Surah አል ነጅም

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ነጅም - Aya count 62
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
وَالنَّجْمِ إِذَا هَوَىٰ ( 1 ) አል ነጅም - Aya 1
በኮከብ እምላለሁ በወደቀ (በገባ) ጊዜ፡፡ አል ነጅም - Aya 1
مَا ضَلَّ صَاحِبُكُمْ وَمَا غَوَىٰ ( 2 ) አል ነጅም - Aya 2
ነቢያችሁ (ሙሐመድ) አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም፡፡ አል ነጅም - Aya 2
وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَىٰ ( 3 ) አል ነጅም - Aya 3
ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡ አል ነጅም - Aya 3
إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ ( 4 ) አል ነጅም - Aya 4
እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ አል ነጅም - Aya 4
عَلَّمَهُ شَدِيدُ الْقُوَىٰ ( 5 ) አል ነጅም - Aya 5
ኀይሎቹ ብርቱው (መልአክ) አስተማረው፡፡ አል ነጅም - Aya 5
ذُو مِرَّةٍ فَاسْتَوَىٰ ( 6 ) አል ነጅም - Aya 6
የዕውቀት ባለቤት የኾነው (አስተማረው፤ በተፈጥሮ ቅርጹ ኾኖ በአየር ላይ) ተደላደለም፡፡ አል ነጅም - Aya 6
وَهُوَ بِالْأُفُقِ الْأَعْلَىٰ ( 7 ) አል ነጅም - Aya 7
እርሱ በላይኛው አድማስ ኾኖ፡፡ አል ነጅም - Aya 7
ثُمَّ دَنَا فَتَدَلَّىٰ ( 8 ) አል ነጅም - Aya 8
ከዚያም ቀረበ፤ ወረደም፡፡ አል ነጅም - Aya 8
فَكَانَ قَابَ قَوْسَيْنِ أَوْ أَدْنَىٰ ( 9 ) አል ነጅም - Aya 9
(ከእርሱ) የሁለት ደጋኖች ጫፍ ያህል ወይም (ከዚህ) ይበልጥ የቀረበ ኾነም፡፡ አል ነጅም - Aya 9
فَأَوْحَىٰ إِلَىٰ عَبْدِهِ مَا أَوْحَىٰ ( 10 ) አል ነጅም - Aya 10
ወደ ባሪያውም (አላህ) ያወረደውን አወረደ፡፡ አል ነጅም - Aya 10
مَا كَذَبَ الْفُؤَادُ مَا رَأَىٰ ( 11 ) አል ነጅም - Aya 11
(ነቢዩም በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም፡፡ አል ነጅም - Aya 11
أَفَتُمَارُونَهُ عَلَىٰ مَا يَرَىٰ ( 12 ) አል ነጅም - Aya 12
ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን? አል ነጅም - Aya 12
وَلَقَدْ رَآهُ نَزْلَةً أُخْرَىٰ ( 13 ) አል ነጅም - Aya 13
በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፡፡ አል ነጅም - Aya 13
عِندَ سِدْرَةِ الْمُنتَهَىٰ ( 14 ) አል ነጅም - Aya 14
በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤ አል ነጅም - Aya 14
عِندَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَىٰ ( 15 ) አል ነጅም - Aya 15
እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡ አል ነጅም - Aya 15
إِذْ يَغْشَى السِّدْرَةَ مَا يَغْشَىٰ ( 16 ) አል ነጅም - Aya 16
ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡ አል ነጅም - Aya 16
مَا زَاغَ الْبَصَرُ وَمَا طَغَىٰ ( 17 ) አል ነጅም - Aya 17
ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም፡፡ አል ነጅም - Aya 17
لَقَدْ رَأَىٰ مِنْ آيَاتِ رَبِّهِ الْكُبْرَىٰ ( 18 ) አል ነጅም - Aya 18
ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡ አል ነጅም - Aya 18
أَفَرَأَيْتُمُ اللَّاتَ وَالْعُزَّىٰ ( 19 ) አል ነጅም - Aya 19
አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? አል ነጅም - Aya 19
وَمَنَاةَ الثَّالِثَةَ الْأُخْرَىٰ ( 20 ) አል ነጅም - Aya 20
ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን (አያችሁን? የምትግገዟቸው ኃይል አላቸውን?) አል ነጅም - Aya 20
أَلَكُمُ الذَّكَرُ وَلَهُ الْأُنثَىٰ ( 21 ) አል ነጅም - Aya 21
ለእናንተ ወንድ ለእርሱም ሴት (ልጅ) ይኖራልን? አል ነጅም - Aya 21
تِلْكَ إِذًا قِسْمَةٌ ضِيزَىٰ ( 22 ) አል ነጅም - Aya 22
ይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍያ ናት፡፡ አል ነጅም - Aya 22
إِنْ هِيَ إِلَّا أَسْمَاءٌ سَمَّيْتُمُوهَا أَنتُمْ وَآبَاؤُكُم مَّا أَنزَلَ اللَّهُ بِهَا مِن سُلْطَانٍ ۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا الظَّنَّ وَمَا تَهْوَى الْأَنفُسُ ۖ وَلَقَدْ جَاءَهُم مِّن رَّبِّهِمُ الْهُدَىٰ ( 23 ) አል ነጅም - Aya 23
እነርሱ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸው ስሞች ብቻ እንጅ ምንም አይደሉም፡፡ አላህ በእርሷ (መግገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፡፡ ከጌታቸውም መምሪያ የመጣላቸው ሲኾኑ ጥርጣሬንና ነፍሶች የሚዘነበሉበትን እንጅ ሌላ አይከተሉም፡፡ አል ነጅም - Aya 23
أَمْ لِلْإِنسَانِ مَا تَمَنَّىٰ ( 24 ) አል ነጅም - Aya 24
ለሰው የተመኘው ሁሉ አለውን? አል ነጅም - Aya 24
فَلِلَّهِ الْآخِرَةُ وَالْأُولَىٰ ( 25 ) አል ነጅም - Aya 25
መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም (ዓለም) የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ አል ነጅም - Aya 25
وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ ( 26 ) አል ነጅም - Aya 26
በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች (ሊማለዱለት) ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ አል ነጅም - Aya 26
إِنَّ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ لَيُسَمُّونَ الْمَلَائِكَةَ تَسْمِيَةَ الْأُنثَىٰ ( 27 ) አል ነጅም - Aya 27
እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት መላእክትን በሴት አጠራር ይጠራሉ፡፡ አል ነጅም - Aya 27
وَمَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ ۖ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا الظَّنَّ ۖ وَإِنَّ الظَّنَّ لَا يُغْنِي مِنَ الْحَقِّ شَيْئًا ( 28 ) አል ነጅም - Aya 28
ለእነርሱም በእርሱ ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ ጥርጣሬም ከእውነት ምንም አያብቃቃም፡፡ አል ነጅም - Aya 28
فَأَعْرِضْ عَن مَّن تَوَلَّىٰ عَن ذِكْرِنَا وَلَمْ يُرِدْ إِلَّا الْحَيَاةَ الدُّنْيَا ( 29 ) አል ነጅም - Aya 29
ከግሣጼያችንም (ከቁርኣን) ከሸሸና አነስተኛይቱን ሕይወት እንጅ ሌላን ከማይሻ ሰው ዙር (ተወው)፡፡ አል ነጅም - Aya 29
ذَٰلِكَ مَبْلَغُهُم مِّنَ الْعِلْمِ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِ وَهُوَ أَعْلَمُ بِمَنِ اهْتَدَىٰ ( 30 ) አል ነጅም - Aya 30
ይህ (አነስተኛይቱን ሕይወት መምረጥ) ከዕውቀት ድካቸው ነው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን በእርግጥ ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም የቀናውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ አል ነጅም - Aya 30
وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ لِيَجْزِيَ الَّذِينَ أَسَاءُوا بِمَا عَمِلُوا وَيَجْزِيَ الَّذِينَ أَحْسَنُوا بِالْحُسْنَى ( 31 ) አል ነጅም - Aya 31
በሰማያት ያለውና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያን ያጠፉትን በሠሩት ሊቀጣ እነዚያን ያሳመሩትንም በመልካሚቱ (ገነት) ሊመነዳ (የጠመመውንና የቀናውን ያውቃል)፡፡ አል ነጅም - Aya 31
الَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَائِرَ الْإِثْمِ وَالْفَوَاحِشَ إِلَّا اللَّمَمَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ وَاسِعُ الْمَغْفِرَةِ ۚ هُوَ أَعْلَمُ بِكُمْ إِذْ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَإِذْ أَنتُمْ أَجِنَّةٌ فِي بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ ۖ فَلَا تُزَكُّوا أَنفُسَكُمْ ۖ هُوَ أَعْلَمُ بِمَنِ اتَّقَىٰ ( 32 ) አል ነጅም - Aya 32
(እነርሱ) እነዚያ የኃጢኣትን ታላለቆችና አስጸያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፡፡ ግን ትናንሾቹ የሚማሩ ናቸው፡፡ ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፡፡ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ ሽሎች በኾናችሁ ጊዜ እርሱ በናንተ (ኹነታ) ዐዋቂ ነው፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ እርሱ የሚፈራውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ አል ነጅም - Aya 32
أَفَرَأَيْتَ الَّذِي تَوَلَّىٰ ( 33 ) አል ነጅም - Aya 33
ያንን (ከእምነት) የዞረውን አየህን? አል ነጅም - Aya 33
وَأَعْطَىٰ قَلِيلًا وَأَكْدَىٰ ( 34 ) አል ነጅም - Aya 34
ጥቂትን የሰጠውንና ያቋረጠውንም (አየህን?) አል ነጅም - Aya 34
أَعِندَهُ عِلْمُ الْغَيْبِ فَهُوَ يَرَىٰ ( 35 ) አል ነጅም - Aya 35
የሩቁ ምስጢር ዕውቀት እርሱ ዘንድ አልለን? ስለዚህ እርሱ ያያልን? አል ነጅም - Aya 35
أَمْ لَمْ يُنَبَّأْ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَىٰ ( 36 ) አል ነጅም - Aya 36
ይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን? አል ነጅም - Aya 36
وَإِبْرَاهِيمَ الَّذِي وَفَّىٰ ( 37 ) አል ነጅም - Aya 37
በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም (ጽሑፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?) አል ነጅም - Aya 37
أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ( 38 ) አል ነጅም - Aya 38
(እርሱም ኃጢያት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም፡፡ አል ነጅም - Aya 38
وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَانِ إِلَّا مَا سَعَىٰ ( 39 ) አል ነጅም - Aya 39
ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም፡፡ አል ነጅም - Aya 39
وَأَنَّ سَعْيَهُ سَوْفَ يُرَىٰ ( 40 ) አል ነጅም - Aya 40
ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል፡፡ አል ነጅም - Aya 40
ثُمَّ يُجْزَاهُ الْجَزَاءَ الْأَوْفَىٰ ( 41 ) አል ነጅም - Aya 41
ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል፡፡ አል ነጅም - Aya 41
وَأَنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ الْمُنتَهَىٰ ( 42 ) አል ነጅም - Aya 42
መጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ አል ነጅም - Aya 42
وَأَنَّهُ هُوَ أَضْحَكَ وَأَبْكَىٰ ( 43 ) አል ነጅም - Aya 43
እነሆ እርሱም አስሳቀ፣ አስለቀሰም፡፡ አል ነጅም - Aya 43
وَأَنَّهُ هُوَ أَمَاتَ وَأَحْيَا ( 44 ) አል ነጅም - Aya 44
እነሆ እርሱም ገደለ፣ አስነሳም፡፡ አል ነጅም - Aya 44
وَأَنَّهُ خَلَقَ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ ( 45 ) አል ነጅም - Aya 45
እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድንና ሴትን ፈጠረ፡፡ አል ነጅም - Aya 45
مِن نُّطْفَةٍ إِذَا تُمْنَىٰ ( 46 ) አል ነጅም - Aya 46
ከፍትወት ጠብታ (በማህጸን ውስጥ) በምትፈሰስ ጊዜ፡፡ አል ነጅም - Aya 46
وَأَنَّ عَلَيْهِ النَّشْأَةَ الْأُخْرَىٰ ( 47 ) አል ነጅም - Aya 47
የኋለኛይቱም ማስነሳት በእርሱ ላይ ነው፡፡ አል ነጅም - Aya 47
وَأَنَّهُ هُوَ أَغْنَىٰ وَأَقْنَىٰ ( 48 ) አል ነጅም - Aya 48
እነሆ እርሱም አከበረ፣ ጥሪተኛም አደረገ፡፡ አል ነጅም - Aya 48
وَأَنَّهُ هُوَ رَبُّ الشِّعْرَىٰ ( 49 ) አል ነጅም - Aya 49
እነሆ እርሱም የሺዕራ ጌታ ነው፡፡ አል ነጅም - Aya 49
وَأَنَّهُ أَهْلَكَ عَادًا الْأُولَىٰ ( 50 ) አል ነጅም - Aya 50
እነሆ እርሱም የፊተኛይቱን ዓድ አጥፍቷል፡፡ አል ነጅም - Aya 50
وَثَمُودَ فَمَا أَبْقَىٰ ( 51 ) አል ነጅም - Aya 51
ሰሙድንም (አጥፍቷል)፤ አላስቀረምም፡፡ አል ነጅም - Aya 51
وَقَوْمَ نُوحٍ مِّن قَبْلُ ۖ إِنَّهُمْ كَانُوا هُمْ أَظْلَمَ وَأَطْغَىٰ ( 52 ) አል ነጅም - Aya 52
በፊትም የኑሕን ሕዝቦች (አጥፍቷል)፡፡ እነርሱ በጣም በደለኞችና እጅግ የጠመሙ እነርሱ ነበሩና፡፡ አል ነጅም - Aya 52
وَالْمُؤْتَفِكَةَ أَهْوَىٰ ( 53 ) አል ነጅም - Aya 53
የተገለበጠችውንም ከተማ ደፋ፡፡ አል ነጅም - Aya 53
فَغَشَّاهَا مَا غَشَّىٰ ( 54 ) አል ነጅም - Aya 54
ያለበሳትንም አለበሳት፡፡ አል ነጅም - Aya 54
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكَ تَتَمَارَىٰ ( 55 ) አል ነጅም - Aya 55
ከጌታህም ጸጋዎች በየትኛው ትጠራጠራለህ? አል ነጅም - Aya 55
هَٰذَا نَذِيرٌ مِّنَ النُّذُرِ الْأُولَىٰ ( 56 ) አል ነጅም - Aya 56
ይህ ከፊተኞቹ አስፈራሪዎች (ጎሳ) የኾነ አስፈራሪ ነው፡፡ አል ነጅም - Aya 56
أَزِفَتِ الْآزِفَةُ ( 57 ) አል ነጅም - Aya 57
ቀራቢይቱ (ኅልፈተ ዓለም) ቀረበች፡፡ አል ነጅም - Aya 57
لَيْسَ لَهَا مِن دُونِ اللَّهِ كَاشِفَةٌ ( 58 ) አል ነጅም - Aya 58
ለእርሷ ከአላህ ሌላ ገላጭ የላትም፡፡ አል ነጅም - Aya 58
أَفَمِنْ هَٰذَا الْحَدِيثِ تَعْجَبُونَ ( 59 ) አል ነጅም - Aya 59
ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን? አል ነጅም - Aya 59
وَتَضْحَكُونَ وَلَا تَبْكُونَ ( 60 ) አል ነጅም - Aya 60
ትስቃላችሁምን? አታለቅሱምን? አል ነጅም - Aya 60
وَأَنتُمْ سَامِدُونَ ( 61 ) አል ነጅም - Aya 61
እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ፡፡ አል ነጅም - Aya 61
فَاسْجُدُوا لِلَّهِ وَاعْبُدُوا ۩ ( 62 ) አል ነጅም - Aya 62
ለአላህም ስገዱ ተገዙትም፡፡ አል ነጅም - Aya 62
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah