجِيلِ وَالْقُرْآنِ ۚ وَمَنْ أَوْفَىٰ بِعَهْدِهِ مِنَ اللَّهِ ۚ فَاسْتَبْشِرُوا بِبَيْعِكُمُ الَّذِي بَايَعْتُم بِهِ ۚ وَذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ ( 111 ) አል-ተውባህ - Aya 111
አላህ ከምእምናን ነፍሶቻቸውንና ገንዘቦቻቸውን ገነት ለእነሱ ብቻ ያላቸው በመኾን ገዛቸው፡፡ በአላህ መንገድ ላይ ይጋደላሉ፡፡ ይገድላሉም፤ ይገደላሉም፡፡ በተውራት በኢንጅልና በቁርኣንም (የተነገረውን) ተስፋ በእርሱ ላይ አረጋገጠ፡፡ ከአላህም የበለጠ በኪዳኑ የሚሞላ ማነው በዚያም በእርሱ በተሻሻጣችሁበት ሽያጫችሁ ተደሰቱ፡፡ ይህም እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 111
التَّائِبُونَ الْعَابِدُونَ الْحَامِدُونَ السَّائِحُونَ الرَّاكِعُونَ السَّاجِدُونَ الْآمِرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَالنَّاهُونَ عَنِ الْمُنكَرِ وَالْحَافِظُونَ لِحُدُودِ اللَّهِ ۗ وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِينَ ( 112 ) አል-ተውባህ - Aya 112
(እነርሱ) ተጸጻቺዎች፣ ተገዢዎች፣ አመስጋኞች፣ ጿሚዎች፣ አጎንባሾች፣ በግንባር ተደፊዎች፣ በበጎ ሥራ አዛዦች ከክፉም ከልካዮች፣ የአላህንም ሕግጋት ጠባቂዎች ናቸው ምእምናንንም አብስር፡፡ አል-ተውባህ - Aya 112
مَا كَانَ لِلنَّبِيِّ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَن يَسْتَغْفِرُوا لِلْمُشْرِكِينَ وَلَوْ كَانُوا أُولِي قُرْبَىٰ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُمْ أَصْحَابُ الْجَحِيمِ ( 113 ) አል-ተውባህ - Aya 113
ለነቢዩና ለነዚያ ላመኑት ለአጋሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶች ቢኾኑም እንኳ እነሱ (ከሓዲዎቹ) የእሳት ጓዶች መኾናቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ምሕረትን ሊለምኑ የሚገባ አልነበረም፡፡ አል-ተውባህ - Aya 113
وَمَا كَانَ اسْتِغْفَارُ إِبْرَاهِيمَ لِأَبِيهِ إِلَّا عَن مَّوْعِدَةٍ وَعَدَهَا إِيَّاهُ فَلَمَّا تَبَيَّنَ لَهُ أَنَّهُ عَدُوٌّ لِّلَّهِ تَبَرَّأَ مِنْهُ ۚ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ لَأَوَّاهٌ حَلِيمٌ ( 114 ) አል-ተውባህ - Aya 114
የኢብራሂምም ለአባቱ ምሕረትን መለመን ለእርሱ ገብቶለት ለነበረችው ቃል (ለመሙላት) እንጂ ለሌላ አልነበረም፡፡ እርሱም የአላህ ጠላት መኾኑ ለእርሱ በተገለጸለት ጊዜ ከርሱ ራቀ፤ (ተወው)፡፡ ኢብራሂም በእርግጥ በጣም ርኅሩኅ ታጋሽ ነውና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 114
وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيُضِلَّ قَوْمًا بَعْدَ إِذْ هَدَاهُمْ حَتَّىٰ يُبَيِّنَ لَهُم مَّا يَتَّقُونَ ۚ إِنَّ اللَّهَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ ( 115 ) አል-ተውባህ - Aya 115
አላህም ሕዝቦችን ከአቀናቸው በኋላ የሚጠነቀቁትን (ሥራ) ለእነሱ እስከሚገልጸላቸው (እስከሚተውትም) ድረስ ጥፋተኛ የሚያደርግ አይደለም፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 115
إِنَّ اللَّهَ لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ يُحْيِي وَيُمِيتُ ۚ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ ( 116 ) አል-ተውባህ - Aya 116
አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና የርሱ ብቻ ነው፡፡ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም፡፡ ለእናንተም ከርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም፡፡ አል-ተውባህ - Aya 116
لَّقَد تَّابَ اللَّهُ عَلَى النَّبِيِّ وَالْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ الَّذِينَ اتَّبَعُوهُ فِي سَاعَةِ الْعُسْرَةِ مِن بَعْدِ مَا كَادَ يَزِيغُ قُلُوبُ فَرِيقٍ مِّنْهُمْ ثُمَّ تَابَ عَلَيْهِمْ ۚ إِنَّهُ بِهِمْ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ ( 117 ) አል-ተውባህ - Aya 117
በነቢዩ በነዚያም በችግሪቱ ጊዜያት (በተቡክ ዘመቻ) ከእነሱ የከፊሎቹ ልቦች (ለመቅረት) ሊዘነበሉ ከተቃረቡ በኋላ በተከተሉት ስደተኞችና ረዳቶች ላይ አላህ በእርግጥ ጸጸታቸውን ተቀበለ፡፡ ከዚያም ከእነሱ ንስሓ መግባታቸውን ተቀበለ፡፡ እርሱ ለእነሱ ርኅሩኅ አዛኝ ነውና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 117
وَعَلَى الثَّلَاثَةِ الَّذِينَ خُلِّفُوا حَتَّىٰ إِذَا ضَاقَتْ عَلَيْهِمُ الْأَرْضُ بِمَا رَحُبَتْ وَضَاقَتْ عَلَيْهِمْ أَنفُسُهُمْ وَظَنُّوا أَن لَّا مَلْجَأَ مِنَ اللَّهِ إِلَّا إِلَيْهِ ثُمَّ تَابَ عَلَيْهِمْ لِيَتُوبُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ هُوَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ ( 118 ) አል-ተውባህ - Aya 118
በእነዚያም በሦስቱ ሰዎች ላይ ምድር ከስፋትዋ ጋር በእነሱ ላይ እስከ ጠበበች፣ ነፍሶቻቸውም በርሳቸው ላይ እስከተጠበቡ፣ ከአላህም ወደርሱ ቢኾን እንጂ ሌላ መጠጊያ አለመኖሩን እስከ አረጋገጡ ድረስ በተቆዩት ላይ (አላህ ጸጸትን ተቀበለ)፡፡ ከዚያም ይጸጸቱ ዘንድ ወደ ጸጸት መራቸው፡፡ አላህ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 118
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَكُونُوا مَعَ الصَّادِقِينَ ( 119 ) አል-ተውባህ - Aya 119
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ ከእውነተኞቹም ጋር ኹኑ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 119
مَا كَانَ لِأَهْلِ الْمَدِينَةِ وَمَنْ حَوْلَهُم مِّنَ الْأَعْرَابِ أَن يَتَخَلَّفُوا عَن رَّسُولِ اللَّهِ وَلَا يَرْغَبُوا بِأَنفُسِهِمْ عَن نَّفْسِهِ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ لَا يُصِيبُهُمْ ظَمَأٌ وَلَا نَصَبٌ وَلَا مَخْمَصَةٌ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَلَا يَطَئُونَ مَوْطِئًا يَغِيظُ الْكُفَّارَ وَلَا يَنَالُونَ مِنْ عَدُوٍّ نَّيْلًا إِلَّا كُتِبَ لَهُم بِهِ عَمَلٌ صَالِحٌ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجْرَ الْمُحْسِنِينَ ( 120 ) አል-ተውባህ - Aya 120
ለመዲና ሰዎችና ከአዕራብም በዙሪያቸው ላሉት ሰዎች ከአላህ መልክተኛ ወደኋላ ሊቀሩ ነፍሶቻቸውንም ከነፍሱ አብልጠው ሊወዱ አይገባቸውም ነበር፡፡ ይህ (ከመቅረት መከልከል) ለእነርሱ መልካም ሥራ የሚጻፍላቸው ቢኾን እንጅ፡፡ በአላህ መንገድ ላይ ጥምም፣ ድካምም፣ ረኃብም፣ የማይነካቸው ከሐዲዎችንም የሚያስቆጭን ስፍራ የማይረግጡ፣ ከጠላትም የሚጎዳን ነገር (መግደልን መማረክን መዝረፍን) የማያገኙ በመኾናቸው ነው፡፡ አላህ የመልካም ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና፡፡ አል-ተውባህ - Aya 120
وَلَا يُنفِقُونَ نَفَقَةً صَغِيرَةً وَلَا كَبِيرَةً وَلَا يَقْطَعُونَ وَادِيًا إِلَّا كُتِبَ لَهُمْ لِيَجْزِيَهُمُ اللَّهُ أَحْسَنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ ( 121 ) አል-ተውባህ - Aya 121
ትንሽንም ትልቅንም ልግስና አይለግሱም ወንዝንም አያቋርጡም አላህ ይሠሩት ከነበረው የበለጠን ምንዳ ይመነዳቸው ዘንድ ለእነሱ የሚጻፍላቸው ቢሆን እንጅ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 121
وَمَا كَانَ الْمُؤْمِنُونَ لِيَنفِرُوا كَافَّةً ۚ فَلَوْلَا نَفَرَ مِن كُلِّ فِرْقَةٍ مِّنْهُمْ طَائِفَةٌ لِّيَتَفَقَّهُوا فِي الدِّينِ وَلِيُنذِرُوا قَوْمَهُمْ إِذَا رَجَعُوا إِلَيْهِمْ لَعَلَّهُمْ يَحْذَرُونَ ( 122 ) አል-ተውባህ - Aya 122
ምእምናንም (ከነቢዩ ጋር ካልኾነ) በሙሉ ሊወጡ አይገባም፡፡ ከእነሱ ውስጥ ከየክፍሉ አንዲት ጭፍራ ለምን አትወጣም፡፡ (ሌሎቹ) ሃይማኖትን እንዲማሩና ወገኖቻቸው ወደነርሱ በተመለሱ ጊዜ እንዲጠነቀቁ ይገስጹዋቸው ዘንድ (ለምን አይቀሩም)፡፡ አል-ተውባህ - Aya 122
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قَاتِلُوا الَّذِينَ يَلُونَكُم مِّنَ الْكُفَّارِ وَلْيَجِدُوا فِيكُمْ غِلْظَةً ۚ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ مَعَ الْمُتَّقِينَ ( 123 ) አል-ተውባህ - Aya 123
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአቅራቢያችሁ ያሉትን ከሓዲዎች ተዋጉ፡፡ ከእናንተም ብርታትን ያግኙ፡፡ አላህም ከሚጠነቀቁት ጋር መኾኑን ዕወቁ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 123
وَإِذَا مَا أُنزِلَتْ سُورَةٌ فَمِنْهُم مَّن يَقُولُ أَيُّكُمْ زَادَتْهُ هَٰذِهِ إِيمَانًا ۚ فَأَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا فَزَادَتْهُمْ إِيمَانًا وَهُمْ يَسْتَبْشِرُونَ ( 124 ) አል-ተውባህ - Aya 124
ሱራም (ምዕራፍ) በተወረደች ጊዜ ከእነሱ (ከመናፍቃን) ውስጥ ማንኛችሁ ነው ይህች (ምዕራፍ) እምነትን የጨመረችለት የሚል ሰው አልለ፡፡ እነዚያ ያመኑትማ የሚደሰቱ ሲኾኑ እምነትን ጨመረችላቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 124
وَأَمَّا الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ فَزَادَتْهُمْ رِجْسًا إِلَىٰ رِجْسِهِمْ وَمَاتُوا وَهُمْ كَافِرُونَ ( 125 ) አል-ተውባህ - Aya 125
እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸውማ በርክሰታቸው ላይ ርክሰትን ጨመረችላቸው፡፡ እነርሱም ከሓዲዎች ኾነው ሞቱ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 125
أَوَلَا يَرَوْنَ أَنَّهُمْ يُفْتَنُونَ فِي كُلِّ عَامٍ مَّرَّةً أَوْ مَرَّتَيْنِ ثُمَّ لَا يَتُوبُونَ وَلَا هُمْ يَذَّكَّرُونَ ( 126 ) አል-ተውባህ - Aya 126
በየዓመቱ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ እነርሱ የሚሞከሩ መኾናቸውን አያዩምን ከዚያም አይጸጸቱምን እነሱም አይገሰጹምን አል-ተውባህ - Aya 126
وَإِذَا مَا أُنزِلَتْ سُورَةٌ نَّظَرَ بَعْضُهُمْ إِلَىٰ بَعْضٍ هَلْ يَرَاكُم مِّنْ أَحَدٍ ثُمَّ انصَرَفُوا ۚ صَرَفَ اللَّهُ قُلُوبَهُم بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَفْقَهُونَ ( 127 ) አል-ተውባህ - Aya 127
(እነሱን የምታነሳ) ምዕራፍም በተወረደች ጊዜ አንድ ሰው ያያችኋልን እያሉ ከፊሎቻቸው ወደ ከፊሉ ይመለከታሉ፡፡ ከዚያም (ተደብቀው) ይኼዳሉ፡፡ እነርሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው አላህ ልቦቻቸውን አዞረ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 127
لَقَدْ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مِّنْ أَنفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُم بِالْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ ( 128 ) አል-ተውባህ - Aya 128
ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን (ላይ) ርኅሩኅ አዛኝ የኾነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ አል-ተውባህ - Aya 128
فَإِن تَوَلَّوْا فَقُلْ حَسْبِيَ اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ ۖ وَهُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ ( 129 ) አል-ተውባህ - Aya 129
ቢያፈገፍጉም አላህ በቂዬ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ በእርሱ ላይ ተጠጋሁ እርሱም የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው በላቸው፡፡ አል-ተውባህ - Aya 129
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah