Surah አል ጣሪቅ

አማርኛ Muhammad Sadiq & Sani Habib

Surah አል ጣሪቅ - Aya count 17
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email
وَالسَّمَاءِ وَالطَّارِقِ ( 1 ) አል ጣሪቅ - Aya 1
በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 1
وَمَا أَدْرَاكَ مَا الطَّارِقُ ( 2 ) አል ጣሪቅ - Aya 2
የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ? አል ጣሪቅ - Aya 2
النَّجْمُ الثَّاقِبُ ( 3 ) አል ጣሪቅ - Aya 3
ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 3
إِن كُلُّ نَفْسٍ لَّمَّا عَلَيْهَا حَافِظٌ ( 4 ) አል ጣሪቅ - Aya 4
ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 4
فَلْيَنظُرِ الْإِنسَانُ مِمَّ خُلِقَ ( 5 ) አል ጣሪቅ - Aya 5
ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 5
خُلِقَ مِن مَّاءٍ دَافِقٍ ( 6 ) አል ጣሪቅ - Aya 6
ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 6
يَخْرُجُ مِن بَيْنِ الصُّلْبِ وَالتَّرَائِبِ ( 7 ) አል ጣሪቅ - Aya 7
ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 7
إِنَّهُ عَلَىٰ رَجْعِهِ لَقَادِرٌ ( 8 ) አል ጣሪቅ - Aya 8
እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 8
يَوْمَ تُبْلَى السَّرَائِرُ ( 9 ) አል ጣሪቅ - Aya 9
ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 9
فَمَا لَهُ مِن قُوَّةٍ وَلَا نَاصِرٍ ( 10 ) አል ጣሪቅ - Aya 10
ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 10
وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الرَّجْعِ ( 11 ) አል ጣሪቅ - Aya 11
የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 11
وَالْأَرْضِ ذَاتِ الصَّدْعِ ( 12 ) አል ጣሪቅ - Aya 12
(በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤ አል ጣሪቅ - Aya 12
إِنَّهُ لَقَوْلٌ فَصْلٌ ( 13 ) አል ጣሪቅ - Aya 13
እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 13
وَمَا هُوَ بِالْهَزْلِ ( 14 ) አል ጣሪቅ - Aya 14
እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 14
إِنَّهُمْ يَكِيدُونَ كَيْدًا ( 15 ) አል ጣሪቅ - Aya 15
እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 15
وَأَكِيدُ كَيْدًا ( 16 ) አል ጣሪቅ - Aya 16
(እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 16
فَمَهِّلِ الْكَافِرِينَ أَمْهِلْهُمْ رُوَيْدًا ( 17 ) አል ጣሪቅ - Aya 17
ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡ አል ጣሪቅ - Aya 17
Facebook Twitter Google+ Pinterest Reddit StumbleUpon Linkedin Tumblr Google Bookmarks Email

Select Translation

Select surah